Site icon

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ባለፈው ሳምንት የተሠገዎ ምሥጢርን በጥንቃቄ ማጥናት መጀመራችንን ታስታውሳላችሁ። በዚህ ጥናት ውስጥ ኢየሱስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው መሆኑን ተምረናል። ነገር ግን በአንድ ሰው ተፈጥሮ ውስጥ እንዴት አድርጎ ፍጹም እግዚአብሔርና ፍጹም ሰው የሆነ የባሕሪ ውህደት ሊኖር ይችላል? ባለፈው ሳምንት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ስላለው የአምላክነትና ሰብአዊነት ውህደት የሚያስተምሩ ሦስት ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶችን መርምረናል። እነርሱም ዮሐንስ 1፥ ፊልጵስዩስ 2 እና ዕብራውያን 2 ነበሩ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ላለ ኢየሱስ ተሠገዎ እንዴት ኣሁን ወደአለችበት የግንዛቤ ደረጃ ልትደርስ እንደ ቻለች ታሪኳን ማጥናት በጣም ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ይህን ስናደርግ የተለያዩ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ እምነታቸው ምን እንደሆነ በትክክል ለማወቅ እንችላለን። ባለፈው ሳምንት ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን፥ እንዴት ቀስ በቀስ ኢየሱስ ሰውም አምላክም መሆኑን ልትረዳ እንደ ቻለች ማጥናት መጀመራችን የሚታወስ ነው። በኒቂያው ጉባዔ ጊዜ ማለትም በ325 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ፍጹምም ሰው ስለ መሆኑ ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሳ ነበር። ሆኖም ግን ጉባዔተኞቹ ፍጹም እግዚአብሔርና ፍጹም ሰው እንዴት በአንድ አካል መዋሃድ እንደ ቻሉ ወደ ማብራራቱ ደረጃ ገና አልደረሱም ነበር። ሆኖም በዚህ ሳምንት ትምህርታችን ላይ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ወደዚህ የክርስቶስ ተሠገዎ ሙሉ ግንዛቤ ላይ እንደ ደረሰችና አያይዘንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥንትም ሆነ ዛሬ የተሠገዎን ምሥጢር እንዴት እንደተረዳችው እንማራለን። 

የመጀመሪያ ቀን 

ባለፈው ሳምንት ትምህርታችን ላይ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢየሱስ የተሠገዎ ባሕርይ እንዴት አድርጋ ግንዛቤዋን ልታዳብር እንደ ቻለች ተመልክተን ነበር። በኒቂያው ጉባዔ ላይ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ እውነተኛ ኣምላክና እውነተኛ ሰው መሆኑን ተቀብላለች። ነገር ግን የክርስቶስ ኣምላክነትና ሰብአዊነት እንዴት በአንድ አካል ውስጥ ተዋሃደ? ብዙ ክርስቲያኖችም ክርስቶስ በአንድ ጊዜ እግዚአብሔርም ሰውም ያለ መሆኑ መወያየት ጀምረው ነበር። ይህ ውይይት ለተራዎቹ ምእመናንም ቢሆን በጣም አንገብጋቢ ነበር። ምክንያቱም ዘላለማዊው ደኅንነታቸው የተመሠረተው በክርስቶስ አምላካዊና ሥጋዊ ውህደት ትክክለኛ እምነት ላይ ስለሆነ ነው። 

አቡሊናርዮሳዊነት 

አቡሊናርዮስ የተባለ አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ክርስቶስ እንዴት መለኮትም ሰውም ሊሆን እንደ ቻለ ለማብራራት ሞክር ነበር። በዚህ ትምህርቱም ክርስቶስ ሰብአዊም፥ መለኮታዊም የሆነ ሁለት ባሕርይ አለው ብሎ መግለጽ ስሕተት ነው ብሎ ኣስተምሮአል። ይልቁኑ ክርስቶስ አንድ ባሕርይ ብቻ አለው ብሎ አስተማረ። ክርስቶስ የተለየ ሰብኣዊ ባሕርይ ካለው ይህ ሰብአዊ የባሕርይው ክፍል እግዚአብሔር ሊሆን አይችልም ሲል አመለካከቱን አስቀመጠ። በመሆኑም ከክርስቶስ ባሕርይ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ውህደት የሌለው ቢኖርበት ኖሮ ዓለምን ከኃጢአቱ ባላዳነው ነበር አለ። ስለዚህም አቡሊናርዮስ የክርስቶስ ኣምላክነት ከሰብአዊነቱ ጋር ፍጹም ስለ ተዋሃደ አምላክነቱ ሰብአዊነቱን ውጦታል ብሎ አስተማረ። በእርሱ እምነት ክርስቶስ ሰብአዊ ነፍስና መንፈስ አልነበረውም። መለኮትነቱ የውስጣዊ ሲሆን፥ ሰብአዊ አካሉ ውጪአዊው ነው በማለት ተናግሮአል። ስለዚህም ክርስቶስ ከሌሎች የሰው ልጆች ሰብአዊነት የተለየ «መለኮታዊ ሰብአዊነት» ነበረው በማለት አስተማረ። በመቀጠልም የክርስቶስ አካልም ቢሆን ከሰው ልጆች አካል የተለየ ነው ሲል ለዚህም የሰጠው ምክንያት ከማይሞት ሥጋ የተሠራ መለኮታዊ አካል በመሆኑ ነው የሚል ነበር። በዚህ አኳኋን የአቡሊናርዮስን አስተምህሮ ስናስተውል፥ ስለ ክርስቶስ የአምላካዊነትና የሰብኣዊነት ተዋህዶ የገለጸው የክርስቶስን ሰብአዊነት በሚያሳንስ ደረጃ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) አቡሊናርዮስ የበለጠ ትኩረት የሰጠው ለክርስቶስ መለኮታዊነት ነው ወይስ ሰብአዊነት? ለ) አቡሊናርዮስ የክርስቶስ ሰብአዊነት ከእኛ ሰብአዊነት የተለየ ነው ሲል ምን ማለቱ ነበር? ሐ) ክርስቶስ ከኃጢአት በስተቀር እንደኛው ሙሉ በሙሉ ሰው ስለ መሆኑ፥ ለአቡሊናርዮስ ለማሳየት በትምህርት 2ና 3 ላይ ከነበሩት መካከል የትኞቹን ጥቅሶች ለማስረጃነት ታቀርባላችሁ? ስለዚህ የኢየሱስ ሰብአዊነት ከእኛ ሰብአዊነት ጋር ተመሳሳይ ስለ መሆኑ በሚያስረዱት ጥቅሶች በመመለስ ከልሷቸው። 

አቡሊናርዮላ የአስተምህሮ ትኩረቱን ያደረገው በክርስቶስ አምላካዊነት ላይ ሊሆን፥ ነገር ግን ለሰብአዊነቱ በቂ የሆነ ትኩረትን አልሰጠም። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከዚህ ከአቡሊናርዮስ አስተምህሮ በመነሣት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊ ነፍስና መንፈስ ያልነበረው ከሆነና የማይሞት ሥጋ የነበረው መለኮታዊ አካል ከሆነ፥ እውነትም እርሱ ልክ እንደ እኛ ሰው ኣልነበረም አሉ። ነገር ግን ኢየሱስ እውነተኛ ሰው ባይሆን ኖሮ የሰው ልጆችን ከኃጢአት ለማዳን ባልሞተ ነበር። በትምህርት 2 ላይ የተጠቀሱት እንደ ማቴዎስ 4፡2፤ 26፡38፤ ሉቃስ 23፡46፤ ዮሐንስ 4፡6፤ 19፡28፥ 34 ዕብራውያን 25-18፤ 4፡5-16 ፊልጵስዩስ 2፡6-11 እና 1ኛ ዮሐንስ 1፡1 ያሉት ጥቅሶች ኢየሱስ ከኃጢአት በስተቀር ልክ እንደ እኛው ሰው መሆኑን ያሳመኑአቸው ነበሩ። ኢየሱስ ሰብኣዊ ነፍስና መንፈስ ነበረው። የኢየሱስ አካልም ልክ እንደ እኛ አካል ያለ ነበር። ስለሆነም የአቡሊናርዮስ አስተምህሮ በቆስጥንጥኒያ በ381 ዓ.ም በተሰበሰበው የቤተ ክርስቲያን ጉባዔ ላይ ኑፋቄነቱ ተረጋግጦ ተወግዞአል። 

ጥያቄ፡- በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ላሉ ምእመናን የኢየሱስ ስብእና ከእኛ ስብእና ይለይ እንደሆነ ጥያቄ ብታቀርቡላቸው፥ መልሳቸው ምን የሚሆን ይመስላችኋል? 

በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትና ሃይማኖት በጥብቅ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች፥ የኢየሱስ ስብእና ከእኛ ስብእና የተለየ እንደሆነ አድርገው ያምናሉ። ኢየሱስ ኣምላክም በመሆኑ በእውነት ሰው መሆኑን አምነው ለመቀበል ያዳግታቸዋል። ኢየሱስ ያለኃጢኣት ከመሆኑ በስተቀር፥ ልክ እንደ እኛው ሰው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ስለዚህ ኢየሱስ በእውነት ሰው ባይሆን ኖሮ የሰውን ልጆች ከኃጢአታቸው ለማዳን ሊሞት ባልቻለ ነበር። 

ንስጥሮሳዊነት

አቡሊናርዮስ በአስተምህሮው ውስጥ የኢየሱስን ስብእና ዝቅ አድርጎ ከማቅረቡ የተነሣ ተወግዞ ነበር። ነገር ግን የኢየሱስ አምላካዊነትና ሰብአዊነት እንዴት በአንድ አካል እንደ ተዋሃዱ ግልጽ በሆነ መንገድ ገና አልተደረሰበትም ነበር። በጊዜው በቆስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን መምህር የነበረ ንስጥሮስ የተባለ ሰው የመፍትሔ አሳብ አቀረበ። መፍትሔ ነው ብሎ አምኖበት ያቀረበው አስተምህሮ፥ ኢየሱስ መለኮታዊና ሰብአዊ ሁለት ባሕርያት አሉት የሚል ነበር። ብዙዎቹ ሰዎች ንስጥሮስ ኢየሱስ ሁለት አንዱ በመለኮታዊ ሌላው ሰብአዊ አካላት አሉት ብሉ ማስተማሩን ተገነዘቡ። ኢየሱስ አንድ አካል የነበረው ቢሆንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ ሰብአዊ አካሉ በመራብ፥ በመጠማትና በመድከም፥ ሌላ ጊዜ ደግሞ መለኮታዊው አካሉ ተአምራትን በማድረግ ራሱን ይገልጽ ነበር። በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም የተለየ መለኮታዊ ኢየሱስና ሰብአዊው ኢየሱስ መኖራቸውን ገለጸ። ንስጥሮስ፥ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በወለደች ጊዜ፥ የወለደችው ሰብአዊውን ኢየሱስን ነው እንጂ መለኮታዊውን ኢየሱስ አልነበረም ሲል ኣስተምሮአል። 

ንስጥሮስ በዚህ ትምህርቱ የተነሣ በግብፅ እስክንድሪያ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን መሪ በነበረው በስሪል (Cyri]) ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ደርሶበት ነበር። ስሪል ኢየሱስ ፍጹምና እውነተኛ ሰው ነው የሚለውን የንስጥሮስ አቋም ቢቀበልም፥ ሰብአዊና መለኮታዊ ባሕርያቱ በአንድ አካል ተዋህደዋል ለሚለው አስተምህሮ ክብደትን ሰጥቷል። የክርስቶስ አንድ ባሕርይ ሁልጊዜ በውህደት እንደሚሠራ ገለጸ። በአንጻሩ ክርስቶስ አንዳንድ ጊዜ በሰብአዊነቱ፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ በአምላካዊነቱ ይሠራል ብሎ መወሰን የክርስቶስን ሕልውና በሁለት አካላት መክፈል ነው ሲል ተከራከረ። ከዚህ የተነሣ ስሪል ክርስቶስ ሁለት የተለያዩ አካላት ቢኖሩት ኖሮ የሰው ልጆችን የማዳን ተግባሩን ባላከናወነ ነበር የሚል አቋም ነበረው። እንዲሁም እንደ ስሪል እምነት፥ ክርስቶስ በሰብአዊ አካሉ ብቻ ተሠቃይቶ ከሞተ፥ በሞቱ ምክንያት የተገኘው ደኅንነት በማንኛውም ዘመንና ጊዜ ለነበሩ የሰው ልጆች የተፈለገውን ውጤት ባልሰጠ ነበር፤ በአጠቃላይም ለፍጥረታት ሁሉ ባልበጀ ነበር። ስለዚህ ለሪል ይህን ሲያብራራ የክርስቶስ የደኅንነት ተግባር በየዘመኑ ለነበሩትና ላሉት የሰው ልጆች ሁሉ ሊጠቅም የቻለውና ውጤታማ የሆነው ክርስቶስ በሰብአዊነቱና በመለኮታዊነቱ ሥቃይን ተቀብሎ በመሞቱ ነው ብሏል። ከዚህ ውጭ ያስተማሩትን ሲቃወምም ክርስቶስ በሰብአዊነቱ ብቻ ተወለደ፥ ተሠቃየ፥ ሞተ፥ ወይም ይህን ወይም ያን ተግባር አከናወነ ብሎ ማስተማር ስሕተት ነው በማለት አቋሙን ገልጾአል። ምንም እንኳን ክርስቶስ በሰብአዊነቱና በአምላካዊነቱ አንዳንድ ጊዜ ልዩነቶችን ያላየ ቢሆንም፥ በሁለት ተከፍሎአል ማለት እንዳልነበረ አመልክቷል። ስሪል በትምህርቱ ውስጥ ክርስቶስ በአንድ አካል አምላካዊውንና ሰብአዊውን ባሕርይ በውህደት አካትቶ ይዟል ሲል አስተምሯል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ንስጥርስ ክርስቶስ ስንት ባሕርያት አሉት ብሉ አስተማረ? ለ) እንደዚሁም ክርስቶስ ስንት አካላት አሉት አለ? ሐህ ንስጥሮስ የኢየሱስን አምላካዊነትና ሰብአዊነት በተመለከተ አጽንኦት የሰጠው ለልዩነት ነው ወይስ ለአንድነቱ? መ) የንስጥሮስ አስተምህሮ ጠንካራና ደካማ ጎን ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሀ) ስሪል ኢየሱስ ስንት ባሕርያት አሉት አለ? ለ) ስሪል ኢየሱስ እንደ ኣምላክና እንደ ሰው ለፈጸማቸው ተግባራት ክብደትና ትኩረትን የሰጠው ለኣንድነቱ ወይስ ለተካፋይነቱ? ሐ) በስሪል አስተምህሮ ውስጥ ምን ጠንካራና ደካማ ጎን አያችሁ? 

የንስጥሮስ አስተምህሮ በአብዛኛው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር የሚቃረን መሆኑ ለብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ግልጽ ነበር። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደ ንስጥሮስ አስተምህሮ ኢየሱስ ሁለት ባሕርይ ይኑረው አይኑረው በጊዜው እርግጠኞች አልነበሩም። ሆኖም ግን ንስጥሮስ በአስተምህሮው ውስጥ በግልጽም ባይሆን እንዳለው ኢየሱስ ሁለት አካላት ስላለመሆኑ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እርግጠኞች ነበሩ። ንስጥሮ በክርስቶስ አምላካዊነትና ሰብአዊነት መከፋፈል ላይ የተጋነነ ክብደት ሰጥቶ ለመግለጽ መሞከሩ ግልጽ ነው። ይህ የንስጥሮስ አስተምህሮ የኢየሱስን ፍጹም አምላክነትና ሰብአዊነት ክብደት መስጠቱ የትምህርቱ ጠንካራ ጎ’ ሲሆን፥ ደካማ ጎኑ ደግሞ ኢየሱስን በሁለት አካላት መክፈሉ ነበር በመሠረቱ ኢየሱስ ንስጥሮስ እንደሚለው አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ሰው የመሆን ባሕርይ አልነበረውም። ኢየሱስ በባሕርይ ምን ጊዜም ቢሆን አምላክነቱና ሰብአዊነቱ ሳይለያይ በውህደት ያለ ነው ይህ ኑፋቄአዊ የሆነ የንስጥሮስ አስተምህሮ በ431 ዓ.ም ኤፌሶን ውስ’ በተደረገው ጉባዔ ላይ ተወግዟል። ምንም እንኳን የስሪል አስተምህt የክርስቶስን መለኮታዊና ሰብአዊ የአንድ አካል ውህደት በማስጠበቁ በኩሪ ጠንካራ አቋም ቢኖረውም፥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እር በሚያስተምረው መንገድ የክርስቶስ መለኮታዊና ሰብአዊ ውህደ መፈጸሙን ለመቀበል ገና ከውሳኔ ላይ አልደረሱም ነበር። አንዳንዶቹ የቤ ክርስቲያን መሪዎች ይህ የስሪል አለተምህሮ ሰዎችን፥ ኢየሱስ ትክክለኛ ሰዐ አልነበረም ወደሚለው የአቡሊናሪዮስ የክህደት ትምህርት ይመልሳል ብለዉ ፈሩ። 

አውጣኪነት 

ቤተ ክርስቲያን አቡሊናርዮሳዊነትንና ንስጥሮሳዊነትን አውግዛለች። ነገ ግን የክርስቶስ አምላካዊና ሰብኣዊ ባሕርይ እንዴት በአንድ አካል ይዋሃዳ የሚለው ጥያቄ ገና አልተመለሰም ነበር። በሶሪያና በግብፅ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ስሪል (Cyril) ኢየሱስ በአንድ አካል የተዋሃደ መለኮታዊና ሰብአዊ ባሕርይ አለው ብሎ ያስተማረውን ትምህርት ፈቅደውታል። በአኳያው ደግሞ የሮም ቤተ ክርስቲያን መሪዎች፥ ሁለት ባሕርያት በአንድ አካል ውስጥ የሚለውን አስተምህሮ መርጠዋል። ስሪል በ444 ዓ.ም ከሞተ በኋላ ደቀ መዝሙሩ የነበረው ዲስቆሮስ ኢየሱስ ሁለት ባሕርያት አለው የሚለውን አስተምህሮ አጥብቆ ይቃወም ጀመር። እንዲያውም አውጣኪ የተባለው መነኩሴ ከዚህ ጠልቆ በመግባት፥ የክርስቶስ አምላክነትና ሰብአዊነት በተዋሃዱ ጊዜ፥ ሁለቱም ባሕርያቱ በአንድ ተጣምረው ሰብአዊነቱ በአምላክነቱ ውስጥ ስለ ተዋጠ ሥጋው እንኳ ሰብኣዊ መሆኑ ቀርቶ መለኮታዊ ሆኗል ሲል አስተማረ። የአውጣኪ አስተምህሮ፥ የአቡሊናርዮሳዊነትን ትምህርት በተሃድሶ ያመጣ ይመስላል። 

ጥያቄ፡- ሀ) በግብፅና በሶሪያ በነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘንድ የትኛው የተሠገዎ አስተምህሮ ተወዳጅነትን አገኘ? ለ) የሮም ቤተ ክርስቲያን መሪዎችስ የትኛውን የተሠገዎ ትምህርት መረጡ? ሐ) አውጣኪ ስለ ክርስቶስ አምላካዊና ሰብአዊ ተዋህዶ ምን አስተማረ? 

በግብፅና በሶሪያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው በአንድ አካል ውስጥ የመለኮታዊና ሰብአዊ ውህደት የሚለውና በሮም ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተመረጠው ሁለት ባሕርያት በአንድ አካል የሚሉት አስተምህሮዎች ለቤተ ክርስቲያናቱ መለያየት ምክንያት ሆኑ። አውጣኪ የክርስቶስ መለኮታዊው ባሕርይ ሰብኣዊውን ባሕርይ ዋጠው ያለው አገላለጽ የኢየሱስን ሰብኣዊነት ዝቅ ያደረገ ነበር። ለዚህ ችግር መፍትሔ ለመሻት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሌላ ጉባኤ መቀመጥ አስፈለጋቸው። 

የኬልቄዶን ጉባዔ (451 ዓ.ም) 

በዚህ በክርስቶስ ባሕርይ ላይ ለቀረቡት አስተምህሮዎችና ክርክሮች ከስምምነት ደርሶ ውሳኔ ለመስጠት፥ በ451 ዓም በኬልቄዶን ላይ በተደረገው ጉባዔ ላይ ብዛት የነበራቸው የቤተ ክርስቲያናት መሪዎች ተሰበሰቡ። በዚህ ጉባዔ ላይ የነበሩት አብዛኛዎቹ የሮም ሊቀ ጳጳሳት የሌዎን አሳብ ለመከተል ወሰኑ። ፓፓ ሌዎ የክርስቶስን ፍጹም አምላካዊነትና ፍጹም ሰብአዊነት መሠረተ እምነት ለመጠበቅ የላቀው አካሄድ ሁለት ባሕርያት ማለትም ሰብአዊና ኣምላካዊ ባሕርያት እንዳሉት መቀበል ነው አለ። በመቀጠልም እነዚህ ሁለት ባሕርያት በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም ሆነው የተዋሃዱ መሆናቸውን ገለጸ። እንደዚሁም የክርስቶስ ሰብአዊ ባሕርያት ከመለኮታዊው ጋር አይነካኩም፤ መለኮታዊውም ባሕርያት ከሰብአዊው ጋር አይነካኩም ሲል ተናግሯል። ክርስቶስ በሥጋዊ ባሕርይው እንደ ረሃብ፥ ጥማትና ሞት ያሉ ኣንዳንድ ሁኔታዎች ታይተውበታል። በአምላክነቱ ደግሞ ተአምራትን የመሳሰሉትን አድርጓል። ይሁን እንጂ ክርስቶስ ምን ጊዜም አንድ አካል 

ነበር እንጂ አንድ ጊዜ እግዚአብሔር በሌላ ጊዜ ሰው አልነበረም። 

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኬልቄዶን ጉባዔ ላይ ኢየሱስ በአንድ አካል ሁለት ባሕርያት አለው ሲሉ የሃይማኖት መግለጫ አውጥተዋል። በምዕራብ የነበሩ ሁሉም ቤተ ክርስቲያናት ይህ የተሠገዎን ምሥጢር ለመገንዘብ የላቀ መንገድ ነው በማለት መግለጫውን ተቀብለውታል። እነርሱም ኢየሱስ በአንድ አካል ሁለት ባሕርያት አሉት፥ በዚህም ፍጹም አምላክነቱና ፍጹም የሆነ ሰብአዊነቱ ፍጹም በሆነ አንድነት ተጠብቆአል በማለት ተስማሙ። በግብፅና በሶሪያ ከነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል ጥቂቶቹም የኬልቄዶንን ውሳኔ ተቀብለዋል። ነገር ግን ብዙዎች የግብፅና የሶሪያ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የኬልቄዶንን ጉባዔ ውሳኔ ሳይቀበሉ ቀርተዋል። እነርሱም ይህን ቅዋማያቸውን ሲያብራሩ፥ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት ማለት ባሕርያቱን ከልክ በላይ መከፋፈል ስለሆነ፥ ይህ ድርጊት በደኅንነታችን ላይ አደጋ ያስከትላል ብለዋል። ከእነዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አንዳንዶቹ አውጣኪ፥ የኢየሱስ ሰብኣዊነትና አምላክነት ውህደት ፍጹም ከመሆኑ የተነሣ ከእኛ ሰብአዊነት የተለየ ነው በማለት ያቀረበውን አሳብ ተቀብለው ነበር። ሌሎች ደግሞ በዚሁ በኬልቄዶን ጉባዔ ላይ የኢየሱስ ሰብአዊነት ከሌሎች ሰዎች ሰብአዊነት ጋር ይመሳሰላል በማለት አምላካዊና ሰብአዊ ባሕርይው በአንድ አካል ውስጥ ይዋሃዳሉ የሚለውን አልተቀበሉም። እነዚህኞቹ ወገኖች ይህ አስተምህሮ ክርስቶስን በጣም የሚከፋፍልና ባለ ሁለት ባሕርያት አድርጎ የሚያቀርብ ነው ባይ ነበሩ። ይልቁንም ኢየሱስ አንዳንድ ጊዜ እንደ አምላክ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሰው የሚታይና የሚሠራ አልነበረም ለሚለው አስተሳሰብ ክብደትን ሰጡ። ይህን ሊያጠናክሩም እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ሲሠራ የታየው ሰብኣዊም መለኮታዊም ባሕርይ ተዋህዶት ነው ብለዋል። 

ጥያቄ፡- ሀ) በኬልቄዶን የተደረገው ጉባዔ ስለ ክርስቶስ መለኮታዊና ሰብአዊ የተገዎ ውህደት የሰጠው ማብራሪያ እንዴት ያለ ነበር? ላህ በኪልቄዶን የተደረገውን ጉባዔ የተቀበሉት የትኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው? ሐ) የኬልቄዶንን ጉባዔ ያልተቀበሉትስ አብያተ ክርስቲያናት የትኞቹ ነበሩ? 

በኬልቄዶን ጉባዔ ያልነበረ አስተምህሮ ወደ ኢትዮጵያ መጣ። 

በምዕራብ የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት በከልቄዶን ጉባዔ ላይ የተገለጸውን ክርስቶስ ሰብአዊ ባሕርይና መለኮታዊ ባሕርይ አለው፥ እነዚህ ባሕርያት በአንድ አካል የተዋሃዱ ናቸው የሚለውን ተቀብለዋል። ነገር ግን በግብፅና በሶሪያ የነበሩ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የኢየሱስ ሁለት ባሕርያት በአንድ ባሕሪ ተጣመሩ የሚለውን አስተምህሮ መረጡ። ለዚህ የኣስተምህሮ ውዝግብ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መልስ ምን ነበር? 

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ከግብዕ ቤተ ክርስቲያን ጋር ትስስር አድርጋ ቆይታለች። ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን ጋር ከነበራት ከዚህ የቅርብ ትስስር የተነሣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ግብፅ ቤተ ክርስቲያን የኬልቄዶን ጉባዔ ያስተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ አድርጋዋለች። እንዲያውም ወደ 400 ዓ.ም መገባደጃ ገደማ ተስዓቱ ቅዱሳን (ዘጠኙ ቅዱሳን) ከመጡ በኋላ ኢትዮጵያ የኬልቄዶንን ጉባዔ ያለመቀበልዋ ሁኔታ ይበልጥ የከረረ ሆነ። እነዚህ ዘጠኝ ቅዱሳን የመጡት ከሶሪያ ሲሆን፥ የኬልቄዶንን ጉባዔ ውሳኔ በጥብቅ ውድቅ አድርገውታል። ቅዱሳኑም የክርስቶስ አካል አሃዳዊነት ሊጠበቅ የሚችለው ስለ እርሱ ባሕርይ ኣሃዳዊነት በማስተማር ነው የሚል እምነት ነበራቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ምክንያት የኬልቄዶኑን ጉባዔ ውሳኔ ስላልተቀበሉ በኣገራቸው ስደት ስለደረሰባቸውና ክርስቶስ አንድ ባሕርይ ብቻ አለው የሚለው ትምህርታቸውን ለማስፋፍት ሳይሆን አይቀርም። እነዚህ ዘጠኙ ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል። በኢትዮጵያ ውስጥም እየተዘዋወሩ ሰብከዋል፤ አስተምረዋልም። ከእነርሱ ስብከትና ትምህርት የተነሣ ብዙ ሰዎች ክርስትናን ሊቀበሉ ችለዋል። በጊዜያቸውም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ተሠርተዋል። በዚሁ ጊዜ የክርስቶስ ሁለት ባሕርያት በአንድ መዋሃዳቸውን አንድ ባሕርይ መሆናቸውን የሚገልጹ፥ በአንጻሩ የኬልቄዶን ጉባዔ ውሳኔ የሚቃወሙ መጻሕፍትን ጽፈዋል። እነዚህ ዘጠኝ ቅዱሳን ክርስትናን በኢትዮጵያ ውስጥ በማስፋፋታቸው ሳቢያና በአስተማሩትም ትምህርት ባስከተሉት ተጽዕኖ የተነሣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ አንድ ባሕርይ ብቻ አለው የሚለውን አስተምህሮ አጥብቃ ያዘች። የኬልቄዶኑንም ውሳኔ አጥብቃ ነቀፈች። 

ጥያቄ፡- ሀ) ዘጠኙ ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ባሕርይ ምን አስተማሩ? ለ) የክርስቶስን ባሕርይ ወይም ማንነትን በተመለከተ እነዚህ ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነት ላይ ምን ተጽዕኖ አደረጉ? 

ዘጠኙ ቅዱሳን የክርስቶስ ሁለት ባሕርያት በአንድ ባሕርይ ውስጥ ተዋሃዱ የሚለውን እምነታቸውን አጥብቀው በመያዝ በዚያ ጸኑ። ይህንንም ትምህርታቸውን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማስፋፋታቸውና ተጽዕኖም በማሳደራቸው፥ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ልክ እንደ እነርሱ የኬልቄዶንን ጉባዔ አስተምህሮ ኣጥብቀው መቃወምን መረጡ። 

ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቶስ በአንድ አካል የተዋሃዱ የተለያዩ ኣምላካዊና ሰብአዊ ባሕርያት አሉት የሚለው የኬልቄዶኑ አስተምህሮ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ሆነው የሚታዩአችሁ ምን ምንድን ናቸው? ለ) ዘጠኙ ቅዱሳን የክርስቶስ ሁለት ባሕርያት በአንድ ባሕርይ ውስጥ ተጣምረዋል ሲሉ የወሰዱት አቋም ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምንድን ናቸው? 

የኬልቄዶኑ ጉባዔ ኣስተምህሮ ጠንካራ ጎን ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ እውነተኛ ሰው ነው የሚለው ግልጽ አቋም ነው። ይሁን እንጂ የዚህ አስተምህሮ ጉድለት፥ ክርስቶስ ኣንዳንድ ጊዜ በሰብኣዊነት በሌላ ጊዜ ደግሞ በመለኮታዊነት ይሠራል የሚለውና ክርስቶስን በጣም የሚከፋፍለው አቋሙ ነው። የዘጠኙ ቅዱሳን ኣስተምህሮ ጥንካሬ የኢየሱስ የባሕርይ ውህደት መጠበቃቸው ነው። ክርስቶስ እግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ወይም ሰው ብቻ ሆኖ የሠራበት ጊዜ የለም። ቢሆንም የዘጠኙ ቅዱሳን አገላለጽ የክርስቶስን ሰብኣዊነት ከሌሎች ሰዎች ሰብአዊነት የተለየ አድርጎ በማቅረብ ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ነገ ደግሞ ከኬልቄዶኑ ጉባዔ አስተምህሮ ጋር ኣንድነት ያልነበረው የዘጠኙ ቅዱሳን ትምህርት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ሥር ሰድዶ እንደ ተመሠረተ አብረን እንማራለን።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version