Site icon የሕይወት እንጀራ

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

This entry is part 35 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

የኢሳይያስ መጽሐፍ በሚመጣው መሢሕ ትንቢቶች የተሞላ ነው፡፡ ልክ እንደ መዝሙራት ከእነዚህ ትንቢቶች ጥቂቶቹ በምድር ላይ የሚሆነውን የእርሱን የክብር አገዛዝ ይዘረዝራሉ። ሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ሊደርስበት ያለውን መከራ ይገልጻሉ። ስለሆነም ዛሬ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉት መካከል ኢሳይያስ ስለ መሢሑ የጻፈውን እንመለከታለን። 

ኢሳይያስ 7 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 7፡19 አንብቡ። ሀ) የይሁዳ ሕዝብ እንዲፈሩ ምን ተደረገ? ለህ እግዚአብሔር ፍርሃታቸውን ላማስወገድ ምን ተስፋ ለጣቸው? 32ኛ ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 7፡10-16 አንብቡ። እግዚአብሔር ተስፋውን እንደሚፈጽም ለንጉሥ አካዝ ምን ምልክት ሰጠው? 

ኢሳይያስ ምዕራፍ 7 የእስራኤል ነገሥታት እና የሶሪያ ነገሥታት አንዳንድ ጊዜ ኤፍሬ” ወይም ሰማሪያ አንዳንድ ጊዜ እራም ወይም ደማስቆ ይሁዳን ለመውጋት መተባበራቸውን በመተረክ ይጀምራል። እነዚህ የተባበሩ ኃይላትም ይሁዳን ድል ካደረጉ በኋላ፥ የራሳቸውን ንጉሥ በይሁዳ ላይ ለማንገሥ ዐቀዱ። ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ኢሳይያስን ወደ ንጉሥ አካዝ ልኮ፥ የእስራኤልና የይሁዳ ሠራዊት ስለሚሸነፉ እርሱን እንደማያሸንፉት ቃል ገባለት። ኢሳይያስ ደርሶ ይህን ቃል በነገረው ጊዜ ንጉሥ አካዝ የተጠራጠረ ይመስላል። እግዚአብሔር ተስፋው እውነት ሆኖ እንደሚፈጸም የሚያሳይ ምልክት ሰጠው። ይህ ተስፋም አንዲት ድንግል ወጣት ባል አታገባ ልጅ ታረግዛለች የሚል ነበር። ይህ የሚወለደው ልጅ ክፉውንና በጎውን ለይቶ ከማወቁ በፊት የእስራኤልና የሶሪያ ነገሥታት ድል ይደረጋሉ። ከዚህም ሌላ፥ ልጁ ከሚኖሩት ስሞች አንደኛው «አማኑኤል» ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው የሚል ይሆናል፥ ብሎ ኢሳይያስ ተናገረ። የልጁ መወለድም እግዚአብሔር ይሁዳን ከጠላቶቹ እንደሚከላከለው ምልክት ነበር። 

የኢሳይያስ ትንቢት ሁለት ፍጻሜ ካላቸው የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች አንዱ ምሳሌ ነው። የመጀመሪያው ትንቢት ፍጻሜ ያገኘው በኢሳይያስና በአካዝ ዘመን ነበር። ኢሳይያስ በመጀመሪያ የሚናገረው በጊዜው በሕይወት ስለነበረች ወጣት ሴት ይመስላል። ይህች ሴት ድንግል ነበረች፥ ምናልባትም ታጭታ ልታገባ የተቃረበች ትሆን ይሆናል። እንዲያውም ይህች ወጣት የኢሳይያስ እጮኛ ልትሆን ትችላለች። ይህ ከሆነ ኢሳይያስ እጮኛውን በምዕራፍ ሰባትና ስምንት መካከል አግብቷታል ማለት ነው። እንዲህ ከሆነም በምዕራፍ ሰባት የኢሳይያስ ወንድ ልጅ መወለድ የትንቢቱ የመጀመሪያው ፍጻሜ ነው ማለት ነው። የልጁም ስም በኢሳይያስ 8፡1 ላይ እንደ ተጠቀሰው «ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛም ቸኮለ» የሚል ይሆናል። ይህኛው ስም ለልጁ የቅጽል ስም ይሆነዋል፤ ወይም ልጁ ሁለት ስሞች ይኖሩታል። እነዚህም «ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ»ና «አማኑኤል» የሚሉት ናቸው። ይህ ትንቢት በመጀመሪያ የተፈጸመው በኢሳይያስ ልጅ ይሁን ወይም አይሁን በኢሳይያስ ትንቢት ዘመን ድንግል ሆና በሕይወት የነበረች ሴት በኋላ አግብታ ወንድ ልጅ ወልዳለች። የዚህ ልጅ መወለድ እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር እንደ ነበረ ምልክት ነበር። ይህ ልጅም አድጎ ክፉና በጎውን ሳይለይ የእስራኤልና የሶሪያ ነገሥታት ተሸንፈዋል። 

ሆኖም፥ ሁለተኛውና ታላቁ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜም ነበር። 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 1፡18-23 አንብቡ። የኢሳይያስ ትንቢት በመጨረሻው ከፍጻማ መድረሱን ማቴዎስ እንዴት ተገነዘበው? 

በሁለተኛው ትምህርታችን ላይ እንደ ተከታተልነው፥ ማቴዎስ በግልጽ እንደ ጻፈው፥ ኢየሱስ በማርያም ማኅፀን በተፀነሰ ጊዜ እርሷ ድንግል ነበረች። ኢየሱስን እስከ ወለደችበት ጊዜ ድረስም ድንግል ነበረች። ስለሆነም ማቴዎስ ኢየሱስ ከድንግል መወለዱ የኢሳይያስ ትንቢት የመጨረሻ ፍጻሜ መሆኑን ተገንዝቧል። እንደዚሁም ለንጉሥ አካዝ በአነስተኛና በተወሰነ ሁኔታ ምልክት በመሆን የተፈጸመው ትንቢት፥ ኋላ እግዚአብሔር ሕዝቡን በተለየ መንገድ ለመጎብኘት ወደ መላው ዓለም መምጣቱን ባላየ ልዩ ሁኔታና ምልክት ከፍጻሜ ደርሷል። ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ክርስቶስ፥ የመጨረሻው አማኑኤልና የኢሳይያስ ትንቢት ሙሉ በሙሉ ፍጻሜ እርሱ ነው። 

ኢሳይያስ 9 

34ኛ ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 9፡1-2 አንብቡ። ሀ) እንደ ቁጥር 1-23 እግዚአብሔር በገሊላ ለሚኖሩ ሰዎች ምን ሊያደርግላቸው አሰበ? ለ) ከቁጥር 6-7 በተጠቀሰው መሠረት፥ ለእስራኤል ደኅንነትን የሚያመጣ ማን ነው? ሐ) ይህንን ሰው የሚገልጹት አራት የማዕረግ ስሞች የትኞቹ ናቸው? መ) የዚህስ ሰው መንግሥት ምን ይመስላል? 

ኢሳይያስ ምዕራፍ 8 በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይና ሕጉን በተላለፉ እስራኤላውያን ላይ ስለደረሰው ፍርድ የሚተነትን ክፍል ነው። ምንም እንኳን የአሶር ሕዝብ የእግዚአብሔር ፍርድ መሣሪያ ቢሆኑም፥ ፍርዱን የሚሰጠው እግዚአብሔር ራሱ ነው። በኢሳይያስ ምዕራፍ 9 እግዚአብሔር ለእስራኤል ወደ ፊት ስለሚያመጣው ደኅንነት በርቀት ያመላክታል። በኢሳይያስ 9፡1 ውስጥ የተገለጸው ንፍታሌምና ዛብሎን በአሶራውያን ፍርዱን ሊያገኝ የነበረው ሰሜናዊው የእስራኤል አካባቢ ነው። ይህ አካባቢ በአዲስ ኪዳን ዘመን የገሊላ አካባቢ ነበር። ምንም እንኳን ቀድሞ የተፈረደባቸው ሆነው ቢቆዩም ወደፊት ግን እግዚአብሔር ብርሃኑን በመካከላቸው በማብራት ይባርካቸዋል። ጠላቶቻቸውም እግዚአብሔር በሚልክላቸው ከዳዊት ዘር በሚወለድ ንጉሥ ክንድ ድል ይደረጋሉ። ይህ ንጉሥም በአራት መንገዶች ይገለጻል። አንደኛው፥ «ድንቅ መካር» የሚለው ስሙ ነው። እንዲህ ማለትም፥ ለማስተዳደር ያለው መርሐ-ግብር በጥበብና በማስተዋል ይመራል ማለት ነው። ሁለተኛ ስሙ፥ «ኃያል አምላክ» ነው። ይህ ትንቢታዊ ስያሜ የሚመጣው መሢሕ በሰብአዊ አካል የሚመጣ ወይም በጦርነት ድልን ለመምታትና ሕዝቡን ለማስተዳደር የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ይኖረዋል ማለት ሊሆን ይችላል። ሦስተኛው፥ «የዘላለም አባት» የሚለው ነው። እዚህ ላይ እንዲህ ማለት እግዚአብሔር ወልድ፡ ከአብ ጋር አንድ አካል ነው ማለት አይደለም። የዚህ ምሥጢሩ የሚመጣው መሢሕ ቸርና አዛኝ መጋቢ እንደ አባት ተንከባካቢና ጠባቂ ማለት ሲሆን፥ ይህ የአባትነቱ እንክብካቤና ጥበቃም ለዘላለም የሚቀጥል ነው። የመጨረሻው ስያሜውም፥ «የሰላም አለቃ» ተብሎ ይጠራል የሚለው ነው። የእርሱ አገዛዝ ጦርነትን አስወግዶ ሰላምን የሚያመጣ ብቻ ሳይሆን፥ ለኅብረተሰቡ አንድነትንና ብልጽግናን ይሰጣቸዋል። ቁጥር 9 ስለ መንግሥቱ ፍጹምና ተጨማሪ ትንተና ይሰጣል። መንግሥቱም በሰላም፥ በፍትሕ፥ በጽድቅና በንጉሡ ፍጹም ሥልጣን ይደገፋል። ለመንግሥቱም ፍጻሜ አይኖረውም። 

ጥያቄ፡ ማቴዎስ 4፡12-16 አንብቡ። የዚህ ትንቢት ፍጻማ መጀመሪያ መች ነበር? 

በማቴዎስ ምዕራፍ 4 ውስጥ እንደምናገኘው፥ ጌታ ኢየሱስ በምድረ በዳ ከተፈተነ በኋላ፥ አገልግሎቱን ለመጀመር ወደ ገሊላ ሄደ። ማቴዎስ እንደሚነግረን የዚህ ትንቢት ፍጻሜ መጀመሪያ ይህ ነበር። ኢየሱስ አብዛኛውን አገልግሎቱን የሰጠው በገሊላ ውስጥ ነበር። ማቴዎስ ሲናገር ይህ አገልግሎት ኢሳይያስ የተነበየው ብርሃን ነበር። ኢየሱስም በዚህ አኳኋን አገልግሎቱን ሲጀምር አምነው በተከተሉት ልብ ውስጥ ግዛቱን ይመሠርት ነበር። እርሱ ተመልሶ በምድር ላይ መንግሥቱን እስከሚያቋቁም ድረስ፥ ይህ አገዛዝ የተሟላ አይሆንም። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ፍጹም የሆነው የጽድቅ፥ የፍትሕና የሰላም መንግሥቱ በምድር ላይ ሙሉ በሙሉ ይመሠረታል። እስከዚያ ድረስ እርሱን የሕይወታቸው ንጉሥ ለሚያደርጉት ሁሉ፥ ኢየሱስ ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባትና የሰላም አለቃ ሆኖ ይኖራል። 

ኢሳይያስ 52-53 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 52፡13- 53፡12 አንብቡ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተፈጸመ እያንዳንዱን ሐረግ ወይም አሳብ ጻፉ። እንደዚሁም ከየሐረጉ ጎን እንዴት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ፍጻሜ እንዳገኙ ያላችሁን አስተያየት ጻፉ። ቀጥሎም በእያንዳንዱ ጥቅስ ውስጥ በክርስቶስ የተፈጸመ ቢያንስ አንድ ሐረግ ወይም አሳብ ለማግኘት ሞከሩ። 

ብዙ ጊዜ ተዘውትሮ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚጠቀሰው የብሉይ ኪዳን ክፍል ኢሳይያስ 52፡13- 53፡12 ነው። ይህ ክፍል ስለ ክርስቶስ የሚናገሩ ብዙ ትንቢቶችን ይዟል። ክፍሉ ስለ እግዚአብሔር አገልጋይ በስፋት የተገለጸበት ነው። በኢሳይያስ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር አገልጋይ አራት መዝሙራት አሉ። ይህ አገልጋይም የሚመጣው መሢሕ ነው። ነገር ግን ኢሳይያስ 52፡13- 53፡12 በጣም ግልጽ የሆኑ ትንቢቶችን የያዘ መዝሙር ነው። 

ይህ ክፍል የሚጀምረው በማጠቃለያ ነው። የእግዚአብሔር አገልጋይ በሕይወቱ ሥራው ሁሉ እንዲከናወንለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጥበብ ያደርጋል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔርም በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ያደርገዋል። ፊልጵስዩስ 2፡9 ደግሞ እንደሚያስታውሰን፥ እንደ ሰው ሆኖ ራሱን በትሕትና ስላዋረደና እስከ መስቀል ሞት ድረስ ስለ ታዘዘ፥ እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ወዳለው የክብር ስፍራ ከፍ ከፍ እንዳደረገው ይገልጽልናል። ነገር ግን ወዲያውኑ የሚያስደንቅ ነገር አለ። ምንም እንኳን ኢሳይያስ 52፡13 ይህ አገልጋይ ከፍ ከፍ ይላል ቢልም፥ ቁጥር 14 ደግሞ ፊቱ የተጎሳቆለ በመሆኑ የሚያዩት ሁሉ ይጸየፉታል ይላል። እነዚህን እርስ በርስ የሚቃረኑ አገላለጾችን ማዛመድ ለብሉይ ኪዳን አንባቢዎች አስቸጋሪ ሳይሆን አይቀርም። ነገር ግን እነዚህ ሁለት አሳቦች በክርስቶስ ሕይወት ፍጻማ አግኝተዋል። ክርስቶስ በወቅቱ ተደብድቦ ስለ ተሰቀለ፥ አካላዊ መልኩ በመበላሸቱ አስፈሪ ሆኖ ነበር። ቁጥር 14 እንደሚናገረው፥ ክፉኛ ስለ ተመታ መልኩ ከሰው ውጭ ሆኖ አስከፊ አደረገው። ነገር ግን እንደዚያ ስለ +መታና ስለ ተሰቀለ እግዚአብሐ ር ከፍ ከፍ አደረገው። ቁጥር 5 ደግሞ ከሰውነት ውጭ ሆኖ የመመታቱን ውጤት ሲነግረን፥ ብዙ ሕዝቦችን ረጭቶ በማንጻት ታላላቅ የዓለም ገዢዎችን እንዲደነቁ አድርጓል ይላል። ይህ የመርጨት ሁኔታ፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ለሚደረገው ሥርዓት በምሳሌነት የቀረበ የማንጻት መርጨት ነው (ዘሌዋ. 14፡7 ዘኁል. 8፡7፣ 19፡18-19፤ ዕብ. 9፡13)። ነገር ግን በክርስቶስ በኩል የመጣው መንጻት፥ ጥቂት ሰዎችን ከመርጨት አልፎ የሄደ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ፍጹም መንጻትን ያስገኘ መርጨት ነው (ዕብ. 9፡14)። የእግዚአብሔር አገልጋይ ብዙ ሰዎችን ለማንጻት መሠቃየቱና መከራ የመቀበሉ ሁኔታ፥ እጅግ አስደናቂ ድርጊት ስለነበር፥ በዓለም ላይ እጅግ የተማሩትና ገናና ሰዎችንም ሳይቀር በመደነቅ አፋቸውን እንዲይዙ አድርጓል። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 15፡20-21 አንብቡ። ጳውሎስ የኢሳይያስ 52፡15ን ፍጻሜ እንዴት ይመለከተዋል? 

የሐዋርያው ጳውሎስ ዋና ዓላማ ወንጌል ባልደረሰበት አካባቢ ወንጌልን መስበክ ነበር። ጳውሎስ የኢሳይያስ 52፡15ን ፍጻሜ ያይ የነበረው ስለ ኢየሱስ ሞት ያልሰሙት እርሱ የተሰቀለውና መሥዋዕት የሆነው እነርሱ ተረጭተውና ከኃጢአታቸው እንዲነጹ እንደሆነ ሊገነዘቡ ነው። 

በኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ውስጥ የተሠቃየው አገልጋይ መዝሙር ይቀጥላል። ቁጥር አንድ ሕዝቡ በሚሠቃየው አገልጋይ በኩል የሚመጣውን ደኅንነት ሰምተው አምነው እንደማይቀበሉ በመረዳቱ ነቢዩ የተሰማውን ኀዘን ይገልጻል። «የእግዚአብሔር ክንድ» የሚለው፥ የእግዚአብሔርን ኃይል ለማመልከት የሚውል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። እንደዚሁም ኢሳይያስ የተጨነቀው በሚሠቃየው መሢሕ በኩል የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ኃያል ደኅንነት ሕዝቡ አይነዘበውም በማለት ነው። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 12፡37-38 እና ሮሜ 10፡14-17 እንብቡ፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስና ጳውሎስ ኢሳይያስ 53፡1 እንዴት እንደ ተፈጸመ ነበር የገባቸው? 

የኢሳይያስ ትንቢት በኢየሱስ ምድራዊ ኑሮና በአገልግሎቱ፥ ኋላም በሐዋርያቱ አገልግሎት ፍጻሜ አገኘ። ምንም እንኳን የእርሱን መሢሕነት የመሰከረ ልዩ ልዩ ታምራትን ቢሠራም፥ እንደዚሁም ሐዋርያት እርሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ መሢሑ የተነገሩትን ትንቢቶች ፍጻሜ ነው ብለው በግልጽ ቢሰብኩም፥ የሚያሳዝነው ነገር ከራሱ ሕዝብ ብዙዎች ሳይቀበሉት ቀሩ። ልክ ኢሳይያስ እንደ ተነበየው፥ አብዛኛዎቹ አይሁዳውያን ስለሚሠቃየው መሢሕ ታሪክ አምነው አልተቀበሉም። 

ኢሳይያስ በቁጥር 2 ላይ የኢየሱስን የልጅነት ዕድሜ ሁኔታ ይገልጸዋል። በጣም ዝቅተኛና ተራ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ተወልዶ አደገ። ሰዎችን ወደ እርሱ የሚስብ የቤተሰብ ደረጃ ፥ የግል ማኅበራዊ አቋም ወይም አካላዊ ገጽታ ምንም አልነበረውም። በቁጥር 3 ላይ ኢሳይያስ፥ በተለይም በሕይወቱ ማብቂያ ላይ የራሱ ሕዝብ እንዳልተቀበለው ይናገራል። በእነርሱ ዘንድ የተናቀና የተገለለ ሰው ሆነ። በሞተም ጊዜ ከራሱ ሕዝብ አብዛኛው ቦታ የሰጠው አልነበረም። እንዲያውም «ስቀለው!» እያሉ ጮኹ። በመስቀልም ላይ ላለ አላገጡበት (ማቴዎስ 27፡22-23፤ 39-44)። በመጨረሻም ላይ ራቁቱን ሆኖ፥ ተመትቶና ደቅቆ በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ፥ ይመለከቱ የነበሩት ማየት ስለ ዘገነናቸው ፊታቸውን አዞሩ (ሉቃስ 23፡48)፡፡ በዚህ ጊዜ ገጽታው እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ተጎሳቁሎ ነበር። ተስፋ የተገባለት የእስራኤል ንጉሥ አይመስልም ነበር። ስለዚህ አንዳንዶቹ ናቁት። ሌሎች ደግሞ በመራራት አዘኑለት። ነገር ግን እንደ ኃያል ንጉሥ ቆጥሮ አክብሮትን የሰጠው ማንም ሰው አልነበረም። 

ታዲያ ክርስቶስ በዚህ ሁኔታ በምን ምክንያት ተሠቃየ፥ ለምንስ ተናቀ? ይህን በተመለከተ፥ ኢሳይያስ ከቁጥር 4-6 ድረስ ገለጻውን ይጀምራል። ምንም እንኳን በሥቃዩ ጊዜ ይመለከቱት የነበሩት ሰዎች በእግዚአብሔር የተቀጣ ቢመስላቸውም፥ እርሱ በእርግጥ የተቀጣውና ያን መከራ የተቀበለው ለእኛ ብሎ ነበር። ኃጢአተኞቹ እኛ ነን (ቁጥር 6)፥ ነገር ግን ለእኛ ኃጢአት ሲል ደግሞ ሥቃይና መከራን የተቀበለ እርሱ ነበር። ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የእኛን በደልና ኃጢአት ስለ መሸክሙ የተነገረው ትንቢት መፈጸሙ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ተጽፎ ይገኛል። ሮሜ 4፡25 እርሱ ስለ እኛ ኃጢአት ወደ ሞት አልፎ ተሰጠ ይላል። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3 ወንጌል ማለት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ ማለት ነው ይላል። 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 እርሱ ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ ይላል። ዕብራውያን 9፡28 እርሱ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ መሥዋዕት ሆኖአል ሲል ይገልጻል። በተጨማሪም 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24-25 ምንም እንኳን እኛ እንደ በጎች ብንቅበዘበዝም፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን ተሸከመ ይላል። 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 8፡17 አንብቡ። ኢሳይያስ በተናገረው ትንቢትና እንደ ተጠቀሰው መሢሑ ሕማማችንን ተሸከመ የሚለው ትንቢት መፈጸሙን ማቴዎስ እንዴት ተመላከተው? 

ይህ በኢሳይያስ 53፡4 ላይ የተጠቀሰው ትንቢት፥ በኢየሱስ የፈውስ አገልግሎት እንደ ተፈጸመ ማቴዎስ ተመልክቶታል። ሰዎች በሚታመሙበት ጊዜ (ዮሐንስ 9፡3) የሕመማቸው ምክንያት በግል ኃጢአት ስለሠሩ ላይሆን ይችላል። ሆኖም በሽታዎች ሁሉ ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ በዓለም ላይ የመጡ መርገም ውጤቶች ናቸው። ኢየሱስ ለእኛ የኃጢአት ይቅርታን ሊሰጠን ብሎ፥ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በመሞት፥ ኃጢአትን፥ በሽታንና ሞትን አሸንፎአል። ለፈውስ በምንጸልይበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ የሚፈውሰን ኢየሱስ በመስቀል በኃጢአት፥ በበሽታና በሞት ላይ ከፈጸመው ድል የተነሣ ነው። በዚህ ሕይወት ሳለን ስለ ፈውስ በምንጸልይበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ፈውስን አይሰጠንም፤ ምክንያቱም በበሽታና በሞት ላይ ያለው የመጨረሻው ድል ኢየሱስ ዳግሞ ከመምጣቱ በኋላ የሚሆን ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ፈውስን ለማግኘት ጸልዮ ፈውሰን ሳያገኝ ሲቀር፥ ሌሎች ክርስቲያኖች በቂ እምነት ቢኖርህ ትፈወስ ነበር የሚል አስተያየት ይሰነዝሩበታል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በቂ እምነት ካገኘህ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይፈውስሃል ይላሉ። ነገር ግን በኢሳይያስ 8፡4 ላይ የተጻፈው ቃል በቂ እምነት ቢኖረንም እግዚአብሔር ሁልጊዜ እንደሚፈውሰን ተስፋ የሚሰጠን አይደለም። ዳሩ ግን ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እግዚአብሔር ኃጢአትን፥ በሽታንና ሞትን ለመጨረሻና ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። ይህ የመጨረሻው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ፥ የበለጠ ቅድስና እየኝተን ኢየሱስን ለመምሰል እንድንችል፥ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ውስጥ፥ ፈተና በሽታና ሞት እንዲኖረን ያደርጋል። ለምንጸልየው ጸሎት መልሶ፥ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሲፈውሰን ይህ ኢየሱስ ዳግም ተመልሶ ሲመጣ በኃጢአት በሽታና በሞት ላይ ለሚቀዳጀው ድል የቅምሻ ያህል ነው። ኢሳይያስ 53፡4 እግዚአብሔር አሁን ፈውስን ለእኛ የሚሰጥበት ምክንያት ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሠራው ሥራ መሆኑን ያስገነዝበናል። 

ኢሳይያስ 53፡7-9 ያለው ክፍል፥ ምንም እንኳን መሢሑ ወንጀል ያልፈጸመ ንጹሕ መሆኑ ቢታወቅም፥ ምንም ሳይናገር ተሠቃይቶ እንደ ሞተ ይገልጻል። እንደዚሁም ነቢዩ በቁጥር 7 ላይ መሢሑ እራሱን ነፃ ለማድረግ አንዳችም ተውሞ ወይም መከላከያ እንዳልተናገረ ይጽፋል። በቁጥር 9 ላይ ደሞ መሢሑ ምንም ወንጀል ሳይሠራም፥ የደረሰበትን መከራ በትዕግሥት 

መቀበሉን ያስረዳል። ኢየሱስ ተይዞ ወደ አይሁድ ሸንጎ ፊት በቀረበ ጊዜ፥ ያላንዳች ጥፋት የሐሰት ክስ ቢመሠረትበትም ምንም አልተናገረም፥ ይህም የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ መሆኑ በተዘዋዋሪ እስከተጠየቀ ድረስ ነው (ማቴዎስ 26፡59-63)። በወቅቱም ኢየሱስ የመለሰው፥ ባጭሩ ሊቀ ካህኑ እንደተናገረው መሢሕ እንደነበር ነው። ኢየሱስ ወደ ንጉሥ ሄሮድስ ፊት በቀረበ ጊዜ፥ ምንም ቃል አልተናገረም ነበር (ሉቃስ 23፡9)። ሐዋርያው ጴጥሮስ፥ ስለ ኢየሱስ መከራ ብዙ ምስክርነትን የሰጠ ሲሆን፥ የኢየሱስን ንጽሕና ወይም ከወንጀል ፈጽሞ ነፃ መሆኑን ለመግለጽ ኢሳይያስ 53፡9ን ይጠቅላል (1ኛ ጴጥሮስ 2፡22)። ከዚያም ኢየሱስ የሰጠውን መልስ እንዲህ ሲል ያጠቃልለዋል፥ «…ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፥ መከራን ሲቀበል፡ አልዛተም» ይላል (1ኛ ጴጥሮስ 2፡23)። ቁጥር 8 እንዲህ ሲል ይጠይቃል፥ «…ከትውልዱ ማን አስተዋለ?» ይህ የኢሳይያስ አገላለጽ መሢሑ ልጆችን ሳያፈራ ገና በወጣት ዕድሜው እጅግ በሚያሰቅቅና በሚያሳዝን አኳኋን እንደሚሞት ያመለክታል። 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 27፡38 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ከእነማን ጋር ተሰቀለ? ለ) ማቴዎስ 257-60 አንብቡ። ኢየሱስ በማን መቃብር ውስጥ ተቀበረ? 

ቁጥር 9 ኢየሱስ በሞተ ጊዜ በአስደናቂ ሁኔታ የተፈጸመ እንግዳ የሆነ ትንቢት ምሳሌ ነው። ይህ ጥቅስ በመጀመሪያ “ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ» ይልና፥ ቀጥሎ ደግሞ «ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ» ይላል። ምናልባት የብሉይ ኪዳን አንባቢዎች እነዚህ ሁለት የተለያዩ ሐረጋት እውነት ስለመሆናቸው ሳይደነቁ አልቀሩም። እንዴት መሢሑ ከክፉዎች ጋር መቃብሩ፥ በአንጻሩ ደግሞ ከባለጠጎች ጋር ሞቱ ሊሆን ይችላል? ለዚህ መልሱ የኢየሱስን አሟሟት ስንመለከት ግልጽ ይሆንልናል። እርሱ እንደ ወንጀለኛ ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር የተሰቀለ ስለሆነ፥ ይጠበቅ የነበረው መቃብሩም ከሌሎች ወንጀኞች ጋር ይሆናል ተብሎ ነበር። ምናልባት አስቀድሞ ለእርሱ የተዘጋጀው መቃብር ለወንጀለኛ የተመደበ መቃብር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በኋላ ባለጸጋው የአርማቲያስ ዮሴፍ የኢየሱስን አካል በወሰደ ጊዜ፥ በራሱ መቃብር ውስጥ ቀበረው። ከዚህ የተነሣ የኢየሱስ መቃብር በሀብታሞች መቃብር ሊሆን ቻለ። በመሆኑም የኢየሱስ መቃብር ከክፉዎችም ጋር ይሆናል ተብሎ ቢመደብም ከሀብታም ሰው መቃብር ! መደረጉ ሁለቱም ሁኔታዎች የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው። 

ጥያቄ፡- የሐዋ. 8፡32-35 አንብቡ። ሀ) ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ፊልጶስ ሊያገኘው የትኛውን ምዕራፍ እያነበበ ነበር? ለ) ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ያነበው የነበረው ምዕራፍና ቁጥሮች ስለ ማን ይናገራሉ አለው? 

በኢሳይያስ 53፡7-9 የሚናገረው ቃል በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ላለችው ቤተ ክርስቲያን በጣም ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ጃንደረባው በፊልጶስ እርዳታ ወደ ክርስቶስ ሊመጣ የቻለው በዚህ ቃል ስለሆነ ነው። ይህ የፊልጶስ ምስክርነት የጥንት ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተነገረውንና በኢየሱስ የተፈጸመውን ትንቢት፥ እንደዚሁም ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት መሢሕና እዳኝ መሆኑን ለመግለጽ ይህን ክፍል ተጠቅሞ እንደነበረ ያመለክታል። 

ኢሳይያስ በቁጥር 10 ላይ ደግሞ፥ ምንም እንኳን መሢሑ ወንጀል ሳይገኝበት ቢሠቃይም፥ እንዲሞት የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ ነቢዩ ያረጋግጣል። ስለ ኃጢአት መሥዋዕት መሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። መሢሑ ስለ ዓለም ኃጢአት የበደል መሥዋዕት ለመሆን ስለ ፈቀደ እግዚአብሔር ባርኮታል። ምንም እንኳን እርሱ የራሱ የሆኑ ከአብራኩ የወጡ ልጆች ባይኖሩትም በኋላ ግን ዘሩ ይበዛለታል። በኋላ ከክርስቶስ ሞት የተነሣ የዘላለምን ሕይወት አግኝተው የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ስለሚሆኑት የሚናገር ነው። ደግሞም መሢሑ ሞቶ አይቀርም። በቁጥር 1 ላይ የተሰጠው ተስፋ የሰው ልጆችን ኃጢአት ከተሸከመ በኋላ መሢሑ ከሞት እንደሚነሣ ነው። እንደዚሁም መሢሑ በሥቃዩ የዓለምን ኃጢአት ለመሸከም ፈቃደኛ በመሆኑ፥ እንደዚሁም ወንጀለኛ ሆኖ መቆጠርን በመቀበሉና (ሉቃስ 22፡37) ስለ እኛ ኃጢአት በመሆኑ፥ በቁጥር 2 ላይ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ እንደሚያደርገውና እንደሚያከብረው ተስፋ ሰጥቷል። ፊልጵስዩስ 2፡9፥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለመሞት ራሱን ስለ ሰጠ እግዚአብሔር ወደ ክብር ስፍራ ከፍ እንዳደረገው ይናገራል። 42ኛ ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 7 ኢየሱስ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት እንደሆነ ይነግረናል። ኢሳይያስ 9 ደግሞ ኢየሱስ ጠቢብ፥ ብርቱ፥ አጽናኝና ሰላምን የሚያመጣ ንጉሥ እንደሚሆን ይገልጻል። እንዲሁም ኢሳይያስ 52 እና 53 ኢየሱስ ስለ እኛ ተሠቃይቶ ፍጹም መሥዋዕትነት በመሆን ኃጢአታችንን እንደ ተሸከመ ያስረዳል። እንግዲህ እነዚህ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ለእናንተም ሆነ ለምታገለግሏቸው ሰዎች በምን ምክንያት ጠቃሚዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማስታወሻ ደብተሮቻችሁ ውስጥ ጻፉ። 

ኢየሱስ ከእኛ ጋር ያለ አምላክ ስለሆነ፥ ሰዎች በመሆናችን የሚደርሱብንን ፈተናዎች፥ ኔግሮች፥ ሥቃዮችና የፍትሕ ወታደሎችን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚገነዘብልን ስናውቅ በጣም እንጽናናለን። ሰዎች በመሆናችን በሚደርሱብን ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር የማይሰማውና የማይንከባከበን አምላክ አይደለም። እርሱ እኛን የሚሰሙን ነገሮች ሁሉ ተሰምተውታል። ስለዚህ እኛን ከመንከባከብ ችላ አይልም። ምክንያቱም ኢየሱስ ጥበበኛ እጽናኝና ሰላምን የሚያመጣ ንጉሥ ስለሆነ፥ ሰብአዊ  ፍጥረት በመሆናችን ለሚያጋጥመን መከራ ሁሉ መፍትሔ ለመስጠት ነገሮችን ለማስተካከል ኃይልና ጥበብ እንዳለው እናውቃለን። በዚህኛው ሕይወት ይሁን ወይም በወዲያኛው፥ ኢየሱስ አንድ ቀን ሰላምን፥ ፍትሕንና ብልጽግናን ለዓለም ያመጣል። ምክንያቱም ኢየሱስ ፍጹም መሥዋዕትነትን በመክፈል ኃጢአታችንን ስለ ተሸከመ፥ እጅግ የከፋ ኃጢአታችን እንኳ ቢሆን በእርሱ ይቅርታ እንዳገኘ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። አንድ ቀን እግዚአብሔር በሚፈጥረው ፍጹምና አዲስ በሆነው ሰማይና ምድር እንደምንኖር እርግጠኞች ነን። ከሁሉም በላይ አንድ ቀን ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም በሚኖረን ኅብረት እንደምንደሰት እርግጠኞች ነን።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 
Exit mobile version