Site icon

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

በማስታረቅ ሥነ ሥርዓት (በሽምግልና) ላይ ተሳትፋችሁ ታውቃላችሁ? ምናልባትም በሁለት ሰዎች መካከል ያለ ግንኙነት ወደ ቀድሞው ስፍራዉ ተመልሶ እንዲታደስ ሸምግላችሁ ይሆናል። ወይም እናንተው ራሳችሁ ከሰዎች ጋር ተጣልታችሁ ይሆናል። ከዚህ የተነሣ በእርቅ ምክንያት በተለያዩ ሽማግሌዎች ፊት ቀርባችሁ ይሆናል። 

ጥያቄ፡– ስለተሳተፋችሁበት የእርቅ ሥነ ሥርዓት ዓይነት አስቡ። ሀ) ሁለት ጸበኞች ሰአስታራቂ ሽማግሌዎች ፊት ሲቀርቡ ከእርቁ በፊት አንዳቸው ስለሌላዉ ምን ዓይነት ስሜት ይኖራቸዋል? ለ) ከእርቅ ሥነ ሥርዓት በኋላስ እርስ በር አንዳቸው ለሌላው የሚኖራቸው ስሜት ምን ይሆናል? ሐ) በእርቅ ሥነ ሥርዓ ምን እንዲፈጸም ይፈለጋል? 

የማስታረቅ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ሁለት የተጣሉ ሰዎች ታርቀa የቀድሞ ሰላምና ወዳጅነት ወደ ቦታው እንዲመለስ ለማድረግ ነው። ሁለ፡ ጸበኞች መራር ጠላትነት ቢኖራቸውም፥ ከእርቁ ሥነ ሥርዓት በኋ በመካከላቸው ሰላም ይሰፍናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረ ከኃጢአታችን የተነሣ እኛ ራሳችንን የእግዚአብሔር ጠላቶች አድርገን ነበ (ሮሜ 5፡10፤ ቆላ. 1፡21፤ ያዕ. 4፡4)። ደኅንነትን ለማግኘት ዳግማ የእግዚአብሔር ወዳጆች መሆን ይገባናል። እንዲሁም ደኅንነትን ለማግኘ፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረን ሰላም መታደስ ይኖርበታል። ስለዚህ ደኅንነ ኃጢአተኞች በሆኑ ሰዎችና በቅዱሱ እግዚአብሔር መካከል ያለውን እር ማጠቃለል አለበት። 

ጥያቄ፡ ሮሜ 5፡1 አንብቡ። በኢየሱስ በእምነት ስለ ጸደቅን ምን እናገኛለን ለዚህ መልስ ለማግኘት አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊረዳችሁ ይችላል። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡10-11 አንብቡ። ሀ) ጠላቶቹ ሆነን ሳለን እግዚአብሔር ለእኛ ምን አደረገለን (ቁጥር 10)? ለ) በማን አማካይነት እርቅን አገኘን (ቁጥር 11)? 

ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡18 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር ምን አደረገልን (ቁጥር 18)? ለ) እግዚአብሔር ምን ሰጠን? 

ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡19 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ለዓለም ምን አደረገ? ለ) የዚህ የእግዚአብሔር ሥራ ውጤትስ ምንድን ነው? ሐ) ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር የጣለብን ኅላፊነት ወይም ሥራ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡20-21 አንብቡ። እኛ የእግዚአብሔር አምባሳደር እንደ መሆናችን መጠን መልእክታችን ምን መሆን አለበት? 7ኛ ጥያቄ፡- ቆላ. 1፡21-22 አንብቡ። ሀ) ከክፉ ባሕሪያችን የተነሣ ቀድሞ ምን ነበርን? ለ) እግዚአብሔር እንዴት አስታረቀን? ሐህ የዚህ እርቅስ ውጤት ምንድን ነው? 

በሮሜ 3፡21–4፡25 ድረስ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰው በእምነት እንደሚጸድቅ ይገልጻል። ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅ ውጤት ምንድን ነው? ጳውሎስ በምዕራፍ 5 የመጀመሪያ ውጤት አድርጎ ያቀረበው ሰላምን ነው። አሮጌው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም «ሰላምን እንያዝ» ይላል። አዲሱ ትርጉም ግን፥ «ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን» ነው የሚለው፥ ይህም የበለጠ የጳውሎስን አሳብ ያብራራዋል። ከሰዎች ኃጢአት የተነሣ፥ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ጠላትነትና ጦርነት ነበር። በሮሜ 5፡10 ውስጥ እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶች ነን ይላል። በቆላ. 1፡21 ደግሞ ከክፉ ሥራችን የተነሣ ከእግዚአብሔር የተለየን ጠላቶቹ እንደ ነበርን ይገልጻል። በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት በመሥራት ቅድስናውን ጥለናል። ነገር ግን ጳውሎስ በሮሜ 5 ውስጥ አሁን የእግዚአብሔር ወዳጆች መሆናችንን ይናገራል። ስለዚህ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን። እንዴት የእግዚአብሔር ወዳጆች ለመሆን በቃን? ይህ ሰላም እንዴትስ ሊታደስ ቻለ? በሮሜ 5፡10-11 እኛ ጠላቶቹ ሳለን እግዚአብሔር «እርቅ» በተባለው በክርስቶስ ሞት ሥራ አማካይነት፥ ሰላምን በራሱና በእኛ መካከል አመጣ ይላል። እርቅ ምንድን ነው? እርቅ ሁለት ጠላት የነበሩ ሰዎች ወደ ሰላምና ወዳጅነት ሲመጡ የሚፈጸመው ተግባር ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ጊዜ እርቅ፥ ለዚህ ክንዋኔ በሚዘጋጅ ሥነ ሥርዓት ሲከናወን እንመለከታለን። 

ጥያቄ፡- በ1ኛው ጥያቄ ውስጥ ስለ ገለጻችሁት የእርቅ ሥነ ሥርዓት አስቡ። ሀ) በዚያ የእርቅ ሥነ ሥርዓት ላይ ማን በማን ተቆጥቶ ነበር? ለ) በሁለቱም በኩል ስሕተት ነበር? ወይስ ስሕተቱ የአንዱ ሰው ነበር? ሐህ በሁለቱ መካከል ሰላም እንዲሆን፥ ሁለቱም ምን እንዲያደርጉ ሽማግሌዎቹ ወሰኑ? ሁለቱም አንድ ነገር እንዲያደርጉ ታዘዙ ወይስ አንዱ ሰው ብቻ አንዳች እንዲያደርግ በየኑበት? መ) እርቁ በሁለቱም መካከል ፍጹም ሰላም መመሥረት ቻለ? ወይስ የምትጠረጥሩት ድብቅ የሆነ ቂም በቀል ለእርስ በርስ አስከተለ? 

መልካም ምሳሌ የሚሆን የእርቅ ተግባር አንድ ጊዜ በራሴው ግቢ ውስጥ አጋጥሞኛል። የራሴ ግቢ ጠባቂዎች የነበሩ ሁለት ዘበኞች እርስ በርስ ተጣሉ። ጥሉ እንደ ተጀመረ ሦስተኛው ዘበኛ ጥሉን አበረደ። ነገር ግን ሲጣሉ በነበሩት በሁለቱ ዘበኞች መካከል የነበረው ቅራኔ ቀጥሏል። የእነዚህን ሰዎች ቅራኔ ለማስቀረትና ለማስታረቅ በርከት ያሉ የአካባቢአችን ሽማግሌዎች ተጠሩ። ሁሉም ቁጭ ብለው ስለተከሰተው ችግር ተወያዩ። ሽማግሌዎቹም ችግሩን ከሁለቱም አቅጣግ ከመረመሩ በኋላ፥ ሁለቱም ሰዎች ለተከሰተው ጥል በከፊል ኃላፊዎች መሆናቸውን ገለጹ። ሁለቱም ጸበኞች ጥሉን ለማብረድና ቁጣቸውንም ለማስታገስ አንድ ነገር እንዲናገሩ ወይም እንዲያደርጉ ታዘዙ። ሁለቱም ሰዎች ይህንን ውሳኔ በመቀበላቸው ምክንያት በመካከላቸው ሰላም ሰፈነ። ሁለቱም ታረቁ። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ አብረው እየተሳሳቁ ሲቀላለዱ ተመለከትኩ። ከእርቅ የተነሣ ጠላቶች የነበሩት ወዳጆች ሊሆኑ ቻሉ። 

በርሜ 5፡10 እና በቆላ. 1፡21 እንደተጻፈው በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህ ሁለት ዘበኞች ይጣሉ እንደ ነበረ ሁሉ፥ እኛም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለ ሠራን ጠላቶቹ ሆነን ነበር። በጥንቃቄ ልታስቡት የሚገባው ነገር፡ የእግዚአብሔር ጠላቶች በሆንን ጊዜ፥ ስሕተቱ ሁሉ በእኛ ላይ ተጣለ። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠራን እንጂ እግዚአብሔር እኛን በምንም ነገር አልበደለንም። ብዙ ጊዜ ሁለት ሰዎች ተጣልተው ወደ ሽምግልና መድረክ በሚመጡበት ጊዜ በሁለቱም ባላንጣዎች ላይ ስሕተት ይገኛል፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በአንዱ ሰው ላይ ትልቅ ስሕተት ሲገኝ፡ በሌላው ላይ ያነሰ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም አንዱ ሰው ሌላውን የበደለበት ሁኔታ ይኖራል። ከጠቀስናቸው ዘበኞች መካከል አንደኛው ጥል ጀምሮ ትል ስሕተት አድርጎአል። ሽማግሌዎቹ (አስታራቂዎቹ) ሌላውም ዘበኛ ቢሆ’ ትንሽ ስሕተት መፈጸሙን አልሸሸጉም። ስለዚህ በሁለቱም በኩል ሰላማ እንዲሰፍን፥ ሁለቱም አንድ ነገር መናገር ወይም ማድረግ ነበረባቸው። ነገ ግን እግዚአብሔር ምንም ዓይነት ስሕተት ወይም በደል በእኛ ላይ በፍጹ አድርጎ አያውቅም። ይልቅስ ስሕተትና፥ በደለን ሁሉ የፈጸምነው እኛ ራሳች ነን። ስለዚህ በስሕተታችንና በበደላችን ልንገሠጽ የሚገባን እኛ ነን። 

በሠራነው ስሕተትና በዴል የምንወቀስ ብንሆንም፥ በእኛና በእግዚአብሔ መካከል ሰላም እንዲሆን የጣረ ማን ነው? እግዚአብሔር ሥራውን ሁ ሠርቷል። በሮሜ 5፡10 የተጻፈው ቃል በእግዚአብሔር ልጅ አማካይነ ታርቀናል ይላል። በሮሜ 5፡11 ደግሞ፥ እርቅን ያገኘነው በጌታችን በኢየሱ ክርስቶስ አማካይነት ነው ይላል። በ2ኛ ቆሮ. 5፡18 እግዚአብሔር በክርስቶ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረቀን በማለት ይገልጻል። በ2ኛ ቆሮ. 5፡19 እግዚአብሔር ዓለምን በሞላ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረ ሲል ይናገራል። የዚህ ሁሉ ውጤት የሚያመለክተው እግዚአብሔ ኃጢአታችንን በእኛ ላይ አለመቁጠሩን ነው። በቆላ. 1፡22 በሥጋው ሰውነ በሞቱ እግዚአብሔር እኛን ከራሱ ጋር አስታረቀ ሲል ጽፎአል። ምን እንኳን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን በመሥራት በእግዚአብሔር ላ ስሕተትን ሁሉ ብንፈጽምና ራሳችንን ጠላቶቹ ብናደርግም፥ እግዚአብሐ ሰላምን ሊያመጣልንና ግንኙነታችንን ለማደስ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶ አማካይነት ሥራውን ሁሉ ሠርቷል። 

እዚህ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንመለከተው እርቅን የማምጣት ተግባርና ሥነ ሥርዓት እግዚአብሔር እርቅን ለማምጣት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሠራው ተግባር መልካም ምሳሌ ነው። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ልዩነቶችም አሉ። በአንዳንድ የእርቅ ሥነ ሥርዓት ላይ፥ ሁለቱም የተጣሉ ሰዎች የሆነ ስሕተት የተሳሳቱ በመሆናቸው፥ ሁለቱም ሰላም ለማምጣት የሚያደርጉት ተግባር አለ። ነገር ግን በእግዚአብሔር የማስታረቅ ተግባር፥ በኃጢአታችን ውስጥ ስሕተቶችን ሁሉ ፈጽመናል። ይህ ሆኖ ሳለ ሰላምን ሊያድስልን እግዚአብሔር በክርስቶስ ሞት አማካይነት ሁሉን ፈጽሞልናል። 

በእግዚአብሔር ማስታረቅና እንደተመለከትነው ባለ የሰብአዊ የማስታረቅ ሥነ ሥርዓት መካከል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ልዩነት አለ። የማስታረቅ ሥነ ሥርዓት ተደርጎ እንኳን ሲያበቃ፥ አንዳቸው በሌላው ላይ በልባቸው ውስጥ ቁጣና መራርነት ያለው ስሜት ሊኖር ይችላል። በሚታረቁበት ጊዜ ሁለቱ ሰዎች እርስ በርስ ይቅር የተባባሉና ግንኙነታቸውም በሙሉ እንደ ታደሰ ሊያስመስሉ ይችላሉ። በውስጣቸው ግን አንዱ ለሌላው ጠላቱ እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል። በእግዚአብሔር ዘንድ በሚደረገው እርቅ መሠረት ግን እርሱ በሚያስታርቃቸው ላይ የቁጡነትም ሆነ የመራርነት ሰማት አያድርበትም። እግዚአብሔር ከራሱ ጋር ካስታረቀን በኋላ፥ ፈጽሞ ይቅር ይለናል፥ ኃጢአታችንንም ጨርሶ አያስበውም። በቆላ. 1፡22፣ «ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፥ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።» ይላል፡፡ ከእግዚአብሔር የማስታረቅ ሥራ የተነሣ እግዚአብሔር ፍጹም ነውር የሌለብንና ቅዱሳን አድርጎ ይቆጥረናል። ምንም ዓይነት ነውር ሊኖርብን አይችልም። በደል ሠራችሁ ብሎ የሚከስሰንም ሊኖር አይችልም። በእግዚአብሔር የሚመሠረተው እርቅ፥ የውጪአዊውን ግንኙነት ከማደስ የበለጠ ነው። የእግዚአብሔር እርቅ እኛ ጨርሶ ጠላቶቹ እንዳልነበርን አድርጎ ያቀርበናል። የእግዚአብሔር እርቅ እኛ ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ወዳጆች እንደ ነበርን ያህል ያስቆጥረናል። 

ሆኖም በመስቀል ላይ የኢየሱስ የማስታረቅ ሥራ፥ በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ሰላምን አምጥቶ፥ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት ወደ ቀድሞው ስፍራ መመለስ ብቻ አይደለም። የኢየሱስ የማስታረቅ ሥራ ሌሎች አስደናቂ በረከቶችም አሉት። 

ጥያቄ፡– ኤፌ 2፡14-16 አንብቡ። እግዚአብሔር ሰማስታረቅ አማካይነት ላአይሁዶችና ለአሕዛብ ምን አደረገ?

እግዚአብሔር በመስቀል ላይ ራሱን ከሰዎች ጋር ባስታረቀ ጊዜ፥ ሁለት ሌሎች የማስታረቅ ተግባራትንም ፈጽሞ ነበር። በመጀመሪያ፥ እግዚአብሔር አይሁድንና አሕዛብን በማስታረቅ ወደ አንድ አካል አምጥቶአቸዋል። በኤፌ. 2፡11-22 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ፥ «ከእስራኤል ወገንነት ርቃችሁ ለኪዳኑም ተስፋ ባዕዳን ሆናችሁ» ይላል። በዚህም አይሁዶችና አሕዛብ ተለይተው ነበር (በኤፌሶን 2፡12) ቀጥሎ፥ በአይሁዶችና በአሕዛብ መካከል ሰላምን አምጥቷል ይላል (ኤፌ. 2፡14)። እነዚህን እርስ በርስ ይጠላሉ የነበሩና ጠላቶችም የነበሩትን ሁለት ብሔረሰቦች እግዚአብሔር አስታረቃቸው። እንደዚሁም ባላንጣነታቸውን ከመካከላቸው አስወግዶ፥ በማስታረቅ ወደ አንድ አካል አመጣቸው (ኤፌ. 2፡16)። 

በአይሁዶችና ስአሕዛብ እርቅ ውስጥ ለሁላችንም የሚሆን የበለጸገ በረከት አለ። በመጀመሪያ፣ በኢየሱስ ያመኑ አሕዛብ በሙሉ ለአይሁዶች የተሰጠው ተስፋ ተቋዳሾች ይሆናሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ አብዛኛዎቹ ሰዎች ብሔረሰባቸው ይሁዲ አይደለም። አብዛኛዎቹ አሕዛብ ናቸው። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ዛሬ አሕዛባዊ አማኞች ከአይሁድ አማኞች ጋር የእግዚአብሔር ተስፋ ተካፋዮች ናቸው (ኤፌ. 3፡6) ሁለተኛ፥ በአይሁዳውያንና በአሕዛብ መካከል የሆነው፥ ማለትም በእነዚህ እርስ በርስ ጠላት በነበሩ ብሔረሰቦች ዘንድ የሆነው በሌሎችም ብሔረሰቦች ዘንድ ሊሆን የሚችል ክስተት ነው። እግዚአብሔር አይሁዶችንም አሕዛብንም ወደ አንድ የክርስቶስ አካል በማምጣት፥ በመካከላቸው ሰላምን መሠረተ። ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምኑበት ጊዜ የአንድ አካል አባል ይሆናሉ። የእግዚአብሔር ጠላት ለነበሩ ሰላምን በማምጣት ወዳጆች እንደሆኑ ያደርጋል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ለእናንተ ብሔረሰብ ጠላቶች ሆነው የቆዩ ዝርያዎች፥ በሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ወይም የብሔረሰብ ቡድኖች አሉ? ለ) ልትወዷቸው የሚያስቸግራችሁ ሌሎች የሃይማኖት ቡድኖች፥ ዝርያዎች ወይም ብሔረሰቦች አሉ? ሐ) በኤፌሶን 2፡14-16 አሳብ አኳያ ሲታይ፥ እነዚህ ሰዎች ክርስቶስን በሚያምኑበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት እንድትይዟቸው ይፈልጋል? 

በኤፈሶን 2፡14-16 ውስጥ እግዚአብሔር ከሌላ ወገን የመጡት አማኞችም በክርስቶስ የእኛው ሰዎች፥ የእኛው ወገኖች፥ የእኛው ብሔረሰቦችና የእኛው ጎሣዎች ናቸው ይላል። ስለዚህ በክርስቶስ ካሉ ከሌሎች አማኞች ጋር ያለን ኅብረት ከፈለገው ጎሣ ወይም ብሔረሰብ ይሁን፥ ከራሳችን ጎሳና ብሔረሰብ ይልቅ ልናቀርባቸውና ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው ልናደርግ ይገባል። በተመሳሳይ መንገድ፥ ሌሎች በሌላ እምነት ውስጥ የነበሩ ሰዎች፥ በክርስቶስ አምነው እርሱን እንደ መድኃኒታቸው ከተቀበሉ በኋላ፥ ከራሳችን ብሔረሰቦች ጋር ከምናደርገው ኅብረትና ግንኙነት የበለጠ ከእነርሱ ጋር ኅብረታችንንና ግንኙነታችንን ማጠናከር ይገባናል። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ጋር አስታርቆናል፤ በተለይም እርስ በርስ ጠላት የነበሩትን ብሔረሰቦችና ሌሎችንም በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ አስታርቆ ወደ ራሱ አቅርቦአቸዋል። በመሆኑም በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ፥ እርሱ ያመጣላቸውን ሰላምና አንድነት ሊለማመዱትና በሥራም ላይ ሊያውሉት ይገባል። 

ጥያቄ፡- ቆላ 19-20 አንብቡ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ደም አማካይነት ለመላው ዓለም ምን አደረገ? 

እግዚአብሔር ሰዎችን ከራሱ ጋር በመስቀል ላይ ባስታረቀ ጊዜ፡ ያደረገው ሁለተኛው የማስታረቅ ተግባር፥ ፍጥረቱን ከራሱ ጋር የማስታረቅ ተግባር ነበር። በአሥራ አንደኛው ትምህርታችን ላይ እንደ ተመለከትነው፥ የሰው ልጅ ኃጢአት በፍጥረት ሁሉ ላይ መርገምን እንዳመጣ ነበር (ሮሜ 8፡20-22)፡፡ ከሰዎች ኃጢአት የተነሣ ፍጥረት ሁሉ የሚሞትና የሚበሰብስ፥ በጥቃትና በአየር ብክለትም የሚሠቃይ ሆነ። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ባስታረቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ራሱን ከፍጥረቱ ጋር እንዲያስታርቅ መሠረቱን አመቻቸ። በዚህም በፍጥረት ውስጥ ያለውን የሰላምን፥ የሕይወትንና የምሉዕነትን መመሪያ ዳግም አደሰ። አዎ፥ እንደ እውነቱ ከሆነ፥ ፍጥረት ሁሉ ክርስቶስ ተመልሶ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊታረቁ አይችሉም። ነገር ግን ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመው የማስታረቅ ተግባር፥ የተሐድሶው መሠረት ተጥሎአል። 

ጥያቄ፦ አማኞች የእግዚአብሔርን ፍጥረት በምን አኳኋን ሊንከባከቡት ይገባል? 

በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁ እንደ መሆናቸው መጠን፥ ለእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ያቀደውን ሰላምን፥ ሕይወትንና ምሉዕነትን ለማስፈን መጣር አለባቸው። የምድሪቱን የተፈጥሮ ሀብት ራስዋን ምድርን በማያጠፋት ሁኔታ ልንጠቀምበት ይገባናል። አየርን፥ ውኃንና አፈርን መበከል የለብንም። እኛ ራሳችን የምናመጣውን ብክለት የግድ ማጽዳት አለብን። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፍጥረት እግዚአብሔር ራሱ በሚፈልገው መንገድ ልንንከባከብ ይገባናል።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version