የዳዊት መዝሙር፥ በብሉይ ኪዳን ጊዜ የእስራኤል የዝማሬ መጽሐፍ ነበር። እንደዚሁም መዝሙረ ዳዊት ጥንት እስራኤላውያን የሚዘምሩትና በቃል የሚደግሙት የቅኔና የመዝሙር መጽሐፍ ነው። አብዛኛዎቹ መዝሙሮች የተጻፉት በዳዊት ነው። ሌሎቹ ደግሞ በመንፈስ በተመሩ ሰዎች የተጻፉ ናቸው። ሰሎሞን ለአብነት የሚጠቀስ ነው (ለምሳሌ፥ መዝሙር 72)። አንዳንዶቹ መዝሙሮች ስለ ደራሲው የሚናገሩ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ነገሥታት ስለ አንዱ የሚናገሩ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ እነዚህ ጸሐፊዎች ስለ ክርስቶስ ትንቢት እንዲናገሩ ጭምር አላቀደላቸውም። ሆኖም አብዛኛዎቹ መዝሙሮች ስለ ዳዊት ወይም ስለ ሌሎቹ ነገሥታት ወይም ስለሚመጣው መሢሕ የሚናገሩ ናቸው። አንዳንዶቹ መዝሙሮች ስለ ዳዊትና ስለ ሌሎች የእስራኤልና የአይሁድ ነገሥታት በአመልካችነት በትምህርት ምሳሊያዊ (ሲምቦል) ወይም በዘይቤአዊ ስልት የሚናገሩ ሲሆኑ፥ ነገር ግን ዋናው ዓላማቸው በመሢሑ ላይ ስለሚደርሰው ሁኔታ አንድ በአንድ በትንቢት ማስቀመጥ ነው። ከእነዚህ ጥቂቶቹ የሥቃይ መዝሙሮች ናቸው (ለምሳሌ፡- መዝሙር 22)። ሌሎቹ መዝሙራት ደግሞ አዲስ ንጉሥ በሚነግሥበት ቀን የሚዜሙ መዝሙሮች ናቸው (መዝሙር 2)። እኛ ዛሬ የምናጠናቸው መዝሙሮች ትንቢታዊ የሆኑትን በእርግጥ በይዘታቸው ስለ ክርስቶስ የሚያስረዱትን ይሆናል።
መዝሙር 2
ጥያቄ፡- መዝሙር 2 አንብቡ። ሀ) የሚነሡት የምድር ነገሥታትና ገዥዎች እነማን ናቸው (መዝ. 2፡2)? ለ) እርስ በርሳቸው ምን ሲሉ ተማከሩ (መዝ. 2፡2)? ሐ) እግዚአብሔር በእነዚህ ገዢዎች ላይ ምን አደረገ? መ) በቅዱሱ ተራራው ላይ እግዚአብሔር ማንን ሾመ (መዝ. 2፡6)? ሠ) በቁጥር 1 ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ትእዛዝ ምንድን ነው? ረ) በቁጥር 8-9 በምድር ሕዝቦች ላይ ምን ይደርስባቸዋል ይላል? ሰ) እግዚአብሔር ለምድር ሕዝቦች ምን ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል?
መዝሙር 2 ስለ ክርስቶስ በመላው ብሉይ ኪዳን ከተጻፉት ትንቢቶች መካከል አንዱና እጅግ በጣም ግልጽ የሆነው ነው። ስለሆነም በመዝሙር 2 ላይ የተጻፈው ትንቢት በክርስቶስ መፈጸሙ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በጥቂቱ ሰባት ጊዜ ተነግሮአል። መዝሙር ሁለት የሚጀምረው የዓለም ሕዝቦች በእግዚአብሔርና እግዚአብሔር በቀሳው ላይ በዐመፅ መነሣታቸውን በመጥቀስ ነው። ሕዝቦቹም የታሠሩበትን ሰንሰለት አውልቀው ለመጣል መፈለጋቸውን ተናገሩ። ይህንን ሲሉ የእግዚአብሔርን የገዢነቱን ሥልጣን ከላያቸው ላይ አውልቀው ለመጣል የነበራቸውን ፍላጎት መግለጻቸው ነበር። እግዚአብሔር ግን በዚህ የዐመፅ ባሕርያቸው ሳቀ። በመሠረቱ እግዚአብሔር ኃያልና ሁሉንም ነገር የሚቆጣጠር በመሆኑ፥ የሰው ልጆች የቁጣ ዐመፅ ሊያስፈራራው ከቶ አይችልም። እግዚአብሔርም በዚህ የሰዎች ሁኔታ ከመሸበር ይልቅ በቀጥታ ወደ ሾመው ንጉሥ ያመለከታል። ይህ ንጉሥ በእርሱ የተቀባው ነው። ይህ መዝሙር በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔርን ይፈሩ ስለነበረ የእስራኤልና የይሁዳ ነገሥታት ለማመልከት ያገለግል ነበር። እነዚህ ነገሥታት እግዚአብሔር ቀብቶ በሕዝቡ ላይ የሾማቸው ስለነበሩ በእርሱ የተቀቡ ነበሩ። ይህ መዝሙር ሕዝቦች በእርሱና የእርሱ በሆኑ ሰዎች ላይ በዓመፃ ቁጣ በተነሡ ጊዜ ማንኛውም ነገር በእርሱ ቁጥጥር ሥር እንደሆነ በማስረገጥ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የማጽናኛ ቃል ሆኖ ያገለገለ ነበር። ስለሆነም ማንኛውም ነገር በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ስለሚውል በዐመፅ የሚነሣው ሕዝቦች የእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ሥጋትን ሊያስከትሉ አይችሉም።
በቁጥር 7 ውስጥ ንጉሡን በተመለከተ፥ እግዚአብሔር ትእዛዙን ይፋ ያደርጋል። በአማርኛው ቃል ትእዛዝ የሚለው አገላለጽ በዕብራይስጡ ግን የእግዚአብሔር ይፋዊ ማስታወቂያ ወይም መግለጫ ነው። እግዚአብሔርም የተቀባውና ከዚያም የሚገዛው ልጁ መሆኑን በይፋ ይገልጻል። ትናንትና ከ2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 7 በተማርነው ትምህርት ይህ ተስፋ በንጉሥ ሰሎሞን አማካይነት መፈጸም እንደ ጀመረ ተከታትለናል። እግዚአብሔርን ይፈሩ የነበሩ የይሁዳ ነገሥታት፥ መለስ ብለው እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውን ተስፋ በማስታወስ እነርሱም የተስፋው ወራሾች እንደሆኑ ያስቡ ነበር። በእግዚአብሔር የተቀቡ ስለነበሩ፥ እነርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ነበሩ። በቁጥር 8 ውስጥም መግለጫው ወይም ማስታወቂያው ይቀጥላል። አንድ ቀን እንደ እግዚአብሔር ልጅነታቸው በአረማውያን ሕዝቦች ላይ ገዥዎች በመሆን፥ የሚያምፁባቸውን ሁሉ ይደመስሳሉ። ስለዚህ የዓለም ነገሥታት ለእግዚአብሔር ሊሰግዱና እርሱን ሊያገለግሉ፥ እንደዚሁም ንጉሥ የሆነውን ልጁን ሊያከብሩ ይገባል።
ምንም እንኳን ይህ መዝሙር እግዚአብሔርን ይፈሩ ወደ ነበሩት ወደ ይሁዳ ነገሥታት በመጠኑም ቢሆን የሚያመለክት ቢሆንም፥ ሰሎሞንም ወይም እግዚአብሔርን ይፈራ የነበረ የትኛው የይሁዳ ንጉሥ በ2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 7 ውስጥ የተጻፈውን ወይም በመዝሙር 2 የተገለጸውን የተስፋ ቃል ሙሉ በሙሉ ሊፈጽሙ አልቻሉም ነበር። ነገር ግን ፍጹም የእግዚአብሔር ልጅ በሆነውና በእግዚአብሔር ተቀብቶ የዓለም ገዥ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ በመዝሙር 2 ውስጥ የተጻፈው ትንቢት መፈጸሙን አዲስ ኪዳን ደጋግሞ ያመለክታል።
ጥያቄ፡- የሐዋ. 4፡25-27 አንብቡ። ሐዋርያት የመዝሙር 2 ትንቢት በዚህ ክፍል መፈጸሙን እንዴት ተገነዘቡት?
ይህ በሐዋርያት ሥራ 4፡25-27 የተጻፈው ቃል የሚያመለክተው፥ የአይሁድ መሪዎች ሐዋርያትን በኢየሱስ ስም እንዳይሰብኩ ካስጠነቀቋቸውና ሰብከው ቢገኙ ግን እርምጃ እንደሚወስዱባቸው ካስፈራሯቸው በኋላ እንደ ጸለዩ ነበር። ሐዋርያት የጌታን ስቅለትና ይህን የደረሰባቸውን ማስፈራሪያ በመዝሙር 2 ውስጥ ለተነገረው ትንቢት ከፊል ፍጻሜ እንደሆነ ተመለከቱ፡፡ ኢየሱስ የጌታ ቅቡዕ ነበር። የምድር ገዥ ዎችና ሕዝቦች እግዚአብሔር በቀባው ላይ እንደሚያምፁ ይህ መዝሙር ተንብዮ ነበር። ስለሆነም ኢየሱስን መስቀላቸውና ወንጌሉንም እንዳይሰብኩ ሐዋርያትን መቃወማቸው በእግዚአብሔር ገዢነትና እርሱ በቀባውም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማመጻቸው ነበር።
ጥያቄ፡– ማቴዎስ 3፡16-17 አንብቡ። በተጠመቀበት ዕለት እግዚአብሔር አብ ጌታ ኢየሱስን ማን ብሎ አለታወቀው?
ጥያቄ፡- የሐዋ. 13፡33 አንብቡ። የኢየሱስ ትንሣኤ ምንን አመለከተ?
ጥያቄ፡- ዕብራውያን 1፡5 እና ዕብራውያን 5፡5 አንብቡ። በእያንዳንዱ ሁኔታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው መግለጫ ምንን ያመለክታል?
እግዚአብሔር የቀባው እርሱ ልጁ መሆኑን የገለጸበትን መዝሙር 2፡7ን የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በመደጋገም ይጠቅሱታል። በተጠመቀበትም ቀን እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ የሚወደው ልጁ መሆኑን አስታውቆአል። ስለሆነም ይህ ጌታ በተጠመቀበት ዕለት በስፍራው ተገኝተው የነበሩት እግዚአብሔርም ስለ ልጁ የተናገረውን ቃል ያዳመጡ ሰዎች በመዝሙር 2 ውስጥ የተነገረው ትንቢት ትዝ ሳይላቸው አልቀረ ይሆናል። እንደዚሁም ኢየሱስ እርሱ የተቀባው መሆኑንና በመዝሙር 2 ውስጥ ተጽፎ የነበረውን ትንቢት ሊፈጽም የሚመጣ ንጉሥ መሆኑን እያስታወቀ እንደ ነበረ ሳይነዘቡት አልቀሩም። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 13፡33 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ፥ ከሞት የተነሣው ልጁ መሆኑን እግዚአብሔር ማስታወቁን ይናገራል። ትንሣኤው ለመላው ዓለም ያሳወቀው የእግዚአብሔር ትንቢትና ስለ ልጁም የሰጠው ተስፋ በኢየሱስ ሙሉ በሙሉ መፈጸሙን ነው። ዕብራውያን 1፡5፤ ኢየሱስ በመዝሙር 2፡7 ውስጥ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜ እንደሆነና ከዚህም የተነሣ ከመላእክት ሁሉ እንደሚልቅ ይናገራል። እንደዚሁም ዕብራውያን 5፡5 እግዚአብሔር ክርስቶስ ልጁ መሆኑን ማሳወቁ እርሱ እግዚአብሔር የቀባው ንጉሥ መሆኑን ብቻ ሳይሆን፥ በተጨማሪም እርሱ እግዚአብሔር የቀባው ካህን መሆኑንም ያመለክታል ይላል።
ጥያቄ፡- ሀ) ራእይ 12፡5፣ 19፡15 እንብቡ። እነዚህ ክፍለ ምንባቦች በመዝሙር 2፡8-9 የተጻፈው ትንቢት እንዴት ይፈጸማል ይላሉ? ለ) ራእይ 2፡26–27 አንብቡ። ክርስቶስ በሕዝቦች ላይ ገዥ በሚሆንበት ጊዜ የሥልጣኑ ተካፋይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
በመዝሙር 2፡8-9 በተሰጠው ትንቢት መሠረት አንድ ቀን የዳዊት ልጅ ማለትም የእግዚአብሔርም ልጅ የሆነው እርሱ መላ ዓለምን ይገዛል።
ስለሆነም ሕዝቦችን በጠንካራ አኳኋን ይገዛል። በእርሱ ላይ የሚያምፁትንም ሁሉ ይደመስሳል። ራእይ 12፡5፥ 19፡15 ደግሞ ክርስቶስ ጠላቶቹን ለማጥፋትና መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት ሲመጣ ትንቢቱ እንደሚፈጸም ያመለክታል። ከዚህም በስተቀር፥ ራእይ 2፡26-27 ድል የሚያደርጉና ለክርስቶስ የሚታዘዙት በዚያን ጊዜ አብረውት እንደሚገዙ አክሎ ይናገራል።
ጥያቄ፡– በመዝሙር 2 ስለተጻፉት የትንቢት ቃላት አስቡ። ሀ) ምንም እንኳን ብዙ ሕዝቦችና ገዥዎች የሚቃወሙት ቢሆንም፥ ክርስቶስ ብሩክ የእግዚአብሔር ልጅና የዓለም ገዢ በመሆኑ ምን ይሰማችኋል? ለ) ክርስቶስ አንድ ቀን መላውን ዓለም እንደሚገዛና፥ የእርሱ ተከታዮች የሆኑትም አብረውት እንደሚገዙ የተገለጸው አሳብ እንዴት ይሰማችኋል?
በመዝሙር 2 ውስጥ የሚገኙት ትንቢቶች ዛሬ አማኞች የሚያገለግሉት የዓለምን ገዢ ስለ መሆኑ ጠንካራ ማሳሰቢያዎች ናቸው። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጁ ለመሆኑና ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ የተቀባ ገዥ ለመሆኑ ትንሣኤው ቋሚ ማረጋገጫ ነው። ምንም እንኳን ብዙ ሕዝቦችና ገዥዎች ክርስቶስን ቢቃወሙና የእርሱ የሆኑትን ሕዝብ ቢያሳድዱም፥ ክርስቶስ ዛሬም በኃያልነት በዙፋኑ ላይ ሆኖ ዓለምንና መላዋን ያስተዳድራል። እርሱን በታማኝነት የሚያገለግሉት ሁሉ አንድ ቀን ከእርሱ ጋር ምድርን አብሮ የመግዛት ሥልጣንን ይቀዳጃሉ። ስለዚህ እኛ ስለ እርሱ በምንሠቃይበት ጊዜ እነዚህ ተስፋዎች ሊያጽናኑን በታማኝነት እንድንቆም ሊረዱንና በአስቸጋሪ ሁኔታዎችም ሳይቀር እንድናገለግለው ሊያደርጉን ይገባል። ይህ ብቻ አይደለም፥ ለእውነተኛው የምድር ገዥ ጸንተን በመቆማችን አንድ ቀን እንሸለማለን፡፡ ስለሆነም የዓለም ገዥዎች ክርስቶስን ሲንቁና ሲሳለቁበት ስናይ እነዚህ ተስፋዎቹ ሲያበረቱን ይገባል። እነሆ፥ አንድ ቀን ክርስቶስ እውነተኛው የምድር ንጉሥ መሆኑ በይፋ ይታወጃ ል።
መዝሙር 22
ጥያቄ፡- መዝሙር 22ን በዝግታና በጥንቃቄ አንብቡ። ከዚያም በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደ ተደገሙ ወይም እንደ ተፈጸሙ የምታስታውሷቸውን እያንዳንዶቹን ሐረጎች ጻፉአቸው።
መዝሙር 22 በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ክፍሎች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ጠለቅ ብሎ የተጻፈ ትንቢት ነው? ይህ ትንቢት በክርስቶስ ስቅለት ሙሉ በሙሉ የተፈጸመ መዝሙር ነው። ምናልባት ዳዊት ይህን መዝሙር ስለ ግል ሕይወቱ ጽፎት ከነበረ ይዘቱ እርሱን ሊመለከተው የሚችለው በተዘዋዋሪ መንገድ ነው እንጂ በቀጥታ ሊሆን አይችልም።
በዚህ መዝሙር በቁጥር 1 ውስጥ መዝሙረኛው እግዚአብሔር ተወኝ ብሎ ይጮኻል። ማቴዎስ 27፡46 (እና በማርቆስ 15፡34) እንደምናነበው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ ይህንኑ ቃል ጠቅሶ ጓል። ይህ በሆነበት ወቅት እግዚአብሔር ወልድ የዓለምን በደልና ኃጢአት በመሸከሙ ምክንያት 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 እግዚአብሔር አብ ክልጁ ጋር የነበረውን ግንኙነት እቁሞ ነበር። ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለያል። ኢየሱስም የዓለምን ኃጢአት በተሸከመ ጊዜ ከእግዚአብሔር ተለይቶአል። ስለዚህ በዚህ ቃል በመጠቀም የሥቃይ ጩኸት ጮኾአል። ከዚህ ወቅት በፊት እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር አብ ለዘላለም ፍጹም የሆነ ግንኙነት ስለነበራቸው ይህ የሥቃይ ጊዜ ለክርስቶስም ሆነ ለአባቱ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ እንደ ነበረ ግልጽ ነው። ሆኖም በሁለቱ መካከል የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው ለእኛ ደኅንነትን ለማምጣት ነበር።
ከቁጥር 3-5 ባለው ክፍል መዝሙረኛው እግዚአብሔር ቀድሞ ሕዝቡን እንዳዳነ በመጥቀስ ሕዝቡ ሲሠቃይ የማዳን ኃይል እንዳለው ያስታውሳል። ነገር ግን መሠቃየቱን ቀጠለ። ሰዎች ልክ እንደ ትል ቆጥረው ናቁት። በቁጥር 7 ውስጥ የተነገረው ትንቢት ኋላ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ሰዎች ያወረዱበትን የስድብ ቃላት ያመለከተ ዝርዝር ትንቢት ነበር (ማቴዎስ 27፡41-43፤ ማርቆስ 15፡31-32፤ ሉቃስ 23፡35)።
መዝሙረኛው ከቁጥር 9-11 ባለው ክፍል ዘማሪው፥ በእግዚአብሔር እንደሚታመን እንደገና ገለጸ፡፡ ምንም እንኳን በተሠቃየ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ የተለየ ቢሆንም፥ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ አብሮት እንደ ነበረ ያውቅ ስለነበር፥ በእርሱ መታመኑን ቀጠለ። ነገር ግን ቁጥር 12-16፥ ውስጥ በወቅቱ ይሰማው ወደነበረው የሥቃይ ሁኔታ ይመለሳል። ይህን ሥቃይ ያመጡትንም ሰዎች እንደ እንስሳት አድርጎ ይገልጻቸዋል። ስለሆነም በሬዎች ሊወጉት እንደ ተንደረደሩ፥ አንበሶች ሊቦጫጭቁት እንደ ተነሡ፥ ውሾችም ሊነክሱት እንደ ከበቡት ይናገራል። እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ኋላ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል በነበረ ጊዜ፥ ሰዎች ያደረሱበትን ስድብ ያመለክታሉ። ቁጥር 14-15 ያለው ደግሞ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በየትም ስፍራ ተለይቶ ባይጠቀስም፥ በሚሰቀል ሰው ላይ የሚያደርሰውን መከራ ሁሉ ዘርዝሮ የሚያስረዳ ነው።
አንድ ሰው በመስቀል ላይ በሚሰቀልበት ጊዜ የሰውነቱ ክብደት አጥንቶቹን ከያሉበት መገናኛዎች ቀስ በቀስ ይስቧቸዋል። ልቡም እየደከመ ወደሚመጣው ሰውነት ደም በማስተላለፍ ረገድ ጉልበቱ እስከሚሟጠጥ ድረስ በኃይል ይገፋል። የተሰቀለ ሰው ትንፋሽን ለማቆየት በሚያደርገው ትንቅንቅ ሰውነቱን ከምስማሮቹና ችንካሮቹ ላይ ለማስለቀቅ ባለው ኃይል ሁሉ ይታገላል። ከዚህም የተነሣ ሰውነቱ ውስጥ ያለውን ፈሳሽ በላብ ስለሚጨርሰው ወዲያው ይደክማል። ዮሐንስ 19፡28 በተገለጸው የስቅላት ደረጃ ላይ ያለውን የኢየሱስን ጥማትና ድካም ያመለክታል። ሰውነቱ በመስቀል ላይ ተወጥሮ ስለነበረ፥ አጥንቶቹ አግጥጠው ቆዳውን ገፍተው ይታዩ እንደ ነበር ቁጥር 17 ይገልጻል። በቁጥር 18 ላይ የኢየሱስ ልብስ መከፋፈሉን በተመለከተ የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን በመጨረሻ በማቴዎስ 27፡35 (እንደዚሁም በማርቆስ 15፡24፤ ሉቃስ 23፡34፤ ዮሐንስ 19፡24) የተገለጸው ያስረዳል።
መዝሙረኛው ከቁጥር 12-18 እንደ ገለጸው ከፍ ያለ ሥቃይ ቢደርስበትም በእግዚአብሔር ላይ የነበረውን እምነት በበለጠ ማሳየቱን በቁጥር 19-21 ቀጠለ። ኢየሱስም ወደ አባቱ መጸለዩን በቀጠለበት ወቅትና በሚሞትበት ሰዓት ነፍሱን በእጁ ያኖረው እምነትም ይህንኑ የመሰለ ነበር (ሉቃስ 23፡26)። ኢየሱስ በውስጡ እያለፈ ከነበረበት የከፋ ሥቃይ ባሻገር፥ እግዚአብሔር አሁንም ታማኝ እንደሆነና ከእርሱ ጋር ወደነበረው ፍጹም የሆነ ግንኙነት መልሶ እንደሚያመጣው ያውቅ ነበር።
ከቁጥር 22-31 ያለው ክፍል ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ የተጻፈ ትንቢት ሆኖ አይታሰብም። ነገር ግን የትንቢቱ ጠቃሚ ክፍል ነው። ምንም እንኳን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ቢሠቃይም፥ እግዚአብሔር ኢየሱስን ችላ ብሎ ወይም ንቆ አልተወውም (ቁጥር 24)፡፡ ከሥቃዩም የተነሣ ሰዎች ከእሥራኤልና (ቁጥር 22–23) ከመላው ዓለም (ቁጥር 26-29) ከመጪው ትውልድም ቢሆን (ቁጥር 30-31) ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ያመልኩታል፥ ያገለግሉታል። እነዚህ ጥቅሶች በአጠቃላይ ኢየሱስ በስቅለቱ ለመላው ዓለም የሚሰጠውን ደኅንነት የሚያሳዩ አስደናቂ የሆኑ የትንቢት ቃላት ናቸው።
ጥያቄ፡- ይህን መዝሙር በምታጠኑበት ጊዜ ምን ያህል ስሜታችሁን ወደ ክርስቶስ ይስበዋል? እያንዳንዳችሁን ምን እንደሚሰማችሁ ጻፉና ይህን ስሜታችሁን ለእርሱ በጸሎት ግለጹለት።
ጥያቄ፡– ከሌሎች ጋር ወንጌልን በመካፈል ረገድ በዚህ መዝሙር እንዴት ትጠቀማላችሁ? ሁለት ወይም ሦስት አሳቦችን ጻፉ።
መዝሙር 22 ክርስቶስን እንደ መድኃኒታቸው ለማያውቁት ሰዎች ለመስበክ ኃይል ያለው መዝሙር ነው። በመጀመሪያ ይህ ክፍል ለተፈጸሙ ትንቢቶች አስደናቂ ምሳሌ ነው። ይህ መዝሙር ከሺህ ዓመታት በፊት ገና ሁኔታው ሳይፈጸም ክርስቶስ በስቅላት እንደሚሞት በሰፊው ጽፎአል። ከዚያም አዲስ ኪዳን እነዚህ ትንቢቶች እንዴት በትክክል እንደ ተፈጸሙ ያሳያል። ስለዚህ ለወዳጆቻችን ስለ ጌታ በምንመሰክርላቸው ጊዜ እነዚህን የተፈጸሙ ትንቢቶች ልንገልጽላቸው እንችላለን። እርሱ የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች እንደ ፈጸመ ልናሳያቸው ዕድሉን እናገኛለን። ሁለተኛው ይህ መዝሙር 22 ክርስቶስ ለኃጢአታችን ብሎ ምን ያህል እንደ ተሠቃየ ያስረዳናል። ስለዚህ እኛ አማኞች ይህን መዝሙር በምናነብበት ጊዜ ሁሉ፥ ስሜታችንን በምሥጋና በተሞላ አምልኮ ለክርስቶስ ማቅረብ ይኖርብናል። ሁላችንም እርሱ ደኅንነትን ሊሰጠን ብሎ ያንን ሁሉ መከራ እንደ ተቀበለ በጸሎታችን አስታወሰን ስለ አድራጎቱ ሁሉ ማመስገን አለብን። እንደዚሁም ምስጋና የተዋሃደ ታዛዥነታችንን ልንገልጽለት ይገባናል። የክርስቶስንም ትእዛዝ በምንፈጽምበት ጊዜ፥ «ስለ እኔ ስለሞትክልኝ ክብር ምስጋና ይድረስህ» የምንልበት አንዱ የከበረው መንገድ ይሆንልናል። ከሁሉም አብልጠን ስለ ጌታ ሞትና ይህም የእርሱ ሞት ሕይወታችንን እንዴት እንደ ለወጠው ለሌሎች ማካፈልን ማዘውተር ይገባናል። ብዙ ሰዎች በአካባቢአችን ክርስቶስ መሰቀሉን ያውቃሉ፤ ነገር ግን በምን ምክንያት እንደ ተሰቀለ አውቀው ጌታን እንዲያመሰግኑ ያስተማራቸው ሰው የለም። ከእነዚህ ሰዎች ብዙዎች ለክርስቶስ ክብርን የመስጠት ፍላጎት ቢኖራቸውም ለመስቀል ሞቱ ላኽ ከሁሉም የሚለው ክርስቶስን የክበሪያ ንግድ ለዮል ኃጢአት ዕዳቸው ሙሉ ክፍያን ያለገኘው ይህ ሞት መሆኑን ማን እንደሆነ ማንም ነገራቸው የለም፡ ይህ በመሆኑ፥ እኛ በክርስቶስ የምናምን ሁሉ ስለ ክርስቶስ ሞት በአካባቢአችን ለሚገኙ ሰዎች ማስተማርና መመስከር አለብን፡
መዝሙር 10
ጥያቄ፡– መዝሙር 110 አንብቡ። ሀ) በቁጥር 1 ውስጥ እዚአብሐር ላማን ነው የሚናገረው? ለ) በዚሁ ቁጥር ውስጥ ምን ሹመትስ ይሰጠዋል? ሐ) እንደ ቀጥር 23 እግዚአብሔር በዚህ ሰው ጠላቶች ላይ ምንን ይፈጽማል? ) በቁጥር 4 ለይህ ሰው ምን ሹመት ይቀበላል?
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ስለ ክርስቶስ መምጣት ከተጻፉት ሁሉ፥ መዝሙር 110 የተናው የመዝሙር ትንቢት መሆኑን ያምናሉ። ስለሚመጣው መሣሕ ኃይል ሥልጣን በቀጥታ የሚያመለክት መዝሙር ነው። በቀር አንድ ላይ በእርሻው እግዚአብሔር ተብሎ የተተረጎመው፥ በዕብራይስጥ ህዌ የሚለው ነው። ጌታዬ ተብሎ በአማርኛ የተተረጎመው ቃል በዕብራይስጥ አዶናይ የተባለው ነው። ባለፈው ሳምንት እንደ ተከታተልነው ሁሉ ህዌ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር የግል ስም ነው። እናይ ለት ጌታ፡ አለቃ» ማለት ነው። እዚህ ላይ ዳዊት የሚለው እግዚአብሔር ለራሱ ላዛዊት ጌታው ለሆነ ሰው እየተናገረ እንዳለ ነው። ይህ ለዊት ጌታው የሆነው ሰው ስእግዚአብሔር ቀኝ እንዲቀመጥ ተፈቀደለት ይላል። በጥንቱ የዙሩን መንበር የንጉሡ ቀኝ የክብርና የሥልጣን ስፍራ ነበር፡ ስለሆነም ጥንት አንድ ሰው በንጉሡ ቀኝ እንዲቀመጥ ከተፈቀደለት፥ ይህ ሰው ራሱ እንደ ልዑላን ቤተሰብ ንግሥናን ተላብሶ ኃይልና ሥልጣን ይሰጠው ነበር፡ ጻዊት ክብረ ንግሥናን ተጎናጽፎ በእግዚአብሔር የሚመጥና መለኮታዊው ኃይልና ሥልጣን ያለው አንድ ሰው እንደሚነግ ትንቢት ይናገራል፡ እስራኤላውያንም ይህን ትንቢት የሚፈጽም ታላቁ ንጉሥ ከዳዊት ቤት ይመጣል ብለው በተስፋ ይጠባበቁ ነበር። ይህ የሚመጣውም ንጉሥ ሚሑ ወይም የተቀባው ሲሆን፥ እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት የእስራኤልን ጠላቶች ሁሉ የሚያሸንፍበት ነው።
ሚሢሑ የእስራኤልን ጠላቶች የሚያሸንፍ ታላቅ ንጉሥ ብቻ ሳይሆን ካህን” ሆኖ ይሾማል፡ ዳዊትና ዘሮቹ ከይሁዳ ሐረቀ የተገኙ ናቸው። በቤተ መቅደስ ውስጥ የሃይማኖት ጉዳዮችን ይፈጽሙ የነበሩ ካህናት የአሮን ዘር ነበሩ፡ አርን ደሞ ከሌዊ ዘር ነበር። ሆኖም አንድ ሌላ እግዚአብሔርን የሚፈራ ካህን የነበረ ንጉሥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ነበር። እርሱም መልክ ዜድቅ ይባል ነበር፡ ባለፈው ሳምንት እንደ ሰማነው፥ መልከ ጸዴቅ የአንዱ እውነተኛ አምላክ ካህንና ንጉሥ ነበር፡ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አማላጅ ሆኖ የሚም፥ አንድ ቀን ንጉሥ ሆኖ በእግዚአብሔር የሚቀባ ካህን ከዳዊት ዘር እንደሚመጣ ነበር።
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 22፡44 አንብቡ። በዚህ ክፍል ኢየሱስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ችለው የማይመልሱትን ጥያቄ ይጠይቃቸዋል። ታዲያ በዚህ ጥያቄ ላይ ውስጠ ታዋቂ የነበረው መልስ ምን ነበር?
ጥያቄ፡- የሐዋ. ሥራ 2፡32-34 አንብቡ። ጴጥሮስ የመዝሙር 110ን ፍጻሜ እንዴት ተመለከተው?
ጥያቄ፡- ዕብራውያን 1፡13 አንብቡ። እንደ ዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፥ መዝሙር 110፡1 ስለ ኢየሱስ ምንን ያመለክታል? 29ኛ ጥያቄ፡- ዕብራውያን 7፡11-19 አንብቡ። ሀ) እንደ ዕብራውያን መልእክት ደራሊ፥ የመልከ ጼዴቅና የክህነት ሹመት ይዞ የመጣ ካህን ምንን ያሳያል? ላ) እንደ ቁጥር 16 ከሆነ የመልከ ጼዴቅን የክህነት ሹመት ለማግኘት መሠረቱ ምንድን ነው?
ኢየሱስና ተከታዮቹ መዝሙር 110ን ስለ እርሱና ስለ አገልግሎቱ የሚናገር ትንቢት አድርገው በመውሰድ ብዙ ጊዜ ከዚህ መዝሙር ይጠቅሱ ነበር። በማቴዎስ 22፡44 ላይ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ከአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ባደረገው የመጨረሻው ውይይት መዝሙር 110፡1 ጠቅሶ ተናግሮ ነበር። ይኸው ነጥብ በማርቆስ 12፡36 በሉቃስ 20፡42 ውስጥ ተጽፎ ይገኛል። በዚህ ውይይቱ እግዚአብሔር የጻዊት ጌታና አለቃ ከሆነው ጋር መነጋገሩን ገለጠላቸው። ኢየሱስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን፥ መዝሙር 110 በእግዚአብሔር ስለሚቀባው ንጉሥ፥ ስለ መሢሑ የሚናገር መሆኑ በአይሁዶች ዘንድ የታወቀ ነበር። ታዲያ ይህ ሰው ከዳዊት ዘር የሚወለድ ከሆነ፥ እንዴት ዳዊት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? እንዴትስ ከእርሱ ዘር የሚነሣ ሰው ጌታው ይሆናል? ይሁን እንጂ የሃይማኖት መሪዎቹ ለማንም ሰው ግልጽ መስሎ የታየውን መልስ ለመስጠት ሐፍረት ያዛቸው። ይህም ነጥብ፥ መሢሑ የዳዊትም ጌታ ሊሆን የሚችለው ከሰብአዊ ፍጡር በላይ ሆኖ ከተገኘ ብቻ መሆኑን ነው። መሢሑ ክዳዊት ዘር የሚወጣና የዳዊት ጌታ ሊሆን የሚችለው መለኮታዊ ከሆነ ብቻ ነው። ኢየሱስ ይህን ጥያቄ በማቅረብ፥ የሚመጣው መሢሕ ከሰብአዊ ፍጡር በላይ መሆኑንና፥ መለኮታዊ ኃይልና ሥልጣን እንዳለው ብሉይ ኪዳን በውስጠ ታዋቂ እንደሚጠቅስ ለሃይማኖት መሪዎች ለይቶ አመልክቷል።
በሐዋ. 2፡34 እንደተጻፈው ጰጥሮስ ሲናገር መዝሙር 110 ኢየሱስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ በልዩ መንገድ ፍጻሜ አግኝቷል። ዳዊትም ቢሆን ከዘሮቹ አንዱ እንኳ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ሰማይ ያረገ እንደሌለ ገለጠላቸው። እንዲህ ማለት መዝሙር 110 በዳዊትም ሆነ በዘሮቹ ገና ከፍጻሜ አልደረሰም ማለት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣትና መንፈስ ቅዱስን በማፍሰስ፥ ወደ እግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ብሎ ውለኮታዊ ኃይልንና ሥልጣንን የ ቀዳጀ መሢሕና በእርሱ የተቀባ ንጉሥ ኢየሱስ መሆኑን አረጋገጠ። በዚህም መለኮታዊ ኃይልና ሥልጣንን ተጎናጸፈ። ትንሣኤ ዕርገትና የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ኢየሱስ መዝሙር 10ን ለመፈጸሙ ማስረጃ ሆነዋል።
እንደዚሁም የዕብራውያን ጸሐፊ ኢየሱስ የመዝሙር 110፡1 ፍጻሜ መሆኑንም አመልክቷል። በመቀጠልም፥ ኢየሱስ ከሹመትም የበለጠ ሹመት አግኝቶ መለኮታዊ ሥልጣንና ኃይል ለብሶ በአባቱ ቀኝ ስለ ተቀመጠ ከመላእክት ሁሉ በላይ ነው በማለት ያስረዳል። እንደዚሁም በመዝሙር 110፡4 ተስፋ መሠረት፥ የአሮን የክህነት ሥልጣን ምሉዕነት የሌለው በመሆኑ እንደሚያበቃና የመልከ ጼዴቅ ዓይነት ካህን እንደሚመጣ ይናገራል። መዝሙር 110 «ከዘላለም ካህን ነው» (ዕብ. 7፡7) ስለሚል፥ በመልከ ጼዴቅ ምሳሌ የሚመጣው ካህን «የማይሻር ሕይወት» (ዕብ. 7፡16) ይኖረዋል ይላል። የኢየሱስ ትንሣኤና ዕርገት ሕይወቱ የማይሻር መሆኑን ስለሚያመለክቱ እርሱ የዘላለም ካህን ይሆናል። ዕብራውያን 7 ኢየሱስ የመዝሙር 110፡4 ፍጻሜ መሆኑን ይነግረናል። እርሱ ክህነቱ ከአሮን የበለጠና አሮንንም የሚተካ ካህን ንጉሥ ነው። ከዚያም በመቀጠል ክርስቶስ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ስለ መሆኑ እንማራለን።
ጥያቄ፡- መዝሙር 110፥ የሚመጣው መሢሕ የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚያሸንፍ ኃይል ያለው ንጉሥና ፍጹም አማላጅ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ታላቅ ካህን እንደሚሆን ይናገራል። በእውነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ኃያል ንጉሥና ፍጹም አማላጅ ከሆነ፥ እኛስ እንዴት ነው ምላሽ ልንለጠው የሚገባን?
መዝሙር 110 አሁን ኢየሱስ ያለበትን ከፍተኛ የክብር ስፍራ የሚያስገነዝብ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ኃያል ንጉሥ በመሆኑ በአፋጣኝ እያንዳንዱን ትእዛዛቱን ሳናንገራግር መታዘዝ አለብን። ሕይወታችንንም እርሱን ለማገልገልና መንግሥቱን ለማስፋፋት አሳልፈን መስጠት አለብን። እንደዚሁም እርሱ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ የሚያቀርበን ፍጹም አማላጃችን ስለሆነ፥ ሌሎች ወደ እግዚአብሔር መምጣት እንዳለባቸው በማስተማርና በማበረታታት ጊዜአችንን ማሳለፍ አለብን።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
