Site icon የሕይወት እንጀራ

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

This entry is part 4 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሕርያት አሉት 

ትናንትና ኢየሱስን በግልጽ «አምላክ» ብለው የጠሩትን ጥቅሶች ተመልክተን ነበር። ዛሬ ደግሞ ኢየሱስ፥ የእግዚአብሔር ባሕርያት እንዳሉትና እግዚአብሔር የሚፈጽማቸውን ተመሳሳይ ተግባራት እንደሚፈጽም የሚያስተምሩንን ጥቅሶች በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንመለከታለን። 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ጥያቄ፡- ሀ) መዝሙር 65፡7፤ 89፡9፤ ኤፌሶን 1፡11 እና ኢዮብ 42፡2 አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምንን ያስተምራሉ? ለ) ማቴዎስ 8፡26-27፤ 14፡19፤ 28፡18፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡22 አንብቡ። እነዚህስ ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ምንን ያስተምራሉ? ሐህ ዮሐንስ 13፤ ቆላስይስ 3፡16-17 እና ዕብራውያን 1፡3 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደ ተገለጸው አንዳንዶቹ የኢየሱስ ሥራዎች ምንድን ናቸው? 

እግዚአብሔር ሁሉን ቻይና ሁሉን ገዢ ነው። ይህ ታዲያ እግዚአብሔር ከባሕርያቱ ጋር የሚቃረኑ ተግባራትን ይፈጽማል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያህል፥ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፤ ኃጢአትን ሊሠራ አይችልም። እግዚአብሔር ሁሉንም ሊያደርግ ይችላል በምንልበት ጊዜ ሥልጣን ሁሉ አለው፥ ዓለም ሁሉ በሥልጣኑ ሥር ነው፥ ለባሕርያቱ ተጻራሪ ያልሆኑትን ተግባራት ሁሉ ይፈጽማል ማለታችን ነው። መዝሙር 65፡7 እና መዝሙር 89፡9 በፍጥረቶቹ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና የዓለምን ሕዝቦችም በሥልጣኑ እንደሚያስተዳድር ይናገራሉ። በተለይ ኤፌሶን 1፡11 እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉትን ማንኛቸውንም ነገሮች በሥልጣኑ፥ እንደ ራሱ ፈቃድ እንደሚመራ ይገልጻል። በተጨማሪም ኢዮብ 42፡2 ስለ እግዚአብሔር የመፍጠር ችሎታ ይናገራል። 

ኢየሱስም እግዚአብሔር መሆኑን የሚያረጋግጥ የማይወሰን ኃይልና ሥልጣን አለው። በመዝሙር 89፡9 ላይ፥ እግዚአብሔር በኃይለኛው የባሕር ማዕበል ላይ ሥልጣን አለኝ እንዳለው ሁሉ፥ ኢየሱስ በማቴዎስ 8፡26-27 ላይ አስደናቂ ምሳሌን አሳይቷል። ማቴዎስ 28፡18 ኢየሱስ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ኃይልና ሥልጣን እንዳለው ይነግረናል። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡22 የኢየሱስ ሥልጣንና ኃይል ከመላእክትና ከሌሎችም ኃይላት በላይ መሆኑንና መንፈሳዊ ኃይላትም እንደ ተገዙለት ይገልጻል። ስለዚህ የኢየሱስ ችሎታ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል። 

የኢየሱስ ኃይልና ሥልጣን፤ በአብዛኛው ሰማይና ምድርን በመፍጠር እና ሥርዓታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ በማድረግ ሥራው ውስጥ በግልጽ ይታያል። እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው። ይሁን እንጂ ዮሐንስ 1፡3 ቃል ማለትም ኢየሱስ ሁሉንም ነገር እንደ ፈጠረ በማያሻማ ሁኔታ ይናገራል። ቆላስይስ 3፡16-17 ይህንን የበለጠ አጉልቶ ይገልጸዋል። ኢየሱስ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ፈጥሯል። ይህ መናፍስት የሆኑትንም ሁሉ ያጠቃልላል። ፈጣሪያቸው እንደ መሆኑ፥ እርሱ ከሁሉም ነገር በፊት ነበር። ሁሉንም ነገር በሥርዓት አድርጎ ደግፎ የያዘ እርሱ ነው (ዕብ 1፡3)። መጽሐፍ ቅዱስ ህልውና ያለውን ሁሉ ኢየሱስ ፈጠረ ሲል በግልጽ ይናገራል። እንግዲህ ይህ ሁሉ እርሱ እግዚአብሔር ለመሆኑ ምስክር ነው። 

ጥያቄ፡– የኢየሱስ ታላቅ ኃይልና ሥልጣን እንዴት መጽናናትን ይሰጣችኋል? ቢያንስ ሁለት መንገዶችን ጻፉ። 

የኢየሱስ ኃይልና ሥልጣን በብዙ መንገዶች ያጽናናናል። ኢየሱስ ወደ ሕይወታችን የሚመጣውን ነገር ሁሉ ይቆጣጠራል። ስለዚህ እርሱ ሳያውቅ በድንገት የሚደርስብን ነገር ሊኖር አይችልም። ኢየሱስ ለዓላማው ብሎ ካልፈቀደ በስተቀር፥ ሰብአዊም ሆነ አጋንንታዊ አደጋ ሊደርስብን ከቶ አይችልም። በእነዚህ አደጋዎች ላይም እርሱ ድልን እንድንቀዳጅ ይረዳናል። ኢየሱስ ለከበረ ዓላማው ካልፈቀደ በስተቀር፥ ምንም ዓይነት በሽታ እንደማያጠቃን እርግጠኞች ልንሆን ይገባል። በሽታውንም እንድንቋቋም እርሱ ኃይልን ይሰጠናል። የኢየሱስ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር፥ ፈተናም ሊያጋጥመን አይችልም። በፈተናም ላይ ድልን እንድንቀዳጅ እርሱ ኃይልን ይሰጠናል (1ኛ ቆሮ. 10፡13)። ኢየሱስ ሕይወታችንን ፍጹም ወደሆነ ፈቃዱ እንደሚመራ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን (ምሳሌ 3፡5-6)።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

የክርስቶስ መለኮታዊነት  ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 
Exit mobile version