ስለ እግዚአብሔር እንዴት መማር እችላለሁ?

ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ያስተምረናል

የእግዚአብሔር ቃል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑ – ሉቃስ 21፡33

የእግዚአብሔርና የቃሉ ስልጣን – ማቴ 4፡4፤ ዮሐ 10፡35

መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ የተደረሰ መጽሐፍ ነው – 2ጢሞ 3፡16

መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፈ ነው – 2ጴጥ 1፡21

ለ) መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ለእኛ ለመግለጽ ሰዋዊ የሆኑ መግለጫዎችን ይጠቀማል

ክንድና እጅ – ዘጸ 3፡20፤ ዘዳ 4፡34፤ ዘጸ 5፡15

ፊት – ዘፍ 4፡14፤ 33፡10፤ ኢሳ 59፡2

አይኖችና ጆሮዎች – ኢሳ 37፡17፤ መዝ 11፡4፤ 34፡15፤ መሳ 15፡3፤ ዘካ 4፡10

መሄድና መምጣት – ዘፍ 11፡5፤ ኢሳ 64፡1-3፤ መዝ 18፡9-19

የእግዚአብሔር ድምጽ ለአዳምና ለሙሴ ተሰማ – ዘፍ 3፡9፣ 10፤ ዘዳ 4፡12

የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት እንችላለን – ዘዳ 5፡24፤ ሐዋ 22፡14

ሐ) እግዚአብሔር፣ ሰዎች ሊረዱት በሚችሉት መንገድ ይገለጣል

በራዕይ – ዳን 7፡9፣ 13፤ ራዕ 4፡3፤ 5፡7

በቀጥታ – አዳም – ዘፍ 3፡8-10 – ያዕቆብ – ዘፍ 32፡24-30 – አብርሃም – ዘፍ 18 ኢያሱ – ኢያሱ 5፡13-15 – ዳንኤል – ዳን 3፡ 25

እግዚአብሔር በኢየሱ በኩል – ማቴ፣ ማር፣ ሉቃ እና ዮሐ

መ) የፈጠራቸውን ነገሮች በመመልከት (ተፈጥሮን)

በ (ሮሜ 1፡18-25) የተጠቀሰውን ትምህርት ይመልከቱ።

ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ – መዝ 19፡1

ተፈጥሮ የእርሱን ዘላለማዊ ሃይልና መለኮትነት ያበስራል – ሮሜ 1፡20

ህሊናችንና/ልባችን የእግዚአብሔርን ሕግ ያውቃል – ሮሜ 2፡14-16

የምድር በረከት ምስክር ነው – ሐዋ 14፡15-17

የእግዚአብሔር እውቀትና ጥበብ – መዝ 19፡1-6፤ 104

የእግዚአብሔር ሃይልና ግርማ ሞገስ – መዝ 18፡7-15፤ 29፤ 66፡1-7

ሠ) እግዚአብሔርን በተፈጥሮ ውስጥ ብቻ የማወቅ ጎዶሎ ጎኖች

ተፈጥሮ ሙሉዉን ድነት ለመረዳት በቂ አይደለም።

የማያምኑ ሰዎች አእምሮ በሰይጣን ታውሯል – 2ቆላ 4፡4

ሰባኪ ያስፈልጋል – ሮሜ 10፡14

የአዳም መውደቅ በተፈጥሮ ውስጥ የነበረውን የእግዚአብሔር ምስል በክሎታል። ለአብነት – በምጥ ጊዜ ያለ ህመም – ዘፍ 3፡16፤ አድካሚ ስራ፤ እሾህና አሜኬላ – ዘፍ 3፡17-18፤ ፍጥረት ሁሉ ለመታደስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል – ሮሜ 8፡18-25

ረ) እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በሙላት ተገልጧል

ወልድ ለሚወደው ሁሉ አብን ይገልጥለታል – ማቴ 11፡27፤ ሉቃስ 10፡22

እኔን ያየ አብን አየ – ዮሐ 14፡6-7፤ 10፡30

ቃልም እግዚአብሔር ነበረ…ቃልም ሥጋ ሆነ – ዮሐ 1፡1-14

ሰ) እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐ 4፡24)

ስለዚህ እራሱን ሊገልጥልን ይገባል – 1ሳሙ 3፡21

አንዳንድ ነገሮች ምስጢር እንደሆኑ ይቆያሉ – ዘዳ 29፡29

አንዳንድ ነገሮችን ለሰው ልጅ ይገልጻል – ዓሞጽ 3፡7፤ ኤፌ 3፡5

ሙሴ የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰማ ነገር ግን እግዚአብሔርን አልተመለከተውም – ዘጸ 4፡12

ሰው እግዚአብሔርን አይቶ በሕይወት መቆየት አይችልም – ዘጸ 33፡20

ማስታወሻ፡- እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ራሱን ሊገልጥልን ይገባል፡፡

ሸ) እግዚአብሔር ለሰዎች ራሱን ለምን ይገልጣል?

በመከራ ጊዜያቸው ወቅት ሊያድናቸው – 2ሳሙ 22፡7፤ መዝ18፡6

ኖሕ ከጥፋት ውሃ ዳነ – ዘፍ 6፡1 – 9፡17

አብርሃም ከ ጣኦት አምልኮ ዳነ – ዘፍ 12፡1 – 22፡19

ሙሴ ከባርነት ነጻ ለመውጣት – ዘጸ 3፡-14፡

ድነትን ለመስጠት – ማቴ 1፡21

የሰይጣንን ስራ ለማፍረስ – 1ዮሐ 3፡8

ስለመጻኢ ጊዚያት ለማስጠንቀቅ – ዓሞጽ 3፡7፤ ራዕ 1፡-22

Leave a Reply

%d bloggers like this: