Site icon

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ባለፉት ሁለት ቀናት እግዚአብሔር ለደኅንነቱ የጥሪ ቃል ይመልሱ ዘንድ ሰዎችን እንደሚጠራ ተገንዝበናል። ነገር ቀን ሰዎች ከኃጢአታቸው የተነሣ በራሳቸው ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጥሪ ሳይቀበሉ ቀሩ። ነገር ቀን እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎች ጥሪውን ሳይቀበሉ ቢቀሩም ለሌሎች ደግሞ ምሕረቱን ይሰጣል። እግዚአብሔር በሉዓላዊ ምርጫው ምሕረትን ለመስጠት ወንዶችንም ሴቶችንም ወደ ራሱ ይጠራቸዋል። ጥሪውም እርሱን ሰምተው ንስሐ ገብተው በማመን ለጥሪው ቃል መልስ እንዲሰጡ ነው። ይህ ጥሪ በዚህ ሳምንት በትምህርት አንድ ላይ ካጠናነው አጠቃላይ ጥሪ የተለየ ነው። ሰዎች ደኅንነቱን እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚያስተላልፈው አጠቃላይ ጥሪ የእግዚአብሔር የወንጌል ጥሪ ወይም አጠቃላይ ጥሪ ተብሎ ይታወቃል። ነገር ገን እግዚአብሔር በሉዓላዊ ሥልጣኑ የሚመርጣቸውና ምሕረቱን የሚሰጣቸው ሌላ ጥሪ ይቀበላሉ። ይህ ጥሪ ከአጠቃላይ ጥሪ ይለያል። ይህኛው ጥሪ ኃይለኛ ጥሪ ነው። ይህ ጥሪ ሰዎች ለእግዚአብሔር የወንጌል ጥሪ መልእክት መልስ እንዲሰጡ የሚያደርገና በልባቸው ውስጥ የሚሠራ ጥሪ ነው። አንዳንድ ጊዜ ይህ ኃይለኛ ጥሪ የእግዚአብሔር «ውጤታማ ጥሪ» ለደኅንነት ይባላል። ምክንያቱም ሰዎች ከልባቸው የእግዚአብሔርን ጥሪ እንዲቀበሉ ስለሚያደርግ ነው። 

1. ለደኅንነት «ውጤታማ ጥሪ» አለ። 

1.1 እውነተኛና ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች «ተጠሩ» ይባላል። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡6-7 አንብቡ። የሮማ ክርስቲያኖች እንዴት ላሉ ሁለት ጉዳዮች ተጠሩ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡2፥9 አንብቡ። በቆሮንተስ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ላሉ ሁለት ጉዳዮች ተጠራች? 

ጥያቄ፡- ገላትያ 1፡15-16 አንብቡ። ሀ) ጳውሎስ ወደ ምን ተጠራ? ለ) ፊልጵስዩስ 3፡14 እንብቡ። ጳውሎስ ወደ ምን ተጠራ? 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 1:8 አንብቡ። የኤፌሶን ክርስቲያኖች ወደ ምን ተጠሩ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ተሰሎንቄ 2፡12 አንቡ። የተሰሎንቄ ምእመናን ወደ ምን ተጠሩ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12 አንብቡ። ጢሞቴዎስ ወደ ምን ተጠራ? 

ጥያቄ፡- ዕብራውያን 3፡1 አንብቡ። ቅዱሳን ወንድሞች ምንን ተካፈሉ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 አንብቡ። ሀ) እኛ የማን ነን? ለ) እኛ ከምን ተጠራን? ሐ) ወደ ምን ተጠርተን ነበር? 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ሰዎችን ውጤታማ በሆነና ሰዎችን ወደ ደኅንነት ሊያመጣ በሚችል መንገድ ይጠራቸዋል። በመጀመሪያ፥ በእውነት ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖች ወደ ደኅንነቱ በረከት «የተጠሩ» ተብለው ይታወቃሉ። ጳውሎስ በሮሜ 1፡6-7 ውስጥ ሲናገር፥ የሮማ ክርስቲያኖች ቅዱሳን እንዲሆኑና ወዲያውም የክርስቶለ እንዲሆኑ መጠራታቸውን ይገልጻል። ይህ ጥሪ ተራ ጥሪ አይደለም። ነገር ግን ጥሪው የሮሜን ክርስቲያኖች ቅዱሳን የሚያደርግ ውጤታማ ጥሪ ነበር። በዚህም የኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ጥሪ ነው፡ እንደዚሁም ሐዋርያው በ1ኛ ቆሮንቶስ 12፥ 9 ውስጥ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ቅዱሳን እንዲሆኑ የተጠሩ መሆናቸውንና እንዲሁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው ጥሪ መቀበላቸውን ይገልጻል። ይህ ጥሪ ለርማ ክርስቲያኖች ተራ ጥሪ አልነበረም። ጥሪው በእግዚአብሔር ፊት ቅዱሳን ያደረገና ከኢየሱስም ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው ያስቻለ ጥሪ ነው። እንዲሁም በኤፈሶን 1፡18 ጳውሎስ ስለ ኤፌሶን አማኞች ሲናገር፥ ለወደፊቱ ተስፋና ውርስ የተጠሩ መሆናቸውን ያሳስባል። ይህ ለኤፌሶን ምእመናን የቀረብ ጥሪ ወደ ፊት የሚያገኙትን ሰማያዊ ውርስ የሚያበስር ውጤታማ ጥሪ ነበር። በ1ኛ ተሰሎንቄ 2፡12 ጳውሎስ፥ የተሰሎንቄ አማኞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥትና ክብር የተጠሩ መሆናቸውን ይናገራል። ለእነዚህ ለተሰሎንቄ ምእመናን የቀረበ ጥሪ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አመጣቸው። እንደዚሁም ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12 ውስጥ ጢሞቴዎስ ለዘላለም ሕይወት መጠራቱን ነግሮታል። ይህ ለጢሞቴዎስ የቀረበ ጥሪ፥ የዘላለምን ሕይወት የሰጠው የእግዚአብሔር ሥራ ነው። ቀጥሎም በገላትያ 1፡15-16 ጳውሎስ፥ ኢየሱስ እንደ ገለጠለት የተጠራ መሆኑን ያስረዳል። በፊልጵስዩስ 3፡14 ላይ ጳውሎስ ከሰማይ የሚሰጠውን ሽልማት ለመቀበል የተጠራ መሆኑን ይናገራል። ለጳውሎስ የቀረበለት ጥሪ ኢየሱስን እንዲያውቀው ከማድረጉም በላይ የሰማይንም ስጦታ አረጋገጠለት፡ በዕብራውያን 3፡1 ቅዱሳን ወንድሞች የሰማይን ጥሪ መቀበላቸውንና ይህም ጥሪ ከሰማይ የመጣና ወደ ሰማይ የሚያደርሳቸው መሆኑን ያስገነዝባል። ደሞም በ1ኛ ጴጥሮስ 2፡12 ውስጥ ጰጥርስ ሲናገር አማኞች የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው፥ እነርሱም ከመንፈሳዊ ጨለማ ወደ እግዚአብሔር ብርሃን ተጠርተዋል ይላል። በእነዚህ የተለያዩ ማስረጃዎች አማካይነት ግልጽ ሆኖ ከቀረበው ሁኔታ እንደምንገነዘበው፥ የእግዚአብሔር ጥሪ በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ የመዳንን በረከት የሚያመጣ ውጤታማ ጥሪ ነው። 

1.2 የእግዚአብሔር ጥሪ ከእግዚአብሔር ጋር ወደአለው የጽድቅ ስፍራ ይመራል። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 8:30 አንብቡ። ሀ) አስቀድሞ ስለተወሰኑ ሰዎች እውነቱ ምንድን ነው? ለ) ለለተጠሩት ሁሉ ያለው እውነት ምንድን ነው? 

ሁለተኛው መንገድ ሰዎችን ወደ ደኅንነት የሚጠራ ውጤታማ ጥሪ ሲኖር እንደዚሁም ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ አድርጎ ለሚያቆም ወደዚያ የሚመራ ጥሪ አለ። ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔር አስቀድሞ የመረጣቸውን የልጁን መልክ እንዲላሉ ወሰነ ይላል። ሮሜ 8፡29 በተጨማሪ አስቀድ የመሰናቸውን ጠራቸው፤ የጠራቸውንም አልደታቸው፥ ያጸደቃቸውንም አከበራቸው ይላል። እግዚአብሔር ምሕረቱን ሊሰጣቸው የመረጣቸው ሁሉ . የእግዚአብሔርን ውጤታማ ጥሪ ይቀበላሉ፥ ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸውና በችሎታቸው በእምነት መልስ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል። የተጠሩት ሁሉ ስለ ከበሩና በእግዚአብሔር ፊትም ጻድቃን ስለሆኑ፥ የእግዚአብሔር ጥሪ ውጤታማ መሆኑን እንገዘባለን። በሮማ 8፡29 ውስጥ እግዚአብሔር ያቀረበው ጥሪ ሰምተው የሚቀበሉት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ሆነው እንዲገኙ ዋስትና የሚሰጥ ጥሪ ነው።

1.3 አንዳንዶች የዳኑት ብቻ የሚቀበሉት የእግዚአብሔር ጥሪ አለ። 

ጥያቄ፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡23-24፥ 26-28 አንብቡ። ሀ) የእግዚአብሔር ጥሪ ወደየት ይመራል? ለህ ይህንን ጥሪ የተቀበሉ ብዙዎች ናቸው ወይስ ጥቂቶች? 

ሦስተኛው መንገድ የምንመለከተው ጥሪ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር የሚያመጣ ጥሪ አለ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ከሚያቀርበው ጥሪ ጋር ሲመዛዘን ጥቂቶች ብቻ የሚቀበሉት ጥሪ ነው። በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡23 28 ውስጥ እግዚአብሔር የጠራቸው የቆሮንቶስ አማኞች ብቻ የእግዚአብሔርን ኃይልና ጥበብ የተቀበሉ መሆናቸውን ጳውሎስ ይነግረናል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ለሰዎች ሁሉ ሳይሆን፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ደካሞችና ሞኞች ተብለው ለተመደቡት ለጥቂቶች ብቻ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ኃይሉንና ጥበቡን ለማሳወቅ በእነዚህ ጥቂቶቹ ውስጥ ይሠራል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥሪ፥ ስለ ኢየሱስ ሞትና፥ ትንሣኤ፥ ማለትም አብዛኛው የዓለም ክፍል የሞኝነትና የደካማነት መልእክት አድርጎ የቆጠረውን ለተቀበሉት ነው። 

1.4 የእግዚአብሔርን ውጤታማ ጥሪ የሚቀበሉ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ይመጣሉ። 

ጥያቄ፡– ዮሐንስ 6፡44 አንብቡ። ሀ) ማንኛውም ሰው ወደ ክርስቶስ እንዲመጣ ምን መደረግ አለበት? ለ) ዮሐንስ 6፡37 አንብቡ። በእዚአብሐር ለኢየሱስ ከተሰውት መካከል ስንቶቹ ወደ ክርስቶስ ይመጣሉ? ደግሞስ እርሱ ስንቶቹን ይቀበላል? 

ጥያቄ፡- ሉቃስ 14:16-23 ያለውን ምሳሌ አንብቡ። በእውነት ወደ ግብዣው እነማን መጡ (ቁጥር 21-23)? 

አራተኛው መንገድ፥ እግዚአብሔር ሰዎች ወደ እርሱ እንዲመጡ ለማድረግ የሚያቀርበው ውጤታማ ጥሪ ብቻ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ያመጣል። ስለሆነም ጥሪውን የሚቀበሉ ሁሉ ወደ እርሱ ይመጣሉ። ኢየሱስ በዮሐንስ 6 ውስጥ ሲናገር፥ ማንም ቢሆን በእግዚአብሔር በኩል ወደ ክርስቶስ ይመጣል ይላል፡ አብ የሳበው ብቻ ወደ ክርስቶስ መምጣት ይችላል። ሰዎች በአብ ወደ ክርስቶስ ሊሳቡ የሚችሉት በእርሱ ውጤታማ ጥሪ አካይነት ነው። ይህን ጥሪ የተቀበሉ ሁሉ ጥሪውን ተቀብለው ሊመልሱና ወደ ክርስቶስ ዘንድ ሊመጡ፥ እርሱም ሊቀበላቸው ይችላል። 

ሰዎች ለክርስተስ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ የእግዚአብሔር ጥሪ ይሠራል፥ እንደዚሁም ሰዎች ክርስቶስን እንዲቀበሉ ያደርጋል። ኢየሱስ ይህንን በሉቃስ 14 ምሳሌ ውስጥ ጠቅሶታል። አንድ ሰው ብዙ ሰዎች ወደ ቀብዣው እንዲመጡ ጠራ። ነገር ግን ከተጠሩት ሰዎች አብዛኛዎቹ ሳይመጡ ቀሩ። ከዚህ የተ የግብዣው ባለቤት ሌሎች ሰዎችን ለመጥራት ተገደደ። ቁጥር 23 ላይ እንደሚለው የግብዣው ጌታ በጎዳና ላይ የነበሩ ሰዎች መጥተው እንዲጋበዙ አስገደዳቸው ይላል። በመጀመሪያ ወደ ግብዣው የተጠሩ ሁሉም አልመጡም ነበር። ነገር ግን በመጨረሻው ላይ ወደ ቀብዣው የመጡት ሁሉ ወደ የብዣው ለመምጣት ፍላጎት እንደነበራቸው ተደርገው እንዲገቡ ሆኑ። 

እዚህ ላይ ማስታወስ ያለብን የእግዚአብሔር ጥሪ ብቻ በራሱ ሰዎችን ሊያድን የማይችል መሆኑን ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥሪ የሚመጣው በወንጌሉ አማካይነት ነው። ይህን የወንጌል ቃል የሰሙ መስማታቸውን በንስሐና በእምነት ማረጋገጥ አለባቸው። ወንጌልን ተቀብሎ ይህን በመሰለ መንገድ ስማት ስለ መግለጥ ወይም ስለ ማረጋገጥ በሚቀጥለው ሳምንት ዘርዘር አድርገን እናጠናለን። በመሠረቱ ግን ሰዎች ጥሪውን መቀበላቸው ጥሪውን ተገንዝበው የደረሳቸው ጥሪ ልባቸውን የነካ ለመሆኑ ስሜታቸውን በነፃ እንዲገልጹና የእግዚአብሔርን የማዳን በረከቶች እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል። 

ጥያቄ፦ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡14 አንብቡ። በምን እማካይነት ተጠራን? 

ጥያቄ፡- የሐዋርያት ሥራ 16፡14 እንብቡ፡ ሀ) በሊዲያ ልብ ውስጥ ምን ሆነ? ለ) ከዚህ በኋላ ሊዲያ ምን አደረገች? 

እግዚአብሔር ሰዎችን እንዴት አድርጎ ይጠራል? 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡14 ላይ እግዚአብሔር ሰዎችን በወንጌሉ አማካይነት ይጠራል ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎች ባነበቡት ወይም ሲሰበክ ሆነ ምስክርነት ሲሰጥ ባደመጡት ቃል አማካይነት ይጠራቸዋል። እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች ወንጌልን በሚያዳምጡበት ጊዜ እግዚአብሔርም ልባቸውን ቀስቅሶ ይጠራቸዋል። እነርሱም ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተቀበሉት የምስራች ቃል የበኩላቸውን ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ለመሰለው ሁኔታ ሊዲያ ጥሩ ምሳሌ ናት። ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን ሲሰብክ እንዳዳመጠች እግዚአብሔር ልቧን ቀስቅሶ ወደ እርሱ ዘንድ ጠራት። እርሷም በነፃ ለጥሪው ምላሽ ሰጥታ በእምነት መልእክቱን ተቀበለች። ከዚያም ከተጠመቀች በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስንና ወዳጆቹን ጠርታ በቤቷ እንዲሰብኩ በማድረግ የኢየሱስ ተከታይ መሆንዋን ገለጸች። 

በሰዎች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ጥሪ ለማቅረብ ቀዳማዊ የእግዚአብሔር ወኪል መንፈስ ቅዱስ ነው። 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡7-10 አንብቡ፡ ሀ) እግዚአብሔር የማዳኑን ምሥጢር ጥበብ በማን ገለጠ? ለ) 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡13 አንብቡ። በሐዋርያው ጳውሎስ የተነገረውን በእውነት ያስተምር የነበረው ማን ነበር? 

ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 1-2 እንደተናገረው ብዙ ሰዎች የወንጌል ነገር ሞኝነት ስለሚመስላቸው ይንቁታል። በእውነቱ የወንጌሉ መልእክት ጥበብ ነው። የወንጌሉ ነገር ጥበብ ሊሆን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ሲሠራ በቆየበት ልብ ውስጥ ብቻ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥበብ በወንጌሉ ውስጥ ይገልጣል። ታዲያ መንፈስ ቅዱስ በልባቸው ውስጥ ያስተማራቸው ብቻ መማራቸውን ገልጠው መልእክቱን ሊቀበሉ ይችላሉ። እግዚአብሔርን የመግለጥ ተግባር የሚያከናውነው መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ዘንድ በመጥራቱና ካማሪው የተነሣ በንስሐ ተመልሰው በክርስቶስ እንዲያምኑ ያደርጋል። 

የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ምርጫ በተመለከተ የእግዚአብሔር ጥብቅ ጥሪ የሚያሳስበን፥ እግዚአብሔር ብቻ ሰዎችን ወደ ደኅንነት ማምጣት እንደሚችል ነው። እዚህ ላይ ክርስቶስን ያልተቀበሉ ብዙ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎች አሉ። ወንጌል እንዲህ ላሉ ሰዎች ይደርስ ዘንድ ጠንክረን መሥራትና የሕይወት መሥዋዕትነት ድረስ መክፈል ይጠበቅብናል። ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ በኃጢአታቸው ተጸጽተው እንዲመለሱና የእግዚአብሔርን እውነት እንዲገለጥላቸው ካላደረገ በስተቀር፥ ጠንክረን መሥራታችንና መሥዋዕትነታችን ከንቱ ሊሆን ይችላል። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔር ጥሪውን ሰምተው ወደ እርሱ ዘንድ እንዲመጡና ፈቅደው ክርስቶስን እንዲቀበሉ ካላደረገ በስተቀር፥ ጠንክረን መሥራታችንም ሆነ እስከ 

መሥዋዕትነት ድረስ መጣራችን ውጤት ሊኖረው አይችልም። 

ጥያቄ፡- በትናንትናው ዕለት የክርስቶስን ወንጌል ለመቀበል ልባቸውን ላጠነክሩ ግለሰቦች ጸልያችሁ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሃይማኖተኛ ስለሆኑ ሰዎች ማለትም ጎሳዎች ወይም ብሔረሰቦችና መላው ሕዝብ ሊሆን ይችላል፥ ስለ እነዚህ ልባቸውን ለወንጌል ስላልከፈቱ ሰዎች አስቡ። ከዚያም በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ቢያንስ በምስት ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጻፉና ጸልዩላቸው። እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን እንዲገልጥላቸውና እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንዲጠራቸው ጸልዩላቸው። 

ጥያቄ፡- 2ኛ ጴጥሮስ 1፡5-10 እንብቡ። ሐዋርያው ጴጥሮስ በቁጥር 10 ላይ ሊናገር፣ «መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ ትጉ» ይለናል። ሐዋርያው ክቀደሙት ጥቅሶች ወደ የትኞቹ እያመላከተን ነው? 

በሰዎች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫና ለሰዎች አስፈላጊ የሆነ ጥሪው የሚገለጠው ሰዎች በሚኖሩት ሕይወት ውስጥ ነው። ሐዋርያው በ1ኛ ጴጥሮስ 2፡5-7 ድረስ ባለው ክፍል በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ሊገለጡ ስለሚገባቸው መንፈሳዊ ባሕርያት እንዲህ ይላል፡ እምነት፥ ደነት፥ እውቀት፥ ራስን መግዛት፥ ጽንዓትና መንፈሳዊነት። በቁጥር 8 ላይ ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲናገር፥ እነዚህ ነገሮች ካሉን በክርስትና ሕይወታችን ውጤታማዎችን እንደምንሆን ያረጋግጥልናል። እልፍ ብሎም በቁጥር 9 ውስጥ አክሎ ሲናገር፥ እነዚህ ነገሮች ወይም ባሕርያት ባይኖሩን ደኅንነታችንን ያላስተዋልን እንሆናለን ይላል። ይህ ሲሆን ደግሞ እውነተኞች ክርስቲያኖች መሆናችንን ያላረጋገጠ ሕይወትን እንኖራለን ማለት ነው። 

ስለዚህ ሐዋርያው በቁጥር 10 ላይ ነገሩን ሊያጠቃልል፥ እነዚህን ክርስቲያናዊ የባሕርይ እሴቶቻችንን አብረውን በሚኖሩ ሰዎች መካከል በተግባር ላይ ብናውል ያን ጊዜ ጥሪአችንንና መመረጣችንን ለሌሎች እንዲታወቅ እናደርጋለን ብሏል። በክርስቶስ ያለ እምነት ውጪአዊ ማረጋገጫዎችን ያሳያል። እግዚአብሔር ወደ ራሱ የጠራቸው ሁሉ፥ በሕይወታቸው ውስጥ የእግዚአብሔር የጥሪ ፍሬ ምን እንደሆነ ይረዳሉ። 

ጥያቄ፡- እንደገና 1ኛ ጴጥሮስ 1፡5-10 አንብቡ። ከእነዚህ መንፈሳዊ ባሕርያት ውስጥ የትኛው በሕይወታችሁ ውስጥ እንዲያድግ ትፈልጋላችሁ? እነዚህን እለፈላጊ ነገሮች በተግባር ላይ ለማዋልና ለሌሎች በእግዚአብሔር የተጠራችሁ መሆናችሁን ለማሳየት ሁለት ነገሮችን ጻፉ።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version