Site icon

መሢሑ እንደ ነቢይ 

የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ መሢሑ ንጉሥና ካህን እንደሚሆን ብቻ አያመለክትም። በብሉይ ኪዳን ውስጥ መሢሑ ነቢይም እንደሚሆን የሚያስረዱ ትንቢቶች ነበሩ። ኢየሱስ መሢሑ ንጉሥ እና መሢሑ ካህን ብቻ አይደለም። እርሱ መሢሐዊው ነቢይም ነበር። ነቢያት የእግዚአብሔርን መልእክት ለዓለም የሚገልጡ ሰዎች ነበሩ። ኢየሱስ ግን ከሁሉም ነቢያት በላይ ነው። እርሱም የእግዚአብሔርን መልእክት ለዓለም የገለጠ ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔርን ለዓለም የገለጠ እግዚአብሔር የቀባው ነቢይ ነበር። 

1. ብሉይ ኪዳን ታላቅ ነቢይ እንደሚመጣ ተስፋ ሰጥቶ ነበር። 

ጥያቄ፡– ዘዳግም 18፡14-19 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር እስራኤላውያን ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው? ለ) እግዚአብሔር ማንን እንደሚያስነሣ ተናገረ? ሐ) እስራኤላውያን ይህንን ሰው እንዴት ያዩታል? መ) ይህ ሰው ማንን ይመስላል? ሠ) ይህ ሰው ምን ያደርጋል? 

ጥያቄ፡- ዘዳግም 10 አንብቡ፡ ከሙሴ ሌላ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያነጋገረ አይ ማን ነው? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 2፡ 6፡14፤ 40 አንብቡ። ሕዝቡ ዮሐንስ መጥመቁን ማን ነው ብለው አሰቡ? 

ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 6፡14 አንብቡ። ሕዝቡ ኢየሱስ ማን መሆን አለበት ብለው አሰቡ? ለ) ዮሐንስ 6፡1-14 አንብቡ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ሕዝቡ ኢየሱስ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ነው ብለው እንዲያስቡ ያደረጋቸው ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 7፡40 አንብቡ። ሕዝቡ ኢየሱስ ማን ነው ብለው አሰቡ? ለ) ዮሐንስ 7፡7-38 አንብቡ። ሕዝቡ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ነው ብሎ እንዲያስብ ያደረገው የኢየሱስ ንግግር ምን ነበር? 

ጥያቄ፡- የሐዋ. 20፥22 አንብቡ፡ በኦሪት ዘዳግም ውስጥ እግዚአብሔር ነቢይ እንደሚልክ የተናገረውን ተስፋ ጴጥሮስ ፈጽሞታል ያለው ማንን ነበር? 

በዘዳግም ምዕራፍ 18 ላይ እስራኤላውያን ስለ ነቢያት ምን ማድረግ እንዳለባቸው መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር። ይኸውም ምዋርተኛችንና ሐሰተኛ ነቢያትን እንደ ከነዓናውያን እንዳይከተሉ ነግሮአቸዋል። እንደ እነዚህ ያሉትን ሐሰተኛ ነቢያት በመከተል ፈንታ፥ እውነተኛ ነቢያትን እንዲከተሉ እግዚአብሔር ፈልጎ ነበር። እግዚአብሔርም ከመካከላቸው እውነተኛ ነቢያትን አስነሥቱ ቃሉንም እንዲሰጣቸው ነገራቸው። እግዚአብሔር እውነተኛ ነቢይ በሚያስነሣላቸው ጊዜ ሕዝቡ ሙሰን ያዳምጥ እንደ ነበረ፥ ይህንንም ነቢይ አድምጦ መታዘዝ ይጠበቅበት ነበር። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን – ብዙ ነቢያትን እንደሚያነሣላቸው ብቻ አልነበረም የነገራቸው። በተጨማሪም የተለየ ተስፋ ለሕዝቡ ሰጥቷቸው ነበር። ይህ ተስፋም ልዩ የሆነ ነቢይ እንዲልክላቸው ነበር። ይህ ነቢይም እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው እንደ ሌሎች ነቢያት ያለ ነቢይ አይደለም። ይህ ነቢይ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት የሚያይ በመሆኑ በሙሰ ይመሰላል። እንደ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት የተነጋገረ ሌላ ነቢይ በእስራኤል ታሪክ ተነሥቶ አያውቅም። ይህ ነቢይ ስለ እግዚአብሔር በጣም በተለየ መንገድ ይናገራል፥ ሕዝቡም ለእርሱ እንዲታዘት መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል። 

በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር በዘዳግም ምዕራፍ 18 ላይ የተናገረውን ተስፋ እንደሚፈጽም በመተማመን እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ እንደጣ ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ይህ ነቢይ ማን እንደሚሆን የተለያዩ ንዛቤዎች ነበሩ። ሳምራውያንና አንዳንድ አይሁዶች በዘዳግም 18 ውስጥ ተስፋ የተሰጠበት ነቢይ ከመሢሑ ጋር አንድ ዓይነት ሰው እንደሚሆን ያምኑ ነበር፡ በአንጻሩ በዚህ በዘዳግም 18 ላይ ተስፋ የተሰጠበት ነቢይ ከመሢሑ የተለየ ሰው እንደ ነበረ አብዛኛዎቹ አይሁዶች ያምኑ ነበር (ዮሐንስ 1፡19 2)። መጥምቁ ዮሐንስ በተነሣ ጊዜ ገሚሶቹ ነቢዩ ሳይሆን አይቀርም አሉ። ነገር ን ዮሐንስ በዘዳግም 18 የተሰጠውን ተስፋ ፈጻሚ እንዳልሆነ በግልጽ ተናገረ። ስለዚህ ሕዝቡ የዚህ ተስፋ ፈጻሚ የሆነውን ነቢይ መጠባበቁን ቀጠለ። በዮሐንስ 6፡1-14 ላይ ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት ዳቦና በሁለት ዓሣ የመመገብ ታምራት አሳይቶ ነበር። ታዲያ በስፍራው የነበሩ ሰዎች ብዛቱ ያንን ያህል የሆነ ሕዝብ በመመገቡ ተደንቀው ነበር። በዚያን ወቅት ምናልባት ብዙዎቹ የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ መና መመገቡ ትዝ ብሏቸው ይሆናል። ከመገረማቸውም የተነሣ ኢየሱስ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ሳይሆን አይቀርም ብለው አሰቡ። በዮሐንስ 7፡7-38 ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑት የሕይወት ውኃ ምንጭ እንደሚሰጣቸው ተስፋ ገብቶላቸው ነበር። ምናልባትም ኢየሱስ ይህን ሲል ብዙዎቹን ትዝ ያላቸው ሙሴ ከዓለት ውኃ ማፍለቁ ሊሆን ይችላል። እንደገና በዚህም ነጥብ ብዙዎቹ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ እርሱ ሳይሆን አይቀርም ብለው በአድናቆት 

ማሰባቸው አልቀረም። 

2. ኢየሱስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተስፋ የሰጠበት ነቢይ ነው። 

ኢየሱስ በዘዳግም ምዕራፍ 18 ውስጥ ቀደም ሲል በእግዚአብሔር ተስፋ የተሰጠበት ነቢይ መሆኑ እርሱ ሞቶ ከተነሣ በኋላ በይፋ ተገለጠ፡ በሐዋ. ሥራ 3 ውስጥ ጴጥሮስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ተስፋ የተሰጠበት ነቢይ መሆኑን ይናገራል። ስለዚህ ጥንታውያን ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር መሢሕ፥ ንጉሥና ካህን፥ ነቢይም እንደ ነበረ ሊነዘቡ ቻሉ። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት የተገናኘና ደግሞም ስለ እግዚአብሔር በቀጥታ ሊናገር የቻለ የተለየ ነቢይ ነበር። 

የአዲስ ኪዳን የተቀረው ክፍል ኢየሱስ መሢሐዊ ነቢይ ስለ መሆኑ የተለየ ክብደት ሰጥቶ አይናገርም። በመልእክታትም ውስጥ ኢየሱስ መሢሐዊ– ነቢይ ተብሎ በፍጹም አልተጠራም። ምናልባት የዚህ ምክንያቱ መሢሑ በዘዳግም 18 ላይ ከተጠቀሰው ነቢይ ጋር አንድ ዓይነት ሰው መሆኑን ብዙ ሰዎች ስላላስተዋሉ ይሆናል። ወይም እነርሱ ያሰቡዋቸው ነቢያት እንደ እግዚአብሔር መሢሕ ጠቃሚ መስለው ስላልታዩዋቸው ሊሆንም ይችላል። ነቢያት ከእግዚአብሔር የሚላኩ መልእክተኞች እንጂ የእግዚአብሔር የራሱ መገለጫዎች አልነበሩም። ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ነቢይ ብለው የሚጠሩት ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያውቁ የነበሩት ጥቂት ነበር (ማቴዎስ 16፡14 ዮሐንስ 4፡19)። እርሱ ልዩ የእግዚአብሔር መልእክተኛ እንደሆነ እንጂ አንዱና ብቸኛው መሢሕ እንደነበረ አድርገው አይገምቱም ነበር። በዮሐንስ 9 ላይ የተጠቀሰውና ኢየሱስ የፈወሰው ዓይነ ስውር በመጀመሪያ ኢየሱስን እንደ ነቢይ አድርጎ ነበር ያሰበው። እንደ መለኮታዊ መሢሕ አድርጎ የተቀበለው በኋላ ነበር ( ዮሐንስ 9፡17፥ 35-38)። ምናልባት አዲስ ኪዳን ኢየሱስ መሢሐዊ ነቢይ ስለመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ አለመጻፉ ሰዎች ነቢያትን እንደ እግዚአብሔር መሢሕ አድርገው ስለማይመለከቱ ይሆናል። ነገር ግን በሐዋ. ሥራ 3፡20ና 22 እንደተጻፈው፥ ኢየሱስ በዘዳግም 18፡5-19 የተጻፈው ተስፋ ፍጻማ ነው። እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያየና እግዚአብሔርን በሚገባ ሊገልጽልን የሚችል እርሱ ነው። 

3. ኢየሱስ የእግዚአብሔር የራሱ ፍጹማዊ መገለጥ ነው። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡18 አንብቡ። እግዚአብሔርን የማወቂያው እጅግ መልካሙ መንገድ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 7፡46 አንብቡ። የቤተ መቅደስ ዘበኞች ስለ ኢየሱስ ቃላት ምን ተናገሩ? ለ) ማቴዎስ 7፡29፤ ማርቆስ 6፡2፤ ሉቃስ 4፡22፤ ዮሐንስ 7፡15 አንብቡ። የኢየሱስ ቃላት ለየት የሚሉት በምንድን ነው? በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የምታገኙዋቸውን መልሶች ሁሉ ጻፉ። 

ዮሐንስ ምዕራፍ 1 ኢየሱስን «ሎጎስ» ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ሲል ይገልጸዋል። ዮሐንስ 1፡18 እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያየው ማንም እንደሌለ ይነግረናል። ነገር ግን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሆኑ፥ የእግዚአብሔር ፍጹም መገለጫ ነው። እግዚአብሔርን ለማየት መንገዱ ኢየሱስን ማየት ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድና ራሱን እግዚአብሔርን ለማወቅ መንገዱ ኢየሱስን ማወቅ ነው። በዮሐንስ 7፡46 የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች ለካህናትና ለፈሪሳውያን እንደ እርሱ የሚናገር ጨርሶ ሰምተው እንደማያውቁ ገልጠውላቸዋል። ሌሎች ክፍሎች ደግሞ የኢየሱስ ቃላት ልዩ ሥልጣን፥ ጥበብና ጸጋ ስለነበሩአቸው ሰዎች ያደንቁት እንደነበሩ ያስረዱናል። ኢየሱስ ይናገራቸው የነበሩት ቃላት ሰብአውያን ነቢያት እንደሚናገሩት ያለ አልነበረም። ምክንያቱም ቃላቱ የእግዚአብሔር የራሱ መገለጫ የሆነው የኢየሱስ ቃላት ስለነበሩ ነው። 

ጥያቄ፡- ዕብራውያን 1፡1-3 አንብቡ። ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ይልቅ በልጦ የተገኘው በምን ምክንያት ነው? 

ዕብራውያን 1፡1-3 ያለው ክፍል ኢየሱስ ከሁሉ በላይ የሆነ የእግዚአብሔር መገለጫ እንደሆነ ይነግረናል። እርሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በነቢያት አማካይነት ከታዩት የእግዚአብሔር መገለጦች ሁሉ በላይ ነው። ምክንያቱም እነርሱ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ብቻ ነበሩ። እነርሱ የእግዚአብሔርን ቃል አዋጅ የሚናገሩ ነበሩ። ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር ክብር የተገለጠበት የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ስለዚህ «እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ነው» (ዕብራውያን 1፡3)። ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል ከመናገር ስላይ የሚፈጽመው አለው። ስለዚህ እርሱ ራሱ እግዚአብሔርን በቀጥታ የሚገልጥ ነው። በመሆኑም ከማንኛውም ነቢይ የላቀና ታላቅ ነው። የእግዚአብሔር ዋና መገለጫ የሆነ፥ ፍጹሙ ነቢይ ነው። እርሱ ራሱም እግዚአብሔር ነው። 41ኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለእኛ የሚገልጥልን ፍጹም መሢሐዊ– ነቢይ መሆኑ ጠቀሜታው ምንድን ነው? 

ኢየሱስ ክማንኛውም ነቢይ በበለጠ እግዚአብሔርንና ቃሉን የሚገልጥ ልዩ ነቢይ ስለሆነ፥ ተከታዮቹ የሆኑ ሁሉ ሊያደርጉት የሚገባ እጅግ ጠቃሚ የሆነው ነገር እርሱን ማወቅ ነው። ኢየሱስን የበለጠ ስናውቀው፥ እገዚአብሔርንና እርሱ ለእኛ ያለውን ፈቃድ ድህና አድርገን ለማወቅ እንችላለን፡፡

ጥያቄ፡– አንድ ወዳጃችሁ ወደ እናንተ ዘንድ መጥቶ እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ፈቃድ ለማወቅ እንደሚፈልግ ይነግራችሁ ይሆናል። ስለ ኢየሱስ መሢሐዊ- ነቢይነት በተማርነው ላይ በመመሥረት እንዴት ብላችሁ ትመልሱለታላችሁ?

ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሕይወታቸው ውስጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ። አዘውትረውም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሕልም፥ ወይም የራእይ ስጦታ ካላቸው ሰዎች ለማየት ይሻሉ። ነገር ግን ስለ እግዚአብሔርና እርሱ ለእኛ ስላለው ፈቃዱ ለማወቅ በምንፈልግበት ጊዜ እጅግ መልካሙ መንገድ የእግዚአብሔር መገለጫ የሆነውን ኢየሱስን ማወቅ ነው። ኢየሱስን እንዴት ልናውቀው እንችላለን? ማንኛውንም ሰው ለመተዋወቅ እንደምናደርገው ሁሉ ኢየሱስንም ቀርበን ማነጋገርና እርሱንም ማዳመጥ ነው። የኢየሱስንም ፈቃድ ልናውቅ የምንችለው የሌሎች ሰዎችን ፈቃድና ምኞት ለማወቅ በምንሞክርበት ጊዜ እንደምናደርገው ሁሉ ከእርሱ ጋር ቆይታ በማድረግ ነው። ቃሉን በምናጠናበት ጊዜ ኢየሱስን እናዳምጣለን፥ በቃሉም አማካይነት ለእኛ የሚነግረንን በጥሞና እናሰላስላለን። በራሱ ቃል ውስጥ ያለውን በጥሞና እንዲናገረን መንፈስ ቅዱስን እንፈቅድለታለን። ለእርሱ ችግራችንንና የልባችንንም ደስታ በመግለጽ ከእርሱ ጋር በጸሎት እንነጋገራለን። 

እግዚአብሔር ለእኛ ሕይወት ያለውን የእርሱን ፈቃድ የማወቂያው ተመራጭ መንገድ የእግዚአብሔር መሢሐዊ– ነቢይ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር ቆይታ ማድረግ ነው።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version