ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን ለመጥራት የሚጠቀምባቸው ስያሜዎች
መንፈስ – ማር 1፡10፤ ገላ 5፡5፤ ራዕ 22፡17
መንፈስ ቅዱስ – ኢሳ 63፡10-11፤ ሉቃስ 11፡13፤ 1ተሰ 4፡8
የእግዚአብሔር መንፈስ – ዘፍ 1፡2፤ ኢዮ 2፡28፤ ሮሜ 8፡14፤ 1ቆሮ 3፡16
የአብ መንፈስ – ማቴ 10፡20
የወልድ መንፈስ – ገላ 4፡6
የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ – ፊሊ 1፡19
የክርስቶ መንፈስ – 1ጴጥ 1፡11
የጌታ መንፈስ – 2ቆሮ 3፡17፤ ኢሳ 63፡14
የጸጋ መንፈስ – ዕብ 10፡29
የእውነት መንፈስ – ዮሐ 14፡17፤ 15፡26፤ 1ዮሐ 5፡6
የሕይወት መንፈስ – ሮሜ 8፡2
የክብር መንፈስ – 1ጴጥ 4፡14
የልጅነት መንፈስ – ሮሜ 8፡15
አጽናኝ – ዮሐ 14፡16፤ 16፡7
የጥበብ መንፈስ፣ የማስተዋል፣ የምክር፣ የኃይል፣ የእውቀት፣ እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ – ኢሳ 14፡16፤ 16፡7
ለ) ስሙ እንደ እግዚአብሔር ስም ጥቅም ላይ ውሏል
– መንፈስ ቅዱስን መዋሸት – ሐዋ 5፡3
– እግዚአብሔርን መዋሸት – ሐዋ 5፡4
– የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ – 1ቆሮ 6፡19፣ 20
– የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ – 1ቆሮ 3፡16፣ 17
– መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ከሞት አስነሳው – ሮሜ 8፡11
– እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት አስነሳው – ሐዋ 2፡24፣ 32
– በመንፈስ ሃይል እየሰበኩ – 1ቆሮ 2፡4
– በእግዚአብሔር ሃይል እየሰበኩ – 1ቆሮ 2፡5
ሐ) መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ባሕሪይ አለው
መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው – ዘፍ 1፡2
መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ያውቃል – 1ቆሮ 2፡10-11፤ ዮሐ 16፡13
መንፈስ ቅዱስ ሃያል ነው – ሉቃስ 1፡35፤ ሮሜ 15፡19
መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ነው – ዕብ 1፡10-12፤ ዕብ 9፡14
መ) መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው እንጂ ሃይል ወይም የእግዚአብሔር ተፅእኖ አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ “ነገር” እያለ ሳይሆን “እሱ” እያለ ይጠራዋል – ዮሐ 16፡13-14፤ ኤፌ 1፡13-14
ኢየሱ፣ እንደ እርሱ የሆነ “ሌላ አጽናኝ” እንደሆነ ተናገረለት – ዮሐ 14፡16
መንፈስ ያስተምራል – ዮሐ 14፡26
ለማን ስጦታ መስጠት እንዳለበት ይወስናል – 1ቆሮ 12፡11
ስለቅዱሳን በመቃተት ይማልዳል – ሮሜ 8፡26
መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን (መከላከል) ትክክል አይደለም – ኤፌ 4፡30፤ ሐዋ 7፡51
መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ኃጢአት ነው – ማቴ 12፡31፤ ማር 3፡29