የክርስቶስ ሥራ በምድር ላይ በትምህርታችን የመጨረሻው ክፍል አጋማሽ ላይ ትልቅ ግምት ስለሚሰጠው ላለ ኢየሱስ እጅግ ጠቃሚ ሥራ፥ ማለትም በመስቀል ላይ ሞቱን በተመለከተ ዘርዘር አድርገን እናጠናለን። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ስለ ሌሎች የኢየሱስ ሥራዎች የምናጠና ስንሆን፥ ይህም ራሱን እንደ ሰው ዝቅ አድርጎ በምድር ላይ ስለ ፈጸመው ተግባር፥ እንዲሁም ራሱን ወደ ክብር ከፍ ከፍ ስላደረገበት ስለ ሰማያዊው ሥራው ይሆናል።
የክርስቶስ መቀባት
በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ ላለፉት አራት መቶ ዓመታት አሳሳቢ ሆኖ የቆየው የክርስቶስ መቀባት ጉዳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ክርስቶስ ስለ መቀባቱ በግልጽ ያስተምረናል (ሉቃስ 4፡18፤ የሐዋ. 4፡26-27፤ የሐዋ. 10፡38)። ነገር ግን ኢየሱስ ተቀባ ሲባል ምን ማለት ነው? የመቀባቱለ ውጤቶች ምን ምን ነበሩ? ኢየሱስ የተቀባው መቼ ነበር? የኢየሱስ መቀባት ስለ ባሕርይውና እርሱ ስላደረገልን ሥራ ምን ያስተምረናል? እነዚህ ጥያቄዎች ያለፉትን ኢትዮጵያውያንን ከፋፍለዋቸው ነበር፤ ዛሬም ቢሆን ብዙ ኢትዮጵያውያንን እንደ ከፋፈሉዋቸው ናቸው። ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ኢየሱስ መቀባት የሚያስተምሩንን ትምህርት ከማጥናታችን በፊት፥ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ቆየው ክርክርና አለመግባባት ታሪክ እናጠናለን።
[ለዛሬው ጥናታችን እነዚህን መጻሕፍትና ጥናታዊ ጽሑፎች እንደ ምንጭነት ተጠቅሜአለሁ፡– Current Christological Positions_of Ethiopian Orthodox Theologians by Tesfazghi Uqbit (ከተስፋ እዝጊ እቁቢት፥ የወቅቱ የኢትዮጵያውያን ሥነ መለኮት መምህራን ስለ ክርስቶስ ያላቸው አቋም)፣ The Ethiopian Orthodox Church and Its Christological Doctrine by Ayala Takle Haymanot (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የክርስቶሳዊ አስተምህሮ፥ በአየለ ተክለ ሃይማኖት)፣ A History of Ethiopia by Jones and Monroe (የኢትዮጵያ ታሪክ በጆንስ ሞንሮ)፥ The Church of Abyssinia by Harry Hyatt (የአቢሲኒያ ቤተ ክርስቲያን በሃሪ ሐያት)፣ Priests and Politicans by Donald Crummey (ካህናትና ፖለቲከኞች በዶናልድ ክራሚ)፣ and A Historical Investigation of Monophysitism in the Ethiopian Orthodox Church by Donald Brake (ስለ ክርስቶስ አካል ታሪካዊ ጥናት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ በዶናልድ ብሬክ):: ]
1. ተዋህዶና ቅባት
(እ ኤ አ በ1630) ላይ ጀስዊቶች (ኢየሱሳውያን) ከኢትዮጵያ እንደ ተባረሩ፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኛች መካከል ስለ ክርስቶስ መቀባት ክርክር ተነሣ። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (ሉቃስ 4፡16፤ የሐዋ. 4፡27፤ 10፡38) እና የኢየሱስ መጠሪያ ስም የሆነው «ክርስቶስ» («መሢሕ»፣ «የተቀባው) የሚሉት ማስረጃዎች በአንዳንድ ሁኔታ መቀባቱን ያመለክታሉ፥ በአጠቃላይ «መቀባት» በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያመለክተው፥ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለየት ባለ መንገድ ለማገልገል የተሾመ መሆኑንና ለዚህም አገልግሎት ኃይልና ሥልጣንን መቀበሉን ነው። ጀስዊቶች፥ በኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ አበክረው ይገልጹት የነበረው ነገር ኢየሱስ የተቀባው በሰብአዊነቱ ብቻ እንደ ነበረ ነው። በአምላክነቱ ሹመትም፥ ኃይልም፥ ሥልጣንም ለአገልግሎት አያስፈልገውም ነበር።
ምክንያቱም እርሱ ኃይልና ሥልጣን ያለው ፍጹም የሆነ አምላክ ነው። እርሱ ለሰብአዊ አገልግሎቱ ብቻ ሹመት፥ ኃይልና ሥልጣን አስፈልጎታል ይሉ ነበር፡፡ ጀስዊቶች ሰብአዊነቱ ብቻ ተቀባ በማለት አስተማሩ። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፥ ኢየሱስ አንድ ባሕርይ ብቻ አለው ስትል አጥብቃ አስተምራለች። ስለሆነም የኢየሱስ መለኮታዊነትና ሰብአዊነት የማይከፋፈሉ ናቸው በማለት ታስተምራለች። ኢየሱስ በሰብአዊነቱ ብቻ አልተቀባም ምክንያቱም ሰብአዊነቱና አምላካዊነቱ በአንድ ባሕርይ ተዋህደዋልና። ኢየሱስ በሰብአዊነቱ ብቻ ካልተቀባ፥ ታዲያ «ክርስቶስ በምን አኳኋን ተቀባ?» የሚለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የትምህርተ መለኮት ምሑራን ዘንድ ጥያቄ አስነሣ።
ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ስለ ክርስቶስ መቀባት ጥያቄ እንዴት ተነሣ?
ስለ ክርስቶስ መቀባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ የተነሣበት ምክንያት ጀስዊቶች ክርስቶስ የተቀባው በሰብአዊነቱ ብቻ ነው ብለው በማስተማራቸው ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የትምህርተ መለኮት ምሑራን ግን የክርስቶስ አምላክነትና ሰብአዊነት በአንድ ባሕርይ የተዋሐዳ ናቸው በማለታቸው ነው። መቼም ተቀባ ሲባል መቀባቱ በሰብአዊነቱ ብቻ ሊሆን አይችልም። ታዲያ በምን አኳኋን ተቀባ፣ ጀስዊቶች እንደ ተባረሩ ወዲያውኑ፥ ሁለት የተለያዩ ክፍሎች በዚሁ የክርስቶስ መቀባት አስተምህር ላይ ብቅ አሉ። ተዋሕዶ የሚባለው ክፍል አቋም በደብረ ሊባኖስ በሚገኝ የአቡነ ተክለሃይማኖት መነኮሳት ዘንድ ተቀባይነትን አገኘ። ይህ አስተምህሮ የክርስቶስ ሁለት ባሕርያት በአንድ በተዋሐዱ ጊዜ፥ ከመወለዱ በፊት ተቀ የሚለውን የሚያራምድ ነው። በዚህ መሠረት ቅብአቱ በአዳም ውድቀት ምክንያት ጠፍቶ የነበረውን ወደ ክርስቶስ ሰብአዊነት መለሰ። የሆነ ሆና ለአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የትምህርተ መለኮት ምሑራን፥ ይህ አስተምህt ክርስቶስን ሁለት ባሕርያት ያሉት በማድረግ የሚከፋፍል ስለሆነባቸው ወ! ጀስዊቶች አስተምህሮ አዘነበሉ። ሁለተኛውና ሌላኛው አስተምህሮ ቅብአ፡ የተባለው ነበር። ይህ አስተምህሮ ከጎጃም በመጡ የኢውስጣጥዮስ መነኮሳት ዘንድ ተቀባይነትን አገኘ። እነርሱም የክርስቶስ መቀባት ሁለቱ ባሕርያት እንዲዋሐዱ አድርጓል የሚል አቋም ነበራቸው። እንደዚሁም የኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርይ ሰብአዊ ባሕርይውን ስለ ዋጠው እርሱ ፍጹም ሰው አልነበረም የሚል ትምህርት ነበራቸው።
ቅባቶች ለሐዋርያት ሥራ 10፡38 ልዩ ትኩረት በመስጠት፥ «አብ ቀቢ፥ ወልድ ተቀቢ፥ መንፈስ ቅዱስ የቅብአቱ ዘይት» ነው በማለት አስተማሩ። ሆኖም ተዋሕዶዎች ይህ አስተምህሮ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን ከአብ የሚያሳንስ ነው ሲሉ ፈሩ። እንዲሁም ክርስቶስ ራሱን የቀባ ካልሆነ፥ ሰብአዊና መለኮታዊ ባሕርይው ሊከፋፈል ነው የሚል ሥጋት ነበራቸው። ተዋሕዶዎች አብ ቀቢ፥ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የሚቀባው ዘይት መሆን የለበትም አሉ። ምክንያቱም ወልድ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ስለሆነና ለዘላለምም የነበረ በመሆኑ መለኮታዊ ባሕርዩ ከሰብአዊው ባሕርዩ ጋር ራሱ እንዲዋሐድ ስላደረገ ነው ይላሉ። እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ያገኘውን ሥጋ ክብር ወዳለው ሰብአዊነት ለውጦታል። ስለዚህ መሪ ቃላቸው፥ «ወልድ ራሱ ቀቢ፥ ወልድ ራሱ ተቀቢ፥ ወልድ ራሱ የቅብአቱ ዘይት» ነው የሚል ነበር።
ተዋሕዶዎች ደግሞ መፈክራቸው ያደረጉት፥ «በተዋሕዶ እርሱ በማንኛውም ነገር ከአብ ጋር አንድ ነው» ትኩረት በመስጠትም ከሁለቱ ባሕርያት መዋሐድ የተነሣ ክርስቶስ ፍጹም መለኮት ነው አሉ። ቅብአቶች ግን ይህን በመጻረር «ክርስቶስ በመቀባቱ በማንኛው ነገር ከአብ ጋር እንድ ነው» የሚል አቋም አሳዩ። እዚህ ላይ ክብደት የሰጡት የክርስቶስ ባሕርያት እንዲዋሐዱ ያደረገው መቀባቱ ነው ለሚለው ነጥብ ነው። እንዲህ ማለትም የእርሱ መለኮታዊነትና ሰብአዊነት በአንድነት ተቀላቅሏል ማለት ነው። ሁለቱም ክፍሎች የክርስቶስን አንድ መለኮታዊና ሰብአዊ ባሕርይ እንደ ያዙ ለመቆየት በአቋማቸው ሲከራከሩ ሰንብተዋል።
ጥያቄ፡- ሀ) የየትኛው ገዳም መነኩሳት የተዋሕዶውን አስተምህሮ አራመዱ? ለ) የየትኛው ገዳም መነኩሳት የቅባቶችን እስተምህሮ አስፋፉ። 3ኛ ጥያቄ፡- ሀ) የተዋሕዶዎችን የእምነት አቋም በራሳችሁ ቃላት ግለጹ። ለ) የቅባቶችን አስተምህሮ በራላችሁ ቃላት ግለጺ።
የአቡነ ተክለሃይማኖት ደብር መነኩሳት የተዋሕዶዎችን አቋም ደገፉ። እነርሱም ክርስቶስ ሥጋ በለበሰ ጊዜ በተሠገዎ) ሁለቱ ባሕርያቱ በአንድ ባሕርይ ሲዋሐዱ ተቀባ ብለው አስተማሩ። በተጨማሪም ቀቢውም ተቀቢውም፥ የቅባቱም ዘይት ራሱ ክርስቶስ ነበር ሲሉ አስተማሩ። እንዲሁም ለክርስቶስ ሁለት ባሕርያት በአንድ መዋሐድና ስለ እርሱ ፍጹም አምላክ መሆን ክብደትና ትኩረትን ሰጡ። የኢውስጣጥዮስ መነኩሳት የቅባቶች አስተምህሮ ደጋፊ ነበሩ። በትምህርታቸውም ላይ፥ ቅባቱ ሁለቱ ባሕርያት በአንድ እንዲዋሐዱ እንዳደረገ ቅባቱን የቀባው አብ፥ የተቀባው ደግሞ ወልድ፥ የቅብአቱ ዘይት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው ሲሉ አስተማሩ። በዚህ አስተምህሮአቸው የክርስቶስ መለኮታዊና ሰብአዊ ባሕርያት ተቀላቅለዋል ማለታቸው ነው።
በዚህ ሁኔታ ተዋሕዶዎችና ቅባቶች የበላይነቱን ለመያዝ ሲሟገቱ የስድስት አፄዎችን የንግሥና ዘመን አሳለፉ። በእነዚህም ዓመታት ውስጥ የሲኖዶስ ስብሰባዎችና ክርክሮች ተደርገዋል፥ ጦርነቶችም ተካሂደዋል፥ ግድያዎች ተፈጽመዋል፥ መፈንቅለ መንግሥት ተደርገዋል፤ ውግዘትም ታውጇል። ነገሥታትም ቢሆኑ አንዳንዶቹ ተዋሕዶን ሌሎች ደግሞ ቅባትን ደግፈው ነበር። በ1687 ቀዳማዊ አፄ ኢያሱ፤ ከተዋሕዶና ከቅባቶች የተውጣጡ መነኮሳት ጣና ባህር በሚገኝ ደሴት ላይ ወዳለው ገዳም ሄደው ሥር ለሰደደው አለመግባባት መፍትሔ እንዲያገኙለት ላኩዋቸው። ነገር ግን ስምምነት ላይ የተደረሰ መፍትሔ ሊያገኙ አልቻሉም። በአፄ ዳዊት ንግሥና ዘመን (1762) የእስክንድሪያው ፓትሪያርክ አስታራቂ አሳብ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ። ነገር ግን ቅባቶች ፓትርያርኩ ያቀረቡትን አሳብ በመቃወም ሌላ አዲስ ግጭት አስነሡ።
2. የጸጋ ልጅና ሦስት ልደት
በዳግማዊ አፄ ኢያሱ ዘመን መንግሥት (1730-55) ሦስተኛ አስተምህሮ የያዘ ቡድን ተነሣ። ይህም የጸጋ ልጅ የሚለው ነው። የጸጋ ልጅ አስተምህሮ፥ ክርስቶስ ለዘላለም ዓለም ከአብ ጋር አልነበረም የሚል ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በጸጋው በሥርዓተ ጥምቀት አማካይነት እንደ ልጁ አድርጎ ተቀበለው ይላል። ይህ የጸጋ ልጅ በመባል የተነሣ አስተምህሮ ቀስ በቀስ ጎልብቶ ሥር ነቀል እስከ መሆን ደርሶ ነበር። ሦስት ልደትም ተብሎ ተጠራ። የሦስት ልደት አራማጆች እግዚአብሔር ክርስቶስን በጸጋ እንደ ልጅ ስለተቀበለው፥ ሦስት ጊዜ ተወልዶአል ብለው ያስተምሩ ጀመር። እነዚህም አንዴ ከዘላለም ዓለም ከአብ፥ አንዴ በተገዎ በድንግል ማርያም ማሕፀን፥ አንዴ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ተወልዷል የሚሉ ናቸው። አንዳንዶች ሦስተኛው ልደት በድንግል ማርያም ማሕፀን ውስጥ፥ በመንፈስ ቅዱስ የተፈጸመ ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ፥ ሦስተኛው ልደት የተፈጸመው ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀበት ወቅት ነው ይላሉ። የሦስት ልደት አስተምህሮ፥ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ እንዲሆን ያደረገው መቀባት መሆኑን ያስተጋባ ነበር።
ከዚህ በኋላ አብዛኛዎቹ የደብረ ሊባኖስ ካህናትና መነኮሳት የጸጋ ልጅ ወይም ሦስት ልደት የተባለውን አስተምህሮ ለመቀበል ረጅም ጊዜ አልወሰደባቸውም። ከዚያም አብዛኛዎቹ ከሰሜን ኢትዮጵያ የሆኑ ቁጥራቸው እናማ የሆነ ካህናትና መነኩሳት የተዋሕዶን አስተምህሮ መደገፋቸውን ቀጠሉበት። ለእነርሱም ካራ የሚል የቅጽል ስም ተሰጣቸው። ካራ ሊባሉ የቻሉበትም ምክንያት ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ የተወለደበትን ሦስተኛውን ልደት «ቆረጡ» በሚል ዘይቤ ነው።
ጥያቄ፡- ሀ) የሦስት ልደት አስተምህር እንዴት እንደ ተነሣ በራሳችሁ ቃላት አሩ። ለ) የሦስት ልደት አስተምህሮ ምን እንደነበረ በራሳችሁ ቃላት ግለጺ።
የሦስት ልደት አስተምህሮ የተነሣው ተዋሕዶና ቅባት ማናቸውም የበላይነትን ለማግኘት ባልቻሉበትና በመካከላቸውም ስምምነት ሊደርስ ባልተቻለበት ጊዜ ነበር። እነርሱም ክርስቶስ ክዘላለም ዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ አልነበረውም፥ ነገር ግን በተቀባ ጊዜ እግዚአብሔር የጸጋ ልጅ አድርጎ ተቀበለው ሲሉ ያስተምራሉ። ይህ ማለት ክርስቶስ ሦስት ጊዜ መወለዱን ያመለክታል። ይኸውም ለዘላለም ከአብ፥ ከድንግል ማርያም፥ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ተወልዶል ይላሉ።
3. ክርክሩ መፍትሔ አገኘ
በ1800ዎች ሲካሄድ የቆየው የአስተምህሮ ክርክር የኋላ ኋላ ኢትዮጵያን የከፋፈላት የፖለቲካ ቅራኔ አካል ሆነ። ስለሆነም፥ እያንዳንዱ አስተምህሮ ወይም ክርክር ያስነሣው ሥነ መለኮታዊ አቋም በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች ይደገፉ ነበር፡፡ ቅብዓት የተሰኘው አስተምህሮ በጎጃም፥ የሦስት ልደት ትምህርት ደግሞ በሸዋና በጎንደር፥ ተዋሕዶ ወይም ካራ የተባለው ደግሞ በትግራይ ተቀባይነት ነበረው። በኋላም አፄ ዮሐንስና ንጉሥ ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ዓላማቸው አካል አድርጎ በማሰብ በ1878፥ ይህን የቆየ የሃይማኖት ክርክር ሊያስቀር የሚችል ጉባዔ በወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ እንዲካሄድ አደረጉ። በዚህ ጉባዔ ላይ የተገኙት መማክርትም የሦስት ልደት አስተምህሮን በማውገዝ፥ የተዋሕዶን ሃይማኖት አቋም አጻደቁ። ከዚያን ወዲህ ክርስቶስ በባሕርይው አምላክ መሆኑና ከዘላለም ከአብ የተገኘ፥ ከድንግል ማርያምም ሰው ሆኖ የተወለደ፥ የተቀባበት ቅባትም እርሱ ራሱ መሆኑ በይፋ ታወጀ። የ«ሦስት ልደት» ደጋፊዎች ይህን ውሳኔ በመቃወማቸው ምላሳቸው ተቆረጠ። አፄ ዮሐንስ ሞተው አፄ ምኒልክ ንጉሥ ነገሥት ከሆኑ በኋላ፥ ምንም እንኳን ጉባዔ ባይጠሩም፥ በቀጥታ የተዋሕዶ እምነትን አቋም አራመዱ። ከዚያን ጊዜ አንሥቶ የተዋሕዶ ሃይማኖት፥ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሆኖ ቀጠለ። ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያኒቱ የቅብዓትና የሦስት ልደትን አስተምህሮ በመጻሕፍትዋ ውስጥ ብታወግዝም፥ ዛሬም ቢሆን በእነዚህ የእምነት ዓይነቶች ላይ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ በብዙ መምህራንና መነኮሳት መካከል ክርክር እንደ ተካሄደ ነው።
ጥያቄ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ የእምነት አቋም ምንድን | ነው? እምነቱ ይፋዊ እምነት እንዲሆን የትኛው ጉባዔ አወጀ?
በቦሩ ሜዳ የመማክርት ጉባዔ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ፥ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፥ የክርስቶስን መቀባት በተመለከተ፥ የተዋሕዶ እምነትን አቋም በይፋ ተቀበለች። ነገር ቀን ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ «ተቀባ» ሲሉ ስትክክል ምን ማለታቸው ነው?
4. የኢየሱስ ክርስቶስ መቀባት በአዲስ ኪዳን ውስጥ
ጥያቄ፡- ሉቃስ 4፡18 አንብቡ። ሀ) ሉቃለ ምን ክፍለ ምንባብን ይጠቅሳል? ለህ እንደዚህ አቀራረብ ከሆነ፥ የክርስቶስ መቀባት ዓላማ ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- የሐዋ. 426–27 አንብቡ። ሀ) ጴጥሮስ የትኛውን ክፍላ ምንባብ ጠቀለ? ለ) እንደ ጴጥሮስ አነጋገር፥ የተቀባው ማን ነበር? 8ኛ ጥያቄ፡- የሐዋ. ሥራ 10፡38 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር ኢየሱስን ከማን ጋርና በምን ቀባው? ለህ የዚህ ድርጊት ውጤትስ ምን ነበር?
በሰባተኛው ክፍለ ትምህርት ላይ እንደ ተከታተልነው፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሦስት ዓይነት ሰዎች ይቀቡ ነበር። እነርሱም ነገሥታት፥ ነቢያትና ካህናት ነበሩ። የእነዚህ ሰዎች መቀባት አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት፥ የተመረጠው ሰው፥ ለእግዚአብሔር የተለየ አገልግሎት ተመርጦ የተሾመ መሆኑን ሁሉ እንዲያውቀው ለማድረግ ነበር። መቀባት እግዚአብሔር አንድን ሰው የመምረጡና የመሾሙም ምሳሌ ነው። በተጨማሪም እግዚአብሔር ለአገልግሎቱ መንፈስ ቅዱስን በላዩ ላይ በማፍሰስ ለሥራ የማለታጠቁ ምልክትም ነው። በመጨረሻ ልዩ ልዩ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች ወደፊት በጣም በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር የተቀባ ወይም መሢሑ ለመሆን ወደሚመጣው እንዲመለከቱ አይሁዶችን እንዳዘጋጁዋቸው ተገንዝበናል። ብዙ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች ኢየሱስ በእግዚአብሔር እንደ ተቀባ ንጉሥ፥ በእግዚአብሔር እንደ ተቀባ ካህንና በእግዚአብሔር እንደ ተቀባ ነቢይ ሆኖ እንዴት የተሰጠውን ተስፋ እንደ ፈጸመ ገልጸዋል።
በሉቃስ በምዕራፍ 4፡18 ውስጥ፥ ሉቃስ፥ ኢሳይያስ 61፡1-2ን ይጠቅሳል። ይህ ክፍል እግዚአብሔር እንዲሰብክና ሕዝቡን እንዲፈውስ ቀብቶ ስለቀባው ይናገራል። ኢየሱስ ይህን ክፍል ባነበበ ጊዜ ያዳምጡት ለነበሩት ሰዎች፥ እርሱ ለመስበክና ለመፈወስ ሥራ በተለየ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተመረጠ መሆኑን መንፈስ ቅዱስ በውስጡ መሆኑንና ይህን ሥራ ለመሥራት ኃይልን እንደሚሰጠው ነገራቸው። በዚህም እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠና ሥልጣን ያለው መሢሕ መሆኑን ገለጸላቸው።
በሐዋ. ሥራ 4፡26-27 ውስጥ ጰጥሮስ ከመዝሙር 2 ላይ ይጠቅሳል። በስድስተኛው ክፍለ ትምህርታችን ላይ እንደ ተመለከትነው፥ ይህ ስለሚመጣውና ስለተቀባው ከሚናገሩት ትንቢቶች ሁሉ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው የትንቢት ክፍል ነው። ጴጥሮስ፥ ኢየሱስ መዝሙር ሁለት ውስጥ የተጻፈው ትንቢት ፍጻሜ ክፍል ነው አለ። ሄሮድስ፥ ጲላጦስና የአይሁድ ሕዝብ ኢየሱስን ለመግደል የጠነሰሱት ሤራ የመዝሙር 2 ትንቢት ፍጻሜ ነው፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ለልዩ ሥራ የተቀባ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች ፍጻሜ መሆኑን እንድናረጋግጥ ይረዳናል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እግዚአብሔር ለሥራው የመረጠውና ሥልጣንን ያቀዳጀው ነው።
ጴጥሮስ፥ በሐዋ. 10፡38 ውስጥ፥ ኢየሱስ ለመፈወስ፥ አጋንንት ለማውጣት፥ እንዲሁም መልካሙን ሁሉ ለማድረግ፥ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባና ኃይልም የተሰጠው ነው ይላል። እንደገናም፥ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ተስፋ እንዲፈጽም እግዚአብሔር የመረጠውና የእርሱንም ሥራ እንዲሠራ እግዚአብሔር ፍጹም ሥልጣን የሰጠው ነው ይላል።
ኢየሱስ የተቀባ ነው ማለት፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን ተስፋ ሁሉ የሚፈጽም፥ በእግዚአብሔር የተመረጠ መሢሕ ነው ማለት ነው። በእግዚአብሔር የተመረጠ እንደ መሆኑ፥ መሢሑ እንዲፈጽመው የተሰጠውን ተግባር እንዲያከናውን በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ሰጥቶታል። የእርሱ መቀባት ኢየሱስ እኔ በተስፋ የሰጠሁት ነው፥ እኔ የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ የሚፈልገውን ሁሉ ሰጥቼዋለሁ፥ የሚል እግዚአብሔር ለዓለም ያስተላለፈው አዋጅ ነው። ስለዚህ የኢየሱላ መቀባት ጉዳይ፥ ከሁለት ባሕርያቱ ውሕደት ጋር ምንም ግንኙነት ያለው ሆኖ አይታይም። በዚህ ፈንታ፥ መለኮትና ሰብአዊነት በኢየሱስ አማካኝነት የተዋሐዱ መሆናቸው ለሕዝብ በይፋ የታወጀበት ክስተት ነው። ሰው የሆነው አምላክ (ሰብአምላክ) ኢየሱስ የተቀባው እንደ አንድ ሰው ነው። ሰው የሆነው አምላክ (ሰብ አምላክ) ኢየሱስ በእግዚአብሔር ተስፋ የተሰጠባት ንጉሥ፥ ካህን፥ ነቢይና አዳኝ መሆኑ የታወጀው እንደ አንድ ሰው ነው። ሰው የሆነው አምላክ (ሰብ አምላክ) ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ተስፋ ለመፈጸም ሥልጣን የተቀበለው እንደ አንድ ሰው ነው።
ጥያቄ፡- አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወዳጃችሁ ስለ ኢየሱስ መቀባት አቋማችሁ እንደሆነ ሲጠይቃችሁ፥ እንዴት ብላችሁ ትመልሱላታላችሁ?
በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፥ ስለ ክርስቶስ መቀባት በሚካሄደው ክርክር ውስጥ መግባት አያስፈልጋቸውም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢየሱስ መቀባት ከምታነሣቸው ጥያቄዎች ሁሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ግልጽ የሆኑ መልሶችን የሚሰጡ ስለማይመስሉ ነው። በዚህ ፈንታ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች፥ የኢየሱስ አምላክነትና ሰብአዊነት በአንድ ባሕርይ ፍጹም የተዋሐዱ መሆናቸውንና የእርሱ መቀባት እርሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ የተሰጠበት፥ እንዲሁም ሥራውን ለመፈጸም ሥልጣን የተቀበለ መሆኑን የሚመሰክሩ መሆናቸውን ማመናቸውን መናገር ይገባቸዋል።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
