ባለፉት በርካታ የትምህርታችን ክፍለ ጊዜያት ላይ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለፈጸማቸው አብዛኛዎቹ ሥራዎች ተመልክተናል። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ በእኛ ፈንታ መሥዋዕት ሆኖ ስለ ኃጢአታችን ሞተ። እግዚአብሔር በኃጢአታችን ላይ የነበረውን የጽድቅ ቁጣ አስታሠልን፡ ከእግዚአብሔርም ጋር አስታርቆ ከኃጢአታችን ተቤዠን፥ ከኃጢአታችን ቅጣትና ከክፉ ውጤቶቹም አዳነን። ነገር ግን የኢየሱስ ሞት በመስቀል ላይ በሰይጣንና በመናፍስቱ ላይ ድልን ለመቀዳጀት ይረዳል? ስኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ሰይጣንና ክፉ መናፍስትን ይፈራሉ። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቶ የሰጣቸው ደኅንነት ሊከላካላቸው ይችላል? ደግሞስ አንድ ክርስቲያን ሰይጣንን የሚፈራበት ምክንያት አለው?
ጥያቄ፡- በአካባቢአችሁ የሚኖሩ ሰዎች ስለ ሰይጣንና ስለ መናፍስቱ ምን ያስባሉ? ይፈሯቸዋል? ከሆነ ሰዎች ከክፉ መናፍስት ለመከላከል የሚያደርጓቸውን ድርጊቶች በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ጻፉ።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ከሰይጣንና ከክፉ መናፍስቶቹ ለመከላከል የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ። የማያምኑ ሰዎች ራሳቸውን ከጠንቋዮችና ከቃልቻዎች ከሚላኩ መናፍስቶች ለመከላከል ይጥራሉ። ሙስሊሞች የሙስሊም ቅዱስ ሰው መምሕር (አሊም) ከሚያደርገው ምትሐት ለመከላከል ይሞክራሉ። እንደዚሁም ራሳቸውን ክርስቲያን አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች ቄስ ወይም ደብተራ ቤታቸው መጥቶ በመድገም በመስቀል ወይም ጠበል በመርጨት ካልተከላከለላቸው በስተቀር ሰይጣንና መናፍስትን ይፈራሉ፥ ሥጋትም ያድርባቸዋል። ሌሎች እንዲህ ያሉ ሰዎች ደግሞ ወንጌላዊ ወይም መጋቢው ከቤታቸው ሕንጻ ውስጥ አለ የሚሉትን ሰይጣን ካላባረረላቸው ፍርሃት ያድርባቸዋል። ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ ሰዎች ክርስቶስ ሰይጣንን ስለ ማሸነፉ መጠነኛ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጽሙት ድርጊት ግን ፡ የክርስቶስ ድል ዛሬም ከሰይጣንና ከዲያብሎስ ሊጠብቃቸው እንደሚችል እንደማያምኑ ሰዎች ዓይነት ነው።
ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያረጋግጥልን፥ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቱና በትንሣኤው በሰይጣን ላይ ድልን ስለ ተቀዳጀ አማኛች ሰይጣንን ከቶ ሊፈሩት አይገባቸውም። እግዚአብሔር ለበጎ ከሚፈቅደው በስተቀር፥ ሰይጣን ማንኛውንም አማኝ የማስፈራራት ወይም የመጉዳት ኃይል የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ በሰይጣን ላይ ስለተቀዳጀው ድል ምን ያስተምረናል? (በዛሬውና በነገው ዕለት የምናጠናው የክርስቶስ ድል በሰይጣን ላይ የሚለው ማውጫ የተወሰደው ጆን ስቶት «The Cross of Christ» [«የክርስቶስ መስቀል»] ብለው ከጻፉት መጽሐፍ ላይ ነው።)
1. በኤድን ትንቢት የተነገረው ድል
ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 3፡14-15 አንብቡ። ሀ) እንግዚእብሔር እባቡን በሴቲቱ ዘር ላይ ምን ታደርጋለህ አለው? ለ) የሴቲቱ ዘር በእባቡ ላይ ምን ያደርጋል አለ?
ስለ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በዘፍጥረት 3 ውስጥ በተጻፈው መሠረት አጥንተናል። በዚህ ታሪክ ውስጥ እንደተመለከትነው ሰይጣን በእባብ ተመስሎ መጥቶ ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጥሳ ኃጢአት እንድትሠራ ፈተናት። በዘፍጥረት 3፡15 ውስጥ ሰይጣን በዓለም ላይ ኃጢአትን በማምጣቱ እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የፍርድን ትንቢት ተናገረ። እግዚአብሔርም ወደፊት ሰይጣን የሴቲቱን ዘር ሰኮና ይቀጠቅጣል። የሴቲቱ ዘር ግን በተራው የሰይጣንን ራስ ይቀጠቅጣል ሲል ተናግሮአል። እግዚአብሔር በሰዎችና በእባብ መካከል ያለውን ጠላትነት ከሰይጣን ጋር ለሚያካሂደው ጦርነት ምሳሌ አድርጎ አቅርቦታል። አንድ ቀን እግዚአብሔር ከሴቲቱ ዘር ፍጹም የሆነን ሰው አዳኝ አድርጎ ያስነሣል። እግዚአብሔር ሰይጣን የሰውን ሰኮና ይቀጠቅጣል ሲል፥ አንድ ዓይነት ጉዳትን ያደርስበታል ማለቱ ነው። ነገር ግን ሰውዬው የሰይጣንን ራስ ይቀጠቅጣል ሲል፥ ሰውዬው ሰይጣንን ጨርሶ ድል በማድረግ ይደመስሰዋል ማለቱ ነው። ያለጥርጥር ትንቢቱ የተነገረለት ሰውም አምላክም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፥ እርሱም ከድንግል ማርያም የተወለደው የሔዋን ዘር ነው። ስለ እርሱ ጉዳት የተነገረው ትንቢት የሚያመለክተው ስቅለቱን ነው፥ ሰይጣን ሥራውን በአይሁድ መሪዎች በጲላጦስና በሮማውያን ወታደሮች አማካይነት በመሥራት ኢየሱስን ለማስገደል ቻለ። ነገር ግን በዘፍጥረት 3 ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ወደፊቱ የሰይጣን መሸነፍ ይተነብያል። እርሱ እንዴት ተሸነፈ?
2. በኢየሱስ አገልግሎት ድሉ ተጀመረ
ጥያቄ፡- ሉቃስ 10፡1-2፥9፥17-19 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ 72ቱን ም እንዲያደርጉ ላካቸው? ለ) ውጤታቸውስ ምን ነበር? ሐ) ኢየሱስ እነዚህን ውጤቶት እንዴት ተቀበላቸው?
ጥያቄ፡- ሉቃስ 11፡20 አንብቡ። ኢየሱስ አጋንንትን ሲያስወጣ፥ ምን ያረጋግጥ ነበር?
ኢየሱስ በምድር ላይ ያገለግል በነበረበት ጊዜ ከተከታዮቹ መካከል ለ ሁለቱን መርጦ እንዲሰብኩ፥ እንዲፈውሱና አጋንንትን እንዲያወጡ ላካቸው ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ የእግዚአብሔርን መንግሥትና እዚአብቁ! በምድር ሁሉ ላይ ገዥ መሆኑን ያሳዩ ነበር። ከተልዕኮአቸው በተመለሰ ጊዜም ትልቅ ስኬት እንዳገኙ ሪፖርት አቀረቡለት። እነርሱም በኢየሱ ስምና ሥልጣን አጋንንትን አስወጡ። ኢየሱስም ይህ ድርጊት የሰይጣን ሽንፈት እንደሚያመለክት ተረዳ። ኢየሱስም በእርሱ ሥልጣን ሥር ሰይጣ ከሚያደርሰው ጉዳት ሁሉ እንደሚጠበቁ ቃል ገባላቸው። ለእነዚህ ሰባ ሁለቱ ኢየሱስ የሰጣቸው ሥልጣን ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ በነበረ ጊዜ ይፈጽማቸው የነበሩትን ተግባራት የሚያመለክት አንድ ምሳሌ ነው። ኢየሱስ አጋንንትን በሚያስወጣበትም ጊዜ ወይም በሰይጣን ኃይል የታመመ ሰውን በሚፈውስበት ጊዜ ሰይጣንን ማሸነፉን የሚያመለክት ነበር። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት እዚሁ በምድር ላይ በእርሱ ውስጥ መሆንዋን ያረጋግጥ ነበር። የሰይጣንንም መሸነፍ መጀመሩ ነበር። የኢየሱስ አገልግሎት በምድር ላይ መጀመር በሰይጣን ላይ ድል የመቀዳጀቱ መጀመሪያ ነበር። እውነተኛው ድል ቀን የተገኘውና የተፈጸመው ሽንፈት በመሰለው በኢየሱስ ስቅለት ነው።
3. በኢየሱስ ስቅላት የተገኘ ድል
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 12፡31 አንብቡ። ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ በሰይጣን ላይ ምን ይደርስ ነበር?
ከስቅለቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለነበሩ ሰዎች ንግግር አደረገ። በመናገርም ላይ ሳለ ድምፅ ከሰማይ መጣ። አብዛኛዎቹ ሰዎች ስለ ድምጹ በግልጽ አልተረዱም ነበር። በዚህን ጊዜ ኢየሱስ ሊያውቁት በሚገባ ቃል እግዚአብሔርን በእርሱ ላይ በሚፈጸመው ነገር እንደሚከብር መናገሩን ገለጸላቸው። ሊሆን ያለው ነገር ምን ነበር? ኢየሱስ የሚሰቀልበት ጊዜ ቀርቧል። ኢየሱስም ቀጥሉ እርሱ በሚሰቀልበት ጊዜ ሰይጣን ወደ ውጭ እንደሚጣል ገለጸላቸው። በተመሳሳይ መንገድ ከግለሰቦች ሕይወት ውስጥ አጋንንትን ባስወጣበት ጊዜ ሁሉ ሰይጣንን ሲያሸንፍ ቆይቷል። አሁን ግን በበለጠ መንገድ ሰይጣንን ሊያሸንፈው ነው። ሰይጣን በዓለም ያለውን የቁጥጥር መረብ ሊበጣጥስበት ነው። በየትም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከሰይጣን ቁጥጥር ነፃ እንዲወጡ መንገድ ሊያመቻች ነው። መስቀል ሰይጣን የሚሸነፍበት ታላቁ ነገር ሊሆን ነው። የኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት እንዴት የሰይጣን መሸነፊያ ሊሆን ይችላል?
ጥያቄ፡- ቆላ. 2፡13-15 አንብቡ፡ ሀ) እግዚአብሔር በሕይወት እንድንኖር ከማድረጉ በፊት ሁኔታችን እንዴት ነበር? ለ) እግዚአብሔር በዕዳው ጽሕፈት ላይ ምን አደረገ? ሐ) ይህ ምን ማለት ይመስላችኋል? መ) እግዚአብሔር ስእለቀችና በሥልጣናት ላይ ምን አደረገ?
በሦስተኛው ክፍለ ትምህርት ውስጥ ስለ ተሠገዎ ምሥጢር ለመረዳት ቆላ. 2፡13-15 በአጭሩ ማጥናታችን የሚታወስ ነው። ነገር ግን ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ እንዴት አድርጎ ሰይጣንን እንዳሸነፈ ለመገንዘብ ይህንን ጥቅስ አሁን በዝርዝር ማጥናት ይኖርብናል። ቆላ. 2፡13-15 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር አዲስ መንፈሳዊ ሕይወትን እንደ ሰጠን ይናገራል። በበደላችንና ሥጋችንን ባለመገረዛችን ሞተን እንደ ነበርን ያሳስበናል። ይህም ከመዳናችን በፊት መንፈሳዊ ሕይወት እንዳልነበረንና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንደማናደርግ ያስረዳል። ስለዚህ ከእግዚአብሔር የተለየንና እርሱንም የምንቃወም ነበርን። እኛ በዚህ መንፈሳዊ ሞትና በእግዚአብሔር ላይ መንፈሳዊ ተቃውሞ ላለን እግዚአብሔር ግን መንፈሳዊ ሕይወትን ሰጥቶ ኃጢአታችንን ይቅር አለን። እግዚአብሔር እንዴት ይህን አደረገ? ይህን ያደረገው ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመው ተግባር ነው።
ጳውሎስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈጸመው ተግባር ሁለት ደረጃ ዎች እንደ ነበሩት ይናገራል። አንደኛው ደረጃ፥ «በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዝ የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው» የሚለው ነው። በመጀመሪያው የግሪኩ ጽሑፍ «ደመሰሰው» የሚለው ቃል በጥቅም ላይ የዋለው ከቁራጭ ወረቀት ላይ ቀለምን ማጠብ ወይም አንዱ ሰው ለሌላው ያበደረውን የዕዳ ገንዘብ መሰረዝና መተው በሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነበር። «የተጻፈ ዕዳ» የሚለው በመጀመሪያው ግሪክ የተመለከተው አገላለጽ የሳለዕዳነትን የምስክር ወረቀት የሚያሳይ ነበር። አንድ ሰው ብድር በሚወስድበት ጊዜ ዕዳ ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ወረቀት ይፈርም ነበር። አበዳሪው ያለውን የብድር ገንዘብ አገልጋዮቹ ይህን ወረቀት በማሳየት ይሰበስቡ ነበር። ጳውሎለም ማለት የፈለገው ሁላችንም ባለዕዳዎች ነን ለማለት ነው። ዕዳው ምንድን ነው? ዕዳው ትእዛዝ አለው ይላል። ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ሕጉ ነው። እርሱ የሚለው እግዚአብሔር ሕጉን የሰጠው ሰዎች እንደ መስፈርት አድርገው እንዲጠብቁት ነው። ሁላችንም ሕጉን የምጠበቅ ዕዳ አለብን። ነገር ግን ሕጉን አልጠበቅንም። የሰው ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሕግ አልታዘዘም። በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር የሚከፍለው ግዙፍ ዕዳ አለበት።
ጥያቄ፡- እናንተ ወይም የቤተሰባችሁ አባል የሆነ ሰው ዕዳ ውስጥ ገብቶ ያውቃል? ሰዎች የሌላው ሰው ባለ ዕዳ ሊሆኑ ምን ይሰማቸዋል?
ዕዳ አደገኛ የሆነ ሸክም ነው። እናንተ ወይም የምታውቁት ሰው ቤት ለመሥራት፥ ወይም ለማደስ፥ ወይም ለልጆቹ ትምህርት፥ ወይም ለጋብቻ ድግስ ተበድራችሁ ይሆናል። ሰዎች የብድር ገንዘብ ሲኖርባቸው ብዙ ጊዜ ይፈራሉ፥ ደግሞም ከባድ የሆነ ሸክም ይሰማቸዋል። በአንዳንድ ሀገራት ውስጥ አንድ ሰው የተበደረውን ገንዘብ መክፈል ካልቻለ ዕዳውን ለመክፈል ቤቱን ወይም ሌላውን ንብረቱን ይነጠቃል። በጳውሎስ ጊዜ ደግሞ ዕዳውን መከፈል ያልቻለ ሰው በባርነት ይወሰዳል፥ ወይም ሚስቱና ልጆቹ ለባርነት ይሸጡ ነበር። ብዙ ዕዳ አስፈሪ ነው። ምክንያቱም ሕይወታችንን ሊያበላሽ ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ያለብን ዕዳ በገንዘብ ዕዳ ምክንያት ከሚደርስብን ችግር ጋር ሲነጻጸር ከምንም አይቆጠርም። ሕጉን መጠበቅ ባለመቻላችን የእግዚአብሔር ቁጣ ይደርስብናል፥ ከዚህም የተነሣ ዘላለማዊ ሞት ይመጣብናል።
ነገር ግን ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ዕዳችንን ስለ ከፈለ፥ ዕዳችን ተደምስሶልናል። የነበረብን ዕዳ ጳውሎስ እንዳለው «በመስቀሉ ላይ በሚስማር ተቸነከረ»። በጥንቱ ዓለም አንድ ሰው በሚሰቀልበት ጊዜ ዕዳው ተጽፎ ከራሱ በላይ በመስቀሉ ላይ ይቸነከር ነበር። ኢየሱስም በተሰቀለ ጊዜ ጲላጦስ፡ «የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ጽሑፍ በመስቀሉ በላይ እንዲቸነክር አስደረገ (ዮሐ 19፡19)፡፡ የኢየሱስ የታወቀ ወንጀል፥ ንጉሥ ነኝ ብሎ መናገሩ ነበር። ጳውሎስ ኢየሱስ የተሰቀለበት እውነተኛው ወንጀል ይህ አይደለም ይላል። በሰዎች ዓይን ያልታየ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓይን የታየ ሌላ ወንጀል በክርስቶስ ላይ ሆኖ በመስቀሉ ላይ ተቸንክሯል። ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋናው ወንጀል የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ባለመቻሉ ነው። ስለዚህ እኛ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ ባለመቻላችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ ተቀበለ። የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ባለመቻላችን በመስቀል ላይ ሥቃይን መቀበል ነበረብን። ጻሩ ግን ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ተቀብሎ በእኛ ፈንታ በመስቀል ላይ ተሠቃየ። እርሱ በመስቀል ላይ በተሠቃየ ጊዜ ዕዳችንን ከፈለ። እኛ ሕጉን ለመጠበቅ ያልቻልንበትን ዕዳ ከፈለ። ሕጉን ለመጠበቅ ያልቻልንበት ዕዳ ስለ ተከፈለ፥ እግዚአብሔር ዕዳችንን አስቀርቶ ንጹሕ በማድረግ ኃጢአታችንን ይቅር አለን።
በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ አዲስ ሕይወትን የሰጠን ሕግን ለመጠበቅ ባለመቻላችን የነበረብንን ዕዳ መሰረዙ ነበር። ይህም ሊሆን የቻለው ኢየሱስ ዕዳችንን በመስቀል ላይ በመክፈሉ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ዕዳችንን በሰረዘ ጊዜ ሁለተኛና አስደናቂ የሆነው ውጤት ኢየሱስ በሰይጣን ላይ ድልን ተቀዳጅቶ፥ ከኃይሉ እኛን ነፃ ማውጣቱ ነበር! ጳውሎስ እንደሚለው ዕዳችን በተሰረዘ ጊዜ አለቆችና ሥልጣናት ዕቃ ጦራቸው ከአገልግሎት ውጭ ሆነ ይላል። «አለቆችና ሥልጣናት» የተባሉት ሰይጣንና መናፍስቱ ናቸው (ኤፌ. 6፡12፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡25)። የእግዚአብሔርን ሕግ ከመጣሳችን የተነሣ ከእርሱ ተለይተን በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ነበርን። ሰይጣንም በኃይሉ ሥር አስገብቶን ነበር። የሰይጣን ባሪያዎች ስለሆንን ማድረግ የነበረብን ለሰይጣንና ለፈተናው መታዘዝ ነበር። በትናንትናው ትምህርታችን ላይ እንደተመለከትነው፥ ለሰይጣን የምንከፍለው ምንም ዓይነት ዕዳ የለብንም። ሕጉን ባለመጠበቃችን ለእግዚአብሔር ዕዳ አለብን። ዕዳችንን ለእግዚአብሔር ልንከፍለው ስላልቻልን ሰይጣን በኃጢአት ባርነት ውስጥ አለገባን። ከዚህ የተነሣ ወጥመድ ውስጥ ገባን፥ ታሰርን፥ በሰይጣን መንግሥት ውስጥ ያላንዳች እርዳታ ቀረን። ከዚህም በስተቀር የኃጢአታችንን ቅጣት እንድንቀበል ተፈረደብን።
በሰይጣን ኃይል ሥር የጣለን ያለመታዘዝ ምሳሌ እነሆ፡ አንድ ሰው አገሩን መክዳቱን አስቡ። ይህ ሰው በጦርነት ጊዜ አገሩን ከድቶ ከጠላት ጎን ተሰልፎ ሲዋጋ ይታሰባችሁ። ይህ ሰው የአገሩን ሕግ ጥሶ አገሩን በመክዳቱ ቅጣት ይገባዋል። ይህ ከሐዲ ሰው ከእስር አምልጦ ወደ ጠላት ካምፕ ሲደባለቅ ይታያችሁ። ሕግን ተላልፎ አገሩን ለለ ክዳ፥ ከአሁን ወዲያ በጠላት ቁጥጥር ኃይል ሥር ይተዳደራል። በገዛ እጁ ራሱን በጠላት ጎራ መደበ። ይህ ሰው ሌላ የሚሄድበት ስፍራ ስለሌለው፥ ጠላት የፈለገውን ነገር አብሮት ይሠራል። እንግዲህ በክርስቶስ ከማመናችን በፊት ሁላችንም ያደረግነው ይሄው ነበር። ኃጢአታችን የእግዚአብሔር ጠላቶች እንድንሆን ስላደረገን፥ 1 የእግዚአብሔር ጠላት በሆነው በሰይጣን ኃይል ሥር አስገባን።
ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ስለ እኛ ኃጢአት ቅጣትን ተቀበለ። እርሱም ስለ እኛ ቅጣት ከተቀበለ በኋላ እግዚአብሔር ዕዳችንን ደመሰሰው። በእግዚአብሔር ላይ የፈጸምነው በደል በይቅርታ ተወገደ ከአሁን ወዲያ ሰይጣን በእኛ ላይ ኃይል የለውም። ከአሁን ወዲያ ከጠላታችን ኃይል ነፃ ወጥተናል። ከጠላት መንግሥት ተላቅቀን ነፃ ወጥተናል። እንግዲህ ወዲህ ልንፈራውም ሆነ ልናገለግለው አይገባንም። ክርስቶስ ታላቅ ድልን በጠላታችን ላይ በመቀዳጀት ለእግዚአብሔር መክፈል የነበረብንን ዕዳ እርሱ ስለ ከፈለልን ከሰይጣን ቁጥጥር ወጥተን ነፃ ሆነናል።
ጳውሎስ ኢየሱስ በሰይጣን ላይ ስለተቀዳጀው ድል ለማስረዳት ግልጽ በሆነ ሥዕላዊ አጻጻፍ ይጠቀማል። እንዲህ ይላል፣ «የአለቆችንና የባለሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ» (ቆላ. 3፡15)፡፡ ጠላት ተሸንፎ በምርኮ በሚወሰድበት ጊዜ መሣሪያውን ይገፈፋል። ክርስቶስ ሰይጣንና ሠራዊቱን ጨርሶ ስላሸነፋቸው መሣሪያቸውን እንዲጥሉና እንዲገፈፉ አደረገ። ከዚያም እንደ ድል አድራጊ ጄኔራል ምርኮዎቹን አስከትሎ ወደ ራሱ ከተማ መራቸው። ጠላቶቹ መሣሪያቸውን ተገፍፈው በሰንሰለት ተቆራኝተዋል። ይህ በመሆኑ አሁን የደከሙና የጠወለጉ፥ ኃይልም የራቃቸው መሆናቸውን ማንም ሊመለከት ይችላል። በዚህም ኢየሱስ ሰይጣንና ክፉ መናፍስቱ ድል መመታታቸውንና በክርስቶስ ሞት ይቅርታ ባገኙት ላይ ሰይጣን ሥልጣን እንደሌለው አሳይቷል።
ጥያቄ፦ ሀ) ክርስቶስ የኃጢአታችሁን ዕዳ ከፍሎ ሰይጣን በእናንተ ላይ የነበረውን ሥልጣን በማሸነፉ ምን ይሰማችኋል? ለ) እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ታስባላችሁ?
ክርስቶስ በሰይጣን ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ለእግዚአብሔር መክፈል የነበረብንን ዕዳ በመከፈሉ ልናመሰግነውና ልናወድሰው፥ ልናመልከውም ይገባናል። ከዚህ በኋላ ሰይጣን በእኛ ላይ የነበረውን ሥልጣን መፍራት አይኖርብንም። ክርስቶስ ባዘጋጀልን ሕይወት ውስጥ መኖር እንፈልጋለን። ከእንግዲህ ወዲያ የኃጢአት ባሪያዎችና የሰይጣን አገልጋዮች ሆነን አንኖርም። አሁን ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ለእኛ የሚጠቅመንንና ለእግዚአብሔርም አገልቀሉት የሚውል ሕይወት ለመኖር እንችላለን።
ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞቱ በሰይጣን ላይ በተቀዳጀው ታላቅ ድል ቢያንስ አንድ ሌላ ውጤት አለ።
ጥያቄ፡- ዕብራውያን 2፡15-18 አንብቡ፡ ሀ) ክርስቶስ በሞተ ጊዜ ዲያብሎስን ምን አደረገው? ለ) ክርስቶስ በሞተ ጊዜ ለእኛ ምን አደረገ?
በሦስተኛው ትምህርት ውስጥ ዕብራውያን 2፡10-18 ያለው ክፍል ለሪ ተሠዎ ምሥጢር የሚሰጠውን ትምህርት ለመረዳት በጥንቃቄ አጥንተ ነበር። ዛሬ ደግሞ ዕብ 2፡14-15 ኢየሱስ ሰውም አምላክም ሆኖ በመዋብ ስለተገኘው ውጤት የሚቀርበውን ትምህርት እናጠናለን። ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ስለሆነ በሞቱ ሰይጣንን አሸነፈ። ቁጥር 14፥ «ሰይጣን በሞት ላይ ኃይል አለው» ይላል። በትምህርታችን በክፍል ሦስት ውስጥ እንደተመለከትነው ሰይጣን ሰዎችን የመግደል ኃይል አለው ወይም በሙታን ዓለም ላይ ይገዛል ማለት አይደለም። ይህ አሳብ የሚያስነዝበው ኃጢአት እንድንሠራ እኛን በመፈተን በኃጢአታችን እንዳስፈረደብን ነው። ይህም፣ የሥጋ ሞት፥ መንፈሳዊ ሞት፥ ዘላለማዊ ሞት ነው። ነገር ቀን በቆላ. 2፡13-15 እንደተመለከትነው፥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ የኃጢአታችንን ቅጣት ተቀበለና የበደላችንን ዕዳ ከፈለ። ኢየሱስ ከኃጢአታችን ቅጣት ነፃ ሊያወጣን በሞተ ጊዜ ሰይጣን በእኛ ላይ የነበረውን ሥልጣን ደመሰሰው። ከዚህ በኋላ በኃጢአት ምክንያት መፍራት ስለማይገባን ሞትንም የምንፈራበት ሰበብ የለም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰይጣን ላይ የተቀዳጀው ድል ከሞት ፍርሃት ነፃ አውጥቶናል። ኃጢአታችን የቀረልን ለመሆኑ ዋስትና ስላለን ከአሁን ወዲያ በሞት ፍርሃት ምክንያት ባሪያዎች መሆናችን ቀርቷል።
ጥያቄ፡- በሦስተኛው ክፍለ ትምህርት ላይ በዚህ ጥቅስ የምታበረታቷቸውን የሦስት ሰዎች ስም ጽፋችሁ ነበር። ለመዳን በክርስቶስ የሚያምኑ ክሆኑ እነርሱም ሆኑ ወዳዶቻቸው ሞትን መፍራት እንደማይገባቸው አብራችሁ ተወያይታችኋል? ካልተወያያችሁ ስለዚሁ ጉዳይ በዚህ ሳምንት ውስጥ ለመወያየት ዕቅድ አውጡ። ነገር ግን አስቀድማችሁ ተወያይታችሁ ከሆነ አንድ የቤተሰብ አባል ባለፉት ወራት የሞተበት ሰው ፈልጋችሁ ይህን የማጽናኛ ቃል አካፍሉት።
በነገው ዕለት ደግሞ ክርስቶስ በሰይጣን ላይ ስለተቀዳጀው ድል ማጥናት እንጀምራለን።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
