Site icon የሕይወት እንጀራ

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

This entry is part 58 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት የከፋ ውጤት እንደሚያመጣባቸው አያውቁም። ስለዚህ «ምንም ያህል ስሕተት ብሠራ፥ እግዚአብሔር ይቅር ስለሚለኝ የምፈልገውን ማድረግ እችላለሁ» ይላሉ። እንዲሁም፥ «እኛ የምንፈጽመው ኃጢአት ይህን ያህል ከባድ ጉዳይ በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ አያደርስም፥ እንዲያው ብቻ ትንሽ ነገር ነው» ይላሉ። 

ጥያቄ፡- በታማኝነት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት መለስ ብላችሁ አስቡ። ከዚያም በዚህን ጊዜ ከፈጸማችሁት ውስጥ የማትጎዳ ትንሽ ኃጢአት ናት የምትሉአትን ለይታችሁ ጻፉ። 

ሁላችንም ብንሆን ይህን ያህል ከባድ ጉዳት አያደርስብንም ብለን በመዘናጋት ኃጢአት የምንፈጽምበት ጊዜ አለ። ችግሩ በዚህ ሁኔታ ኃጢአትን በምንፈጽምበት ጊዜ ኃጢአት ምን ያህል መጥፎ መሆኑን ከልብ አንዓዘብም። እንዲሁም የኃጢአት ውጤት ምን ያህል እንደሚከፋ አንረዳም። ታዲያ የኃጢአት ውጤት ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 2፡17 አንብብ። አዳምና ሔዋን ክፉና በጎውን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ በበሉ ቀን ምን እንደሚሆን ነበር? ለ) ዘፍጥረት 3፡8 አንብብ። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩና እግዚአብሔር ወደ አትክልቱ ውስጥ ሊመጣ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ምን አደረጉ? ሐ) ዘፍጥረት 3፡22-23 አንብብ። እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን በምን ምክንያት ከኤድን ገነት አውጥቶ አባረራቸው? 

ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡12 አንብብ። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ወደ ዓለም ምን መጣ? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 6፡23 አንብብ። የኃጢአት ውጤቶች ምንድን ናቸው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 75 አንብብ። ኃጢአተኛው ምኞታችን ምን ፍሬ ያፈራል? 

ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡15 አንብብ። ኃጢአት ካደገች በኋላ ምንን ትወልዳለች? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡50-57 አንብቡ። ሞት በመጨረሻ የሚደመሰሰው መቼ ነው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡20-21 አንብቡ። ሀ) ፍጥረት ለከንቱነት እንዲገዛ አልፎ ለምን ተሰጠ? ለ) ፍጥረት ለከንቱነት ከመገዛት መች ነፃ ይወጣል? 

የኃጢአት ውጤት ወይም ዋጋ በመሆን በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ በብዛት የተጠቀሰው ሞት ነው። ሮሜ 5፡12 ኃጢአት በአንድ ሰው ማለትም በአዳም ወደ ዓለም ወይም በዓለም ባሉ ሰዎች ሁሉ ላይ መጣ ይላል። እንዲሁም ሮሜ 6፡23 ላይ ሰዎች ከሥራቸው ክፍያ ደመወዝ እንደሚቀበሉ ሁሉ፥ ለኃጢአታቸውም ዋጋ ሞትን ያለጥርጥር ይቀበላሉ ይላል። ሮሜ 7፡5 ላይ ደግሞ ኃጢአት የሰፈነበት ምኞታችን የሞትን ፍሬ ያፈራል ይላል። በያዕቆብ 1፡5 ደግሞ፥ ኃጢአት ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች በማለት ይናገራል። ትክክለኛው የኃጢአት ውጤት ወይም ዋጋ ሞት ነው። 

ታዲያ ሞት ምንድን ነው? ሞት መለየት ነው። የሥጋ ሞት የመንፈስ ከአካል መለየት ነው። የመንፈስ ሞት ደግሞ የሰው ከእግዚአብሔር መለየት ነው። ዘላለማዊ ሞት ደግሞ ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው። እንግዲህ ኃጢአት ከእነዚህ የመለየት ዓይነቶች ቢያንስ አንዱን ያመጣል። እንደዚሁም ኃጢአት ሁልጊዜ ከእነዚህ የሞት ዓይነቶች አንዱን ያስከትላል። 

1. ኃጢአት የሥጋ ወይም የአካል በሞት መለየትን ያመጣል። 

እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ፍሬ አትብሉ ባላቸው ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው፥ «ከዚህ ዛፍ ፍሬ በበላችሁበት ቀን በእርግጥ ትሞታላችሁ።» ነገር ግን በዘፍጥረት ምዕራፍ 3ና4 ላይ ከተጻፈው ክፍል በግልጽ እንደምንረዳው አዳምና ሔዋን ከዛፉ ፍሬ በበሉበት ቀን ወዲያውኑ የሥጋ ሞት አልሞቱም ነበር። ታዲያ ምን ሆኑ? የሆነው ነገር ይህን ፍሬ ከተመገቡበት ዕለት ጀምሮ አዳምና ሔዋን የሥጋ ሞት መሞት ጀመሩ። ግን የዚህን ዛፍ ፍሬ ባይመገቡ ኖሮ፥ ለዘላለም ሕያዋን ሆነው በኖሩ ነበር። ግን ምን ያደርጋል። ኃጢአት ከሠሩበት ቀን ጀምሮ ሁለቱም አካላቸው ማለትም ሥጋቸው መበስበስ ጀመረ። በመጨረሻም ሟች ሆነ። 

ከዚህ ሰበብ የተነሣ ሥጋቸው ማለትም ሰውነታቸው ያረጅ ጀመር። ይህም ብቻ አይደለም፥ አካላቸውን ታማሚ የሚያደርጉ በሽታና ጀርሞች ወደ ዓለም ገቡ። ለዘላለም እንዲኖሩ ሊያደርጋቸው ከሚችለው የዛፍ ፍሬ እንዳይባሉ እግዚአብሔር ከለከላቸው (ዘፍጥረት 3፡22-28)። ከዚህ የተነሣ አዳምና ሔዋን ከዚህ የዛፍ ፍሬ ከተመገቡበት ቀን አንሥቶ በአካል መሞት ጀመሩ። 

የአካል ወይም የሥጋ ሞት በኃጢአት ምክንያት እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡54-5 «ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፡- ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ» ይላል። ይህ እንግዲህ የሥጋ ሞት የኃጢአት ውጤት መሆኑን ያስረዳናል። ሮሜ 8፡18-25 እንደሚለው ከኃጢአት ውጤት የተነሣ የሰው ተፈጥሮ ሁሉ የተሸነፈበት የሚያበቃው ክርስቶስ ለሕዝቡ ደኅንነትን በመጨረሻ በሚያመጣበት ጊዜ ነው። ይህ የሚያመለክተን በሞት ምክንያት የሚመጣው መበስበስ የኃጢአት ውጤት መሆኑን ነው። 2 ኃጢአት በመንፈስ ሞት መለየትን ያመጣል አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በአካላቸው መሞት ጀመሩ። እንዳይበሉ ከታዘዙት ፍሬ በበሉበት ቀን በተለይም በመንፈሳቸው ሞቱ። አዳምና ሔዋን ይህን ኃጢአት ከመፈጸማቸው በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ደስታ የሞላበት አንድነት ነበራቸው። ኃጢአት ከሠሩ በኋላ እግዚአብሔር ሊገናኛቸው ሊመጣ ፈርተው ተሸሸጉ (ዘፍጥረት 3፡8)። ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ቅርበትና አንድነት ከዚህ ዕለት ጀምሮ መቋረጡንና ራሳቸውን ከእግዚአብሔር መለየታቸውን ተረዱ። የመንፈስ ሞት የሚባለው የሰዎች ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው። አዳምና ሔዋን ኃጢአትን በፈጸሙበት ቀን ከእግዚአብሔር ተለዩ። 

መጽሐፍ ቅዱስ ራሳችንን ከእግዚአብሔር ስለ መለየታችን ሲገልጽ ራሳችንን የእግዚአብሔር ጠላቶች ማድረግ፥ እግዚአብሔርን መጥላትና ቁጣውንም በእኛ ላይ ማምጣት መሆኑን ያስገነዝባል። 34ኛ ጥያቄ፡- ዘዳግም 7፡10 አንብብ። ለእግዚአብሔር የማይታዘዙት፥ በዚህ ክፍል | በምን ሁኔታ ተገለጹ? 

ጥያቄ፡- መዝሙር (106)፡40 አንብብ። አቁጥር 39=40 ያለው ክፍል የእግዚአብሔር ሕዝብ ለለፈጸሙዋቸው የኃጢአት ዓይነቶች ዘርዝር ይዟል። በቁጥር 40 ላይ እግዚአብሔር ምን አደረገ? 

ጥያቄ፡– ኤርምያስ 4፡4 አንብብ። ሕዝቡ በፈጸሙት ክፋት ምክንያት ምን ሆነ? 

ጥያቄ፡- ያዕቆብ 4፡4 አንብብ። የዓለም ወዳጅ በሚሆን ሰው ላይ ምን ይደርሳል? 

ጥያቄ፡- ቆላስይስ 1፡21 አንብብ። በአሳባቸውና በክፉ ሥራቸው ባሕርይ የሚመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡18 አንብብ። ከሰዎች ክፋት የተነሣ እግዚአብሔር በሰዎች ላይ ምንን ይገልጣል? 

ሰዎች ኃጢአትን በሚፈጽሙበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላቶች በመሆን ከእግዚአብሔር ራሳቸውን ይለያሉ። እግዚአብሔርም በኃጢአታቸው ላይና ኃጢአትን በመሥራታቸው በእነርሱም ላይ ቁጣውን ያወርዳል። እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች ይቆጣቸዋል ሲባል ደግሞ ሰዎቹን በሰውነታቸው ይጠላል ማለት አይደለም። እነዚህ ሰዎች በኃጢአት ምክንያት ራሳቸውን የእርሱ ጠላቶች ቢያደርጉም፥ ደግሞም ከእርሱ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ቢያቋርጡም፥ እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ኃጢአታቸውን ብቻ ይጠላል። እግዚአብሔር ራሳቸውን ጠላቶቹ ባደረጉት ሁሉ ላይ ያሚያወርደው ቁጣ የጻድቅነቱ ምላሽ ነው። በዘዳግም 7፡10 ላይ የተጻፈው ቃል ኃጢአትን የሚሠሩትንና የማይታዘዙትን እግዚአብሔርን እንደ ጠሉ አድርጎ ይገልጻቸዋል። መዝሙር (106)፡34-39 ደግሞ እስራኤላውያን የፈጸሙዋቸውን ብዙ ዓይነት ኃጢአቶች ዘርዝሮ ይገልጻል። በቁጥር 40 ላይ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ተቆጣቸው ይናገራል። ምንም እንኳን የእርሱ ወራሾች ቢሆኑም፥ ኃጢአታቸው ከእርሱ እንዲለዩ በማድረግ ቁጣውን ሊያመጣባችው ቻለ። ኤርምያስ 4፡4 ሲናገር በክፉ አድራጊዎች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይወርዳል ይላል። ይህ ቁጣውም ማንም ሰው ሊያጠፋ እንደማይችለው እሳት ተገልጾአል። የእግዚአብሔር ቁጣ ሲባል ጨርሶ ትዕግሥቱን አሟጧል ማለትም አይደለም። ይልቁን ይህ ባሕርዩ የሆነውን የእርሱን ንጹሕና በጎነት ለሚጻረር ማንኛውም ነገር እርሱ የሚሰጠው የጽድቅ ምላሽ ነው። ይህ ምላሽም ለዓለም እንደሚበጅ እርሱ ያውቃል። ያዕቆብ 44 በዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ጠላቶች መከተል በፈቀድንበት ጊዜ ራሳችንን የእግዚአብሔር ጠላቶች እናደርጋለን ማለት ነው። ቆላስይስ 1፡21 ደግሞ ወደ ክርስቶስ ያልተመለሱ ሰዎች ያላቸው ክፉ ባሕርይ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል ይላል። ሮሜ 1፡18 በኃጢአታቸውና በክፋታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ይገለጥባቸዋል በማለት ያስጠነቅቃል። 

ማስታወስ የሚገባችሁ ቁም ነገር እግዚአብሔር ራሱን የሰዎች ጠላት ለማድረግ ያልመረጠ መሆኑን ነው። ነገር ግን ሰዎች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላቶች መሆንን ይመርጣሉ። ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ለመለየት ይመርጣሉ። ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን መሥራት በሚመርጡበት ጊዜ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆኑና የእግዚአብሔርን የጽድቅ 

ቁጣ በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። 

ጥያቄ፡- ሆሴዕ 11፡1-4 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል የነበረው ልማት እንዴት ነበር? ለ) እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ምን አደረገ? 41ኛ ጥያቄ ሆሴዕ 11፡5-7 አንብብ። ከኃጢአታቸው የተነሣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምን ደረሰ? 

ይህ ትንቢተ ሆሴዕ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምን ያህል ፍቅር እንዳለውና ኃጢአት በሚሠሩበትም ጊዜ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የሚሰማውን ስሜት ደህና አድርጎ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው። በሆሴዕ ከምዕራፍ 1-3 ባለው ክፍል እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ከሆሴዕ አመንዝራ ሚስት ከጎሜር ጋር ያመሳስላቸዋል። በመሠረቱ እግዚአብሔር፥ አንድ ባል ሚስቱን በጣም እንደሚወዳት ሁሉ፥ እስራኤልን ይወዳል። ነገር ግን እስራኤላውያን እንደ አመንዝራ ሴት አምላካቸውን ትተው ወደ ባዕድ አምልኮ ወደ ጣዖት በሄዱ ጊዜ እግዚአብሔርን በደሉት፥ አስቀየሙት፥ ልክ አንድ ባል ሚስቱ እርሱን ከድታ ወደ ሌላ ስትሄድ እንደሚሰማው ማለት ነው። በሆሴዕ 11፡1-4 እግዚአብሔር እስራኤልን አንድ አባት ልጁን የሚወደውን ያህል እንደሚወድ ይናገራል። እንዲሁም ልክ አንድ አባት ልጁን የሚንከባከበውን ያህል እግዚአብሔርም እስራኤልን ይንከባከባል። ስለዚህም መራመድ እንዲችል ይመራዋል፥ ከበሽታው ይፈውሰዋል፥ ሸክምንም ከራሱ ላይ ያነግለታል። ዳሩ ግን እስራኤል ይህን ሁሉ ዘንግቶ እግዚአብሔርን ችላ በማለት እንዳይታዘዘው ዐመፀ። በዚህም ሕዝቡ እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ በመምረጣቸው እግዚአብሔር ሊቀጣቸው ወሰነ። ስለሆነም ከተማቸው ተደምስሶ እነርሱም በምርኮ ወደ ግብፅና ወደ ሶሪያ እንደሚወስዱ ይገልጻል (ሆሴዕ 11፡5-7)። 

ምንም እንኳን እግዚአብሔር ሰው ባይሆንም፥ ስብእና አለው። ስለዚህ ይወደናል፥ ከእርሱም ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረን ይፈልጋል። ሆኖም ኃጢአት በምንፈጽምበት ጊዜ ስሜቱን እንጎዳለን። እግዚአብሔርን በኃጢአታችን ስንጎዳው፥ በጣም አድርጎ ይቀየመናል፥ ኋላም ከእርሱ ጋር የነበረን ግንኙነት ይቀጫል። ከዚያም የእርሱ ወዳጅ መሆናችን ይቀርና ራሳችንን የእርሱ ጠላቶች እናደርጋለን። ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር ከፍቅሩና ከወዳጅነቱ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ከነበረን ግንኙነት ጨርሶ ይለየናል። ከዚያ በኋላ ኃጢአታችን የእግዚአብሔርን ቁጣ የምንቀበል የእግዚአብሔር ጠላቶች ያደርገናል። 

ጥያቄ፡– ኃጢአት መንፈሳዊ ሞትን ከእግዚአብሔርም መለየትን ያመጣል፡፡ ይህን ሁኔታ ማወቃችሁ ኃጢአት በመሥራት ፈንታ ለእግዚአብሔር ታዛዦች እንድትሆኑ እንዴት ሊቀሰቅሳችሁ ይችላል? 

እግዚአብሔር ከሁሉ የሚበልጥብን ወዳጃችን ነው። ይወድደናል፥ ከእርሱ ጋርም አንድነት እንዲኖረን ይሻል። ስለሆነም ከእርሱ ጋር የተሟላ ግንኙነት በሚኖረን ጊዜ እጅግ በጣም ደስተኞች እንሆናለን። ነገር ግን ኃጢአታችን እግዚአብሔርን ክፉኛ ይጎዳዋል። ከዚያም ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ይደመስሰዋል። ይህን ግንኙነታችንን በምናበላሽበት ጊዜ እግዚአብሔር ያዝናል፥ ይከፋል። ኃጢአት ለመሥራት በምንፈተንበት ጊዜ የሰማይ አባታችንን እንደምናስከፋው፥ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት እንደምናበላሽ እናም ወደ ሐዘን፥ ተስፋ መቁረጥና ትካዜ እንደሚጥለን ማወቅ አለብን። በሚመጣው ሳምንት በሦ ስተኛው ቀን ጥናታችን ላይ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ኃጢአት ምን ዓይነት ውጤት እንደሚኖረው ሰፋ አድርገን እንመለከታለን። 

3. ኃጢአት በዘላለማዊ ሞት መለየትን ያመጣል። 

ጥያቄ፡– ራእይ 20፡14 አንብቡ፡ ሁለተኛው ሞት ምንድን ነው? 

ሰዎች በመንፈሳቸው የሞቱ ሆነው (ከእግዚአብሔር የተለዩና የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነው) እና በአካል በሚሞቱበት ጊዜ (አካላቸው ሞቶ ከመንፈሳቸው ሊለይ) ወደ ዘላለማዊ ሞት ይገባሉ። ዘላለማዊ ሞት ደግሞ ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው። ራእይ 20፡14 የእሳት ባሕር ስለሆነው «ስለ ሁለተኛው ሞት» ይናገራል። የመጀመሪያው ሞት የሥጋ ወይም የአካል ሞት ነው። ይህም አካል ከመንፈስ የሚለይበት ሁኔታ ነው። የመጀመሪያውን ሞት የሚሞቱ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈና ከእግዚአብሔር የተለዩት፥ ወደ እሳት ባሕር ይጣሉና በዘላለማዊ ሞት ምክንያት ከእግዚአብሔር ይለያሉ። 

4. ኃጢአት ለሞት ያደርሳል፥ ደግሞም በዕለታዊ ሕይወታችንም ላይ ጥፋትን ያመጣል። 

ኃጢአት የሥጋ፥ የመንፈስና የዘላለም ሞትን ያመጣል የሚለው እውነታ ኃጢአት ዕለታዊ ሕይወታችንን ወደ ሞት ይመራዋል ከሚለው ጋር አብሮ መታየት አለበት። ኃጢአት አጥፊ ነው፥ የበከለውን ሁልጊዜ ወደ ሞትና ወደ ጥፋት ይመራል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ ጊዜ ከምንሸነፍባቸው ኃጢአታዊ ፈተናዎች ቢያንስ ሦስት ምሳሌዎችን ጻፉ። ለ) እነዚህን ኃጢአቶች ማድረጋችሁ ሕይወታችሁን እንዴት ይጎዳል? ከእነዚህ ከጻፋችኋቸው ከሦስቱ የፈተና ዓይነቶች ትይዩ እነዚህ ኃጢአቶች ሕይወታችሁንና ከሌሎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንዴት እንደሚያበላሹባችሁ ጻፉ? 

ጥያቄ፡– ገላትያ 6፡7-8 አንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የምትመለከቱትን መሠረተ አሳብ ወይም መርሖ በራሳችሁ ቃላት ጻፉት። 

በሕይወታችን ውስጥ በየዕለቱ የሚፈጸሙ ኃጢአቶች ወደ ሞትና ወደ ጥፋት እንደሚያደርሱን የሚያስገነዝቡ ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ፡– 

በማንኛውም ጊዜ በሰዎች ላይ ምሬት የምናሳይ ከሆነና ይቅርታም የማናደርግላቸው ከሆነ፥ ምሬቱ በውስጣችን ይከማችና ራሳችንኑ መራራ ሰዎች ያደርገናል። አዘውትረን ለወደፊት ስለሚሆነው ነገር በምንጨነቅበት ጊዜ ሁሉ ውስጣዊ ሰላምና መጽናናትን እናጣለን። ምሬትና ጭንቀት ተደማምረው ጠናችንን የሚያቃውስ አካላዊ በሽታ ያመጡብናል። ከዚህም በስተቀር፥ ምሬትና ይቅርታን አለማድረግ በእንድ ሆነው ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት ያበላሻሉ። የምሬት፥ ይቅርታን ያለማድረግ፥ የጭንቀት ኃጢአቶች ተባብረው በጤናችንና በግንኙነታችን ላይ ሞትን ያመጣሉ። 

ትዕግሥት አጥተን በሌሎች ሰዎች ላይ በምንቆጣበት ጊዜ ሁሉ በመካከላችን ባለው ግንኙነት ላይ ሞትን እናመጣለን። አሉባልታን በማስተጋባት ሰዎችን በምናማበትና በምንሰድባቸው ጊዜ ሁሉ ሰዎች ከሌሎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እናበላሽባቸዋለን። 

ሰዎች ከትዳር ጓደኛቸው ሌላ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ ጋብቻቸውን ይበድላሉ። ገና ያላገቡም ከሆኑ ተገቢ ትዳር ለመመሥረት ያላቸውን ዕድል ያጣብቡታል። እንዲሁም በግብረ ሥጋ የሚመጣ ኃጢአት ወደ አባላዘር በሽታና ኤድስን ወደ መሳሰሉ ገዳይ የሆኑ በሽታዎች ይደርሳል። የምኞት ኃጢአት እንኳን ትዳርን ያጠፋል፤ ምክንያቱም ምኞት ሌላውን እንድንፈልግና እግዚአብሔር በሰጠን በባል ወይም በሚስት እንዳንረካ ያደርገናል። 

በምንዋሽበት ጊዜ ሁሉ ክብራችንንና ሰዎች በእኛ ላይ ያላቸውን እምነት እናበላሻለን። ከዋሸንበት ጊዜ ጀምሮ ሰዎች በእኛ ላይ እምነት ሊጥሉ ይሳናቸዋል። ኃጢአትን በፈጸምን ቁጥር በሕይወታችን ላይ በግንኙነቶቻችንና በአካባቢአችን ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ ሞትን እናመጣለን። እንዲሁም የኃጢአት ተግባራችንን በሕይወታችን ውስጥ አብሮን የሚዘልቅ ኃጢአት እንዲሆን በምናደርግበት ጊዜ ራሳችንን፥ ጋብቻችንን፥ ቤተ ክርስቲያናችንን፥ እንዲሁም ቤታችንንና ሙያችንን እናጠፋለን፥ እንገድላለን። ይህ ብቻ አይደለም ኃጢአት አካላዊ፥ መንፈሳዊና ዘላለማዊ ሞትን ያመጣል። ሰዎች ብዙ ጊዜ ኃጢአታቸው ምን ያህል ከባድ መሆኑን አይገነዘቡም። ከዚህም የተነሣ ኃጢአት ቢሠሩ የከፋ ውጤት እንደሚደርስባቸው አይሰማቸውም። ነገር ግን በገላትያ 6፡6-7 የተጻፈው መመሪያ ኃጢአት ሁልጊዜ ወደ ጥፋት እንደሚያደርሰን በውል ያስጠነቅቀናል። ልክ አንድ ዘር በቅሎ ተክል እንደሚሆን ሁሉ፥ ኃጢአትም በቅሎ ወደ ጥፋት ያድጋል። የኃጢአት ተፈጥሮአዊ ውጤት ሞት ነው። ኃጢአት ብዙ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ሥጋ ሞት አያደርስም። ነገር ግን አካላዊ ሕይወታችንና ሰብአዊ ግንኙነቶቻችንን ሁልጊዜ ያበላሻል። ደግሞም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ሁልጊዜ ያቋርጥብናል። በሚመጣው ሳምንት በሦስተኛው ቀን ኃጢአት በእውነት እንደገና የተወለደን ክርስቲያን እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት እንደሚጎዳ እንማራለን። ነገር ግን በክርስቶስ እውነተኛ እምነት የሌላቸው ሰዎች ከእግዚአብሔር እንደ ተለዩ ሆነው የሥጋ ሞት በሚደርስባቸው ጊዜ ዘላለማዊ የሆነ የሥቃይ ሞትን ይሞታሉ። ሁልጊዜ ኃጢአት ለሞት አሳልፎ ይሰጣል።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ኃጢአት ከየት መጣ?  ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል
Exit mobile version