ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን ለመግለጽ ይጠቀምበት የነበረው የማዕረ መጠሪያው የሰው ልጅ የሚለው ነበር። ይህ የሰው ልጅ፥ የሚለው መጠሪያ በወንጌሎች ውስጥ ሰማንያ ሁለት ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሰማንያ አንዱን ጊዜ ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር የተጠቀመበት ነው።
1. «የሰው ልጅ» በብሉይ ኪዳን።
ጥያቄ፡- ዘኁልቁ 23፡19 አንብብ። ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ምን አይደለም ይላል?
ጥያቄ፡– መዝሙር 8፡3-4 አንብቡ። ሀ) በቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው «የሰው ልጅ» የሚለው አባባል ትርጉሙ ምንድን ነው? ለ) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥስ ለዚህ ስም ምን አጽንኦት ተሰጥቶታል?
ጥያቄ፡- ሀ) ሕዝቅኤል 2፡1፥3} 3፡1፥ 3፥ 4፥ 10፥ 16 አንብቡ። በእነዚህ በእያንዳንዱ ቁጥር ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ምን ብሎ ጠርቶታል? ለ) በአጭሩ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 1-3 ያለውን ክፍል ተመልከቱ። እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን በዚህ ስም ሲጠራው በተለይ ትኩረት የሰጠው ለምኑ ይመስላችኋል?
ጥያቄ፡- ዳንኤል 7፡13-14 አንብቡ። ሀ) ለሰው ልጅ ምን ተሰጠው? ለ) ሰዎችና መንግሥታት ስለ ሰው ልጅ ምን ይላሉ? ምንስ ይሰማቸዋል?
ብሉይ ኪዳን «የሰው ልጅ» የሚለውን መጠሪያ በሁለት የተለያዩ መንገዶች ያቀርበዋል። የመጀመሪያውን ትርጉም በዘኁልቁ 23፡19 እና በመዝሙር 8፡4 ላይ እናገኘዋለን። በእነዚህ ሁለት ክፍሎች «የሰው ልጅ» ማለት «ሰው» ማለት ነው። በእነዚህ ሁለት ክፍሎች ውስጥ «የሰው ልጅ» ‘ የሚለው መጠሪያ በጥቅም ላይ የዋለው፥ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር በማነጻጸር፥ ሰው ምን ያህል ደካማና ትንሽ ፍጡር መሆኑን ለማሳየት ነው። ዘኁልቁ 23፥ እግዚአብሔር ሐሰትን ይናገር ዘንድ «የሰው ልጅ» አይደለም ይላል። በመዝሙር 8 ላይ የተጻፈው ቃል ደግሞ «የሰው ልጅን’ ማንነት ከእግዚአብሔር ታላቅነትና በሰማይ ካለው ፍጥረቱ ስፋት ጋር ያነጻጽራል። «የሰው ልጅ ማለት ደካማና ፋይዳ-ቢስ ሰብአዊ ፍጡር ማለት ነው።
እግዚአብሔር በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ሕዝቅኤልን ሠላሳ ጊዜ «የሰው ልጅ» ሲል ይጠራዋል። በሕዝቅኤል ምዕ. 1-3 ባለው ውስጥ፥ ሕዝቅኤል ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትና ክብር ራእይ ያያል። ሕዝቅኤል ይህን ራእይ እያየም ሆነ ካየ በኋላ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እየደጋገመ«የሰው ልጅ» እያለ ይናገረዋል። እግዚአብሔርም በዚህ ራእይ ውስጥ የሕዝቅኤልን ሰብአዊ ደካማነት፥ ትንሽነት ከእግዚአብሔር ከራሱ ግርማና ተደናቂነት ጋር ያነጻጽራል። በዘኁልቁ 23 እና በመዝሙር 8 ላይ እንደተገለጸው ሁሉ «የሰው ልጅ» የሚለው ቃል የሚያመለክተው አቅመ-ቢስና ከምንም የማይገባ ፍጡርን ነው።
ነገር ግን ወደ ዳንኤል 7 በምንመጣበት ጊዜ «የሰው ልጅ» የሚለውን መጠሪያ ለየት ባለ ሁኔታ እንመለከተዋለን። ዳንኤል ምዕራፍ 7 የሚያወሳው፥ ስለ አራት አራዊቶች፥ አሥር ቀንዶችና ስለ አንዲት ትንሽ ቀንድ ነው። እነዚህ አራት አራዊቶች እያንዳንዳቸው የዓለምን አብዛኛውን ክፍሎች በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉ የሰው ልጆችን መንግሥታት ይገልጻሉ። ዳንኤል እነዚህን አራዊቶች ወዲያው እንዳየ በዘመናት የሸመገለውን ተመለከተ። ይህ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ዓለምን በክብርና በግርማ ሲገዛና እልፍ አእላፋት መላእክት ሲሰግዱለት ዳንኤል ያየው እግዚአብሔር ራሱ ነበር። ዳንኤል በራእዩ መጨረሻ ላይ አንድ ሰው ያያል፥ «እርሱም የሰውን ልጅ እንደሚመስል ይናገራል። ይህ የሰው ልጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን፥ እግዚአብሔር ራሱ ወደ አለበት ይቀርባል፤ ከዚያም መላ ዓለምን የሚገዛበት ሥልጣን፥ ክብር፥ ልዕልናና ኃይል ይሰጠዋል። በዓለም ያሉ ሕዝቦችም በአክብርት ውዳለና አምልኮ ያቀርቡለታል። እርሱ የሚገዛው መንግሥትም ለዘላለም የጸና ይሆናል።
ዳንኤል «የሰውን ልጅ» የመሰለ አየሁ ሲል ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ሲቀርብ ቀደም ሲል ከአያቸው አራዊቶች ጋር ሲነጻጸር ይኸኛው ሰውን ይመስል ነበር ማለቱ ነው። በኋላ ላይ ይህን ሰው ስለ አጋጠመው ሁኔታ ስናስብ በአድናቆት እንሞላለን። ይህ ሰው ወደ ራሱ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እንዲቀርብ ይፈቀድለታል። ለእግዚአብሔር ለራሱ ብቻ የተጠበቀ ሕዝቦችን የመግዛት ሥልጣን ይሰጠዋል። ሰዎች ለእግዚአብሔር ብቻ ሊያቀርቡ የሚገባውን አምልኮ ሕዝቡ ሁሉ ለዚህ ሰው ያቀርቡለታል። ደግሞም ለዘላለም በጸና መንግሥት ላይ ገዥ እንዲሆን ይደረጋል። ይህ ደሞ ለእግዚአብሔር ብቻ የተጠበቀ ሉዓላዊነት ነው። ስለሆነም ዳንኤል በራእዩ ውስጥ ያየው የሰው ልጅ የሰው ልጅነት ባሕሪ ያለው ቢሆንም፥ በአኳያው ለእግዚአብሔር የሚገባ ክብርም ተሰጥቶታል።
ስለ ሰው ልጅ ዳንኤል ያየው ይህ ራእይ፥ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ዘመናት መካከል ይኖሩ በነበሩ አይሁዳውያን ላይ ተጽዕኖ አሳድሮ ነበር። በአንዳንድ ታሪክ- ጠቀስ መጽሐፎቻቸው ውስጥ እንዳስቀመጡት፥ «የሰው ልጅ» የተባለ መሢሕ እንደሚመጣ ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበረ ተናግረዋል። እርሱም ከሰማይ መጥቶ ሰዎችን ሁሉ የሚወክል እጅግ ከፍ ያለ፥ ከሰዎች በላይ የሆነ፥ ሁሉን ያሟላ ሰው ይሆናል። በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያማልዳል። እርሱም በፍጹም ሰውነቱ፥ እንደ አዳም በመሆን ሰዎችን ሁሉ ይወክላል።
2. ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው።
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 8፡19-20፤ 12፡8፤ 16፡13-5፤ 26፡45-46፤ ሉቃስ 24፡7 ዮሐንስ 6፡53-54፤ 9፡35-37 ድረስ እንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ «ስለ ሰው ልጅ» በሚናገርበት ጊዜ፥ ስለ ማን መናገሩ ነበር?
ኢየሱስ ራሱን «የሰው ልጅ» እያለ ይጠራ እንደ ነበረ ወንጌሉች ሰማንያ ሁለት ጊዜ መዝግበውታል። በእነዚህ ማጣቀሻዎች መሠረት ኢየሱስ «የሰው ልጅ» ባለ ቁጥር ስለ ራሱ መናገሩ እንደ ነበረ ግልጽ ነው። በማቴዎስ 8፡19-20፥ አንድ ሰው ኢየሱስን ሊከተል ወደደ። ኢየሱስም እርሱን መከተል ከባድ መሆኑን፥ «ለሰው ልጅ ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም» በማለት አስረዳው። ኢየሱስ በዚህ ክፍል ራሱ የተመቻቸና ቋሚ የሆነ ቤት እንደሌለው ገልጾ፥ ሊከተለው የፈለገው ሰው የሚያርፍበትን ምቹ ስፍራ ሊሰጠው ዋስትና እንደማይገባ ነገረው። በዚሁ መሠረት ኢየሱስ ስለ ራሱ ባገለጠ ቁጥር ራሱን «የሰው ልጅ» ይል ነበር። በማቴዎስ 12፡8 ላይ ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎችን ልምድና አመለካከት በመንቀፍ፥ የሰንበትን እውነተኛ ትርጉም ያስተምራል። ትምህርቱንም ሲያጠቃልል፥ «የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው» ይላል። እርሱ ራሱ ስለ ሰንበት ተገቢ አጠቃቀም በተለያዩ ጊዜያት ያብራራና ያሳወቀ ሲሆን፥ እዚህ ላይ በግልጽ እንደሚታየው እርሱ የተናገረው ራሱን የሰው ልጅ በማድረግ ነው። እንዲሁም በማቴዎስ 16፡13 15 ባለው ክፍል ኢየሱስ፥ «ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?» ካላቸው በኋላ ቀጥሎ፥ «እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?» በማለት ይጠይቃቸዋል። ኢየሱስ፥ «የሰው ልጅ» በማለት በሚናገርበት ጊዜ ስለ ራሱ መናገሩን ደቀ መዛሙርቱ በግልጽ ተገንዝበው ነበር። በማቴዎስ 26፡45-46 ኢየሱስ «ሰው ልጅ» አልፎ ይሰጣል ካላቸው በኋላ፥ በማከል፥ «እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል» ይላል። በሉቃስ 24፡7 ደግሞ ኢየሱስ «የሰው ልጅ» አልፎ ይሰጣል፥ ይሰቀላል፥ ከሙታንም ይነሣል ይላል። በዮሐንስ 6፡53-54 የሰውን ልጅ ሥጋ መብላት ደሙንም መጠጣት፥ የኢየሱስን ሥጋ እንደ መብላትና ደሙንም እንደ መጠጣት ይቆጠራል ይላል። በዮሐንስ 9፡35-37 ኢየሱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ዓይነ-ሥውር ለነበረው ሰውዩ የሰው ልጅ መሆኑን ነግሮታል። እንግዲህ እነዚህ ጥቅሶች በቅደም ተከተል፥ ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅነቱ በተናገረ ቁጥር ስለ ራሱ መናገሩን ይገልጹልናል።
ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲገልጽ በምን ምክንያት «የሰው ልጅ» በሚለው መጠሪያ ይጠቀም ነበር? እንግዲህ «የሰው ልጅ» ብሎ ራሱን ሲጠራ፥ አድማጮቹ ምናልባት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያጠናናቸው ክፍለ-ምንባቦች ትዝ ብለዋቸው ይሆናል። እንደዚሁ በዘኁልቁ 23 በመዝሙር 8 ና በሕዝቅኤል «የሰው ልጅ» ተብሎ የተጠቀሰው ከነድክመቱና ጉድለቱ ከነፋይቶ=ቢስነቱ ያለን ሰብአዊ ፍጡርን የሚያመለክት ዓይነት አድርገው ወስደውት ይሆናል። ኢየሱስ ራሱን የሰው ልጅ ብሎ ሲጠራ፥ ራሱ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ዐቅዶ ነው። ነገር ግን ስለ ዳንኤል ምዕራፍ 7 ገለጻና ከዚህ ምዕራፍ የተነሣ ስላደረባቸው ተስፋ አስበው ይሆናል። ልክ እንደ እነርሱ በግልጽ ሰው የነበረው ኢየሱስ ከሰው የላቀ ቢሆን ኖሮ በጣም በተደነቁ ነበር። በዳንኤል የተገለጸው «የሰው ልጅ እርሱ ነውን?» ብለው ባሳቡ ነበር። የሚሰገድለትና ዓለምን የሚገዛው የሰው ልጅ የሆነው መሢሕ እርሱ ነውን?» ብለው በጠየቁም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ስለ ራሱ ለመግለጽ ራሱን «የሰው ልጅ» ሲል ሁለት ነገሮችን ማድረጉ ነበር። በመጀመሪያ፥ ለሰብአዊነቱ አጽንኦትን ወይም ትኩረትን ሰጠ። እርሱ በትክክል የሰው ልጅ ነበር። ሁለተኛ፥ ሰዎች እርሱ መሢሕ መሆኑን እንዲያስቡ ረቀቅ ባለ መንገድ ይገልጽላቸው ነበር። እንዲሁም እርሱ መሢሕ መሆኑን ለግብት በማያነሣሣ መንገድ ሰዎች እንዲረዱት ለማድረግ ችሏል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች «የሰው ልጅ» የሚለውን መጠሪያ «የተሸፈነ መሢሐዊ ገለጻ » ይሉታል። ምክንያቱም ኢየሱስ በዚህ ዘዴ በመጠቀም በግልጽ ራሱን «እኔ መሢሕ ነኝ» ብሎ ቢያስተዋውቅ ኖሮ ሊመጣ የሚችለውን ትርምስና ቅራኔ እንዲወገድ አድርጎአል።
3. የሰው ልጅ ታላቅ ሥልጣን ይኖረዋል፥ ሆኖም ግን ይሠቃያል
ኢየሱስ ራሱን የሰው ልጅ ብሎ ሲገልጽ የሚቃረኑ የሚመስሉ፥ ብዙ ልዩ ልዩ አሳቦችን በአንድነት አስቀምጦአል።
3.1 የሰው ልጅ ከተራ ሰው የተለየ ታላቅ ሥልጣን አለው
ጥያቄ፡– ማቴዎስ 3፡40-41 19፡28፤ 16፡27-28 አንብቡ። ኢየሱስ በእነዚህ ከፍለ ምንባቦች በእያንዳንዳቸው ውስጥ፥ የሰው ልጅ ምን ያደርጋል አላ?
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 9፡6 እና ዮሐንስ 5፡27 አንብቡ። በእነዚህ ክፍሎች በእያንዳንዳቸው ውስጥ የሰው ልጅ ምን እንዲያደርግ ሥልጣን ተሰጥቶታል?
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 3፡13-14 አንብቡ። የሰው ልጅ ከየት መጣ?
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 6፡27 አንብቡ። የሰው ልጅ ምንን ይሰጣል?
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 26፡64 አንብቡ። የሃይማኖት መሪዎች አንድ ቀን ምንን ያያሉ?
ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅ ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ራሱና የእርሱ መሢሕ የሚያከናውኑት ተግባር፥ የሰው ልጅ ለመፈጸም ሥልጣን እንዳለው አስተምሮአቸዋል። በማቴዎስ 19፡40-41 ውስጥ፥ የሰው ልጅ ሐሰተኛ ተከታዮችን ከመንግሥቱ ውስጥ ነቅለው እንዲጥሉ መላእክቱን እንደሚልክ ይናገራል። እግዚአብሔር ራሱ ብቻ መላእክትን የማዘዝ ሥልጣን አለው። በማቴዎስ 19፡28 ላይ ደግሞ የሰው ልጅ በክብር ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ዓለምን ይገዛል ይላል። እንዲሁም በማቴዎስ 16፡27-28 (እናም ስድስት ጊዜ በማቴዎስ ምዕራፍ 24-25) በምድር ላይ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም እንደሚመጣ ይገልጻል። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ እንደ የሰው ልጅነቱ መላ ዓለምን ለመዛት ሥልጣን ያለው ሢሑ እርሱ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። እዚህ ላይ ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅ ሊገለጽ የ መዛሙርቱ በሰሙ ጊዜ በዳንኤል ውስጥ ስለ ሰው ልጅ የተጻፈው ትዝ ብሎአቸው ይሆናል። እንዲሁም ኢየሱስ “የሰው ልጅ ሊላ፥ በሥልጣን ዓለምን የሚገዛ ኃያል መሣሕ መዛኑን ሳያምኑ አልቀሩ እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሰው ልጅ ተራ ሰው ሊያከናውነው የማይችለውን ሥራ ለመሥራት ሥልጣን እንዳለው አስተምሮአቸዋል፡ እርሱ በጣም ልዩ ሰው ሲሆን፥ ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ንንነት የነበረውና ልዩ ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነበር። በመላ 9፡6 ላይ የሰው ልጅ ኃጢአትን ይቅር ሊል ሥልጣን አለው ይላል፡ ኢየሱስ ሽባውን ሰው ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ባለው ጊዜ፥ ፈሪሳውያን ይህንን በመስማታቸው ተሸማቀቁ። ኃጢአትን ይቅር የሚል እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ዝባውን ሰው ኃጢአቱን ይቅር ሊለውና እርሱን” ለመፈወስ፥ መለኮታዊ ኃይልና ሥልጣን እንዳላው ወዲያው እረጋገጠላቸው። በዮሐንስ 527 ውስጥ ኢየሱስ የሰው ልጅ በሙታን ላይ ሊፈርድ ሥልጣን አለው ይላል። ይህ እንግዲህ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ያለ ሥልጣን ነው፡ በዮሐንስ 3፡13-14 ውስጥ ኢየሱስ ከሰማይ መምጣቱን ይናገራል። ይህ ከመወለዱ በፊት እንደ ነበረ ከእግዚአብሔር ጋር ከመወለዱ በፊት”ንኙነት እንደ ነበረውና እንደ እግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሆኖ እንደ ሞጣ ያመለክታል። በዮሐንስ 6፡27 ውስጥ ኢየሱስ፥ የሰው ልጅ የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል ይላል። ይህም ነገር እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርገው የሚችለው ነው። በማቴዎስ 26፡64 ደግሞ አንድ ቀን የሃይማኖት መሪዎች የሰው ልጅ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ያዩታል ሲል ኢየሱስ ይናገራል። (ይህም ማለት እርሱ የእግዚአብሔር ሥልጣንና ልዩ መብት ይኖረዋል ማለት ነው። በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሉች ሁሉ ኢየሱስ ሲናገር የምናገኘው እርሱ ከተራ ሰብአዊ ፍጡር የላቀ መሆኑን ነው። ስለሆነም የእግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣና የእግዚአብሔርም ሥልጣን ያለው ነው። በእርግጥ በማቴዎስ ምዕራፍ 26 ውስጥ ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት መለኮታዊ ሥልጣንና ልዩ መብት እንዳለው የሚያመለክቱ ስለነበሩ ይህን ምክንያት በማድረግ የሃይማኖት መሪዎች እንደ ተሳደበ አድርገው ክለ በመመሥረት እንዲሞት አደረጉ።
3.2 የሰው ልጅ ሊሠቃይና ሊያገለግል መጣ።
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 17፡9፤ 7፡12፥ 22፤ 20፡1ai 28 አንብቡ። በእዚህ ጥቅሶች ሁሉ ውስጥ ኢየሱስ የሰው ልጅ ምን ያደርጋል አለ?
ጥያቄ ዮሐንስ 1፡34 አንብቡ፡ ሕዝቡ ምንን ማወቅ ፈለጉ?
ነገር ግን ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅ ባስተማረው አንዳንድ ትምህርት አድማቹን ሊያስደንቃቸው ችሎአል። የሰው ልጅ በሥልጣኑ ታላቅነት ከተራ ሰው በላይ የላቀ መሆኑ ብቻ አይደለም። እርሱ ይሠቃያል ደግሞም ያግለግላል። በማቴዎስ 12፥ 22 እና 20፡18 ውስጥ ለደቀ መዛሙርቱ የሰው ልጅ አልፎ እንደሚሰጥና እንደሚሠቃይ ነግሮአቸዋል። እንደዚሁም በማቴዎስ 7፡9 ውስጥ ሞቱ ካበቃ በኋላ ከሙታን እንደሚነሣ ገልጾላቸዋል። በማቴዎስ 20፡28 ውስጥ፥ እርሱ እንደ ሰው ልጅ የመጣበት ምክንያት ለመግዛትና ሥልጣኑን ለማሳየት ሳይሆን ሌሎችን ለማገልገል እንደሆነም ተናግሮአል። እንዲያውም ሕይወቱን እስከ መስጠት ድረስ ሌሎችን እንደሚያገለግል አስገንዝቧል። ጌታ ይህን ሲናገር አባባሉ ደቀ መዛሙርቱን ለጊዜው እንዲደናገሩ ሳያደርግ አልቀረም። የሰው ልጅ በሥልጣን የሚገዛው መሢሕ ከሆነ፥ ታዲያ እንዴት ሊያገለግል፥ ሊሠቃይና ሊሞት ደግሞ ይችላል? ኢየሱስ ይህን ማለቱ የሰው ልጅ የሚሠቃየው አዳኝ መሆኑን ለደቀ መዛሙርቱ ሲያመለክታቸው ነበር። እንዲሁም መሢሑ -ንጉሥ መሢሑ አዳኝም ነው።
ነገር ግን ኢየሱስ ስለ ሰው ልጅ ጠቅሶ ደቀ መዛሙርቱን ባስተማራቸው ጊዜ ብቻ አልነበረም ያደናገራቸው። እንደዚሁም ሕዝቡን ስለ ሰው ልጅ ሥቃይና መከራ ባስተማራቸው ጊዜም ሕዝቡ በትምህርቱ ተደናግረዋል። በዮሐንስ 12፡23 ውስጥ፡- «እነሆ፥ የሰው ልጅ የሚከበርበት ሰዓት ደርሶአል» ይላል። ከዚያም ወዲያውኑ ስለ ሞቱ መናገር ጀመረ። ይህ እንግዲህ ሕዝቡን አደናግሯቸዋል። እነርሱ ሲጠባበቁት የነበረው የሰው ልጅ ኃያልና ባለሥልጣን የሆነ መሢሕን ነበር፡ ከእነዚህ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ኢየሱስ የሰው ልጅ መሆኑን በይፋ ሲገልጽ ሰምተዋል፥ እግዚአብሔር ራሱ ብቻ ያለው ኃይልና ሥልጣን ለሰው ልጅ እንደሚሰጠው ሲናገርም አድምጠዋል። መሢሑ ለዘላለም ንጉሣቸው እንደሚሆን፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተረድተዋል (ምሳሌ፡- ኢሳይያስ 9፡7 ሕዝቅኤል 37፡25፤ መዝሙር 89፡35 37። ነገር ግን አሁን ኢየሱስ እንደሚሞት ሲናገር እየሰሙ ናቸው። ታዲያ ኢየሱስ የሚሞት ከሆነ እንዴት አድርጎ ኃያል፥ መሢሕ ሊሆን የሚችል ሥልጣን ያለው የሰው ልጅ፥ እንዲሁም የዘላለም ገዢአቸው ሊሆን ይችላል? እናም እንዲህ ሲሉ ይጠይቁታል፥ «ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?» ኢየሱስ የሰው ልጅ ስለመሆኑ እንደ ተናገረ አስበው ነበር። እንግዲህ ያ ኢየሱስ ካልነበረ፥ ኢየሱስ ማን ነው? ኢየሱስ በግልጽ ይናገር የነበረው እንዴት ስላለው የሰው ልጅ ነበር?
ደቀ መዛሙርቱን ቀራ አጋብቶ የነበረው እውነታ የተሰበሰበውንም ሕዝብ አደናግሯል። የሰው ልጅ ሥልጣን ያለው መሢሐዊ ንጉሥና የሚሠቃይ መሢሐዊው- አዳኝ ነበር። የሰው ልጅ በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሰለት መለኮታዊ ገዥና እንዲሁም በዘኁልቁ ምዕራፍ 23 እና በሕዝቅኤል ውስጥ የተነገረለት ደካማና በቀላሉ የሚጠቃ ሰው ነበር።
«የሰው ልጅ» የሚለው መጠሪያ ስለ ኢየሱስ ኃይልና ሥልጣን፥ እንዲሁም ስለ እርሱ ትሕትናና ሰብአዊነት ያስታውሰናል። እርሱ መላእክትን ያግዛል፤ ኃጢአትንም ይቅር ይላል። አምልኮአችንም የተገባው ነው። ነገር ግን ደግሞ በዓለም ሚዛን ሲታይ እርሱ ደካማና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል ትንሽና ከቁጥር የማይገባ ሆኖ ይታያል። እርሱ የመላው ዓለም ገዥ ሆኖ ሳለ፥ ሊያገለግል መጣ። እርሱ የሰዎች ሁሉ ፈራጅ ሆኖ ሳለ፥ ራሱን መሥዋዕት ስማድረግ ለሰው ዘር ሁሉ ሲል ሞተ።
4. ኢየሱስ የሰው ልጅ የመሆኑ አግባብነት አስፈላጊነት
ጥያቄ፡- ኢየሱስ ሌሎችን ሊያገለግል የመጣ የሰው ልጅ ከመሆኑ የተነሣ እናንተ ከእርሱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት እንዴት ያለ ሊሆን ይገባዋል?
ጥያቄ፡- ኢየሱስ እንዲህ ያለ የሰው ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር በየቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ምን ዓይነት መሪዎችን የሚፈልይመስላችኋል?
ኢየሱስ የሰው ልጅ እንደ መሆኑ መጠን የመላው ዓለምም ገዥ ስለሆነ ሊከበርና ሊመለክ ይገባል። እርሱ ኃጢአትን ይቅር የሚልና የመላው ዓለም ፈራጅ ነው። ነገር ግን እርሱ ፈራጃችን ብቻ አይደለም፥ ወዳጃችንና እኛን ሊያገለግል የመጣም ነው። ወደ ምድር የመጣው ሰዎች እንዲያከብሩትና እንዲያገለግሉት ሳይሆን፥ የሚፈልጉትንም ሁሉ ሊያሟላላቸውና ሊያገለግላቸው ነው። ኢየሱስን በአምልኮትና በአክብርት ልንቀርበው ይገባል። ነገር ግን ራሱን ስለ እኛ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበ መሆኑን ተገንዝበን ወዳጃችንን እንደምንቀርብ ልንቀርበው ይገባል። ከእርሱ ጋር ጊዜአችንን ለማሳለፍና እርሱን ለማገልገል፥ ዕድል በማግኘታችን ምንኛ ደስተኞች እንደሆንን ለመግለጽ በምስጋናና በናፍቆት ወደ እርሱ መቅረብ አለብን።
ኢየሱስ እንደ ሰው ልጅነቱ፥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሆኑት ላሌ ይሰጣቸዋል። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የምእመናን አገልጋዮች እንጂ ገዢዎች ሊሆኑ አይገባቸውም። መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ ቢሆንም እንኳን፥ ዋና ተግባራቸው የምእመናኑን ችግር ማቃለልና ፍላጎታቸውን ማሟላት መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። ምንም እንኳን ሥልጣን ቢኖራቸውም፥ በአመራራቸው ላይ አምባገነኖች መሆን አይኖርባቸውም። ሕዝበ ክርስቲያኑን በፍቅር ሊንከባከቡና ሊያጠናክሩ ይገባል። እንደ ሰው ልጅነቱ ኢየሱስ የእርሱ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን የሥልጣን ዓላማው ማገልገል እንጂ መገልገል እንዳልሆነ ያስገነዝባል።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
