ዛሬ፥ ብዙ ጊዜ የምናነሣውን «የእግዚአብሔር» ስለሚለው የኢየሱስ መጠሪያ እናጠናለን። ራሳቸውን ክርስቲያኖች ብለው የሚጠሩ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን «የእግዚአብሔር» ብለው ይጠሩታል። ነገር ን የዚህ መጠሪያ ምሥጢር ምን እንደሆነ በእርግጥ አይነዘቡም። ሙስሊሞች ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለውን አባባል አይቀበሉትም። ምክንያቱም ይህ ከሆነ እግዚአብሔር እንደ ማንኛውም ሰው ልጅ ወለደ ማለት ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው። ይሁንና ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
1. «የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን ውስጥ
ጥያቄ፡– ዘፀአት 4፡22 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር «የበኲር ልጂ፡ ያለው ተንን ነበር? ለ) ሆሴዕ 11፡1 አንብቡ፡ እግዚአብሔር፡ ከግብፅ የጠራሁት ልጄ ያለው ማንን ነው?
ጥያቄ፡– ኢዮብ 6፡1 2፡1 በቀድሞ የአማርኛ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ። ሀ) በዚህ ትርጉም መሠረት፡ በእግዚአብሔር ፊት ሊቆሙ የመጡት እነማን ነበሩ? ለ) እንደ 1980 ዓም የአማርኛ ትርጉም አጻጻፍ ወይም እንደ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት ሊቆሙ የመጡት እነማን ነበሩ?
ጥያቄ፡– 2ኛ ሳሙ 12-16 እንብቡ። ሀ) በቁጥር 4 ላይ እግዚአብሔር ልጅ ብሎ የጠራው ማንን ነው? ለ) መዝሙር 2፡4-7 እንብቡ። ቁጥር 6ን በጥንቃቄ ተመልከቱ። በቁጥር 7 ውስጥ እዚእብሔር ልጁን ሲናገር ስለ ግን መላጹ ነበር? ሐ) መዝሙር 89፡20-29 አንብቡ፡፡ በቁጥር 27 ውስጥ እግዚአብሔር በምድር ላይ እጅ ከፍ የሚለውን የበኩር ልጁን ይሾማል። ቀደም ሲል በተመለከትናቸው የጥቅስ ከፍሎች ውስጥቶ ይህ እግዚአብሔር የሚሾመው ሰው ማን ነው?
1. እስራኤል እንደ «እግዚአብሔር ልጅ
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ የሚለው መጠሪያ በተለያዩ መንገዶች በጥቅም ላይ ውሎአል። በመጀመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ መጠሪያነት ነበር የዋለው። በአፀአት 4፡22 ላይ ሙሴ ለፈርዖን እስራኤል የበኩር ልጁ መሆኑን እንዲነግረው እግዚአብሔር አዝዞት ነበር። እግዚአብሔር ለፈርዖን እርሱ እስራኤልን ከዓለም ሕዝቦች መካከል የተለየ ሕዝብ አድርጎ እንደ መረጣቸው መንገሩ ነበር፡ የእስራኤልን ሕዝብ የመረጠው ከእርሱ ጋር የተለየ ቀንኙነት እንዲኖረው ነበር። በሆሴዕ 1፡1 እንደ ገናም እግዚአብሔር እስራኤል ከግብፅ ሊወጣ ልጄ ብሎ ጠርቶታል።
ተዎላ ይህንኑ ክፍል ስለ ኢየሱስ እንደ ትንቢታዊ ቃል አድርጎ ተጠቅሞበታል (ማቴዎስ 2፡5)፡ ሆሴዕ በምዕራፍ 11 ላይ፡- ከእስራኤል ኅብን ለቅቆ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፥ ነገር ግን ይኸው እስራኤል እንደ እግዚአብሔር ልጅ ትእዛዙን ጠብቆ ለፈቃዱ ሳይገዛ ቀረ ብሏል። ማቴዎስ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑንና ለእግዚአብሔር የታዘዘውና ፈቃዱን የፈጸመው ከግብፅ ከተመለሰ በኋላ መሆኑን ጽፎአል። የኢየሱስ ሕይወት ከእስራኤል ታሪክ ውስጥ በጣም የጎሉ ሁኔታዎችን እንደሚያንጸባርቅ ማቴዎስ ተገንዝቦ ነበር፡ ነገር ግን እስራኤል ኃጢአት ሠርቶ በወደቀበት በእያንዳንዱ ነጥብ፥ ኢየሱስ ለአባቱ ታዘዘ፥ ተባሩም ተዋጣለት ያስኬታማ ሆነህ።
1.2. መላእክት እንደ እግዚአብሔር ልጆች»
በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው ስያሜ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተሰጠበት መንገድ የእስራኤል መግለፃ በመሆን ነበር። ይህ ሕዝብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተለየ ቀንኙነት እንዲኖረው አድርጎ የመረጠወ ሕዝብ ነበር፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰው ልጅ የሚለው ስያሜ በሁለተኛ መንገድ በጥቅም ላይ የዋለው ለመላእክት መጠሪያ በመሆን ነበር። ኢዮብ 1፡6 ና 2፡1 የእግዚአብሔር ልጆች በሰማይ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚቆሙ ይገልጻል። ይህ የእግዚአብሔር ልጆች የሚለው አጠራር፥ በአዲሱ መደበኛ ትርጉምና በእንግሊዝኛው ሊቪንግ ሳይብል (ሕያው ቃል) ውስጥ «መላእክት» ተብሎ ተተርጉሟ። ኢዮብ የእግዚአብሔር ልጆች የሚለው ስለ መላእክት ነበር። የእግዚአብሔር ልጆች የሚለውን ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በኢዮብ ውስጥ የሚረዱት እንደዚሁ ነው፡ «የእግዚአብሔር ልጅ ለሚለው የተሰጠው ይህ ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌላ ስፍራ አይገኝም። ነገር ግን የሚያስታውስን፥ «የእግዚአብሔር ልጅ» ሊባል፥ እግዚአብሔር በተለይ ራሱ ለመረጣቸው የሚጠቀምበት መጠሪያ እንደ ነበረ ነው።
1.3. ዳዊትና ዘር ማንዘሮቹ (ተወላጆቹ) እንደ «እግዚአብሔር ልጆች»
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው መጠሪያ በጥቅም ላይ የዋለበት ሦስተኛው መንገድ፥ ዳዊትንና ተስፋ የተገባላቸው የዘር ሐረጉን ለመግለጽ ሲሆን፥ በተለይም የተቀባውን እስራኤልን ለመግዛትና ለማዳን እንደሚመጣ ተስፋ የተገባለትን የዳዊት ልጅ መሢሑን ነበር፡ በ2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር የጻዊት ዙፋን ለልጅ ልጅ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቶት ነበር። እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን ለዳዊት በገባበት ጊዜ ልጁ ከእርሱ በኋላ እንደሚነግሥና ለእርሱ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራለት ተስፋ ሰጥቶት ነበር። እግዚአብሔር ራሱ ለዳዊት ልጅ አባት እንደሚሆነውና የጻዊትም ልጅ የራሱ ልጁ እንደሚሆን ነግሮታል። በዚህ ክፍል ትክክለኛው የእስራኤል ገዥ የሆነውን የተመረጠውን ዳዊትን ብሉይ ኪዳን «የእግዚአብሔር ልጅ» ሲል ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዳዊትንና ሐረገ ትውልዱን፥ እንዲገዙና ከእርሱም ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖራቸው መርጧቸዋል። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከዳዊት ዘር የሚመጣውን፥ የሚዛቸውንና አዳኝ የሚሆናቸውን መሢሕ፥ በእግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የተመረጠ የእግዚአብሔር ልጅ አድርገው ይጠባበቁት ነበር።
ስለ ዳዊትና ዘሮቹ በተለይም ስለሚመጣው መሢሕ በእግዚአብሔር የተመረጡ ልጆች ስለመሆናቸው በመዝሙር 2 እና በመዝሙር 89 ውስጥ ተደገሞ ተነግሮአል። ከሁለት ሳምንታት በፊት የጻዊት ቤተሰብ የሆኑ እግዚአብሔርን ይፈሩ የነበሩ ነገሥታት መዝሙር 2ን ስለ እነርሱ እንደ ተነገረ አድርገው ይጠቀሙበት እንደ ነበረ ተመልክተናል። ነገር ግን በዚህ መዝሙር ላይ የተነገረውን ተስፋ አንዳቸውም አልፈጸሙም ነበር። የእስራኤል ሕዝብም ከዚህ መዝሙር በመነሣት እግዚአብሔር ከዳዊት ዘር የተገኙ ነገሥታት እንዲገዙዋቸው የመረጣቸውና ከእርሱም ጋር ልዩ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያደረገ መሆኑን ያምኑ ነበር። ነገር ግን በአኳያው ደግሞ በዚህ መዝሙር ውስጥ የተጻፈውን የሚፈጽም ከዳዊት ዝርያ የሚወጣ ታላቅ የሆነ ሰው ገና እንደሚመጣ ግንዛቤ ነበራቸው። ይህ ከዳዊት ቤተሰብ የሚመጣው ንጉሥ በጣም በተለየ አኳኋን የያህዌ ልጅ የሚሆነው ነው። መዝሙር 89 እግዚአብሔር ጻዊትንና ቤተሰቡን እንደ ልጆቹ አድርጎ የተናገረውን አባባል ደግሞ ይገልጻል። በመዝሙር 89፡27 ውስጥ እግዚአብሔር ዳዊትን «የበኩር ልጄ» ይለዋል። እንደገና ዳዊትና ዘሩ ሕዝቡን እንዲገዙ፥ እንደዚሁም ከእርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖራቸው የመረጣቸው መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ ይናገራል።
ብሉይ ኪዳን እንግዲህ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን መጠሪያ በሦስት መንገዶች ይጠቀምበታል። ስለ እስራኤል፥ ስለ መላእክት እና ስለ ዳዊት ዘር ነገሥታት በተለይም ስለሚመጣው መሢሕ በሚናገርበት ጊዜ ማለት ነው። እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ዳዊት እንደ ልጆቹ አድርጎ በተናገረ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ የተናገረው ከእርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንደሚኖራቸው ነበር።
2 «የእግዚአብሔር ልጅ» በማቴዎስ፥ በማርቆስና በሉቃስ ወንጌል ውስጥ
2.1. የእግዚአብሔር ልጅ ተስፋ የተገባለት መሢሕ ነው።
ኢየሱስ በነበረበት ዘመን የኖሩ ግሪኮችና ሮማውያን ንጉሥ፥ ጀግና ወይም ፈላስፋ ለማለትም ሆነ ስለ እነርሱ ለመግለጽ ሲፈልጉ፥ ብዙ ጊዜ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን ሐረግ ይጠቀሙበት ነበር። ይህም አጠራር የተመሠረተው እነዚህ ሕዝቦች ይከተሉዋቸው በነበሩ ብዙ ዓይነት አማልክት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም፥ ይህ አሳብ በአይሁዳውያን ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ አይመስልም። በዚህ ፈንታ በኢየሱስ ዘመን የነበሩ አይሁዳውያን «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን ስያሜ መሢሑን ለመግለጽ ይጠቀሙበት ነበር። ከክርስቶስ ልደት በፊት በአይሁዳውያን ደራሲያን በተጻፉ በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ ይመጣል የተባለለት መሢሕ «የእግዚአብሔር ልጅ» ተብሎ ተጠቅሷል። (እነዚህ መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያልተጻፉ ስለሆኑ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጠቃለሉም። ነገር ግን በኢየሱስ ጊዜ ስለነበረው ታሪክ ያስተምሩናል።) ስለዚህ ማቴዎስ፥ ማርቆስና ሉቃስ ኢየሱስን፥ የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ሲገልጹት፥ በመጀመሪያ አጽንኦት ሰጥተው መናገር የፈለጉት፥ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ የተሰጠበት መሢሕ እንደ ነበረ ነው።
ጥያቄ፡– ማቴዎስ 16፡16 አንብቡ። ጴጥሮስ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ (መሢሕ) ነው ብሎ የተናገረውን እንዴት ባለ ተጨማሪ ማስረጃ ይገልጸዋል?
በማቴዎስ 16 ውስጥ ኢየሱስ ሕዝቡ እርሱን ማን ብለው እንደሚያምኑ፥ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቀ። እነርሱም አንዳንዶቹ፥ መጥመቁ ዮሐንስ ነህ ይላሉ፥ ሌሎችም ኤልያስ ነህ ይሉሃል፥ ሌሎቹ ደግሞ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን አይቀርም ይሉሃል አሉት። ከዚያም ኢየሱስ እነርሱን ራሳቸውን ሲጠይቃቸው «እኔ ማን እንደሆንኩ ታምናላችሁ?» አላቸው። ጴጥሮስም በሁላቸው ስም ሲመልስ፥ «አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ» አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ፥ እርሱና የቀሩት ደቀ መዛሙርቱ፥ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ የተሰጠበትና በእግዚአብሔር የተቀባ መሢሕ መሆኑን እንደሚያምኑ አረጋገጠለት። ቀጥሎም ኢኢየሱስ መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማመኑን አብራርቶ ገለጸ። እንዲሁም ጴጥሮስና ማቴዎስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው ሲያስታውቁ፥ በአኳያው ኢየሱስ መሢሕ ነው ማለታቸው ነበር። 2.2 የእግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ የሆነ ግንኙነት አለው።
ነገር ግን ማቴዎስ፥ ማርቆስና ሉቃስ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ብቻ ያስተማሩ ሳይሆኑ፥ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው ሲናገሩ፥ ምን ዓይነት መሢሕ እንደሆነም ልዩ ትኩረት ሰጥተው ገልጸዋል። ስለዚህ እርሱ ከእግዚአብሑር ጋር ልዩ ቀንኙነት ያለው መሢሕ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል። እንደዚሁም ኢየሱስ ራሱ መለኮታዊ የሆነ መሢሕ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ጠቅሰዋል። 19ኛ ጥያቄ፡- ማርቆስ 1፡11ና 9፡7 እንብቡ። በእነዚህ ሁለት ምንባቦች ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ልጁ ምን ይላል?
ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜም ሆነ መልኩ የሚያንጸባርቅ ሆኖ በተለወጠበት ወቅት እግዚአብሔር አብ፥ በቀጥታ በሰማይ ሆኖ በመናገር፡ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ገልጾአል። በሁለቱም ስፍራዎች እግዚአብሔር አብ፡ «እርሱ የሚወደው ልጁ» መሆኑን ገልጾአል። እግዚአብሔር አብ ይህን ሲል ኢየሱስ ልጁ እንደ መሆኑ መጠን ከእርሱ ጋር ልዩ ግንኙነት እንዳለው መናገሩ ነበር። አንድ ሰው ለሁሉም ልጆች ፍቅሩን የሚገልጽ መልካም ሰው ሊሆን ይችላል። ቀን ለራሱ ልጆች የተለየ ለእነርሱ ብሎ የሚቆጥበው ፍቅር ይኖረዋል። ይህም ማለት ከእነርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት ይኖረዋል፥ ስለዚህ ከሁሉ አስበልጦ ይወዳቸዋል። በተመሳሳይ መንገድ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ቢወድም፥ ከሁሉ በላይ ግን ኢየሱስን ወደደ። አብ ከልጁ ጋር የተለየ ቅርበትና ቀንኙነት አለው፥ ምክንያቱም ለዘላለም ዓለም ይወደው ስለነበረ ነው። እግዚአብሔር በዚህ በተጠመቀና መልኩም በሚያንጸባርቅ ሁኔታ ከተለወጠ ኢየሱስ ጋር በዘላለማዊ ፍቅርና ግንኙነት ደስ ተሰኘ። ማርቆስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሲል፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ባለው በዚህ የተለየ ግንኙነት ደስ የሚሰኝበት ነው ማለቱ ነው። 20ኛ ጥያቄ፡- ማቴዎስ 1፡27 አንብቡ። ሀ) ልጅን የሚያውቀው ማን ነው? ለ) አባትን የሚያውቀው ማን ነው? እርግጠኞች በመሆን የተሟላ መልስ ስጡ።
በአብና በወልድ መካከል ልዩ ፍቅር ያለበት አንድነት ነበረ ማለት፤ ማንም ሰው ሊገነዘበው በማይችለው መንገድ እርስ በርስ ይተዋወቃሉ ማለት ነው። አብ ብቻ በትክክል ወልድን ፍጹም በሆነ ቅርበት ባለው አኳኋን ያውቀዋል። ወልድ ብቻ አብን ስለሚያውቀው እርሱ ብቻ አብን ለሌሎች ሊገልጥ ቻለ። ስለዚህ አብን የማወቂያው መንገድ በኢየሱስ አማካይነት ብቻ ነው። ብቸኛው ሰው የሆነው ኢየሱስ ራሱም እግዚአብሔር ስለሆነ እግዚአብሔርን ያውቃል። በመሆኑም ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ቢፈልግ ወደ እርሱ ዘንድ መድረሻ ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው። እንደዚሁም በአሰና በመላድ መካከል የተለየ ቀንኙነት አለ ማለት አብና ወልድ እርስ በርስ በሚገባ ይተዋወቃሉ ማለት ነው፥ ስለዚህም ወልድ ብቻ አብን ለሌሎች ሰዎች ሊገልጥ ይችላል።
ጥያቄ፡– ማቴዎስ 24፡43 አንብቡ፡፡ በኢየሱስ ላይ ያፌዙበት የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ ምን ይደረግለት አሉ?
በወቅቱ ኢየሱስን የከሰሱትና ያረዙበት አይሁድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጀ ነኝ ብሎ በተናገረ ጊዘ ምን ማለቱ እንደሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ገብቶአቸዋል። በዚህ አነጋገሩም ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ቀንኙነት እንዳለው ተረድተዋል። በተሰቀለም ጊዜ፥ በእውነት እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ እግዚአብሔር መጥቶ ያድነው ሲሉ ተሳለቁበት። ይህ አባባላቸው፥ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነት ያለው መሢሕ ከሆነ እስኪ እግዚአብሔር ያድነው ማለታቸው ነበር። ኢየሱስ ስለ ተሰቀለ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ የፍቅር ግንኙነት ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ይwናል ብለው አላመኑም። እግዚአብሔር ኢየሱስን እንዳይሰቀል ያላደረገበት ምክንያት በሞቱ የዓለምን የኃጢአት ቅጣት ሁሉ እንዲሸከም ዕቅዱ ስለነበር ነው፡ ጻሩ ን በኢየሱስ ላይ ያፈዙ የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች ይህን አልተገነዘቡም ነበር።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
