የደኅንነት በረከተች – ክፍል 2
በትምህርት 11ና 12 ውስጥ ከኃጢአታቸው የተነሣ በሰዎች ስለሚደርሰው አላከሪ ሁኔታ ተመልክተናል። በመጀመሪያ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው በመወለዳቸው፥ እንደዚሁም በዮላቸው ኃጢአት ከመሥራታቸው ሁሉም በመንስ ሞተዋል! ደሞ በሥጋ ይሞታሉ። ሁለተኛ፤ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛነትን ባሕርይ ይዘው ስለ ተወለዱና በየግላቸውም ኃጢአትን በመሥራታቸው፥ ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአታቸው የተነሣ በደለኞች ናቸው። ነገር ን እግዚአብሔር እነዚህን የኃጢአት ውጤቶች ሁሉ የምናሸንፍበትን ብዙ አስደናቂ የደኅንነት በረከቶችን ሰጥተናል። ባለፈው ሳምንት ስለ እነዚህ የደኅንነት በረከቶች አጥንተናል። በጥናታችንም ጊዜ ሰዎች በእምነት ንስሐ ሲገቡና ወደ እግዚአብሔር ሊመለሱ፥ እርሱም ከክርስቶስ ጋር በሚያደርጉት ኅብረት አዲስ ሕይወትን የሚሰጣቸው መሆኑን ተገንዝበናል። በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትም ዳግም መወለድ በኃጢአት ምክንያት ለመጣው የመጀመሪያ ችግር መፍትሔ የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር በመንፈስ ለሞቱት ሕያውነትን ይሰጣል! እንደዚሁም በሥጋቸው ለሞቱ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት ቃል ይገባል። ነገር ን ኃጢአት በሰዎች ላይ ሞትን ብቻ እያስከትልም፥ አክሎም በሰዎች ሁሉ ላይ በዴላን ያመጣና ከእግዚአብሔር ይለያቸዋል። በዚህ ሳምንት የደኅንነት በረከቶች ስለሆኑት ስለ መጽደቅና ይቅርታ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ልጅነትና ቅድስና እንማራለን፡ መጽደቅና ይቅርታ ከበደላችን እኛን ነፃ በድረ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኞች ያደርጉናል። የእግዚአብሔር ልጅነትና ቅድስና ደሞ እኛን የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል በማድረግና ከኃጢአት በመለየት በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ እንድንገባን እንድንደሰት ያደርጉናል።
ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ
ሰዎች ከሚሸከታቸው ሸክሞች አንዱ የኃጢአት በደል ነው። በትምህርት 1 እና 2 ውስጥ እንደ ተመለከትነው፥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው ተመልፍል፡ ሰኞች ሁሉ ኃጢአትን ይሠራሉ፡ ሁላችንም በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናችንን እናውቃለን። የኃጢአታችን በደል ስለ ወደፊቱ ሁኔታ ትልቅ ፍርሃትና መጠራጠርን ያስከትልብናል። ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንደሚላቸው እርግጠኞች አይደሉም፡፡
1ኛ ጥያቄ፦ ስለታውቃቸው ሰዏች አስብ። ሀ) አንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን የህነን ሰው እግዚአብሔር ፍርፋን በሚሰጥበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል+ በምንም ኃጢአት ስለኛ አይደለህም እንደሚለው እርጠኛነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ን የሚል ይመስልሃል? ሀ) እንዲሁም አንድ ሙስሊም የሆነን ሰው እግዚአብሔር ፍርፋን በሚሰጥበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፥ ምንም ዓይነት የኃጢአት በደል የለብህ” እንደሚለው እርጠኝነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ምን ምላሽ ይሰጥህ ይሆን? ሐህ አን፥ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን አባል የሆነን ሰው እዚአብሖር በሚፈርድበት ጊዜ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፥ ምንም ዓይነት የኃጢአት በደል የለህም እንደሚለው እርግጠኛነቱን የምትጠይቀው ቢሆን ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን?
ዛሬ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ፈራጅ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት በሚቆሙበት ጊዜ የኃጢአታቸውን ይቅርታ እንደሚቀበሉ እርግጠኛች አይደሉም። እንዴዚሁም እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ መጽደቃቸውን እንደሚያውጅላቸው እርግጠኞች አይደሉም። ብዙ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ይቅር ባይነት እርገጠኞች ነን ብሎ መናገርን እንደ አጉል ድፍረትና እብሪት ይቆጥሩታል። ብዙ ሰዎች ደግሞ በርካታ ኃጢአት መሥራታቸው ይሰማቸዋል። ስለዚህ ተስፋ የሚያደርጉት እግዚአብሔር በምሕረት ዓይኑ ተመልክቶ ኃጢአታቸውን እንደሚተውላቸው ነው። ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ለመፈጻም እንደሚጣጣሩና እግዚአብሔርም ይህን መልካም ምግባራቸውን አስቦ ይቅር እንደሚላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ፈራጅ ሆኖ ሲመጣባቸው ምን ሊደርስ እንደሚችል ማሰብ አይፈልጉም። የኃጢአት በደል እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ ሆኖም የኃጢአታቸው ውጤት ምን እንደሚያመጣባቸው ማዕብ አይሹም፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር ለአማኞች ሁሉ በደኅንነታቸው ውስጥ አስደናቂ በረከትን ሰጥቶአቸዋል። ይህ በረከትም የኃጢአት ይቅርታና ጽድቅ ነው። «ጽድቅ» ማለት እግዚአብሔር፥ በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ከኃጢአትና ከበደል ነፃ ናቸው ብሎ አውጆአል ማለት ነው። ጽድቅ ማለት በኢየሱስ ለሚያምኑት ሁሉ እግዚአብሔር ለኃጢአታቸው ይቅርታን ይሰጣቸዋል፥ ከእርሱ ጋር የታረቁ መሆናቸውንም በይፋ አስታውቋል ማለት ነው። ባለፈው ሳምንት እግዚአብሔር በሚያድነን ጊዜ ሁለት በረከቶችን እንደምንቀበል ተነጋግረን ነበር። እነዚህም ዳግም መወለድና ከክርስቶስ ጋር መተባበር ናቸው። እግዚአብሔር አዲስ መንፈሳዊ ሕይወትን በመስጠት ከእርሱ ጋር እና ለዘላለም ሐሰት በማድረግ ሕይወት እንድንኖር አዲስ ሰው አድርጎ በመመለስ ብቻ አላበቃም። ከእርሱ ጋር አንድ እንድንሆን የተባበርን ብቻ አይደለንም፥ ነገር ግን እግዚአብሔር የኃጢአት ይቅርታን በመስጠት ከኃጢአታችን ነፃ መሆናችንንም ያስታውቃል። እኛ በእርሱ ዘንድ መጽደቃችንንም ይፋ ያደርገዋል። በዚህም እግዚአብሔር መጽደቃችንን ያረጋግጥልናል።
ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡20-26 አንብብ። በዚህ ክፍለ ምንባብ ውስጥ ስለ ጽድቅ ልታገኝ የምትችለውን እውነት አንድ በአንድ ጻፍ።
ጥያቄ፦ ገላ. 2፡16፥ 21ና 3፡6፥ 11-13፣ 24 አንብብ። ሀ) ላው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ የማይሆነው እንዴት ነው? ለ) ሰው በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቀውስ እንዴት ነው? ሐ) ሰው በሕግ የሚጸድቅ ከሆነ (ገላ 3፡6)፥ ክርስቶስ ሞት እውነትነት ምን በሆነ ነበር? ) ክርስቶስ እኛን ለማዳን ምን ደረሰበት (ገላ 2፡21)?
ጥያቄ፡- ሉቃስ 18፡9-14 አንብብ። ሀ) በእግዚአብሔር ፊት ከሁለቱ ሰዎች የትኛው ጽድቅን አገኘ? ለ) ሌላኛው ላይሆን ይሄኛው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅን ማግኘቱ በምን ምክንያት ነው?
ዮሐንስ 3 ስለ ዳግም መወለድ ቁልፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሆነ ሁሉ፣ ሮሜ 3ም ጽድቅን በተመለከተ ቁልፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ዛሬና ነገ ስለ ጽድቅ የሚናገሩ ብዙ ክፍሎችን እናጠናለን፡ ሆኖም ውይይታችንን የምንከፍተው በርማ ምዕራፍ 3 ይሆናል። እነዚህ ክፍሎች ስለ ይቅርታና ስለ ጽድቅ ስምንት ጠቃሚ እውነቶችን እንደሚያስተምሩን እናጠናለን።
1. ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ ማንም በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቅ የለም።
ሮሜ 3፡20 ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮሜ 1፡18 ጀምሮ ለሰጠው ትምህርት እንደ ማጠቃለያ የተጠቀመበት ክፍል ነው። ይህም ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም የሚለው ነው። ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል። ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ ጥሰዋል። ይህ ሕግም በሙሴ አማካይነት ለአይሁድ የተሰጠ ሕግ ወይም እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ሕሊና ላይ የጻፈው ሕግ ሊሆን ይችላል (ሮሜ 2፡14-15)። ሁሉም የበደሉ በመሆናቸውና የእግዚአብሔርንም ሕግ ስለ ጣሱ፣ ሕግን በመጠበቅ ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን አይችልም። በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ስለ ጽድቅ የምንማረው የመጀመሪያው እውነት ሕግን በመጠበቅ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን እንደማይችል ነው። ጳውሎስ ይህን እውነት ለገላትያ ሰዎች ደግሞ ሊነግራቸው፥ ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም እንደማይድን አሳስቦአቸዋል (ገላ. 2፡16፤ 3፡11)። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አንድ ሰው ሕግን በመጠበቅ የሚጸድቅ ቢሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ሞት ከንቱ በሆነ ነበር (ገላ. 2፡21)። ሕግን በመጠበቃችን በእግዚአብሔር ዘንድ ብንጸድቅ ኖሮ፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት ባልተገባው ነበር።
ጥያቄ፡- እንተ የምታውቃቸው ሰዎች ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት እንዲጸድቁ የሚያደርጉት ጥረት ምንድን ነው?
ዛሬ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ለመሆን ይጥራሉ። አንዳንድ ሰዎች ሕጎችን ሁሉ ለመጠበቅ ይጣጣራሉ። ነገር ትን ችግሩ ማንም ሰው ሕጎችን ሁሉ አሟልቶ መጠበቅ ወይ መታዘዝ አይችልም (ሮሜ 3፡9-10 እና 19-20)። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ እንድ ዝረት ወይም ጥምቀት ያሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን በመፈጻም በእግዚአብሔር ዘንድ ሊጸድቁ ይሻሉ። ነገር ግን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን በመፈጸም ለመጽደቅ መሞከር፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እኛን በማጽደቅ ፈንታ ከእግዚአብሔር ይለዩናል (ገላ. 5፡2)። ሌሎች ሰዎች ደግሞ በጸሎት፥ በጾምና የዚህን ዓለም ደስታ ሁሉ በመናቅ ጽድቅን ይሻሉ። ምንም እንኳን መንፈሳዊ ሥርዓት ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመኖር አጋዥ ቢሆንም፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ ሆኖ ሊቆጠርልን አይችልም። ማንም ሰው ቢሆን ሕግን በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊጸድቅ እንደማይችል የመጽሐፍ ቅዱስ አቋም ግልጽ ነው።
2. በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው።
ሮሜ ምዕራፍ 3 የተጻፈው ቃል እንደሚያረጋግጥልን ከሆነ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሊያጸድቅ የሚችል ሌላ መንገድ አለ። ይህ መንገድም አሁን በእግዚአብሔር የተገለጠ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ መጽደቅ የሚያስገነዝበው ሌላው መንገድ ምንድን ነው? ይህ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ነው። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቃን ይሆናል (ሮሜ 3፡22)። በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ስለ ጽድቅ የምንማረው ሁለተኛው እውነት በእምነት በእግዚአብሔር ፊት እንደምንጸድቅ መታወቁ ነው። ጳውሎስ ለዚህ እውነት በገላትያ መልእክቱም ላይ አጽንዖት ሰጥቶታል። ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት ይጸድቃሉ (ገላ. 2፡16፤ 3፡24)፤ ልክ አብርሃም እንደጸደቀው ማለት ነው (ገላ. 3፡6)። በእምነታቸው ጻድቃን መሆናቸው የተረጋገጠላቸው ይኖራሉ (ገላ. 3፡11)። በ16ኛው ትምህርታችን ውስጥ የደኅንነታችን በረከቶችን ሁሉ በኢየሱስ በሞቱና በትንሣኤው በማመን እንደሚገኙ አጥንተናል። በኢየሱስ ማመን ማለት በተለይ በእግዚአብሔር ፊት ያጸድቁናል ብለን በሠራናቸው መልካም ሥራዎች አለመታመን ነው። ምክንያቱም እኛ ኃጢአተኞች ስለሆንን፥ መልካሙ ሥራችን ፍጹም ቅዱስ በሆነው እግዚአብሔር ፊት መልካም ሊያደርገን ብቁ አይደለም። በኢየሱስ ማመን ማለት ለደኅንነታችን በኢየሱስ ላይ ብቻ እንመረኮዛለን ማለት ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ ልንጻድቅ የምንችለው ወደ እርሱ ዘንድ በተሟላ እምነትና አለኝታ ስንመጣ ብቻ ነው።
3. በእምነት በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ መሆን አዲስ የደኅንነት መንገድ አይደለም። በብሉይ ኪዳን ውስጥም የተገለጠ ጉዳይ ነው።
በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ስለ ጽድቅ የምንማረው ሦስተኛው እውነት፥ ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ዘንድ «በእምነት» የመጽደቂያው መንገድ አሁን በግልጽ እየተገለጠ ቢሆንም፥ በመሠረቱ ግን አዲስ አይደለም። በብሉይ ኪዳን ውስጥም እንኳ ሰዎች በእምነታቸው እንደሚጸድቁ የታወቀ ነገር ነው። አብርሃም በእምነቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የጸደቀ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግንባር ቀደም ምሳሌ ሆኖ ተገልጧል (ሮሜ 4፡1-25፤ ገላ. 3፡6-9)። ነገር ግን ሌሎች ምሳሌዎችም ተጠቅሰዋል። በእርግጥ፣ በመላው ብሉይ ኪዳን ውስጥ የነበረው የደኅንነት መንገድ (ሕግና ነቢያት ርማ 3፡2) እግዚአብሔር ባቀረበው የደኅንነት ተስፋ በማመን ነበር። ሰዎች ሁልጊዜ ጻድቅ መሆናቸው የተነገረላቸው፥ በመልካም ሥራቸው ምክንያት ‘ ሳይሆን በእምነታቸው አማካይነት ነበር። አሁን ቀን ክርስቶስ ስለ መጣ ሕን በመጠበቅ ለመጽደቅ እንደማንችል በግልጽ የታወቀ ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅን የምንቀበለው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በሚኖረን እምነት ብቻ ነው።
4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአታችንን ቅጣት በሞቱ ስለ ከፈለ ጽድቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘው ነፃ ስጦታ ነው።
ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን። ሁላችንም ብዙ የኃጢአት ተግባራትን ፈጽመናል። እግዚአብሔር እንዴት ኃጢአተኛ የሆኑትን ሰዎች ያጸድቃል? እኛስ ብንሆን በሆነ መንገድ ጻድቃንና መልካሞች የመሆን ብቃት ኖሮን በእግዚአብሔር ፊት ይህን ስጦታ ማግኘት እንችላለን? አንችልም። ምክንያቱም ቀደም ሲል እንደ ተመለከትነው ማንም በፍጹምነት ሕጉን ሊጠብቅ እንደማይችል ተገንዝበናል። ማንም ሰው በንጽሕናው ብቃት ኖሮት በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ሊሆን አይችልም። ከእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅን በጥረቱ የሚጎናጸፍ ማንም የለም። በሮሜ 3፡24 ውስጥ ጳውሎስ ሲናገር፥ እግዚአብሔር በነፃ አጽድቆናል ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር በጸጋው ያጸድቀናል። እንዲህ ማለትም እግዚአብሔር እኛ ለማግኘት የማይገባንን ቸርነት በራሱ ፈቃድ ይሰጠኛል ማለት ነው (ሮሜ 3፡24)። ይህ ድርጊት እግዚአብሔርን ራሱን ኢ-ፍትሐዊ አያደርገውም? ጻድቅ የሆነ አምላክ ጻድቃን ባለመሆናቸው ጽድቅን ሊያገኙ ያልቻሉ ኃጢአተኞችን እንዴት እንዲጸድቁ ያደርጋል? እግዚአብሔር በነፃ እንድንጸድቅ የሚያደርግበት ምክንያት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ብሎ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የኃጢአታችንን ቅጣት ስለ ከፈለልን እና የኃጢአታችንንም ቅጣት ስለ ወሰደ ነው። የኃጢአታችንን ቅጣት በመክፈል ኢየሱስ በደላችንን አስወግዶ የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣም እንዲያልፈን አደረገ (ሮሜ 3፡5)። የኃጢአታችንን ቅጣት በጌታ ኢየሱስ በመከፈሉ ምክንያት እግዚአብሔር ከበደላችን ነፃ አድርጎናል።
ጳውሎስ ይህንን በገላ. 3፡13 ውስጥ ሰፋ አድርጎ የገለጸው ሲሆን፥ ሕጉን ባለመጠበቃችንና ባለመታዘዛችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተረግመን ነበር ብሏል። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ መርገማችንን ሁሉ ተሸከመ። በእርሱ የሚያምኑ በኃጢአታቸው ምክንያት የተረገሙ ሆነው እንዳይቀሩ እርሱ የኃጢአታችንን እርግማንና ቅጣት ሁሉ ወሰደ። ኢየሱስ በዚህ አኳኋን እርማንን ስላስወገደልን፥ በእግዚአብሔር ፊት እኛ ጻድቃን እንሆናለን። በ2ኛ ቆሮ. 5፡21 ጳውሎስ ሲናገር፥ በእውነት ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ ይላል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ኃጢአታችንን ፣ ራሱ ተሸከመ። ስለ ኃጢአታችንም በእኛ ፈንታ ሞተ። ጌታ ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ኃጢአታችንን በመውሰዱ እግዚአብሔር በፊቱ ጻድቃን አድርጎ ይቆጥረናል።
ስለ ጽድቅ በሮሜ 3፡20-26 ባለው ክፍል ውስጥ የምንማረው አራተኛው እውነት፥ ምንም እንኳን እኛ ለጽድቅ ብቃት ባይኖረንም፥ እግዚአብሔር እንዳጸደቀን ነው። እርሱ እኛ ልናገኘው የማይገባንን የጽድቅ ስጦታ በጸጋው ወድዶ ሰጠን፡፡ እንዲሁም ጌታ ኢየሱስ የኃጢአታችንን ቅጣት ስለ ከፈለልን፥ እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቀን። በኃጢአታችንም ምክንያት የተቃጣብን የእግዚአብሔር ጽድቃዊ ቁጣም አለፈን። በዚህ ምክንያት ጳውሎላ በሮሜ 3፡26 ውስጥ እግዚአብሔር ጻድቅና (ምክንያቱም ኃጢአት ተቀጥቷልና የኃጢአት ቅጣትም ተከፍሏልና) በኢየሱስ የሚያምኑትን ኃጢአተኞች እንዲያጸድቅ ይላል።
እኛ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ሆነን ስለ መገኘታችን በጣም ጠቃሚና አስደናቂ ከሆኑት ምሳሌዎች መካከል አንዱ ፈሪሳዊውና የቀራጩ ሰው (ብር ሰብሳቢው) ነው። ፈሪሳዊው ሕን ሁሉ በጥንቃቄ የሚጠብቅ ጻድቅ ሰው ነበር፡ ምንም ዓይነት ትልቅ ኃጢአት አልፈጸመም። በየጊዜው ይቆም ነበር። ለእግዚአብሔር ሥራና ለድሆች ገንዘብ ይሰጥ ነበር። የብር ሰብሳቢው ቀን ከራሱ ሰዎች ገንዘብ የሚያጭበረብር፥ እግዚአብሔርን ከማይፈሩ ከሮማውያን ጋር የሚሠራ ነበር። ምንም እንኳን ፈሪሳዊው መልካም ሰው የነበረ ቢሆንም፥ ራሱ ኃጢአተኛ መሆኑን አላወቀም ነበር። በራሱ ጽድቅ ታመነ፥ ሕግን መጠበቁም በእግዚአብሔር ፊት የሚያጸድቀው መሰለው። እናም ኢየሱስ ሲናገር፣ እግዚአብሔር ይህን ሰው ጻድቅ አድርጎ በፊቱ አልተቀበለውም ይላል። በሰዎች አስተያየትና ምዘና ይህ ሰው ጻድቅ መስሎ ቢታይም እንኳ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀን ፍጹም አልነበረም። ጻድቅ ያልሆነበት ምክንያት በራሱ ጵድቅ ስለ ታመነ ሲሆን፥ ማንም ሰው ደግሞ በራሱ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም። ነገር ግን ግብር ሰብሳቢው ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን ተረድቷል፤ እግዚአብሔርም ይቅር እንዲለው በልቅሶ ተማጥኖታል። በ13ኛ ትምህርት ውስጥ እንደ ተመለከትነው፣ ግብር ሰብሳቢው፣ «እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ይቅር በለኝ» ሲል፥ በእውነት ማለት የፈለገው፥ «በምሕረት መክደኛው ላይ ያለው ደም በኃጢአቴ ምክንያት ከተሰነዘረብኝ የጽድቅ ቁጣህ ያድነኝ» ማለቱ ነበር። ይህ ግብር ሰብሳቢ በምሕረት መክደኛው ላይ ያለው ደም በኃጢአቱ ላይ የተቃጣውን የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ እንደሚያስቀርለት ያምን ነበር። እናም ጌታ ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ጽድቁን አረጋግጦለታል ይላል። በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊያስደስተው አለመቻሉን በመገንዘቡና ኃጢአቱን ይቅር ለማለት የሚችለው እግዚአብሔር ራሱ መሆኑን በማመኑ እግዚአብሔር ሊያጸድቀው ፈቅዱል። በዚህ መንገድ በራሳቸው ጽድቅ የማይመኩትን እግዚአብሔር ያጸድቃቸዋል። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የጌታ ኢየሱስ ሞትና ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ለጽድቅ እንደሚያበቃቸው ማመን አለባቸው።
ጥያቄ፡- በዚህ ምሳሌ ውስጥ እንደ ቀረበው ፈሪሳዊ ያላ ኃጢአት ባለመሥራታቸው ወይም በማቸውና ምጽዋት በመስጠታቸው የሚጸድቁ የሚመስላቸው ሌሎች የምታውቃቸው ሰዎች አሉ? ሊጸድቁ የሚችሉት በክርስቶስ ባላቸው እምነት ብቻ መሆኑን መገንዘብ እንዲችሉ ለመርዳት: ዛሬ ከተማራችሁት ክፍል የትኛውን አብረሃቸው ትካፈላለህ?
መላው የሰው ልጆች በራሳቸው ጽድቅ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ይሻሉ። ስለሆነም በገዛ መልካም ሥራችን በእግዚአብሔር ፊት መጽደቅ የማንችል መሆናችንን ለመቀበል አንፈልግም፡ ምናልባት ትንሽ የእግዚአብሔር ጸጋ ለመቀበል ፈቃደኞች እንሆን ይሆናል። ነገር ቀን እንደዚህ በምሳሌነት እንደተጠቀሰው ብር ሰብሳቢ መሆን አንፈቅድም። በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅን ለማግኘት የምናርገው ተባር ምንም እንደሌለ መቀበልን አንሻም፡ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ብቻ በእግዚአብሔር ፊት ያጸድቀናል። እኛ ማድረግ ያለብን በትሕትና ቀርበን በጌታ ኢየሱስ ላይ ወደገፍ ብቻ ነው። ይህን በምናደርበት ጊዘ እንደምንጸድቅ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔርን ፍርድ እንፈራም፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ይፈርድብን ይሆን ብለን ጥርጣሬ ላይ አንወድቅም። በሮሜ 3፣ በገላ. 2-3 እና በሉቃስ 18 ላይ በትሕትና ወደ እርሱ በመቅረብ ይቅር ባይነቱን የሚያምኑ ሁሉ እንደሚጸድቁ እግዚአብሔር ተስፋ ይሰጣል። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ተስፋ አምናችሁ ትቀበላላችሁ?
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
