Site icon የሕይወት እንጀራ

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

This entry is part 64 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

አንዳንድ ሰዎች ይቅርታ የማይደረግበት አንድ ኃጢአት አለ ብለው ይፈራሉ። ስለዚህ ይህን ኃጢአት ብናደርግ ደኅንነትን እናጣለን፥ ይቅርታም አይደረግልንም ብለው ይጨነቃሉ። ታዲያ ይህ «ይቅርታ የማይደረግለት ኃጢአት» ተብዬው ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ማቴ. 2፡22-32 አንብብ። ሀ) ፈሪሳዊያን ኢየሱስን በሰይጣን ኃይል አጋንንትን ያወጣል ማለታቸው በምን ምክንያት ሞኝነት ሆኖ ተቀጠረባቸው? (ቁ 26) ለ) ኢየሱስ አጋንንትን በእግዚአብሔር ኃይል የሚያወጣ ከሆነ፥ ይህ ምንን ያረጋግጣል? (ቁ 28) 

በማቴ. 12፡22-32 ውስጥ ኢየሱስ ጋኔን ያደረበት ዓይነ ሥውርና ዱላ ሰው መፈወሱ ተጽፎአል (ቁ 22)። ይህን ተአምር የተመለከቱ ሰዎች ድርጊቱ መሢሐዊ ድርጊት መሆኑን ወዲያውኑ አስተዋሉ (ቁ 23)። እንደ መዝ (146)፡8፤ ኢሳ. 29፡18፤ 38፡5-6 ካሉት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች በመነሣት መሢሑ እንዲህ ያሉ ተአምራትን ይፈጽማል ብለው ይጠባበቁ እንደ ነበር ተጽፎአል። ስለዚህ «ይህ ሰው ኢየሱስ በእውነት መሢሑ የዳዊት ልጅ ይሆንን?» ሲሉ በአድናቆት ጠየቁ። ፈሪሳውያን ግን ስለ ኢየሱስ ኃይል ሌላ የሚሉት ነገር ነበራቸው። በብዔል ዜቡል ኃይል ይጠቀማል ሲሉ ከሰሱት፥ ብዔል ዜቡል የሰይጣን ሌላ ስሙ ነው (ቁ 24)። 

ኢየሱስ ግን ፈሪሳውያን የመሠረቱበትን ክስ በሦስት መንገዶች መለሰ። በመጀመሪያ፥ ሰይጣን የራሱን ሥራ የሚያበላሽ ሞኝ አይደለም በማለት ትክክለኛ ያልሆነ ክሳቸውን ውድቅ አደረገው። ሰይጣን የሰውን ሕይወት በውስጡ በሚኖረው አጋንንት የሚያጠፋ ከሆነ አጋንንቱ ከሰውዬው እንዲወጣና ሰውዬውም ሕይወቱ ዳግም ታድሶ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ፈጽሞ አያደርግም። ይህ ደግሞ በሰውዬው ሕይወት ውስጥ የሚፈጽመውን ክፉ ሥራ የሚገታና መንግሥቱን የሚያፈርስበት ነው። ሰይጣን ደግሞ የራሱ የሆነ አጋንንትን አባሮ በማውጣት በፍጹም መንግሥቱን አያፈርስም አላቸው (ቁ 25-26)። ኢየሱስ በመጀመሪያ ለፈሪሳውያን የመለሰላቸው መልስ ሰይጣን ራሱን ስለማያጠፋ ክሳቸው ሐሰት መሆኑን የሚያመለክት ነው። 

የኢየሱስ ሁለተኛው መልስ እርሱ አጋንንትን ያወጣበት የኃይሉ ታላቅነት፥ ያደረገው ታምራት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ ከሰይጣን አለመሆኑን በማረጋገጥ ክሳቸው ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚያሳይ ነበር። እርሱ አጋንንትን ያወጣበትን ኃይል፥ እንዳንድ አይሁዳውያን ከሚፈጽሙት አጋንንትን የማስወጣት ሙከራ ጋር አመዛዝኖታል (ቁ. 27)፡፡ እነዚህ አጋንንትን እናስወጣለን የሚሉ አይሁዳውያን እንደተጠቀሱት የአስቄዋ ሰባት ልጆች ዓይነት ነበሩ (በሐዋ. 19፡13-16)። እነዚህ ሰዎች አጋንንትን በማውጣት ረገድ በመጠኑም ቢሆን የተሳካላቸው ይመስል ነበር። ግን ውጤታቸው የተወሰነና ጊዜያዊ ነበር። ይህ ሊሆን የቻለው እውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል ስላልነበረባቸው ነው። ከአይሁዶች ይልቅ የኢየሱስ አጋንንት አወጣጥ የሰይጣን መንግሥት በማፈራረስ ረገድ የበረታ ነበር። ታዲያ ፈሪሳውያንና ሕዝቡ የእነርሱ ወገን የሆኑ አጋንንትን እናወጣለን ሲሉ በሰይጣን ኃይል ትጠቀማላችሁ ብለው አይከስሱም ነበር። ግን ተአምራቶቹ በኃይል የተሞሉና የሰይጣንን መንግሥት ደምሳሽ የሆነ ኢየሱስ በሰይጣን ኃይል ትጠቀማለህ ብለው መከሰሳቸው እንዴት ሞኝነት ነበር? ለነገሩ ኢየሱስ አጋንንትን ያወጣ የነበረው በእግዚአብሔር ኃይል ነበር። 

ፈሪሳውያን ተአምራቶቹን ከሰይጣን ኃይል ጋር ማያያዛቸው እንዴት ጅልነት (ሞኝነት) እንደ ነበረ የኢየሱስ የመጀመሪያዎቹ ሁለት መልሶች አረጋግጠዋል። በቁጥር 28 ውስጥ በሚገኘው በሦስተኛው መልሱ ፈሪሳውያን ተአምሩን ካዩ በኋላ ወደ ምን ዓይነት ድምዳሜ መድረስ እንደ ነበረባቸው አሳይቷቸዋል። እርሱ በተለየ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ መሆኑን ተረድተው፥ «የእግዚአብሔር መንግሥት» እንደ መጣላቸው መቀበል ነበረባቸው። ማለት እርሱ የእስራኤል መሢሕ መሆኑን መገንዘብ ይገባቸው ነበር። ፈሪሳውያን ይህንን ማወቅ ለምን ነበረባቸው? ኢሳ 11፡1-5፤ 42፡1 እና 61፡1፤ እነዚህ ክፍሎች ሁሉ መሢሑ በልዩ ሁኔታ በእግዚአብሔር መንፈስ የተቀባ መሆኑን ይገልጻሉ። ኢየሱስ አጋንንትን የማስወጣት ከፍተኛ ኃይሉ፥ ይህን ልዩ ቅባት ለመቀባቱ ምስክር መሆኑን ተናግሮአል። በሌላ አነጋገር፥ አጋንንትን ሲያስወጣ፥ እርሱም መሢሑ፥ የእግዚአብሔር ንጉሥና የእግዚአብሔርን መንግሥት ወደ ምድር የሚያመጣ መሆኑን ማስመስከሩ በቁጥር 29 ውስጥ፥ አጋንንትን ማውጣቱ የመሢሕነቱ ማረጋገጫ ለመሆኑ ምሳሌ ያቀርባል። 

አንድ ሌባ ወደ ኃይለኛ ሰው ቤት ገብቶ ንብረቱን ለመዝረፍ ያለው ብቸኛ መንገድ አስቀድሞ ኃይለኛውን ሰው ማሰር ነው ይላል። ኢየሱስ ያን ሲል ሰይጣንን በኃይለኛው ሰው ማስመሰሉ ነው። የሰይጣን አጋንንት ተሸነፉ 

ማለት ሰይጣን ራሱ ተሸንፎ ታሰረ፥ ስለታሠረም አጋንንቱን ሊረዳቸው አይችልም ማለት ነው። ሰይጣን በኢየሱስ ከተሸነፈ፥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መሢሕ መሆኑ ነው። ለፈሪሳውያን የሰጠው ሦስተኛው የኢየሱስ መልስ አጋንንትን ያወጣበት ልዩ የሆነ የኃይል አጠቃቀም ሁኔታ እርሱ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠበት መሢሕ መሆኑን እንደሚመሰክር ነበር። 

እነዚህ ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን መሢሕና የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚጠባበቁ መሆናቸውን የሚናገሩ ሰዎች ነበሩ። መሢሑ ሊመጣ እንደሚቀበሉት ያወሱ ነበር። ነገር ግን ስማቴ. 12፡25-29 ውስጥ እንደተጻፈው ኢየሱስ «እኔ መሢሕ መሆኔን በልባችሁ ታውቃላችሁ ይላቸው ነበር። የብሉይ ኪዳንንም ትንቢቶች ታውቃላችሁ። ግልጽ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችንም በዓይናችሁ አይታችኋል። በአእምሮአችሁም እኔ መሢሕ መሆኔን አውቃችሁ ደምድማችኋል። ነገር ግን ይህን ሁሉ እያወቃችሁ አልተቀበላችሁኝም። እኔ መሢሕ መሆኔን እያወቃችሁ አልተቀበላችሁኝም፥ ሥራዩንም የሰይጣን ሥራ አደረጋችሁት» አላቸው። በዚሁ ምዕራፍ ከቁጥር 30-32 ባሉት ቁጥሮች ኢየሱስ ንግግሩን ያጠቃልላል። በልቡ ኢየሱስ ማን እንደሆነ እያወቀ የማይቀበለው የእርሱ ጠላት ነው (ቁ. 30)። ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን በግልጽ የሚያረጋግጡ ሥራዎች መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ውስጥ ሲፈጽም እነዚህ ሥራዎቹም መሢሕ መሆኑን እንደሚመሰክሩ የተረዳ፥ ነገር ግን አሁንም እርሱን በመሢሕነቱ የማይቀበል፥ እርሱ ይቅር አይባልም (ቁ 31)። እናም ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን እያወቀ፥ እርሱ ከሰይጣን ነው ብሎ የሚከስውም ይቅርታ ውጭ ነው (ቁ 32)። እንዲህ ያለው ሰው ልቡን ያደነደነ ሰው በመሆኑ ወደ ክርስቶስ መጥቶ እንደ መሢሕ፣ እንደ መድኅንና ጌታ አድርጎ ሊቀበለው አይችልም። 

ስለዚህ በማቴ. 12፡31 ውስጥ፥ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የተናገረ ይቅር አይባልም የተባለው ምን ማለት ነው? ይህ እንግዲህ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ብቻ አይደለም። እግዚአብሔርን መናቅም ብቻ አይደለም። ወንጌልንም ሰምቶ ክርስቶስን አለመቀበልም ብቻ አይደለም። እነዚህ ሁሉ የከፉ ተግባራት ስለሆኑ እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል። ነገር ግን ማቴዎስ በምዕራፍ 12፡31 መንፈስ ቅዱስን ስለ መሳደብ ሲናገር ስለ እነዚህ ጥፋቶች መናገሩ አይደለም። ከጥቅሱ ጭብጥ እንደምንረዳው መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ማለት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በልዩ ሁኔታ የተቀባ መሢሕና አዳኝ መሆኑን እያወቁ ነገር ግን ልብን አደንድኖ ሆን ብሎ እርሱን አለመቀበልና ሥራውንም መቃወም ነው። ፈሪሳውያን ይህን ባደረጉ ጊዜ፥ ኢየሱስን ላለመቀበል ልባቸውን አጠነከሩ። ስለዚህም የእርሱን ይቅርታ ሳይቀበሉ ቀሩ። 

ዛሬስ ቢሆን አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስን በመሳደብ ይህንኑ ኃጢአት ሊሠራ ይችላል? መልሱ አዎን እና አይደለምም ይሆናል። ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሠራቸውን ታምራት ማንም ሰው ዛሬ በትክክል በግንባር እንደነበረው ሁኔታ ሊያይ አይችልም። ስለሆነም ማንም ሰው ይህን ፈሪሳውያን የሠሩትን ኃጢአት ራሱን መልሶ መሥራት አይችልም። በሌላ በኩል ግን የማያምኑ ሰዎች አሁንም ቢሆን በጣም ተመሳሳይ ኃጢአትን ሊፈጽሙ ይችላሉ። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለመሆኑና የዓለም መድኃኒት ስለመሆኑ ብዙ ምልክቶችን ያሳያል። አሁንም የእርሱ መንፈስ በመጽሐፍ ቅዱስ በተሰበከው ቃል፥ በአማኞች ሕይወትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተደረጉ ታምራት አማካይነት እየሠራ ነው። የማያምን ሰው እነዚህን የኢየሱስ ሥራዎች ተመልክቶ እርሱ በእውነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ መሆኑን አውቆ ነገር ግን ችላ ቢለውና ባይቀበለው፥ ይህ ሰው ወደ ክርስቶስ ዘንድ በሚያድን እምነት ሊመጣ እስከማይችል ልቡን ያደነድናል። 

እንግዲህ በማቴዎስ ምዕራፍ 12 ውስጥ መንፈስ ቅዱስን በመሳደብ ምክንያት ይቅር የማይባለው ኃጢአት፥ በዚህ ረገድ በማያምኑ ሰዎች የሚፈጸም ኃጢአት ነው እንጂ በእውነት ዳግም በተወለዱ ክርስቲያኖች የሚፈጸም በደል አይደለም። ስለሆነም ኢየሱስ ማን እንደሆነ እያወቁ በአንጻሩ እርሱን ያለመቀበል ኃጢአት ነው። ይቅርታ የማይደረግለት ኃጢአት ነው የተባለበት ምክንያት አንድ ሰው ክርስቶስ ማን እንደሆነ ካወቀ በኋላ ችላ ቢል፥ ልቡን ፍጹም ስለሚያደነድን እርሱን እንደ አዳኙ ለመቀበል በምንም ዓይነት አይመርጥም ማለት ነው። አንድ ሰው ሌላው ሰው ይህን ኃጢአት መፈጸሙን ሊያውቅ ይችላል? ኢየሱስ ፈሪሳውያን ይህን ኃጢአት መፈጸማቸውን አውቆ ነበር። ነገር ግን ዛሬ አንድ ሰው ሌላው ሰው ይህን ኃጢአት ለመፈጸሙ እርግጠኛ ሊሆን አይችልም። በሰብአዊና በውስን ግንዛቤአችን የሌላውን ሰው ልብና አእምሮ ማወቅ አንችልም። አንድ ሰው የክርስቶስን ማንነት ፍጹም ተገንዝቦ ሲያበቃ፥ ነገር ግን ከናካቴው ችላ በማለት ሳይቀበለው መቅረቱን ጠንቅቀን ማወቅ ፈጽሞ ያዳግተናል። ስለዚህ አንድ ወዳጃችን የሆነ ሰው ወይም ቤተሰብ ክርስቶስን ባለመቀበሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። በቃላችንና በተቀደሰ ሕይወት መመስከራችንን መቀጠልና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ወደ እራሱ መልሶ እንዲያመጣቸው ጸሎታችንን አለማቋረጥ ያስፈልገናል። በመሆኑም ማንም በእውነት ዳግም የተወለደ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ስለ ተሳደብኩ ይቅር የማይባል ኃጢአት ሠርቻለሁ ብሎ ሊፈራና ሊጨነቅ አይገባም።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን?  የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 
Exit mobile version