Site icon

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ደኅንነትን ሊሰጠን ብሎ ስለፈጸመው ተግባር ተምረናል። ኢየሱስ ኃጢአት በሌለበት ሕይወቱ፥ መሥዋዕትነትን በከፈለበት ሞቱና ድልን በተጎናጸፈበት ትንሣኤው፥ የኃጢአታችንን ቅጣት በመቀበል ከኃጢአትና ከሰይጣን ቁጥጥር ነፃ አወጣን። የኢየሱስ ሕይወት፥ ሞትና ትንሣኤ የደኅንነታችን መሠረቶች ናቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው እንዴት ይህን ደኅንነት ሊቀበል ይችላል? የክርስቶስ ተግባር በእውነት ወደ እያንዳንዳችን ደኅንነትን ያመጣልን ዘንድ፥ እግዚአብሔር ምን ያደርጋል? እኛስ የክርስቶስን ደኅንነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በዚህ ሳምንት እግዚአብሔር ሰዎችን ለመምረጥና ለመጥራት ስለሚፈጽመው ተግባር እናጠናለን። በሚመጣው ሳምንት ደግሞ የክርስቶስን ደኅንነት ለመቀበል ምን ማድረግ እንደሚገባን እንማራለን፡ 

እግዚአብሔር ወደ ደኅንነቱ እንዲመጡ ብዙዎችን ይጠራል፤ በአንጻሩ ግን ጥቂቶችን ይመርጣል

የእግዚአብሔር የወንጌል ጥሪ ለሁሉ 

ሰዎች ከኃጢአታቸው የሚድኑበትን ደኅንነት ሊሰጣቸው እግዚአብሔር ወደ እርሱ ዘንድ ይመጡ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል። ይህ ጥሪ የእግዚአብሔር የወንጌል ጥሪ ወይም የእግዚአብሔር አጠቃላይ ጥሪ ተብሎ የሚጠራበት ጊዜ አለ። ሰዎች ሁሉ ወንጌልን ማለት የምሥራቹን ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ለሁሉም የሚያቀርበው ጥሪ ነው። 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 45፡22 አንብቡ፡ ሀ) እግዚአብሔር ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እነማንን ጠራ? ለ) ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱት ምን ያገኛሉ? 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 55፡1 አንቡ። ሀ) እግዚአብሔር ማን ወደ እርሱ ይመጣ ዘንድ ጠራ? ለ) ወይንና ወተት ለመዛት የሚመጡ ምን ያህል ዋጋ ይጠየቃሉ? 

3ኛ ጥያቄ፡- ማቴዎስ 11፥28-30 ንቡ። ሀ) ኢየሱስ ወደ እርሱ ይወጡ ዘንድ እነማንን ጠራ? ለ) ኢየሱስ ወደ እርሱ ዘንድ ለሚመጡት ምን ተስፋ ሰጣቸው? 

4ኛ ጥያቄ፡- ማቴዎስ 22፡44 አንብቡ። ሀ) የተጠሩት ምን ያህሉ ናቸው? ለ) ምን ያህሉን ተመረጡ? 

5ኛ ጥያቄ፡- ራእይ 22፡17 አንብቡ። የሕይወትን ውኃ መጥተው በነፃ ይወለዱ ዘንድ የተጠሩት እነማን ናቸው? 

የእግዚአብሔር የወንጌል ጥሪ፥ ሰዎች ሁሉ በኃጢአታቸው ከበደሉት በደል ሁሉ ነፃ ወጥተው ደኅንነትን እንዲያገኙ ነው። በኢሳይያስ 45፡22 ውስጥ በምድር ዙሪያ ያሉ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብላቸዋል። ቃሉን ሰምተው ቢታዘዙ ደኅንነትን ለማግኘት እንደሚችሉ ተስፋ ይሰጣቸዋል። በሚቀጥሉት የጥቅስ ቁጥሮች ውስጥ፥ ጠላቶቹ እንደሚቀጡ እግዚአብሔር በራሱ ይምላል። ዳሩ ግን ወደ እርሱ ዘንድ የሚመጡ ጻድቃን ተብለው እንደሚጠሩ ይናገራል። እንዲሁም በኢሳይያስ 55፡1 የመንፈስ ጥማት ያለባቸው ሁሉ ወደ እርሱ ዘንድ መጥተው መንፈሳዊ ወይንና ወተት በነፃ ጠጥተው ከጥማቸው እንዲረኩ ሰዎችን ሁሉ ይጋብዛል። ኢየሱስም ወደዚህ ምድር በመጣበት ጊዜ እርሱ የእነዚህ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች ፍጻሜ መሆኑን ግልጽ አድርጎ ተናግሮ ነበር። ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ዘንድ መጥተው የደኅንነቱ ቡራኬ ተሳታፊዎች ይሆኑ ዘንድ ነፃ ጥሪ አቅርቧል። በማቴዎስ 11፡28–30 ደግሞ የተጨነቁትና ሸክምም የከበደባቸው ወደ እርሱ ዘንድ ይመጡ ዘንድ ኢየሱስ ጥሪ አቅርቦላቸዋል። እረፍትን በተለይም የነፍስ ዕረፍትን ሊሰጣቸው ፈቅዷል። ኢየሱስ በማቴዎስ 22 ላይ ስለ አንድ ሠርግ ዝግጅት ተርኮ ነበር። ሠርጉን ያዘጋጀው ንጉሥ ብዙ እድምተኞችን ጠራ። ነገር ግን ከተጠሩት ብዙዎቹ ለመምጣት ባለመፈለጋቸው እንዲሁም ጥሪውን እክብረው ከመጡት መካከል አንዳንዶቹ ንጉሡ በፈለገው አኳኋንና ሥነ ሥርዓት በመምጣት ፈንታ በራሳቸው መንገድ ስለ መጡ፥ እነዚያ ጥሪውን አክብረው የንጉሡን ሥነ ሥርዓት ጠብቀው የመጡት ጥቂቶቹ ብቻ የሠርጉን ደስታ ሊካፈሉ ቻሉ። ኢየሱስ ይህን ታሪክ ተናገር በቁጥር 14 ላይ እንዲህ ብሎ ትረካውን ደመደመ፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የተጠሩት ብዙዎች ሲሆኑ፥ ወደ መንግሥቱ ገብተው የደስታው ተካፋይ ለመሆኑ የተመረጡ ጥቂቶች ናቸው። በእግዚአብሔር ጋባዥነት ወደ መንግሥቱ ለመግባትና የደኅንነቱን ደስታ ማግኘት ማለት ሰፊ ግብዣ ወይም ጥሪ ነው። ጥሪው ለዓለም ሁሉ የተላለፈ ጥሪ ነው። ነገር ግን ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ጥሪ ችላ በማለታቸው፥ እንዲሁም ወደ ግብዣው እንዳሻቸው ስለ መጡና እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ ባለመምጣታቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚገቡት ጥቂቶቹ ናቸው። ራእይ 22፡17 የኢሳይያስ 5፡1ን ጥሪ የሚያስተጋባ ሲሆን፥ ማንኛውም የተጠማ ሰው መጥቶ የዘላለምን ሕይወት ነፃ ስጦታ ይቀበል ዘንድ ጥሪ ያቀርባል። 

እያንዳንዱ ሰው በራሱ ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ መስጠት አለበት 

እግዚአብሔር በዓለም ላሉ ሰዎች ሁሉ ደኅንነቱን ይሰጣል። እንዲህ ሲባል ደሞ ማንኛውም ሰው ይድናል ማለትም አይደለም። ይህን ደኅንነት ለማግኘት ሰዎች ይህን መልእክት አድምጠው ለጥሪው መልስ ሲሰጡ፥ ያን ጊዜ ይህን የተዘጋጀላቸውን ደኅንነት ሊያገኙ እንደሚችሉ ቅዱስ መጽሐፍ ያስገነዝባል። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡11-12 አንብቡ፡ ሀ) ኢየሱስ ለእነማን መጣ? ለ የእግዚአብሔር ልጅነትን መብት እነማን አገኙ? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 10፡12-15 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሐር የደኅንነትን በረከ፡ ለእነማን ሰጠ? (ቁ 12) ለ) እንድ ሰው ይህን ደኅንነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርበታል? (ቁጥር 13-14) አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች ከመፈጸሙ በፊት ምን መደረግ ይኖርበታል? (ቁጥር 14-) 

ጥያቄ፡- ራእይ 3፡20 አንብቡ፡ ኢየሱስ ወደ ሰው ሕይወት መጥቱ ከእርሱ ጋር አንድነት እንዲኖረው ምን መደረግ ይኖርበታል? 

እግዚአብሔር ደኅንነቱን ለሰዎች ሁሉ ይሰጣል። ቢሆንም ሰዎች ይህን የደኅንነት ስጦታ ለማግኘት በግላቸው ለዚህ የእግዚአብሔር ስጦታ የሚጠበቅባቸውን ምላሽ መስጠት አለባቸው። በዮሐንስ 1፡11-12 ያለው ክፍል ኢየሱስ ወደ ወገኖቹ ወደ አይሁድ ቢመጣም እነርሱ ገን እንዳልተቀበሉት ይገልጻል። ታዲያ እነዚያ ጥቂቶቹ የተቀበሉትና ያመኑበት ብቻ የእግዚአብሔር ልጅነትን መብት አግኙ። እንዲሁም በሮሜ 10፡12 አይሁድም ሆነ አሕዛብ ሁሉም የእግዚአብሔርን የደኅንነት ስጦታ ሊቀበሉ መጠራታቸውን ያብራራል። ነገር ግን ቁጥር 13-14 ባለው ክፍል ታክሎ እንደምንመለከተው የጌታን ስም የሚጠሩና በእርሱ የሚያምኑ ብቻ ‘ እንደሚድኑ ይናገራል። ስለሆነም ሰዎች የጌታን ስም ለመጥራትና በእርሱም ለማመን እንዲችሉ የተሰበከላቸውን የክርስቶስን መልእክት ማዳመጥ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳን ደኅንነት ለሁሉም ቢሆንም፥ እያንዳንዱ ሰው በግሉ ደኅንነትን ተቀብሎ ለመዳን የክርስቶስን ጥሪ አድምጦ የሚፈለግበትን መፈጸምና ለጥሪውም ቃል ምላሽ መስጠት አለበት። በራእይ 3፡20 ውስጥ ኢየሱስ፡- በእያንዳንዱ ሰው ልብ መዝጊያ አጠገብ ቆሞ እንደሚያንኳኳና ለመግባትም እንደሚፈልግ ይናገራል። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የልቡን ስር ለመክፈት ፈቃደኛ መሆን አለበት። በመሆኑም፥ ሰዎች ኢየሱስ ወደ እነርሱ እንዲገባና ከእነርሱ ጋር አንድነት እንዲኖረው ካላደረጉ በስተቀር አይገባም። እግዚአብሔር የደኅንነት ስጦታውን ለሰዎች ሁሉ ያቀርባል። ይህን ጊዜ ሰዎች ይህን ስጦታ ለመቀበል በግላቸው ዝግጁዎች መሆን አለባቸው። ያለበለዚያ ይህን የእግዚአብሔር ደኅንነት ማግኘት አይችሉም። 

ከኃጢአት የተነሣ ቢተዉ፥ ሰዎች ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ጥሪ ግድም አይኖራቸውም

ጥያቄ፦ ሮሜ 3፡11 እንብቡ። ስንት ሰዎች መንፈሳዊ ነገርችን ተገንዝበው እግዚአብሔርን ይፈልጉታል? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 6፡44 አንብቡ፡ አንድ ሰው ወደ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ምን መደረግ ይኖርበታል? 

ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4 አንብቡ። ሰይጣን የሚያምኑትን ዓይን ምን አደረገ? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡18-19 አንብቡ። ሀ) የእግዚአብሔር ቁጣ በሰዎች ላይ በምን ምክንያት ተገለጠ? ለ) እዚህ ላዎች ስለ እግዚአብሔር አንዳች እውቀት ነበራቸው? (ቁ 19) ሐ) ሮሜ 1፡21፣25 አንብቡ። እግዚአብሔርን ሳወቁት መጠን እዚህ ሰዎች ምን አደረጉ? 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 23፡37 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ለሰዎቹ ምን ሊያደርግላቸው ፈለገ? ለ) መልሳቸው ወይም አስተሳሰባቸው ምን ነበር?  

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 5፡40 አንብቡ። ሰዎች ለኢየሱስ ምላሽ የሰጡት እንዴት ነበር? 

15ኛ ጥያቄ፦ ዮሐንስ 8፡44 አንብቡ። አይሁዳውያን የማንን ፈቃድ መፈጸም ይፈልጉ ነበር? 

በ12ኛው ትምህርት ውስጥ፣ ሰዎች በተፈጥሮ ኃጢአተኛች ሆነው እንደሚመለፉ፥ እንዲሁም ሁሉም ሰዎች ኃጢአት እንደሚሠሩ ተምረናል። እንደዚሁም ከዚህ ኃጢአት የተነሣ ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብሎ ወደ እርሱ ሊመጣ እንደማይችል ተመልክተናል። የማያምኑ ሰዎች እውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ንዛቤ የላቸውም (ኤፌሶን 4፡18፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡13)፥ በኃጢአታቸውም የሞቱ ናቸው (ኤፌሶን 2፡1)፥ የኃጢአትም ባሪያዎች ናቸው (ዮሐንስ 8፡34)። ኃጢአት ሰዎች የእግዚአብሔርን የደኅንነት ጥሪ ተቀብለው ወደ እርሱ እንዳይመጡ ያደርጋቸዋል። የማያምኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሥራ እንዳይመለከቱ ዓይናቸውን ስለሚያሳውርሳቸው፥ እግዚአብሔር ጣልቃ ካልገባ በስተቀር፥ የወንጌልን ብርሃን ሊያዩ አይችሉም (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4)። እግዚአብሔር ወደ ሕይወታቸው ከመግባቱ በፊት ማንኛቸውም ስለ እግዚአብሔር ሊነዘቡና እግዚአብሔርንም ሊፈልጉት አይችሉም (ሮሜ 3፡1ህ። ስለዚህ ያላመኑ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ቢተዉ ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት አይችሉም። እግዚአብሔር ራሱ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ካልሳበ በስተቀር ወይም እርሱ ሥራውን ካልሠራ ሊመጡ አይችሉም (ዮሐንስ 6፡44)። 

እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ የደኅንነትን ነፃ ስጦታ ያቀርባል። ሆኖም እያንዳንዱ ሰው በግሉ ስጦታውን ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል። እያንዳንዱ ሰው በኃጢአት ከመወለዱም በላይ ኃጢአትን ስለሚሠራ የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብሎ ወደ እርሱ ሊመጣ አይችልም። በዚህ ፈንታ፥ እያንዳንዱ ሰው ስለ እግዚአብሔር የሚያውቀውን ላለማወቅ፥ እግዚአብሔር የሰጠውን የደኅንነት ስጦታ ላለመቀበል የራሱ ምርጥ ነው። ሮሜ 1፡18-19 እንደሚለው እግዚአብሔርን እያወቁ እንዳላወቁ ስለሆኑ፥ የእግዚአብሔር ቁጣ ተገለጠባቸው። ሁሉም ስለ እግዚአብሔር በመጠኑ እያወቁ፥ በሚያውቁት ተጠቅመው እርሱን በማክበር ፈንታ፥ በራሳቸው ነፃ ፍላጎት ለጣዖት መስገድን መረጡ (ሮሜ 1፡21፣ 25)፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ሊሰበስባቸው፥ ሊንከባከባቸውና ዶሮ ጫጩቶችዋን ሰብስባ እንደ ምትጠብቃቸው፥ እርሱም የእርሱ የሆኑትን ሊንከባከብ መፈለጉን ነሮአቸው ነበር። ነገር ግን ሕዝቡ አልሰሙትም፥ አልተቀበሉትም። አብዛኛዎቹ አይሁዶች ኢየሱስ የሰጣቸውን የደኅንነት ስጦታ ናቁት (ማቴዎስ 23፡37)። በዮሐንስ 5፡40 ውስጥ ኢየሱስ ለሕዝቡ ሊሰጣቸው የነበረውን ነክ የደኅንነት ስጦታና የዘላለም ሕይወት አንቀበልም ብለው አሻፈረን ማለታቸውን ተናግሮአል። እንዲሁም በዮሐንስ 8፡44 ላይ የእርሱን ቃል በመስማት ፈንታ ለሰይጣን መታዘዝን መረጡ ይላል። በኢየሱስ ስጦታ ፈንታ በነህ ፍላጎታቸው የሰይጣንን ምኞትና ፍላጎት መከተል መረጡ። 

እኛም ብንሆን እንዳለን ችላ ተብለን ብንተው መልሳችን እንዲህ ይሆናል። ማንም ቢሆን የእግዚአብሔርን ነፃ ስጦታ ለመቀበል መምረጥ አይችልም። ታዲያ ማን ሊድን ይችላል? እግዚአብሔር የሚሰጠውን ነፃ የደኅንነት ስጦታ ለመቀበል ሰዎች ለጥሪው እንዴት ሊመልሱ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጥልን፥ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ወደ እርሱ የሚመጡትን በመምረጥና በመጥራት ለጥሪው ምላሽ እንዲሰጡ አስችሎአቸዋል። 

እግዚአብሔር ለጥሪው ምላሽ የሚሰጡ አንዳንድ ጥቂት ሰዎችን ይመርጣል፡፡ 

ጥያቄ፡- ኤፌሶን 1፡4 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር ለእኛ ምን አደረገልን? ለ) ኤፈሶን 1፡5 አንብቡ። እግዚአብሔር ለእኛ ምን አደረገልን? ሐ) ኤፌሶን 1፡11 አንብቡ። እግዚአብሔር እንደ ፈቃዱ ምንን ይፈጽማል? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 15፡16 አንብቡ። ደቀ መዛሙርቱ እንዴት ወደ ኢየሱስ መጡ? 

ጥያቄ፡- የሐዋርያት ሥራ 13፡48 አንብቡ። ሀ) ያመኑት እነማን ነበሩ? ለ) የሐዋ. 16፡14 አንብቡ። ሊፈያ የወንጌልን መልእክት እንድትቀበል ልብዋን የከፈተላት ማን ነበር? ሐ) የሐዋ. 18፡10 አንብቡ፡ እግዚአብሔር በቆሮንቶስ ውስጥ እነማን ነበሩት? 

እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ዘንድ እንዲመጡ የጠራቸው ቢሆንም፣ ከኃጢአታቸው የተነሣ የዓለም ሕዝቦች የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ በገዛ ፈቃዳቸው ሳይቀበሉት ቀሩ። እንዲህ ላለው ችግር መፍትሔው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ከእነዚህ ሳይቀበሉት ከሚቀሩት መካከል የሚመርጣቸው ቃሉን ተቀብለው ወደ እርሱ በመመለስ የደኅንነቱን ጸጋ እንደሚያገኙ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ኤፌሶን 1፡4-5 እንደሚለው እግዚአብሔር ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ልጆቹ አድርጎ አስቀድሞ መረጠን። የተወሰኑ ሰዎች ቃሉን ሰምተው በምርዓው ለሰሙት ቃል ምላሽ እንዲሰጡ የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፥ እናም በእርሱ አምነው ወደ እርሱ በሚመጡበትም ጊዜ ኃጢአታቸው ይወገድላቸውና የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ስጦታ ያገኛሉ። እግዚአብሔርን ይህን እርሱ እንደ ፈቀደና ደስ እንዳለው ያደርጋል። ኤፌሶን 1፡11 ጨምሮ ሲያስረዳ፥ «ሁሉን ነገር በገዛ ራሱ ፈቃድ በሚሠራ በእግዚአብሔር ዕቅድ መሠረት አስቀድመን ስለ ተወሰንን፥ አሁንም በክርስቶስ አማካይነት ተመረጥን» ይላል። እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነውን እንደ ፈቃዱና እንደ አሳቡ እንደሚፈጽም ይህ ጥቅስ ደህና አድርጎ ያስረዳል። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ክርስቶስ የሚያመጣው ራሱ ባቀደው መሠረት እንጂ በሰዎች ውሳኔና አስተሳሰብ ላይ ያተኮረ አይደለም። ኢየሱስ ይህን እውነተኛ ድርጊት በደቀ መዛሙርቱ ላይ መጠቀሙን ዮሐንስ 15፡16 ይገልጻል። ወደ እርሱ ሊመጡ መርጠው እንዳልነበሩ ነርአቸዋል። በዚህ ፈንታ እርሱ እንደ መረጣቸው አስረድቷቸው ነበር። እርሱ ባይመርጣቸው ኖሮ እነርሱም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ባልሆኑ ነበር። እግዚአብሔር ሰዎችን መርጦ ወደ ራሱ ስለ ማምጣቱ ጉዳይ፥ የሐዋርያት ሥራ በርከት ያሉ ምሳሌዎችን ይዟል። ስለሆነም በሐዋርያት ሥራ 13፡48 እንደምናየው፥ እግዚአብሔር ለዘላለም ሕይወት የመረጣቸው ነበሩ። ያመኑት ሰዎች እንዲሁም በሐዋርያት ሥራ 16፡44፥ እግዚአብሔር የሊዲያን ልቦና ስለ ከፈተላት የጳውሎስን መልእክት ልትቀበል ቻለች፡ በሐዋርያት ሥራ 18፡10 ደግሞ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ከተማ ቆይቶ የእግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ለሆኑት ወንጌልን እንዲሰብክ እግዚአብሔር አዝዞታል። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች በጳውሎስ ስብከት አማካይነት ወደ እርሱ እንዲመጡ እግዚአብሔር የመረጣቸው ናቸው። 

ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ዘንድ በራሱ በእግዚአብሔር ምርጥ እንደመጡ ጠንካራ የሆነ መልእክት አለበት የምንለው ክፍል ሮሜ 9፡6-24 ነው። ስለዚህ የዚህን ጥቅስ መጀመሪያውን ክፍል ዛሬ እንመለከትና ቀሪውን ደግሞ ነገ እናጠናዋለን። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 9፡6-9 አንብቡ። ሀ) የአብርሃም እውነተኛ ልጆች እነማን ናቸው? ለ) ጳውሎስ በዚህ ክፍል ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም የሚላቸው እነማን ናቸው? ሐህ የእግዚአብሔር ተስፋ ፍጻሜ የተባለው የማን ልጅ ነበር? ጥያቄ፡- ሮሜ 9፡10-13 አንብቡ። ሀ) ርብቃ ስንት ልጆች ነበሩዋት? ለ) እነዚህ ልጆች በምን ይመሳሰላሉ? ሐ) የትኛው ልጅ የእግዚአብሔርን ተስፋ እንደሚቀበል ያልወሰነው ምን ነበር? መ) የትኛው ልጅ የእግዚአብሔርን ተስፋ እንደሚቀበል የወሰነው ምን ነበር? 

ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮማ ምዕራፍ 9-11 ባሉት ክፍሎች በእግዚአብሔር ተመርጠው የነበሩ የአይሁድ ሕዝብ በምን ምክንያት አዳኛቸውን መሢሕ እንዳልተቀበሉ በሰፊው ይገልጻል። ማብራሪያውንም አይሁዶች ሁሉ የተስፋ ልጆች ስላልነበሩ፥ ሁላቸውም ኢየሱስን አለመቀበላቸውን በመግለጽ ይጀምራል። እዚህ ላይ ብዙ አይሁዶች በሥጋ ብቻ የአብርሃም ዘር ስለሆኑ ብቻ እግዚአብሔር እያንዳንዳቸውን የሚያድናቸው መስሎአቸው ተሳሳቱ። ጳውሎስ ግን በሥጋ ብቻ ከአብርሃም ዘር መወለድ ማንንም ለደኅንነት እንደማያበቃ አበክሮ ተናገረ። በሥጋ የአብርሃም ልጅ የሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች አይደሉም። ስለሆነም የሥጋ ዝርያነት ብቻ ለእግዚአብሔር ልጅነት አያበቃም። 

ጳውሎስ ከአብርሃም በሥጋ የተወለዱ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠውን ተስፋ እንዳላገኙ ከብሉይ ኪዳን ውስጥ ሁለት ምሳሌዎችን ያቀርባል። የመጀመሪያውን የግራ ልጅ ይስሐቅ የእግዚአብሔርን ተስፋ እንደ ተቀበለ የሚናገረው ክፍል ነው። አብርሃም በአጠቃላይ ስምንት ልጆች ነበሩት (ዘፍጥረት 16፡15፤ 21፡2-3፤ 25፡1-2)። ነገር ገን እግዚአብሔር ውርስ የሰጠው ለግራ ልጅ ለይስሐቅ ብቻ ነበር። ይስሐቅ ተስፋ የተሰጠው እውነተኛው የአብርሃም ልጅ እንደሆነ ሁሉ፥ የተስፋ ልጆች የሆኑ ብቻ እውነተኞች የእግዚአብሔር ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ። 

ነገር ማን ይለሐቅ ከሣራ በመወለዱ ምክንያት የተስፋ ልጅ ሆነ ብለው አንባቢዎቹ እንደሚከራከሩት ጳውሎስ ያውቅ ነበር። ስለዚህ ሐዋርያው ከአብርሃም የተወለዱ ሁሉ የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት ሊያገኙ እንደማይችሉ፥ የያዕቆብንና የዔሳውን ታሪክ በሁለተኛ ምሳሌነት ያቀርባል። እንደሚታወቀው ያዕቆብና ዔሳው የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። ሁለቱም መንትዮች ነበሩ። በውልደታቸው ሁኔታ በመካከላቸው ልዩነት አልነበረም። ግን ከሁለቱ አንዱ የተስፋ ልጅ ሆነ፡ ከሁለቱ አንዱ ብቻ የእግዚአብሔርን የማዳን ተስፋ በረከትን ሊቀዳጅ ቻለ። ይህ የእግዚአብሔርን በረከት ያገኘው ልጅ በተወለደበት ወቅት አንጋፋው ልጅ አልነበረም። የእግዚአብሔርን በረከት የማግኘት ሁኔታ በልደት ላይ የተመሠረተም አይደለም። የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ከአብርሃም ዘር መወለድ ብቻ በቂ አይደለም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን በረከትና የእግዚአብሔርን ደኅንነት ለመቀበል የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን ይሻል። 

ይህ የያዕቆብና የዔሳው ታሪክ የእግዚአብሔርን የደኅንነቱን በረከት በሥጋ ልደት ማግኘት እንደማይቻል ብቻ የሚያመለክት አይደለም። ይህ ታሪክ ጨምር የሚያስተምረው ቁም ነገር የደኅንነት በረከት የመልካም ሥራ ውጤትም እንዳልሆነ ነው። በመሠረቱ ያዕቆብም ሆነ ዔሳው መልካም ሰዎች አልነበሩም። ያዕቆብ አታላይና ሌባ ነበር። ስለዚህ የወንድሙን ብኩርና ከመንጠቁም በላይ በረከቱንም ወስዶበታል። ዔሳው በበኩሉ እግዚአብሔርን የማይፈራና ሥነ ምግባር የጎደለው ሰው ነበር። ነገር ግን አይሁዶች ያዕቆብ ከዔሳው የተሻለ በመሆኑ የእግዚአብሔር ተስፋ እንደ ተሰጠው አድርገው ያሰቡ ነበር። ለእነዚህ ያዕቆብ ከዔሳው የተሻለ በመሆኑ የእግዚአብሔርን በረከት አገኘ ብለው ለሚያምኑ ሰዎች ጳውሎስ ሲናገር፥ ሁለቱም ልጆች ከመወለዳቸው በፊት እግዚአብሔር ለርብቃ ለእናታቸው ታናሹ ወንድሙ ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ልዩ የተስፋ በረከት እንደሚቀበል ነርአታል። እንግዲህ ከሁለቱ አንዳቸውም ክፉም ሆነ በጎ ሳይሠሩ ከሁለቱ አንዱ የተስፋ ልጅ እንዲሆን ተመረጠ። የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት በማግኘት ረገድ ልደት ወይም መወለድ ልዩነትን ሊያመጣ እንደማይችል ሁሉ፥ መልካም ሥራና ሕይወትም በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነትን ሊያስከትል አይችልም። 

የእግዚአብሔርን በረከት በመቀበል ረገድ መልካም ስራ ስፍራ እንደሌለው ጳውሎስ ለማስገንዘብ ሚልክያስ 1፡2-3 ያለውን ሲጠቅስ፡ «ያዕቆብን ወደድሁ፥ ~ ዔሳውን ግን ጠላሁ» የሚለውን ይናገራል። በመጀመሪያ ይህን ጥቅስ ስናነብ እግዚአብሔር በዔሳው ላይ መጥፎ ስሜት እንዳለውና በያዕቆብ ላይ ግን መልካም አመለካከት ያለው ሆኖ ይሰማን ይሆናል። ነገር ግን የዚህ ቃል ትርጉም ወይም ዓላማ ይህ አይደለም፡ ለጥንቶቹ አይሁዳውያን፥ አንድን ሰው «መውደድ» ማለት ያንን ሰው ለአንድ መልካም ነገር መምረጥ ማለት ነበር። በአንጻሩ አንድን ሰው «መጥላት» ሊባል ደግሞ ያንን ሰው ችላ ማለትና ማራቅ ማለት ነው። ያዕቆብ የእግዚአብሔርን የደኅነቱን ተስፋ ያገኘው በፈጸመው መልካም ምግባር አልነበረም። ይህን ሊያገኝ የቻለው እግዚአብሔር ስለ መረጠው ብቻ ነው። ነገር ግን ዔሳውን ችላ ብሎት ወዳሻው እንዲሄድ ተወው። 

ስለዚህ መልካም ሥራ ማንኛውም ሰው የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት እንዲያገኝ ሊያደርገው አይችልም። 

ነገር ግን ይህ ጳውሎስ ከሚልክያስ መጽሐፍ ውስጥ የጠቀሰው ቃል ጥያቄዎችን ወዲያውኑ ሊያስነሣ ይችላል። እዚህ ላይ ታዲያ እግዚአብሔር ለያዕቆብ እደላ ማለት ነው? በአንጻሩ ዔሳውንስ በደለው ማለት ነው? ለምንድን ነው እግዚአብሔር ዔሳው የያዕቆብ አገልጋይ ይሆናል ያለው? «እግዚአብሔር በምርግ ረገድ ያለውን ዓላማ ለማሳየት ነው»? እግዚአብሔር ያዕቆብን መርጦ ዔሳውን መናቁ ፍትሐዊ ነበር? 

ጳውሎስ ለእነዚህ አስቸጋሪ ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ፥ እግዚአብሔር እነዚህን ሁኔታዎች በልዕልናው ሥልጣን እንደሚቆጣጠር ያውቃል፥ ግን ስለ ምሕረቱ ለመናገር ብሎ ነው። በነገው ትምህርታችን ወደዚህ ጥቅስ መለስ ብለን እግዚአብሔር በልዕልናው ሥልጣን ደኅንነቱንና ምሕረቱን እንዴት እንደሚሰጥ እናጠናለን። 

ብዙዎቹ አይሁዳውያን በሥጋ ልደት ከአብርሃም ዘር በመወለዳቸው ብቻ የእግዚአብሔርን ደኅንነትና የደኅንነቱን በረከት የሚያገኙ ይመስላቸው ነበር፡ እንዲሁም ለብዙ አይሁዳውያን መልካም ሥራቸው የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ደኅንነት ለማግኘት ዋስትና የሚያስገኝላቸው ሆኖ ይታያቸው ነበር። እንደ አይሁድነታቸው በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ የታዘዙትን መልካም ተግባራት ሁሉ ፈጽመዋል። 

ከዚህ በመነሣት ነበር በመልካም ሥራቸው ዋስትና የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት የሚያገኙ የመሰላቸው። ጳውሎስ ግን ተሳስተዋል ይላል። እግዚአብሔር ከአብርሃም በሥጋ ለተወለዱ ወይም መልካም ሥራ ለሠሩ የደኅንነቱን በረከት አይሰጥም፥ እርሱ ይህን በረከት የሚሰጠው የተስፋ ልጆች ለሆኑት ብቻ ነው፡፡ 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን የነበሩ አይሁዶች የተሳሳቱትን ስሕተት የመሰለ፥ የሰፈራችሁ ነዋሪዎች እንዴት ባለ ሁኔታ ይሳሳታሉ? ለ) እነዚህ ሰዎች ስሕተታቸውን ለማወቅ ይችሉ ዘንድ አሁን ከተማራችሁት ክፍል የትኛውን አብራችሁ ለመወያየት ትፈቅዳላችሁ? 

ድሮ በጳውሎስ ጊዜ የነበሩ አይሁዶች ያደርጉት የነበረውን ስሕተት ዓይነት ዛሬም የሚሳሳቱ ብዙ ሰዎች አሉ። እነርሱም በክርስቲያን ቤተሰቦች መካከል በመወለዳቸው ብቻ ደኅንነትንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንደሚያገኝ ይመስላቸዋል። ምናልባትም አባቶቻቸው ካህናት ወይም ወንጌላውያን ሊሆነ ይችላሉ። ወይም በሕፃንነታቸው በክርስቲያን ቤተ ክርስቲያናት ተጠምቀወ ይሆናል። ምናልባትም ተወልደው አርባ ቀን ሲሆናቸው ወላጆቻቸው ወያ ቤተ ክርስቲያን አምጥተዋቸው ይሆናል። ወይም ከልጅነት ዕድሜያቸዉ ጀምረው የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሆነው ይሆናል። እነዚህ ሁላ አስደናቂ የሆኑ የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው። ልክ እስራኤላውያ ከእግዚአብሔር ዘንድ አስደናቂ በረከቶችን ያገኙ እንደ ነበረ ማለት ነው ነገር ግን ማንም ሰው ቢሆን፥ ይህ የቤተሰብ ውርስ የደኅንነት ዋስት እንደሚሆናቸው አድርገው የሚያስቡ ከሆነ ልክ እንደ አይሁዳውያኑ ስሕተትን ይሠራሉ። በተመሳሳይ መንገድ ሁላችንም ይህን ዓይነት አስተሳሰብ ካለን የአይሁዶችን ስሕተት እንደግማለን ማለት ነው። ስለሆነም በክርስቲያን ቤተሰቦች ውስጥ መወለዳችን የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት ለመቀበል ዋስትና ሊሆነን አይችልም። እንደዚሁም በምትኖሩበት አካባቢ ካሉ ሰዎች በጎ ሥራ በመሥራት የተለያችሁ ሆናችሁ መገኘት ብቻ የእግዚአብሔርን የደኅንነት በረከት ለማግኘት ማረጋገጫ ሊሆን አይበቃም። ነገር ግን በክርስቶስ ባለን እምነት የእግዚአብሔር ልጆች ስንሆን ያን ጊዜ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔርን የደኅንነት ስጦታ ለማግኘት ዋስትና ይኖረናል።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version