Site icon

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

በትናንትናው ትምህርታችን እግዚአብሔር በዓለም ያሉ ሰዎች ሁሉ ደኅንነቱን እንዲቀበሉ አጠቃላይ ጥሪ እንደሚያቀርብ አጥንተናል። ነገር ን በዓለም ያሉ ሰዎች ኃጢአት ስለ ሠሩ፣ በኃጢአት ስለ ታወሩ፣ የኃጢአት ባሪያዎች ስለሆኑ፣ በኃጢአታቸው ስለ ሞቱና እንዳሻቸው ስለሆኑ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የደኅንነት መብት እንደ ናቁ ተመልክተናል። ነገር ግን የእግዚአብሔርን የደኅንነት ስጦታ ቸል ከሚሉት መካከል ለጥሪው ጆሮአቸውን የመስጠት ዝንባሌ ያላቸውን እግዚአብሔር እንደሚመርጥም አስተውለናል። በሮሜ 9 ውስጥ እግዚአብሔር የመረጣቸውን፣ «የተስፋ ልጆች» ሲል እንደ ጠራቸውም ልብ ብለናል። ከሌሎች የአብርሃም ልጆች መካከል ይስሐቅ እንደ ተመረጠ ሁሉ፥ እንደዚሁም ያዕቆብ ከዔሳው ይልቅ ምርማን እንዳገኘ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር የመረጣቸውና እርሱንም የተቀበሉ ብቻ እርሱ የሚሰጠውን ደኅንነት ይቀበላሉ። በአንጻሩ እግዚአብሔር ያልመረጣቸውን እርሱም ችላ ስለሚላቸው እነርሱ ወደ ፈቀዱት ወደ ራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ። 

ነገር ግን ይህ ፍትሐዊ ነው? እግዚአብሔር ያዕቆብን መርጦ ዔሳውን ሲነጋው ፍትሐዊ ያልሆነ ተግባር መፈጸሙ ነው? እንደዚሁም እግዚአብሔር አንዳንዶቹን ሰዎች በመምረጡና እነርሱም የደኅንነት ጥሪውን እንዲሰሙ ሲያደርግና በአንጻሩ ደግሞ ሌሎችን ወደ እርሱ ሳያመጣ ችላ በሚላቸው ጊዜ አድልዎ ማድረጉ ነውን? ጳውሎስ ለእነዚህ ከባድ ጥያቄዎች በሮሜ 9 ውስጥ መልስ ሲሰጥ፥ እግዚአብሔር የደኅንነትን ሉዐላዊ ቁጥጥር በመዘንጋት አልነበረም። በዚህ ፈንታ ሲገልጽም፥ እግዚአብሔር በደኅንነት ላይ ሥልጣን ቢኖረውም ሥልጣኑን የተወሰኑ ሰዎችን ለመምረጥና ሌሎችን በመተው ሥልጣኑን በነሲብ እንዳልተጠቀመበት ይናገራል። በአንጻሩ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ምሥጢራዊና አስደናቂ በሆነ መንገድ የቁጥጥር ሥልጣኑን ምሕረትን ለማዳረስ ይጠቀምበታል። እንዲሁም እርሱ ብዙ ጊዜ የቁጥጥር ሥልጣኑን ደኅንነቱን ሌሎች ብዙ ሰዎች ለማዳረስ ይጠቀምበታል። የእግዚአብሔር ሥልጣን እንዴት እኛ ስለ ደኅንነት ካለን ኃላፊነት ጋር እንደሚስማማ ለሚኖሩት ጥያቄዎች ሐዋርያው ጳውሎስ መልስ የሚሰጠው ትኩረቱን በእግዚአብሔር ታላቅነት ላይ በማድረግና እኛን ስላዳነን እርሱን 

እንድናመልክ ጥሪ በማድረግ ነው። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 9፡14-16 አንብቡ፡፡ ሀ) ደኅንነት በምን ላይ አይመረኮዝም? ለ) ደኅንነት በምን ላይ ይመረኮዛል? 

ጳውሎስ፥ በሮሜ 9፡14-29 ባለው ክፍል እግዚአብሔር በደኅንነት ላይ ስላለው ሥልጣንና አስቸጋሪ ስለሆነው ነገር በመጥቀስ ማብራሪያውን ይጀምራል። ታዲያ እግዚአብሔር የተወሰኑ ሰዎችን መርጦ ሊያድን ሳለ ሌሎችን ደግሞ አለማዳኑ ፍትሐዊ አይደለም ያለኘዋል? እግዚአብሔር በሥልጣኑ ሰዎችን ለማዳን የሚሠራባቸውን ሁኔታዎች በሦስት ጠቃሚ መንገዶች አማካይነት መልስ ይሰጥበታል። 

1. ለጥያቄዎቹ የጳውሎስ የመጀመሪያው መልስ፡- የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት ማንኛውም ሰው ሊድንበት የሚችል ብቸኛው መንገድ ስለ መሆኑ ነው። 

በመሠረቱ ማንም ሰው ለምሕረቱ ስጦታ ብቁ ስላልሆነ እግዚአብሔር ምሕረቱን ለጥቂቶች መስጠቱ ፍትሐዊ አይደለም አያሰኘውም። ለዚህ ማስረጃ ጳውሎስ በቁጥር 5 ውስጥ ከዘጸአት 33፡19 በመጥቀስ ያቀርባል። ይህ የእግዚአብሔር ቃል የመጣው የእስራኤል ልጆች በሲና ተራራ የወርቅ ጥጃ በማምለክ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ ነበር። ሙሴ እስራኤላውያን ለዚህ የወርቅ ጥጃ መስገዳቸውን እንዳወቀ የጥጃ ውን ምስል ደምስሶ የእግዚአብሔርን ምሕረት ለመለመን ወደ ሲና ተራራ ሄደ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር መላ እስራኤልን ለማጥፋት ሥልጣን እንደ ነበረው ሙሴ ያውቅ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር በምሕረቱ ሕዝቡን እንዲታደገው እንጂ እንዳያጠፋው ለመነው። 

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ የመለሰለት እንዴት ነበር እግዚአብሔር መልሱን የሰጠው እርሱ የምሕረት አምላክ መሆኑን በማሳወቅ ነበር፡ ለእርሱ ምሕረት መሠረታዊ ባሕርይው ስለሆነ ለሕዝቡ ራራለት ለጣዖታት እንዳይሰግዱ ሕግ ሰጥቶአቸው ነበር። እስራኤል ግን ያንን ሕግ ትእዛዝ ሻረ። ምንም እንኳን ሕዝቡ ጥፋት የሚገባው ቢሆንም፥ እግዚአብሔ በዚህ ምክንያት ሕዝቡን በሙሉ አልደመሰሰም። ይልቅለ መሐሪ አምላ በመሆኑና ርኅራኄ ባሕርይው ስለሆነ ምሕረቱን ሰጥቶ አብዛኛዎቹን ከጥፋት ተቤዣቸው። 

ጳውሎስ ይህን ክፍል ካዘጸአት ውስጥ በመጥቀስ ማንም ሰዉ ለእግዚአብሔር ደኅንነት በራሱ ብቁ አለመሆኑን አመልክቷል። እንዲህ ሮሜ 9፡16 ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ምሕረት ስለፈለገ ወይም ጠንክ በመሥራቱ እንደማያገኝ በግልጽ አስቀምጦታል። ይህ እንግዲህ ሁሉም ወ የመንገዳቸው እንዲሄዱ ስለተተዉ የእግዚአብሔርን ምሕረት የሚሻ ወይና ለማግኘት የሚጥር አልነበረም! ማንም ቢሆን ምሕረትን ሊያገኝ የሚችለዉ እግዚአብሔር በሥልጣኑ ምሕረትን ሊሰጥ ሊፈቅድ ብቻ ነው። እንደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማንኛውም ሰው በደለኛ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ቅጣት መቀበል ይኖርበታል። እግዚአብሔር እንደ ሰዎች ክፋት አፀፋውን ፍርድ ሊሰጥ ቢወስን ኖሮ ሰዎች ሁሉ ወደ ሲኦል በወረዱ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር የምሕረት አባት ስለሆነ፥ ቸርነትን ለማድረግ የዘወትር ፈቃዱ ከመሆኑ የተነሣ አዛኝና ርኅሩኅ ነው። ስለዚህ በሥልጣኑና በሁሉን ቻይነቱ ለጥቂቶች ደኅንነትን ለመስጠት መረጠ። 

አንድ ጊዜ አንድ ወታደር የጦር ሠራዊቱን ደንብ በመተላለፉ ምክንያት የሞት ቅጣት ተፈረደበት። የወታደሩም እናት ይህን ጊዜ ወደ ጄኔራሉ ዘንድ መጥታ ልጅዋን ምሕረት ሰጥቶ ከሞት እንዲያተርፍላት ተማጠነችው። ጄኔራሉ ግን መልሶ፥ ወታደሩ ደንብ የተላለፈ ወንጀለኛ በመሆኑ ፍትሕ የእርሱን ሞት እንደሚጠብቅ ነገራት። የልጁም እናት፥ «እኔ ስለ ፍትሕ እልጠየቅሁህም፥ የእኔ ልመና ምሕረት ነው» አለችው። ጄኔራሉም መልሶ፣ «ግን እኮ ምሕረት የማይገባው ሰው ነው» አላት። ከዚህ በኋላ የወታደሩ እናት ጥበባዊ መልስ ሰጠችው፣ «ክቡር ጄኔራል፣ ምሕረት የሚገባ ነገር ከሆነማ ምሕረት ሊባል አይችልም፥ እኔ ግን የምጠይቀው ስለ ምሕረት ነው» አለች። ጄኔራሉ በዚህች ሴት መልስ ተደነቀ። ከዚያም በሰጠው ምሕረት ወታደሩ ልጅዋ ከሞት ሊድን ቻለ። 

በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጆች ሁሉ በኃጢአታቸው ምክንያት በድለዋል። የፍትሕ ጥያቄም በደለኛች ሁሉ ለሠሩት ኃጢአት ቅጣት የእግዚአብሔርን ቁጣ እንዲቀበሉ ነው። ማንም ምሕረት አይገባውም። ልክ እንደዚህ ጄኔራል፥ ሰዎች ምሕረትን ስለ ተመኙ ወይም ለማግኘት በጎ ሥራ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር ምሕረትን አይሰጣቸውም። ደግሞም እግዚአብሔር ባለብዙ ምሕረት የሚሆነው ሰዎች ምሕረትን ለማግኘት ብቁዎች ስለሆኑ አይደለም፡፡ ሰዎች ምሕረትን ለማግኘት ብቃት ካላቸውማ ምሕረትም ምሕረት አይሆንም። ልክ እንደዚህ ጄኔራል፤ እግዚአብሔር ምሕረቱን የሚሰጠው ምሕረትን ለመስጠት በሥልጣኑና በሉዓላዊነቱ ስለሚፈቅድና ስለሚመርጥ ነው። ምሕረት ምሕረት ሊሆን እንዲችል ሁልጊዜ ሥልጣናዊ የምርጫ ስጦታ መሆን አለበት። ምሕረት ምሕረት ይሁን ከተባለ በራስ ብቃት ወይም በመልካም ሥራ የሚገኝ መሆን የለበትም። እንዲሁም ምሕረት ምሕረት ይሁን ከተባለ በምሕረት ሰጪው በጎ ፈቃድ የሚሰጥ ሊሆን ይገባል። ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉ ቅጣት የሚገባቸው ቢሆኑም፣ እርሱ የምሕረት አምላክ በመሆኑ በሥልጣኑ ጥቂቶችን ለማዳን ምሕረቱን ይሰጣቸዋል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህ የእግዚአብሔር ምሕረት ሰለ እርሱ ይሰማችሁ ዘንድ እንዴት ያደርጋል? ለ) ስለ ደኅንነታችሁላ እንዴት እንድታስቡ ያደርጋል? 

አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች በደኅንነት ጉዳይ ላይ ስለሚኖራቸው ድርሻ ከፍ ያለ አስተሳሰብና ምት አላቸው። ስለሆነም አንዳንድ ጊዜ እነርሱ የጻኑ ሲሆኑ ሌሎች ባለመዳናቸው ስለ ራሳቸው በመጠኑ ኩራት ይሰማቸዋል። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ትንሽ ብልጥነት፥ ትንሽ ታዛዥነትና ትሕትና ደግሞም ክርስቶስን ካልተቀበሉት ሰዎች ይልቅ መንፈሳዊ ነገሮችን የመገንዘብ ችሎታ ያላቸው መስሎ ይሰማቸዋል። በተጨማሪም በአካባቢአችው ከሚገኙ አማኝ ካልሆኑ ሰዎች ይልቅ መድኃኒት እንደሚያስፈልጋቸው በማወቃቸው የተሻሉ የመሆን ስሜት ይከሠትባቸዋል። ስለዚህ ይህ ክፍል እግዚአብሔር ለእኛ ራርቶ ምሕረቱን እንዲሰጠን ያደረገው ግንዛቤአችን ወይም ለመዳን የምናደርገው ጥረት አይደለም። ሁላችንም እንደ ሌሎች ሁሉ በኃጢአታችን ምክንያት በድለናል። እንደ ማንኛውም ሰው የእግዚአብሔር ቅጣት የሚገባን ነን። እኛ ሁልጊዜ ማስተዋል የሚገባን ደኅንነትን ልናገኝ የቻልነው እግዚአብሔር የምሕረት አባት በመሆኑና እኛንም ለማዳን ስለ ጠራን ነው። 

ጥያቄ፡- ስለ ደኅንነታችሁ በልባችሁ ውስጥ ስለተሰማችሁ የኩራት ሁኔታ በማስታወሻ ደብተራችሁ ውስጥ ጻፉ። ይህን አጉል ስሜታችሁን እየተናዘዛችሁ አጭር ጊዜ በጸሎት እሳልፉ። እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የምሕረትና የርኅራኄ አሳት ስለሆነ አመስግኑት። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 9፡17-29 አንብቡ። ሀ እግዚአብሔር በምን ምክንያት ፈርዖንን አስነሣው (ቈ 17)? ለ) ሐዋርያው ጳውሎስ በሸክላ ሠሪውና በሸክላው ምላሱ ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ምንን እስተማረ፧ በአሳባችሁ ውስጥ የሚመጡትን ነገሮች በሙሉ ጻፉ። ሐ) እግዚአብሔር ሊቀበሉት ያልፈለጉትን በምን ምክንያት ይታሣቸዋል? 

ጥያቄ፡- በሮሜ 9፡25-26 ላይ ጳውሎስ ሆሴዕ 2፡23ና እንዲሁም ምዕራፍ 1፡10 ይጠቅሳል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የእግዚአብሔር ሕዝብ ባልሆኑት ላይ ምን ይደርሳል? 

ጥያቄ፡- በሮሜ 9፡27-29 ባለው ክፍል ጳውሎስ ኢሳይያስ 10፡22-23 ና ምዕራፍ 1፡9ን ይጠቅሳል። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት፥ ከእስራኤል ሕዝብ ስንቱ ይድናሉ? ለ) እግዚአብሔር እስራኤልን ለማዳን ጣልቃ ባይገባ ኖር በእስራኤል ላይ ምን ይደርስ ነበር? 

2. ሁለተኛው ትምህርት ሰዎችን ለማዳን የእግዚአብሔር ምሕረት እንዴት እንደሚሠራ ሲሆን፥ ይህም የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት የተሰጠው እጅግ ጥበበኛ፥ ሁሉን ቻይና ፍትሐዊ በሆነ ፈጣሪ ነው። 

ጥንታውያን ግሪኮችና ሮማውያን በዓለም ላይ ለሚታየው ክስተት ሁላ ምክንያት ሊሰጥበት አይችልም ብለው ያምኑ ነበር። እነርሱም እንደሚያምኑት፥ የዓለም ዕድል ወይም መጨረሻም እንዲሁም በውስጥብ የሚኖሩ ሰዎች ዕድልና ዕጣ ጨካኝና ፍርደ ገምድል በሆነ «እግዜር» እጅ ነወ ይሉ ነበር። ጳውሎስ በሮሜ 9፡19-21 ውስጥ እንዳመለከተው፥ እግዚአብሔር ጨካኝና ውሳኔውን በዘፈቀደ የማያደርግ ደግሞም ለሚፈጽመው ተግባር ጥንቃቄ የሚያደርግ አምላክ መሆኑን ይገልጻል። እግዚአብሔር ተንከባካቢ ፍጹማዊ፥ ሙሉ በሙሉ ጠቢብ፣ የሚያደርገውን በዕቅድ የሚፈጽም የፍጥረቱን ሕይወት ሁሉ የሚቆጣጠር አምላክ ነው። እግዚአብሔር እን ፈጣሪነቱ ከሰዎች ይልቅ ጠቢብና ሁሉን ቻይ ነው። በዚህ ምክንያትም እርስ በፍጹምነቱና በጻድቅነቱ የሚታመንበት አምላክ ነው። የሸክላ ሠሪው ውሳኔ ሁልጊዜ ለመልካም ዓላማ እንደ መሆኑ ሁሉ፥ በእግዚአብሔር ውሳኔም ውስጥ መልካም ዓላማ አለ። ሸክላ ሠሪ ሁልጊዜ ጠንካራና ያማረ፥ ለጥቅምም የሚበጅ የሸክላ ዕቃ ለመሥራት ይጥራል። እግዚአብሔርም ለፍጥረታቱ ሕይወት የሚጠቅመውን ሁሉ ያደርግላቸዋል። የሚሠራ የሸክላ ዕቃ የሠሪውን አሳብና ፈቃድ ካለመረዳቱም በላይ ሠሪው የሚሠራውን ለምን ዓላማ እንደሚያደርገው እንደማያውቀው ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ፍጥረታትም እንደዚሁ የእግዚአብሔርን አስተሳሰብና ዓላማ ሊደርሱበት ስለማይችሉ የሚሠራውን ለምን እንደሚሠራው መረዳት ያቅታቸዋል። አንድ ነገር ግን እውነት ነው። ይህም የእግዚአብሔር ውሳኔ የተመሠረተው እርሱ ለፍጥረታቱ ሁሉ ለመስጠት በፈቀደው የምሕረት ስጦታ ላይ ነው። እንደዚሁም እግዚአብሔር ከፍጥረታቱ በላይ ታላቅና ጠቢብ ስለሆነ እርሱ ስለሚያደርገው ውሳኔ ማንኛውም የመጠየቅ መብት የላቸውም። 

ነገር ግን ጳውሎስ ሲናገር፥ «የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል» ይላል (ቁጥር 18)፥ እናም ከፍጥረታቱም ጥቂቶቹ «ለጥፋት የተዘጋጁትን» (ቁጥር 22) ናቸው። ታዲያ እንዲህ ማለት እግዚአብሔር ጥቂቶቹ ወይም አንዳንዶቹ ደኅንነትን እንዳያገኙ ይከለክላቸዋል ማለት ነው? ደግሞስ እርሱ እንዲቀጣቸው አንዳንዶቹን ሰዎች ጨካኞች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል? የዚህ መልስ በሦስተኛው ትምህርት፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት በሚለው ክፍል ይቀርባል። 

3. ሦስተኛው ትምህርት፥ እግዚአብሔር በሉዓላዊ ሥልጣኑ ሰዎችን በምሕረቱ ያድናል ሲባል ራሱን ለማክበርና ለሌሎችም ምሕረቱን ለመስጠት እርሱን ለመቀበል ችላ ባሉት ነፃ ውሳኔ ይጠቀማል። የሌሎችን ነፃ ፈቃድ በመጠቀም እግዚአብሔር ለአንዳንዶች ሉዓላዊ ምሕረቱን ያበዛል። 

ጳውሎስ አንዳንድ ዕቃዎች «ለጥፋት የተዘጋጁ» ናቸው ሲል፥ እግዚአብሔር አንዳንዶቹን ሰዎች ጨካኞች በማድረግ ለቅጣት ያቀርባቸዋል ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ምሕረትን እንዲያገኙ ያደርጋቸዋልም ማለት አይደለም። በአንጻሩ የሚለው፥ ሰዎች እግዚአብሔርን ለመቀበል ችላ ሲሉ፥ እግዚአብሔር ባዘጋጀውና ወደ ጥፋት በሚወስደው መንገድ ላይ ራሳቸውን ያደርጋሉ ማለቱ ነው። ሰዎች ራሳቸው የገዛ መንገዳቸውን ይመርጣሉ። ነገር ግን እግዚአብሔርም ይህ መንገድ ወደ ጥፋት እንደሚያደርስ ወስኖአል። አንድ ሰው በራሱ ፈቃድ ይህን መንገድ ሲመርጥ እግዚአብሔርም በራሱ መንገድ ወይም በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ይተዋቸዋል። 

ሰዎች ይህን ወደ ጥፋት የሚመራቸውን መንገድ በሚመርጡበት ጊዜ እግዚአብሔር ውሳኔአቸውን ለራሱ መከበሪያ ይጠቀምበትና ምሕረቱን ለሌሉች ይሰጣል። ምሕረቱንም ወደ እርሱ ክብር የሚወስደውን መንገድ ለመረጡት ለመስጠት ሲል እርሱን የሚቃወሙትን ችላ በማለት በትዕግሥት ይቀበላል (ቁጥር 22-23)። 

ጳውሎስ ይህን ትምህርት ለማስተማር በሦስት ምሳሌዎች ይጠቀማል፦ 

ሀ. የመጀመሪያው ምሳሌ ትናንት በትምህርታችን ውስጥ ያገኘነው የኤሳው ምሳሌ ነው (ሮሜ 9፡10-13)። ዕብራውያን 12፡16-17 ያለው ክፍል እንደሚያስተምረው፥ ኤሳው በነፃ ፈቃዱ ቁሳዊ ነገሮችን ከእግዚአብሔር ማስቀደምን መረጠ። ሌሎችን ነገርች ከእግዚአብሔር ባስቀደመ ጊዜ ወደ ጥፋት የሚወስደውን ጎዳና መረጠ። እግዚአብሔርም እርሱ በራሱ በፈቀደው መንገድ እንዲሄድ ተወው። እግዚአብሔር ምሕረቱን ለያዕቆብ ለመስጠት ወደደ። እግዚአብሔር የኤሳውን የልብ ጥንካሬ ለያዕቆብ ምሕረት ወደ መስጠት ለወጠው። ሊ ሁላተኛው ምሳሌ ፈርዖን ነው። 

ጥያቄ፡- ዘጸአት 8፡15፣ 32 እና 9፡34 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት የፈርዖንን ልቦና ማን አጠነከረው? 

ዘጸአት 8፡15፥32 እና 9፡34 እንደሚያስረዳን፥ ፈርዖን በመጀመሪያ በነፃ ፈቃዱ ልቡን ለማጠንከርና እስራኤልን በባርነት ለማቆየት መረጠ። ፈርዖን በነፃ ፈቃዱ ይህን መንገድ መረጠ፤ እግዚአብሔርም ወደ ጥፋት የሚወስደውን ይህን መንገድ ይሄድባት ዘንድ ተወው። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ በበለጠ በማጠንከር በዐመፅ ምርጫው እንዲገፋበት አደረገ። ከዚያም እግዚአብሔር በፈርዖን ዐመፀኝነት ምርጫ ተጠቅሞ እርሱ ከግብፅ ጣዖታትና ከግብፅ ሠራዊት በላይ ኃያል መሆኑን ለእስራኤልና ለዓለም ለማሳየት ቸነፈር ላከበት። እግዚአብሔር የፈርዖንን ዐመፀኝነት ተጠቅሞ፥ የእርሱን የማዳን ኃይልና እስራኤልን በምሕረቱ ከባርነት እንደሚያላቅቃቸው አሳየ። እግዚአብሔር የማዳንና የምሕረት ኃይሉን በመግለጽ ራሱን አከበረ። ከዚያም የፈርዖን የልብ ድንዳኔ ለእስራኤል ምሕረት በመስጠት ተጠቀመበት። 

ሐ. ሦስተኛው ምሳሌ የእስራኤልና የአሕዛብ ነው። ጳውሎስ በሮሜ 9፡25-26 ውስጥ ትንቢተ ሆሴዕ 2፡23 እና 1፡10ን ይጠቅሳል። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ሳቢያ ሊያስተምረን የፈለገው እግዚአብሔር አሕዛብን ለማዳን ሲል ግድ ያልነበራቸውንና ለእግዚአብሔር ጥሪ መልስ የማይሰጠ አይሁዶችን እንደታሠ ነው። የሆሴዕ ታሪክ እግዚአብሔር ዐመፀኞች ለነበሩ እስራኤላውያን የነበረውን የትዕግሥት ፍቅርን የሚያመለክት ነው። እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ናቁ፥ ስለዚህ «ሕዝቡ አልሆኑም»፥ እንዲሁም «እርሱ የሚወዳቸው አልሆኑም» (ሮሜ 9፡25)። ሊጠፉ ሲገባቸው ሊያጠፋቸው አልፈቀደም። ይልቅስ ታገሳቸው። ለምን? ትዕግሥቱም አንዳንዶቹን ለማዳን ነበር። እነዚያ የእርሱ ሕዝብ ያልሆኑት አንድ ቀን መልሰው የእርሱ እንዲሆኑ በማሰብ ነበር። ጳውሎስ ይህን ክፍል እግዚአብሔር ለእሕዛብ ላለው የደኅንነት ዓላማ ይጠቀምበታል። እግዚአብሔር፥ እስራኤላውያን ክርስቶስን ንቀው ላይቀበሉት ሲቀሩ ታገሣቸው። ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ግልጽ ለሆነ ዓላማ ሲሆን፥ ዓላማውም አሕዛብን ለማዳን ነበር። 

እንደዚሁም እግዚአብሔር ከአይሁዶች መካከል ቅሬታዎቹን ለማዳን ሲል እርሱን ያልተቀበሉትን ታሣቸው። የእነርሱ ዐመፅ ማለት ቅሬታዎች ብቻ እንደሚኖሩ ነው። እነዚህን ቅሬታዎች በጸጋው ይጠብቃል። ቁጥር 27-29 ውስጥ ጳውሎስ ከኢሳይያስ 10፡22-23 እና 1፡9 ይጠቅሳል። በዚህ ክፍል ከእስራኤል መካከል ቅሬታዎችን በምሕረቱ እንደሚጠብቅ እግዚአብሔር ያስተምረናል። አዎን፣ በእስራኤል ላይ ሳይዘገይ በፍጥነት ይፈርዳል። ነገር ግን እስራኤልን አይረሳትም። የሕዝቡንም ዐመፅ ጥቂቶች አማኞችን ለማትረፍና ለመጠበቅ ይጠቀምበታል። እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ሳይሆን ኖሮ መላው እስራኤል እንደ ሰዶምና ገሞራ ጨርሶ በጠፋ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ በጥቂቶች ዐመፀኝነት ተጠቅሞ ቅሬታዎችን ለመጠበቅ ለሌሎች ምሕረቱን ይሰጣል። 

ስለ እስራኤል ልጆች ከብሉይ ኪዳን ውስጥ በተጠቀሱት ሰእነዚህ ሁለት ክፍሎች እንደተመለከትነው የእስራኤል ልጆች በራሳቸው ፍላጎት የጥፋትን መንገድ መረጡ። ስለሆነም እግዚአብሔር በጥፋት መንገዳቸው እንዲቀጥሉ ተዋቸው። ከዚያም እግዚአብሔር ውሳኔአቸውን ለራሱ መከበሪያ በመጠቀም ምሕረቱን ለሌሎች አይሁዶችና ለአሕዛብ ሰጠ። 

ስለ ኤሳው፣ ፈርዖንና እስራኤል የቀረቡት ትምህርታዊ ምሳሌዎች እንደሚያስገነዝቡት እግዚአብሔር የፍጥረታቱን ነፃ ፈቃድ ሳይጥስ ሉዓላዊ ምሕረቱን በሥራ ላይ ለማዋል በሚመርጡበት መንገድ እርሱም ጉዞአቸውን እንዲቀጥሉበት ያደርጋል። ከዚያም እርሱን ለመቀበል በሚያሳዩት ዳተኝነት ተጠቅሞ ራሱን በማክበር ምሕረቱን ለሌሎች ይሰጣል። 

እግዚአብሔር በሉዓላዊ ምሕረቱ አማካይነት እንዴት ሰዎችን ወደ እርሱ እንደሚያመጣ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። እንደዚሁም እግዚአብሔር በሉዓላዊ ሥልጣኑ ምሕረቱን ለጥቂቶች ሲሰጥ፥ ለሌሎች ደግሞ ሳይሰጥ ይቀራል። ታዲያ በእነዚህ እርስ በርስ በሚቃረኑ ሁለት ድርጊቶች መካከል ስላለው ልዩነት ስናስብ ተስፋ አለመቁረጣችን መልካም ነው። ምንም እንኳን ስለ እነዚህ ሁለት ድርጊቶች እኛን መገንዘብ ቢያዳግተንም መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም ነጥቦች ልጽ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ሁለት አስቸጋሪ እውነቶች እንዴት ሊስማሙ እንደሚችሉ የሚያስረዳ አንድ የቀድሞ ታሪክ አለ። እርሱም ወደ ሰማይ በሚወስደው መንገድ በር ላይ እንዲህ የሚል ምልክት አለበት «ማንም ሰው ሎጥቶ በነፃ ሊገባ ይችላል።” ግን አንድ ሰው በበሩ አልፎ ሲገባ የበሩን ሌላ ቀን ይመለከታል። በበሩ ውስጠኛው ጎን እንዲህ የሚነበብ ልዩ ምልክት ይታያል «ዓለም ከመመሥረቱ በፊት የተመረጠ» ይላል። ሰዎች በነ ፈቃዳቸው ተመርጠው ክርስቶስን ሊቀበሉ ወይም ላይቀበሉ ይችላሉ፡ ምርጫው የራሳቸው ነው። ጻሩ ን ሰዎች ሁሉ በኃጢአት የጠሩ በመሆናቸው ምክንያት የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ምሕረት ያገኙት ብቻ ወደ ሰማይ በር ዘልቀው ይገባሉ። 

እ.ኤ.አ. በ1800 ዓ.ም መጨረሻ ቻርልስ ስፐርጀን የተባለ ሰባኪ በእንግሊዝ አገር ነበር። እርሱም በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት አጥብቆ ያምን ነበር። አንድ ጊዜ ይህ ሰባኪ ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥልጣንና ታላቅነት ለሚጠራጠሩ ክርስቲያኖች እንዲሰብክ ተጋበዘ። ሰዎቹም ስለዚህ ሉዓላዊነት ይጠራጠሩ የነበሩት ሁኔታው እግዚአብሔርን ፍትሕን የማይሰጥና የሰውን ነፃ ፈቃድ የሚያጠፋ ያደርገዋል ብለው ስለፈሩ ነበር። ስፐርጀን ስብከቱን ሊያሰማ ሳለ ምእመናኑ ለማታቸው ተነክቶ ነበር፥ ኋላም እንዲህ አለ፥ «አሁን ጥቅሌ ወደ ምርጫ አስተምህሮ ያመጣኛል» አለ። ይህን ጊዜ ምእመናኑ ጸጥ አሉ። ኋላም ስፐርጀን ምእመናኑን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፥ «ክርስቲያኖች ከሆናችሁበት ጊዜ ጀምሮ በሕይወታችሁ ውስጥ ለውጥ ታይቷል?» ምእመናኑንም ቀበል አድርገው፣ «አዎን፥ አሜን» ሲሉ አፀፋዊ መልስ ሰጡ። «ታዲያ ለውጡ እንዲመጣ ያደረገው እናንተ ናችሁ? ወይስ ጌታ ነው?» ሲል ጠየቃቸው። «እግዚአብሔር ነው ለውጡን ያመጣው» አሉ ምእመናኑ። «አዎን፥ እንግዲህ ይህ የምርጫ አስተምህሮ ነው» አላቸው። «ጌታ ልዩነትን ያመጣል።» 

እንግዲህ ይህ ጳውሎስ በሮሜ 9 ውስጥ እና በሌሎችም ክፍሎች በትናንቱ ትምህርታችን ላይ የተመለከትነው ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ለውጥን ያደርጋል። ያለ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት በስተቀር፥ ማንም ሰው ቢሆን ለወንጌል ጥሪ መልስ በመስጠት ወደ ክርስቶስ ሊመጣ ከቶ አይችልም። እንደዚሁም ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት በስተቀር ማንም ሰው ሲሆን የእግዚአብሔር የተስፋ ልጅ መሆን አይችልም። እንግዲህ ይህ ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ስለ ሰው ልጅ ኃላፊነት ያሉንን ጥያቄዎች ሊመልስ አይችልም። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ታላቅ ክብርና አምልኮን ሊያመጣ ይችላል። 

ጥያቄ፡- ስለ አንድ ልቡን በክርስቶስ ወንጌል ላይ ስላጠነከረ ወዳጃችሁ አስቡ። ሀ) ይህን ሰው ወደ ክርስቶስ ሊያመጣው የሚችል ብቸኛው ነገር ምንድን | ነው? ለህ ይህ ሰው ወደ ክርስቶስ እንዲመጣ፥ እንዴት ልትረዱት ትችላላችሁ? 

የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ምሕረት ባንቀበል የእግዚአብሔርን ጥረ ሰምተን ክርስቶስን ለመቀበል አለመቻላችንን የሚያስገነዝበን ትምህርት ለሕይወታችን ተግባራዊ ትምህርት አለው። አንድ ሰው ልቡ ወይ አእምሮው ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ ለመቀበል የሚያስችለዉ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህ እንግዲህ ክርስቲያኖች ሁሉ በአእምሮአቸe ውስጥ ሊይዙት የሚገባ ጠቃሚ ነገር ነው። ምንም እንኳን ሁላችንን፡ እምነታችንን ለሌሎች ማካፈል ቢኖርብንም፥ ማንም ሰው በራሱ ችሎ፡ ወይም በማግባቢያ ቃላቱ ስቦ ሌላውን ሰው ወደ ክርስቶስ ሊያመ አይችልም። ስለሆነም የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምሕረት ብቻ የሰውን ልብ ከፍቶ ወደ ክርስቶስ ደኅንነት ሊያመጣ ይችላል። አንድ ሰው ሌላውን ሰ« ወደ ክርስቶስ ለማምጣት እግዚአብሔር ምሕረቱን ለዚህም ሆነ ሌሎ ለሚያምኑ ሰዎች ይሰጥ ዘንድ በትሕትና መጸለይ አለበት። ሰዎችን ዉ ክርስቶስ የሚያመጡ አማኞች በመጀመሪያ መመስከር አለባቸው። ይህን በራሳቸው ኃይልና ጥበብ ላይሆን በእግዚአብሔር ኃይልና በእግዚአብሐ መንፈስ ጥበብ ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አለባቸው። ስለዚህ የእግዚአብሎ ምሕረት ብቻ ሌላውን ሰው ወደ ክርስቶስ ሊስበው ይችላል። 

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version