Site icon የሕይወት እንጀራ

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

This entry is part 11 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

ጥያቄ፡– ማርቆስ 2፡23-27 አንብቡ። ሀ) በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የሃይማኖት መሪዎችን ያስቀየመ ምን ተግባር ፈጸሙ? ለ) ይህ በምን ምክንያት የሃይማኖት መሪዎችን እስከፋ? ሐ) ኢየሱስ በቁጥር 28 ላይ ስለ 

ምን ሥልጣን ተናገረ? 

በማርቆስ 2፡23-27 ድረስ እንደተነገረው፥ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደ አገሩ ባሕል በመንገድ ዳር ካገኙት እሸት ጥቂት ወስደው በሉ። ሆኖም ይህን ያደረጉበት ቀን ሰንበት ነበር። በኢየሱስ ዘመን የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች ደግሞ በሰንበት ቀን እሸት ተቀጥፎ መበላት የለበትም ባይ ነበሩ። ስለዚህ ይህ እንዳይደረግ ከልክለዋል። ኢየሱስ ግን ደቀ 

መዛሙርቱ ከእሸቱ ወስደው እንዲበሉ ፈቀደላቸው። በዚህ ምክንያት ፈሪሳውያን ሕግ አፍርሷል ብለው በከሰሱት ጊዜ ኢየሱስ ስለ ሰንበት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የመተርጎም ሥልጣኑን ተጠቀመ። የሰንበት ሕግ የተሰጠው በእግዚአብሔር በራሱ ነው (ዘፀአት 20፡8-10። ኢየሱስ ሕጉን ተረጎመ ማለት እርሱ ከሃይማኖት መሪዎች ባላይ ነው እንደ ማለት ነው። ስለዚህ በሰንበት ቀን ምን መሠራት እንዳለበት ሊናገር፥ 

መለኮታዊ ሥልጣኑን መግለጹ ነበር። እርሱ የሚናገረው ሥልጣን ምን እንደሆነ በእርግጥ ይነዘቡ ዘንድ በቁጥር 28 ላይ፥ «የሰው ልጅ ለሰንበት ጌታዋ ነው» አለ። ኢየሱስ ራሱን «የሰው ልጅ ብሎ ሲጠራ ምን ማለቱ እንደሆነ በሌላ ክፍለ ትምህርት እናጠናለን። ይህ የኢየሱስ የተለመደ መጠሪያ ነው። በዚህ አገላለጹ ስለ እራሱ እንደሚናገር ገባቸው። እዚህ ላይ ኢየሱስ፤ «የሰው ልጅ ለሰንበት ጌታዋ ነው» በማለት እግዚአብሔር ስለ መሠረታት ሰንበት ሊናገር፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስለሆነው ሥልጣኑ ማስረዳቱ ነበር። 

28ኛ ጥያቄ፡- ሀ) ማቴዎስ 5፡21-22፥ 27-28፥ 31-32፥ 33-34፥ 38-39፥ 43-44 ያሉትን ክፍሎች አንብቡ፡ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ተረጋግመው የተነሡ ሐረጎች የትኞቹ ናቸው? ለ) ኢየሱስ በእነዚህ ሁለት ሐረጎች ደጋግሞ ሲጠቀም ምን ለማለት የፈለገ ይመስላችኋል? 

ማቴዎስ 5-7 ያለው ክፍል ኢየሱስ በተራራ ላይ ስላሰማው ስብከት ይዘግባል። ወደዚህ ስብከት መጀመሪያ አካባቢ ኢየሱስ ሁለት ሐረጎች ስድስት ጊዜ ደጋግሞ ይጠቅሳል። የመጀመሪያው ሐረ፥ «እንደተባለ ሰምታችኋል” የሚል ነው። ኢየሱስ እነዚህን ሐረጎች በተጠቀመ ቁጥር ከብሉይ ኪዳን ሕግ ይጠቅስ ነበር። አንዳንድ ጊዜም ባሕላዊውን የሕግ ትርጉም ያክልበት ነበር። ሁለተኛው የሚደጋግመው ሐረግ ደግሞ፥ «እኔ ቀን እላችኋለሁ” የሚለው ነው። ኢየሱስ በዚህ ሐረግ በሚጠቀምበት ጊዜ፥ ለብሉይ ኪዳን ሕግ የጠለቀ ትርጉም ይጨምርበት ነበር። ለምሳሌ ያህል፥ በማቴዎስ 5፡21-22 እንዲህ ይላል፥ «አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ገን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።» ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ መግደል የተነገረው ማንም ሰው ሌላውን እንዳይጠላው የሚል መሆኑን በሥልጣን ያስገነዝባል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በተደጋጋሚ፥ ኢየሱስ፥ «እንደ ተባለ ሰምታችኋል እኔ ግን እላችኋለሁ።» ሲል የእርሱ ትምህርት ልክ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሁሉ የሚታመን መሆኑን መግለጹ ነበር። እንደዚሁም ኢየሱስ የእርሱ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል መሆኑን ያስረዳል። ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ ትምህርቱን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል በማድረግ፥ በተዘዋዋሪ መንገድ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይገልጻል። 

ከፍ ብለን ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር በማለትና ቃሉ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካለው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል እንደሆነ በማሳወቅ በተዘዋዋሪ መንገድ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንደ ገለጻ ተከታትለናል። እንደዚሁም፥ እርሱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አለኝ ባለው ልዩ ግንኙነት በተዘዋዋሪ መንገድ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ገልጾአል። ጌታ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ግንኙነት እንዳለው ሲናገር፥ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ዓይነት የተፈጥሮ ባሕርይ እንዳለው ማስገንዘቡ ነው።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል  ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 
Exit mobile version