መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

መንፈስ ቅዱስ 1፡ ረዳት

ስለ መንፈስ ቅዱስ ሰምተው ያውቃሉ? በርካታ ሰዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንንነት ግራ ይጋባሉ። ኢየሱስ በዮሐንስ 14፡16 ላይ፣ “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” ሲል ይናገራል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተለይቷቸው ወደ አባቱ በሚያርግበት ጊዜ ረዳት እንደሚያስፈልጋቸው ያውቅ ነበር። በጥቅሱ ውስጥ “ሌላ” የሚለው ቃል፣ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ሁሉ፣ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር እንደሆነ ያሳያል። ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሊኖር ወደ እኛ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ ወደ እኛ ለምን ይመጣል? ሊረዳን እና እግዚአብሔር እንድንኖረው የሚፈልገውን ኑሮ ለመኖር የሚያስችለንን ሃይል ሊሰጠን። ብዙ ጊዜ የራሳችን መርከብ ካፒቴኖች (ሾፌሮች) መሆን እንሻለን። ነገር ግን ስፍራውን ለመንፈስ ቅዱስ ብንለቅ፣ የሕይወታችንን መሪ እንዲጨብጥ ስለፈቀድንለት እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ሕወታችንን እንዲመራ እድል እንሰጠዋለን። ብቸኞች አለመሆናችንን ማወቅ የሚያስደንቅ ነገር አይደለምን? ይህ ብቻ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚፈፅማቸውን ሌሎች ተጨማሪ የእርዳታ ተግባራት  አሉ። ለአብነት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ ወደ እውነት ይመራናል፣ ምስክሮቹ እንድንሆን ሃይልን ይሞላናል፣ በምንፀልይበት ጊዜ ቃልን በመስጠት ይማልድልናል፣ በሃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ከሃጢአት ሃይል ነፃ በማውጣት በውስጣችን እንደሚኖረው እነደ ኢየሱስ ያለ ፃድቅ ባሕሪይ እንዲኖረን ያደርጋል። ስለ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ ለማወቅ ይሻሉ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዮሐንስ ወንጌል ስለ እርሱ በስፋት ስለሚተርክ ይህን ክፍል ያንቡት፤ በእጅጉ ይወዱታላ።

መንፈስ ቅዱስ 2፡ አዲስ ማንነት እና ሃይል

ስለ መንፈስ ቅዱስ የተማርኩበትን ጊዜ አስታውሳለው። ኢየሱስ በዮሐንስ መንጌል ምዕራፍ 14 እና 15 ላይ የተናገረው ነገር ስለ መንፈስ ቅዱስ ለመረዳት በእጅጉ ጠቅሞኝ ነበር። ይህ ክፍል፣ የክርስትና ሕይወታችንን ከዛፍ ጋር ያነፃፅራል። ዛፉ በውስጡ ከሚያልፈው ፈሳሽ፣ የምግብ ንጥረ ነገሮችን እና ሃይል ያገኛል። ይህ፣ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ካለው ተግባር ጋር ይመሳሰላል። ከእርሱ ጋር ስንጣበቅ/ስንያያዝ፣ ከእግዚአብሔር የሆነ መልካም ፍሬን ማፍራት እንጀምራለን። ይህ ፍሬ የተለወጠን ሰው ሕይወት የሚወክል ከመሆኑ ባሻገር ዘላለማዊ ዋጋም ይኖረዋል። ገላቲያ 5፡22-23 ይህን ፍሬ እንዲህ በማለት ይዘረዝራል፦ ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ እና ራስን መግዛት። አስተውሉ፣ መንፈስ ቅዱስ በውጣችን መገኘቱ፣ ከውስጥ የሚነሳ የማንነት ለውጥ ያመጣል እንጂ ያለንን አሮጌ ማንነት አያሻሽልም። የፖም ተክል የፖም ፍሬን ለማፍራት መግተርተር ወይም መታገል አያስፈልገውም። ዛፉ በደረሰ ጊዜ ፍሬውን ማፍራቱ አይቀርምና። ኢየሱስን እየመሰልን እንድናድግ በውስጣችን እየሰራ ያለው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጉዞህን ብትቀጥል፣ እምነትህ መልካሙን እግዚአብሔራዊ ፍሬ ሲያፈራ መመልከትህ የማይቀር ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ርዕስ ስር “ፍለጋውን መከተል” የሚለውን ክፍል፣ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን እንድታነብ እንመክራለን፣ ገላቲያ 5፡22-23 ን በቃልህ ለመያዝ ሙከራ አድርግ።

መንፈስ ቅዱስ 3፡ አዲስ ማንነት

ክርስቶስን ከተቀበልክ በኋላ በሕይወትህ ልዩነት አስተውለሃል? መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል” ይላል – 2ቆሮንቶስ 5፡17። ኢየሱስ በአንተ ፈንታ ስለሃጢአትህ እንደሞተ በእውነት ካመንህ፣ ያ አሮጌና ኋጢአተኛ ሕይወትህ አልፏል። ከአሮጌና ኋጢአተኛ ሕይወትህ ነፃ በመውጣት ለእርሱ እንድትኖር እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ሰጥቶሃል። ከዚህ ቀደም የሃጢአት እና የሞት ባሪያ እንደነበርክ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ሆኖም ግን እግዚአብሔር ከዚህ ባርነት በልጁ ሞት መልሶ በመግዛት ተቤዥቶሃል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ስትቀበለው፣ እንደ ልጁ አድርጎ ተቀብሎሃል። አዲስ ማንነት ሰጥቶሃል፤ ይህም ማንንት የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሆነህ እንድትቆጠር አድርጎሃል! የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን ለስጋዊ ምኞቶቻችን መኖር አይገባንም። አዲስ ሕይወት ለመኖር በክርስቶስ ነፃ ወጥተናልና። “አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።” – ሮሜ 8፡15-16። ኢየሱስ የሞተው አንተን የእርሱ ባሪያ ለማድረግ ሳይሆን ከአንተ ጋር ሕብረት ማድረግ ስለሚፈልግ ነው። የእርሱ ልጆች መሆናችን የፀና መሆኑ ይረጋገጥ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል። እኛም ከፍርሃት የተነሳ ሳይሆን እርሱ አባችን በመሆኑ ምክንያት እንታዘዘዋለን፣ ደስ እናሰኘዋለንም።

ቤተሰቡ ስላደረገህ እግዚአብሔርን አመስግነኧው ታውቃለህ? እስቲ አሁን እናመስግነው። እግዚአብሔር ሆይ፣ በልጅህ በኢየሱስ በኩል ስላፈሰስክልን ፍቅር እናመሰግንሃለን። ልጆችህ ተብለን መጠራታችን ምን ማለት እንደሆነ ይበልጥ እንድንረዳው እና በዚህም እውነት መኖር እንድንችል እርዳን፣ አሜን!

መንፈስ ቅዱስ 4፡ ትዕዛዝ እና ተስፋ

ገላቲያ 5፡22፦23 ን በቃልህ ያዝክ? ጥቅሱ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ሊያፈራቸው የሚፈልጋቸውን ፍሬዎች ዝርዝር የያዘ ክፍል ነው። እነዚህ ፍሬዎች በራሳቸው ግቦች እንዳይደሉ አስተውል። ግቡ፣ ክርስቶስ በአንተ ሕይወት ውስጥ ለሌሎች መገለጡ ሲሆን፣ ፍሪዎቹ ደግሞ ለዚህ ግብ ተግባራዊ መሆን እንደ ግብዓቶች ናቸው። እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት እንድትኖር በውስጥህ እየሰራ ያለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ማወቅ የዚህ ሃሳፍ ቁልፉ ነጥብ ነው። ኤፌሶን 5፡15-18 እንዲህ ይላል፣ “እንግዲህ … እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ … የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና።” በስካር እና መንፈስ ቅዱስን “በመሞላት” መካከል ቀጥተኛ ንጽጽር አለ። ስትሰክር፣ በአልኮል መጠጡ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ ስር ትሆናለህ። በመንፈስ ቅዱስ “መሞላትም” ከዚህ ሀሳብ ጋር ይመሳሰላል። መንፈስ ቅዱስ ሀሳባችንን እና ተግባራችንን እንዲቆጣጠር ልንፈቅድለት ይገባል። በውጤቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን በሕይወታችን እናያለን። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እና ትዕዛዝ ጭምር መሆኑን ልብ በል። ትዕዛዝ እንጂ አማራጭ አይደለም። “ይህን እንዴት ላደርግ እችላለው?” የሚል ጥያቄ አንስተህ ከሆነ መልሱ “በእምነት፣” የሚል ይሆናል። በ 1ኛ ዮሐንስ 5፡14-15 መሰረት፣ እንደፈቃዱ አንዳች ብንለምን፣ እግዚአብሔር ይሰማናል፣ ያደርገውማል። መንፈስ ቅዱስ ሕይወታችንን እንዲመራ እና እንዲቆጣጠር መፀለይ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና እንደፈቃዱ የሆነ ፀሎት መሆኑ ማንንም አያጠያይቅም። እናም፣ በቃሉ መሰረት ፀሎታችንን ሰምቶ እንደሚያደርገው ልናምነው እንችላልን። እስቲ አሁን ይህን ፀልይ። እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ትችል ዘንድ ጥበብ እና ሃይል እንዲሰጥህ መንፈስ ቅዱስን ለምን፤ እርሱም ይህንኑ ያደርጋል።   

መንፈስ ቅዱስ 5፡ ጦርነት እና ውትድርና

ክርስቶስን እንደ ጌታ በመቀበል የጀመርከው አዲስ የሕይወት ጉዞ አስደሳች እየሆነልህ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ሕብረት እና በአለም ስላለው ክፋት ተጨባጭነት የሚያወራውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላካፍልህ እፈልጋለው። መጽሐፍ ቅዱስ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4 ላይ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።” ውትድርና ከባድ ሙያ ነው፤ ብዙ ጊዜ መከራንም ይጠይቃል። ወታደር መከራ የሚቀበል ብቻ ሳይሆን አጋር ወታደሮችን የሚረዳ ጭምር ነው። የአንድ ሰራዊት ሕይወት እያንዳንዱ ወታደር የግል ድርሻውን በተገቢው ሁኔታ በመፈፀሙ ላይ የተመሰረተ ነው። የክርስቲያን ሕይወት ቀላል አይደልም። ቤተ ክርስቲያን፣ እያንዳንዳችን ለጦርነት የምንዘጋጅበትና የምንከትበት ስፍራ እንጂ ተራ ማሕበራዊ ክለብ አይደለችም። አብረውን ለጦርነት የዘመቱት ሁሉ በጦርነቱ ድልን እንዲቀዳጁ ሁላችን የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ለዚህ ጦርነት ስንዘጋጅ ማወቅ ስላለብን ነገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ያሳስበናል፦ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” – ኤፌሶን 6፡12። በጦርነት ውስጥ ነን ካልን ዘንድ ጠላታችን ማን ነው? ኤፌሶን 6፡10-11 ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ወይም ሰይጣን እንደሆነ ይነግረናል። የሰይጣን እና የክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊቱ ህልውና ተጨባጭ እውነታ ነው። እነዚህ የክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊቶች ክርስቲያኖችን ይዋሻሉ፣ ይከሳሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረትም ለማጥፋት ይጥራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን የሃሰት አባት እንደሆነ ይነግረናል። እንዴት ነው ይህን ጠላታችንን የምንዋጋው? ልክ ኢየሱስ እንዳደረገው። የጦር መሳሪያችን እውነት ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል እና ፀሎት። በዚህ ጦርነት ውስጥ ቁልፉ ነገር በእኛ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ በዓለም ካለው ሰይጣን እንደሚበልጥ ማወቅ ነው። እግዚአብሔር ላንተ ያለው የተስፋ ቃል እንዲህ ይነበባል፣ “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና” – 1ዮሐንስ 4፡4። ስለዚህ ተስፋ ምን ታስባለህ?     

መንፈስ ቅዱስ 5፡ ስላሴ

ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋር ሕብረት ማድረግ ምንኛ መታደል ነው! እርሱ የአፅናፈ-ዓለሙ ፈጣሪ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው  እኛ እግዚአብሔርን በሙላት ልንረዳው ፈፅሞ አንችልም። እውቀታችን ውስን ስለሆነም ሃሳቡን ልንገነዘብ ያዳግተናል። በርካቶቹ የእግዚአብሔር ባሕሪያት ከእኛ የመረዳት አቅም እና ልምምድ በላይ ናቸው፦ በአንድ ግዜ በሁሉ ቦታ እንዴት ሊኖር ይችላል? ሊመጣ ያለውን ጨምሮ እንዴት ሁሉን ሊያውቅ ይችላል? እንዴት ሶስት አካል፣ አንድ አምላክ ሊሆን ይችላል? ይህን መራዳት እጅግ አዳጋች ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ በግልፅ ይናገርና በተጓዳኝ ደግሞ ይህንኑ አንድ አምላክ በብዙ ቁጥር ሲጠራው እናነባለን። “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” – ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26። ከዚህ በተጨማሪ ኢየሱስ፣ “እኔና አብ አንድ ነን”፣ “እኔን ያየ አብን አይቶአል” ሲል ተናግሯል። በማቴዎስ 28፡19 ላይ የተዘገበውና ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የመጨረሻው ትዕዛዝ እንዲህ ይነበባል፣ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው”። እዚህ ላይ ኢየሱስ ለሶስቱም እኩል ቦታና ስልጣን ሲሰጥ እናነባለን። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር ምድራዊ በሆኑ ነገሮች በቀላሉ አነፃፅረን ልንረዳው አንችልም። ሰው ሳይቀር የሶስት ማንነቶች ባለቤት ተደርጎ ነው በእግዚአብሔር የተፈጠረው፦ መንፈስ፣ ነፍስ እና አካል። የራሳችንን ተፈጥሮ በአግባቡ መረዳት የእግዚአብሔርን አንድነት እና ሶስትነት (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) ለመረዳት ጠቃሚ ሚና ይኖረዋል። የእግዚአብሔር ምስጢራት፣ ከእኛ የመረዳት አቅም በላይ ቢሆኑም በርካቶቹን በቃሉ በኩል እንድንረዳው ገልጾልናል።

3 thoughts on “መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?”

  1. Be GETA selam elachihuwalehu endet nachu ene betam dehna negn : eskahun and fetena bicha new yetelakelign . Ke 11 mi’irafoch 3tun atiniche cherishalehu. Tebareki!!!

Leave a Reply

%d bloggers like this: