በትናንትናው ዕለት ስለ ዳግም መወለድ ማጥናት ጀምረናል። ስለ ዳግም መወለድም እንደ ቁልፍ የሆነ ጥቅስ ያጠናን ሲሆን፥ እርሱም ዮሐ 3፡1-8 ነበር። በዚህ ጥቅስ ላይም ዳግም መወለድ ሊባል የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ሊሰጠን የሚፈጽመው ሉዓላዊ የማንጻት ተግባር እንደሆነ ተምረናል። ዛሬ ደግሞ በተቀሩት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ ጳም መወለድ ወይም ልደት የሚነግሩንን ቁልፍ የሆኑ ጥቅሶችን በመቃኘት ጥናታችንን እንቀጥላለን።
ጥያቄ፡- ዮሐ 1፡12-13 አንብብ። ሀ) የእግዚአብሔር ልጅነትን መብት ያገኙ እነማን ነበሩ? ለ) የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑት ያልተወለዱት ከምንና ከምን ነው? ሐ) የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑት ከምን ተወለዱ?
ጥያቄ፡- ዮሐ 3፡14-16 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ በሙሴ የተሰቀለውን የነሐስ እባብ ምንን ለማመልከት ተጠቀመበት? ለ) በልጁ የሚያምን ምንን ይቀበላል?
ጥያቄ፡- ዮሐ. 5፡24 አንብብ። የኢየሱስን ቃል የሚሰማ የላከውንም የሚያምን ምንን ያገኛል?
ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥ. 1፡3 አንብብ። ሀ) አዲሱ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል? ለ) የአዲስ ልደት መጨረሻ ውጤት ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥ. 1፡23 አንብብ። አዲስ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል?
ጥያቄ፡- ያዕ. 1፡18 አንብብ። ሀ) አዲስ ልደት በምን አማካይነት ይገኛል? ለህ የአዲስ ልደት መጨረሻ ውጤት ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 5፡1 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ስለሚያምን ለው የተረጋገጠለት ምንድን ነው? ለ) 1ኛ ዮሐ 2፡29፤ 3፡9፤ 4፡7፤ 5፡4፥ 18 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከእግዚአብሔር ስለተወለዱት የተነገረውን እውነታ ሁሉ ጻፍ።
ጥያቄ፡– ኤፌ. 2፡4-5 እና ቆላ. 2፡13 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ከመግባቱ በፊት የነበረን ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ለ) እግዚአብሔር ጣልቃ በገባ ጊዜ ምን አደረገልን?
ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮ. 5፡17 አንብብ። «በክርስቶስ ለሆኑት» የተረጋገጠላቸው ነገር ምንድን ነው?
ጥያቄ ቲቶ 3፡3-8 አንብብ። ሀ) እንዴት ያለን ሰዎች ነበርን? (ቈ 3) ለ) እግዚአብሔር እንዲህ ካለው ሕይወት መቼ አዳነን? ሐህ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው ሕይወት እንዴት አድርጎ አዳነን? (ቁ 5) መ) እግዚአብሔር የሰጠን ዳግም የመወለድ ውጤቶች ምንድን ናቸው? (ቁ. 7-8)
1. ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ ነው።
በመጀመሪያ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ዳግም መወለድ የምናገኘው ትምህርት ላም መወለድ ማለት የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ተግባር መሆኑን የሚያስረዳ ነው። ትናንትና በዮሐ 3፡8 ላይ እንደተመለከትነው፣ መንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደትን ለእኛ በመስጠት ተግባሩ በነፋስ እንደሚመሰል ነው። ሰዎች ነፋስን ሊቆጣጠሩም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ሊገነዘቡት አይችሉም፤ እንዳሻው ወዳሻው ይነፍሳል። መንፈስ ቅዱስም እኛን በማይገባን ሁኔታ በፈቀደው መንገድ ሥራውን ይፈጽማል። በዮሐ 1፡13 ላይ የተጻፈው ቃል የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን የሰው ልጅ ከመሆን ሁኔታ ጋር ያነጻጽረዋል። ልጆች በወላጆቻቸው ውሳኔና ተግባር ከወላጆቻቸው ይወለዳሉ። ነገር ግን እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ ውሳኔና ተግባር ከመንፈስ እንወለዳለን።
2. ዳግም መወለድ ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ይገኛል።
ሁለተኛው ስለ ዳግም መወለድ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ዳግም መወለድ ወይም ልደት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እንደሚገኝ ነው። በዮሐንስ 3 ውስጥ ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር ውይይቱን በቀጠለ ጊዜ፣ የመስቀል ሥራውን ሙለ በምድረ በዳ ከሰቀለው የነሐስ እባብ ጋር በማመሳሰል ተናግሯል። በዘዳግም 21 ውስጥ እስራኤላውያን ስለ አጉረመረሙ እግዚአብሔር መርዘኛ እባቦች እንዲነድፉአቸው ወደ ሰፈራቸው ሰደደባቸው። ይህን ጊዜ ሕዝቡም ወደ ሙሴ ፊት ቀርበው ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይላቸው ለመኑት። ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴ የነሐስ እባብ ሠርቶ በሕዝቡ መኖሪያ መሃከል በዓላማ ላይ እንዲሰቅለው አዘዘው። ከዚያም እባብ የነከሰው ሁሉ ወደ ነሐሱ እባብ በተመለከተ ጊዜ ይድናል። በዚህም እግዚአብሔር ቸርነቱን በእምነት ለተቀበሉት ሕዝቡ አዲስ ሥጋዊ ሕይወትን ሰጣቸው። ኢየሱስም ለኒቆዲሞስ ሲያስረዳው፥ ሙሴ ሕዝቡ ሁሉ ይመለከተው ዘንድ የነሐሱን እባብ ከፍ አድርጎ በዓላማ ላይ እንደ ሰቀለው እንዲሁ፥ ሁሉም ይመለከቱት ዘንድ የሰው ልጅ ከፍ ብሎ ተሰቅሉ ይታያል አለው። ይህን ሲልም በኋላ ራሱ በመስቀል ላይ እንደሚሰቀል ሲገልጽለት ነበር። በእግዚአብሔር ያመኑ እስራኤላውያን በነሐስ እባብ አማካኝነት ሥጋዊ ፈውስን እንዳገኙ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ስኢየሱስ የመስቀል ሞት አማካይነት የሰጠውን የኃጢአት ይቅርታ አምነው ለሚቀበሉ ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወትን ይሰጣቸዋል። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን የሚሰጠው በመስቀል ላይ በተፈጸመው በኢየሱስ ሞት አማካይነት ነው። እንደዚሁም 1ኛ ጴጥ. 1፡3 እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን በኢየሱስ ትንሣኤ በኩል እንደሚሰጥ አክሎ ይናገራል። በ8ኛውና በ14ኛው ትምህርታችን ላይ እንደተመለከትነው፣ የክር ስቶስ ሞትና ትንሣኤ ደኀንነትን፥ እርቅን፣ የእግዚአብሔርን ከጽድቃዊ ቁጣው መመለስን እና በኃጢአትና በሰይጣን ላይ ድልን ይሰጠናል። እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ መሥዋዕት አድርጎ ስላቀረበ፣ እርሱ በፈጸመው ለሚያምኑት ሁሉ አዲስ ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
3. ዳግም ልደት በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ይገኛል።
ዳግም መወለድ በክርስቶስ የመስቀል ሞት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ ሉዓላዊ ሥራ አማካይነትም ይፈጸማል። ነገር ግን እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ዳግም መወለድን ለማምጣት በተለያዩ መንገዶች ይጠቀማል። የዳግም ልደት ከፍተኛውና ዓይነተኛው መንገድ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 1ኛ ጴጥ. 1፡23 ካማይጠፋው ከእግዚአብሔር ቃል ጻም መወለጻችንን ይነግረናል። ያዕ. 1፡18 ደግሞ እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ አዲስ ሕይወት ለማምጣት በመጀመሪያ የሚጠቀመው በቃሉ ነው።
ጥያቄ፡– ዳግም መወለድ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራና በቃሉ አማካይነት የሚመጣ ከሆነ፥ ቤተሰቦቻችንና የምናውቃቸውን ሁሉ ወደ እዲስ ልደት በማምጣት ረገድ የእኛ ኃላፊነት ምንድን ነው?
አዲስ ልደት ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ የሚገኝ በመሆኑ፣ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ ለማድረግ በማግባባትና በስሜታዊ አቀራረብ ብቻ ልባቸውን ለማምጣት እንደማንችል ማወቅ ይኖርብናል። ሰዎችን ለማሳመን ምንም ያህል ብንማፀን፥ በልመናና በመለማመጥ አሳምነን ወደ ክርስቶስ ልናመጣቸው አንችልም። እንደዚሁም ስለ መንግሥተ ሰማይ ድንቅነት፥ በአንጻሩም ስለ ገሃነም አስፈሪነት ምንም ያህል ብንነግራቸው፣ በራሳችን ኃይልና እውቀት ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ማድረግ አንችልም። በልባቸው ውስጥ የሚሠራ የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ አሳምኖ ወደ አዲስ ሕይወት ሊያመጣቸው ይችላል። የእኛ ኃላፊነት ሊሆን የሚችለው የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥራ በልባቸው ውስጥ ፍሬ ያፈራ ዘንድ መጸለይ ነው። እንዲሁም እግዚአብሔር ኃጢአታቸው ተሰምቷቸው ንስሐ እንዲገቡ እንዲያደርግ መጸለይ ይገባናል። በተጨማሪም እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንዲስባቸው እርሱን መለመን አለብን። እግዚአብሔር የሚሰጠውን ዘላለማዊ ሕይወት በጉጉት የሚሹ እንደሚያደርጋቸውና በተጨማሪም እግዚአብሔር ወደ እምነት ያመጣቸው ዘንድ መጸለይ ይኖርብናል።
ሆኖም፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ከማያምኑ ወዳጆቻችንና ጎረቤቶቻችን ጋር የመወያየትና የመካፈል ኃላፊነት አለብን። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ራሉ የሚያመጣበት መንገድ ቃሉ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንደሚሠራ በየአጋጣሚው ሁሉ ለሰዎች መመስከር አለብን። እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተማርነውን አሳልፈን ለሌሎች በማሰማት የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ማድረግ ይጠበቅብናል። ሰዎች እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን አዲስ ሕይወት እንዴት ባለ ሁኔታ ሊያገኙ እንደሚችሉ በመግለጽ የእግዚአብሔር ቃል እንዲደርሳቸው ለማድረግ ምን ጊዜም ዝግጁዎች ልንሆን ይገባናል። አንዳንድ ጊዜ ይህን የታዘዝነውን ኃላፊነት ለመወጣት በምናደርገው ጥረት ላይ ለምእመናን ስብከትን እንደምናሰማው ዓይነት በዛ ላሉ ሰዎች ቃሉን እንድናካፍል እግዚአብሔር ዕድል ይሰጠናል። በሌላ ጊዜ ደግሞ ከግለሰቦች ጋር በግላቸው ቃሉን አብረን እንድንካፈል ዕድል ያዘጋጅልናል። በእነዚህ ሁሉ አጋጣሚዎች ላይ አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር እግዚአብሔር ወደ እነዚህ ሰዎች ለመቅረቢያና ወደ አዲስ ሕይወት እንዲመጡ ለማድረግ የሚገለገልበት መሣሪያ ቃሉ መሆኑን ነው። ከሁላችን የሚጠበቀው ኃላፊነት ታዲያ ቃሉን ከሰዎች ጋር ለመካፈል ዝግጁ መሆን ነው።
ጥያቄ፡- አንድ ጊዜ አማኝ ስላልሆኑ ወዳጆቻችሁና ጎረቤቶቻችሁ አስቡ። ከዚያም የሦስቱን ስም ጻፉ። በሦስቱም ስሞች ጎን በየአጋጣሚው አብራችኋቸው ልትወያዩ የምትችሉዋቸውን፥ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣቸውን እምነት ሊሰጧቸው የሚችሉትን አንዳንድ ነገሮች ከእግዚአብሔር ቃል ጻፉ።
4. ዳግም መወለድ በእምነት ይገኛል።
አዲስ ኪዳን ስለ ዳግም መወለድ በግልጽ የሚሰጠው አራተኛው ትምህርት በእምነት እንደሚገኝ ነው። ዮሐ 1፡12 ኢየሱስን ተቀብለው በስሙ የሚያምኑ ብቻ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚሆኑ ይናገራል። ኢየሱስ የነሐሱን እባብ ምሳሌ አድርጎ በተናገረ ጊዜ (ዮሐ 3፡14-15)። «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ» እግዚአብሔር ልጁን ከፍ ያደርገዋል ብሏል። ኢየሱስ ለኃጢአት ዕዳችን የከፈለው ሞቱና ትንሣኤው ብቁ መሆኑን ብናምን የዘላለምን ሕይወት እናገኛለን (እንዲሁም ዮሐ 3፡16 ተመልከት)። ዮሐ 5፡24 እንደሚለው ኢየሱስን የሚሰማና በላከውም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞት ወደ ሕይወት ይሻገራል፡፡ በ1ኛ ዮሐ 5፡1 ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ከእግዚአብሔር ተወልዷል። መንፈስ ቅዱስ በሉዓላዊነት ሥልጣኑ በግለሰቡ ሕይወት ውስጥ በሚያደርገው መልካም ተግባር በተለየ ሁኔታ የዳግም መወለድን ሥራ ይሠራል። ነገር ግን እርሱ በሉዓላዊነት መንፈስ ቅዱስ ለእነዚህ ወንዶችና ሴቶች አዲስ ሕይወትን ለመስጠት በእነርሱ ውስጥ የሚሠራው እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ሲያደርጉና ለደኅንነታቸውም በእርሱ ላይ ሲደገፉ ብቻ ነው፡፡
5. ዳግም መወለድ «ዘላለማዊ ሕይወትን» ይሰጣል፡፡
የ«ዳግም መወለድ» መሠረታዊ ትርጉም እግዚአብሔር መንፈሳዊ ሕይወት የሆነውን አዲስ ሕይወትን ይሰጣል ማለት ነው። ዮሐ 5፡24፥ እንዲሁም ኤፌ. 2፡1-3 እና ቆላ. 2፡13 ሰዎች ሁሉ በኃጢአት በመወለዳቸውና ከዚያም በላይ ብዙ የኃጢአት ተግባራትን ስለሚፈጽሙ በመንፈስ ሙታን እንደሆኑ በግልጽ አብራርተው ይናገራሉ። እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠረው፥ እርሱን እንዲያውቁት፥ በእርሱ ደስ እንዲሰኙና ፍቅር የተሞላ ግንኙነት እንዲኖራቸው ነው። ነገር ግን በመንፈስ ሙታን ስለሆንን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም። ዳግም መወለድ ማለት ባለንበት ጊዜና ቦታ ሕያው የሚያደርገን እግዚአብሔር በቅጽበት የሚፈጽመው ተግባር ነው (ኤፌ. 2፡4-5፤ ቆላ. 2፡13)። ዳግም መወለድ እግዚአብሔርን እንድናውቅና በእርሱ እንድንደሰት፥ በተቀበልነውም እዲለ መንፈሳዊ ሕይወት ለዘላለም እንድንኖር ያደርገናል። በዮሐ 3፡15 ውስጥ እንደተጻፈው «የዘላለም ሕይወት» ማለት «ለሚቀጥሉት ዘመናት የሚኖር ሕይወት» ማለት ነው። በክርስቶስ በማመናቸው «የዘላለምን ሕይወት» የሚያገኙ በሚመጣው ዘመን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሙላት የመግባት ዋስትና አላቸው። የዘላለም ሕይወት «የመንግሥት ሕይወት» ነው። 1ኛ ጴጥ. 1፡3 እግዚአብሔር በአዲስ ልደት «ሕያው የሆነውን ተስፋ» ሰጠን ይላል። በሚቀጥሉት ቁጥሮች አያይዞ ሲናገር፥ ይህ ሕያው የሆነ ተስፋ የማይበላሽና የማያረጅ ርስት ሆኖ በሰማይ እንደሚቆየን ይገልጻል። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን በሚሰጠን ጊዜ፣ በሰማይ ያለውን የምንወርሰውን መንግሥት እንደምናገኝ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። በዚህ አዲስ ሕይወት መደሰትን ገና ወደ ሰማይ እስከምንሄድበት ጊዜ ልናቆየው አይገባም። ኢየሱስም ወደ ምድር የመጣው ሰዎች በዚህ ሕይወት በመደሰት መኖር እንዲችሉ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ነው (ዮሐ 10፡10)። እግዚአብሔር ይህን አዲስ ሕይወት ስለ ሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ጋርና ከሌሎች ሰዎችም ጋር ባለን ግንኙነት የሚመጣውን የእግዚአብሔርን መንግሥት በረከቶች አሁንና እዚህ መጀመር እንችላለን።
ጥያቄ፡- ሀ) ከእግዚአብሔር ዘንድ ባገኛችሁት አዲስ ሕይወት አሁን እየተጠቀማችሁበት ያላችሁት በብዛት ነው? በጥቂቱ ነው? ወይንስ ጨርሶ አልተጠቀማችሁበትም? ላ) እግዚአብሔር በሰጣችሁ አዲስ ሕይወት እሁን እዚህ በበለጠ ለመጠቀም ምን ማድረግ ይኖርባችኋል?
አማኛች ጊዜአቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማሳለፍ ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር፥ ከእርሱ ያገኙትን አዲስ ሕይወት በሚገባ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ጊዜያችንን ከእርሱ ጋር በማሳለፍ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት እንደምናዳብር ሁሉ ከእግዚአብሔርም ጋር ያለንን ግንኙነት ልናዳብር እንችላለን። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር በየዕለቱ የምንነጋገርበትን (በጸሎት) እና እንደዚሁም ከእርሱ የምናደምጥበትን (ማለትም ቃሉን በጥሞና አንብበን በማሰላሰል ከዚያም መንፈሱ ለልባችን እንዲናገር መፍቀድ) ጊዜ ለይተን ማስቀመጥ ይገባናል። ከዚህም በስተቀር በእያንዳንዱ ቀን ስምንፈጽመው ተግባር መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የምናሳልፈው ጊዜ ሊኖር ያስፈልጋል። በዚህም ጊዜ የእያንዳንዱን ቀን ተግባርና ስለሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ከእግዚአብሔር ጋር መወያየት እንችላለን። በተሰጠን ቀን የእግዚአብሔርን ቃል ልናሰላስል እንችላለን። ስለ እግዚአብሔር በምናስብበት በምናነጋግረውም ጊዜ፥ ገና በምድር ላይ እያለን በአዲሱ ሕይወታችን በመኖር መደሰትን እንለማመዳለን።
በአዲሱ ሕይወታችን በመኖር መደሰት የምንጀምርበት ሌላም መንገድ አለ፦
6. ዳግም መወለድ አዲስ ሕይወትን የሚኖሩ አዲስ ሰዎችን ያስገኛል።
እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን በሚሰጠን ጊዜ፣ አዲስ ሕይወትን እንድንኖር ችሎታና ፍላጎት ያለን ሰዎች ያደርገናል። ይህን አዲስ ሕይወት መኖር ስንጀምር፤ በእግዚአብሔር በራሱና በሚሰጠንም ሕይወት በበለጠ መርካት እንጀምራለን። በ2ኛ ቆሮ. 5፡17 ላይ ማንም ከክርስቶስ ጋር ሲተባበር አዲስ ፍጥረት ነው ይላል። ያ ሰው የነበረበት የቀድሞ ሁኔታ ቀርቷል ማለት ነው። ስለሆነም ይህ ሰው አሁን አዲስ ሕይወት ስላገኘ በአዲስ ሕይወት ውስጥ ሊኖር ይችላል።
እግዚአብሔር በሰጠን ሕይወት አማካይነት፥ ምን ዓይነት አዲስ ሕይወትን መኖር እንችላለን? ከእግዚአብሔር የተወለደ ሰው እንዴት ያለ ሕይወትን መኖር እንዳለበት 1ኛ ዮሐንስ ብዙ ምሳሌዎችን ያቀርባል። ከእግዚአብሔር የተወለደ ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል (1ኛ ዮሐ. 2፡29)። ከእግዚአብሔር የሆነ ወይም የተወለደ ኃጢአትን በማድረግ አይቀጥልም (1ኛ ዮሐ 3፡9፤ 5፡18)፡ ዓለምን ያሸንፋል እንጂ ዓለም አያሸንፈውም (1ኛ ዮሐ 5፡4)። እነዚህ ጥቅሶች ላም የተወለዱ ሰዎች ኃጢአት በፍጹም አይሠሩም፥ በፈተናም አይወድቁም ማለታቸው አይደለም። በክፍል 12 ትምህርታችን በ1ኛ ዮሐ 1፡8-10 ድረስ በተመለከትነው ጥናት ከኃጢአት ጨርሶ ነፃ የሆነ አማኝ እንደሌለ ተገንዝበናል፡፡ ነገር ግን ኃጢአት በአማኞች ሕይወት ላይ የነበረው የመቆጣጠር ኃይል ቀርቷል። አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፈተናን በመቋቋም፡ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ቀንኙነት እርሱን በመምሰል ሊያድግ ይችላል። በእውነት ከእግዚአብሔር የተወለዱ ሰዎች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ ይሰማቸዋል። በየጊዜው ወደ ኃጢአት ተግባር እያሽቆለሉ በመስጠም አይቀጥሉም። በዚህ ፈንታ፣ በሕይወታቸው በኃጢአትና በፈተና ላይ አሸናፊነትን እየተቀዳጁ ይሄዳሉ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሰው ሌሎች በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎችን ያፈቅራል፥ ከእነርሱ ጋር ጊዜውን ማሳለፍም ደስ ይለዋል (1ኛ ዮሐ 4፡7)። በመጨረሻም፣ 1ኛ ዮሐ 5፡18 ከእግዚአብሔር የተወለደውን ሰው «ሰይጣን አይነካውም» ይላል። እግዚአብሔር በአማኞች ሕይወት ላይ ሰይጣን ስደትን፥ ጉዳትን፥ እንዲሁም በሽታን እንዲያመጣ ከቶ አይፈቅድም ማለት አለመሆኑን ማስተዋል ይገባል። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ሰይጣን በአማኞች ሕይወት ላይ ችግር እንዲያመጣ እንደሚፈቅድለት ከኢዮብ መጽሐፍና ከጳውሎስ ሕይወት (2ኛ ቆሮ. 12፡7-9) እንመለከታለን። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰይጣን በአማኞች ሕይወት ላይ ችግር እንዲያመጣ የሚያደርግበት ሁልጊዜ በጎ ዓላማ አለው። 1ኛ ዮሐ 5፡18 ውስጥ በይዘቱ የሚናገረው እግዚአብሔር አማኞች ኃጢአትን መቋቋም እስከማይችሉ ድረስ በሕይወታቸው ላይ ሰይጣን ፈተና እንዲያመጣባቸው እንደማይፈቅድለት ነው። አማኞች ከእግዚአብሔር የተወለዱ ስለሆኑና ኢየሱስ ክርስቶስም ስለሚጠብቃቸው፥ የሰይጣንን ፈተና ተቋቁመው በአሸናፊነት እንዲወጡ ብርታትን ይሰጣቸዋል። አማኞች ከእግዚአብሔር የተወለዱ በመሆናቸው ሰይጣን የሚያመጣባቸው ውጊያም መንፈሳዊ ጉዳትን ሊያስከትልባቸው አይችልም፡፡
ሌሎች በዛ ያሉ ጥቅሶችም እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን ስለ ሰጣቸው አማኞች ስለሚኖሩት አዲስ ሕይወት አብራርተው ይገልጻሉ። ኤፌ. 2፡10 መልካም ሥራዎችን እንድንሠራ እግዚአብሔር ሕያውና አዲስ ፍጥረት አድርጎ ፈጥሮናል ይላል። ያዕ. 1፡18 እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን ይላል። በዚሁ ዐውደ ንባብ፣ ያዕቆብ እንዴት አድርገን ፈተናን መቋቋም እንደምንችል ይገልጣል። ያዕቆብ የፍሬ ሁሉ መጀመሪያ ሲል ያስብ የነበረው በዘሌዋ. 23፡9-14 የእስራኤላውያን በሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ነበር። በመጀመሪያ ተመቅቶ ወደ ጎተራ የሚገባው እህል እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ሰብል ለሕዝቡ እንደሚሰጥ ማረጋገግው ነበር። እግዚአብሔር አሁን የሚሰጠን አዲስ ሕይወት እንደ መጀመሪያ ሰብል የሚታይ ነው። እዚአብሐር በሚመጣው ዘመን በመንግሥተ ሰማይ የተትረፈረፈ ሕይወት እንደሚሰጠን ይህ ማረጋገማው ነው። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን አሁንና ባለንበት ስፍራ ይሰጠናል። አዲስ ሕይወት ካሚሰጠን በረከቶች አንዱ ፈተናን ለመቋቋም መጀመር መቻላችን ነው። ስለዚህ ይህን አዲስ ሕይወት አሁንና ባለንበት ስፍራ መኖር እንጀምራለን። ፈተናን ተቋቁመን እግዚአብሔር የሰጠንን አዲስ ሕይወት መኖር ስንጀምር፥ እግዚአብሔር በክርስቶስ በማመን ወደ እርሱ ለሚመጡት የሚሰጠውን የዘላለም ሕይወት ምሳሌ ለሌሎች እናሳያለን። ይህ አዲስ ሕይወትም፥ መልካም ሥራ ወደ መሥራትና እግዚአብሔር የሰጠንን የዘላለም ሕይወት የመጀመሪያ ፍሬ ወይም በኩራትን ወደ ማሳየት ይመራናል።
7. ማጠቃለያ፡- እንደገና መወለድ፥ በመንፈስ ለሞቱ ሰዎች አዲስ ሕይወትና ዘላለማዊ ሕይወትን ይሰጣል።
ቲቶ 3፡3-8 ዛሬ ለላ ዳግም መወለድ የተመለከትነውን አብዛኛውን ትምህርት የሚያጠቃልልልን አስደናቂ ክፍል ነው። ቁጥር 3 ምን እንደ ነበርን ሲገልጽልን፦ ሞኞች፥ የማንታዘዝ፥ ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን ነበርን ይላል። ነገር ግን ቀጥሎ በቁጥር 4፣ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ጣልቃ ገብቶ በደግነቱና በፍቅሩ አዳነን ይላል። ከዚያ ካረጀ ሕይወት «በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በተገኘው መታደስ አዳነን»። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች «መታጠብ» የሚለውን ቃል በዚህ ጥቅስ ላይ በሚያነቡበት ጊዜ ጥቅሱ ስለ ጥምቀት የሚናገር ይመስላቸዋል። ነገር ግን ማስተዋል ያለባችሁ ስለ ጥምቀት የተገለጸ ነገር የለም። ቁጥር 4 ግልጽ አድርጎ የሚናገረው የዳንነው በሠራነው ሥራ ወይም በጽድቃችን አለመሆኑን ነው። ጥምቀት ለጽድቅ ብለን የምንፈጽመው ሥራ ሲሆን፥ የጽድቅ ሥራ ግን አያድነንም። በዚህ ፈንታ ቁጥር 5 የሚያጥበን አዲስ ልደት ወይም ዳግም መወለድ ነው ይላል። አዲስ ልደት ራሱ መታጠብ ነው! እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በተሐድሶ አዲስ ሕይወትን በሚሰጠን ጊዜ፥ ንጹሐን አድርጎ ያጥበናል። እግዚአብሔር የሚሰጠን የዚህ አዲስ ሕይወት ውጤት ምንድን ነው? የዘላለም ሕይወት ዋስትና ይኖረናል (ቁ 7)፥ እንዲሁም መልካም ሥራ እየፈጸምን መኖር እንችላለን (ቁ 8)።
ጥያቄ፡- የዳግም መወለድ በረከት እንዴት ምሥጋና እንድታቀርቡና እንድታወድሱ ያነግሣችኋል?
የዳግም መወለድ በረከት እግዚአብሔር ከመንፈስ ሞት አድኖ ለዛሬም ሆነ ለዘላለም መንፈሳዊ ሕይወትን እንደ ሰጠን የሚያሳስበን ሁኔታ ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር የምናቀርበውን ምሥጋናና ውዳሴ በሦስት መንገድ ልንገልጽ እንችላለን። በመጀመሪያ፥ እግዚአብሔር የፈጠረን እርሱን እንድናውቅ ነው፤ አሁን ደግሞ አዲስ ሕይወት ስላለን እርሱን በማወቅ በረከት ልንደሰት እንችላለን። ይህን ዕድል በመጠቀም ከእርሱ ጋር አብሮ ማሳለፍን፥ በእርሱ መደሰትንና እርሱን ማወቅን በትጋት መሻት ይገባናል። ሁለተኛም፥ እግዚአብሔር በሰጠን አዲስ ሕይወት ለመኖር መጣር ይገባናል። በመሆኑም እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን ለእኛ ከመስጠቱ በፊት ወደ ነበርንበት አሮጌና ሙት ሕይወት መመላለ ጨርሶ ሞኝነት ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እግዚአብሔር በሰጠን አዲስ ሕይወት በመኖር፥ የዘላለማዊ መንግሥተንም ሕይወት አሁንና እዚሁ መኖር መጀመር እንችላለን። ሦስተኛ እሁንም በኃጢአታቸው እየሞቱ ላሉ ወዳጆቻችንና ጎረቤቶቻችን እግዚአብሔር አዲስ ሕይወትን እንዲሰጣቸው ወደ እርሱ መጸለይዘ፣ እንደዚሁም በየአጋጣሚው የእግዚአብሔርን ቃል ከእነርሱ ጋር ለመካፈል ዝተችዎች መሆን አለብን። በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት የሚሠራ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ተግባር ብቻ ለሰዎች የዳግም መወለድን በረከት ሊሰጥ ይችላል።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
