የእግዚአብሔር ስሞች

የእግዚአብሔር ሰዎች ባሕሪያቶቹን ይገልጻሉ

እግዚአብሔርን ለመሰየም በእብራይስጥ ቋንቋ በርካታ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ወደአማርኛ ሲመለሱ “እግዚአብሔር” ወይም “ጌታ” ወይም “ጌታ እግዚአብሔር” ተብለው ተተርጉመዋል፡፡ ከዚህ በታች የተወሰኑ በእብራይስጥ ቋንቋ የእግዚአብሔር ስያሜዎችና ትረጉሞቻቸው ቀርበዋል፡

ሀ) ያህዌ፡ በራሱ ህያው የሆነ

በፍጥረት መጀመሪያ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስያሜ ዘፍ 2፡4

– ያህዌ- ይርኤ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አብርሃም ይስሃቅን እንዲሰዋ በተጠየቀ ጊዜ የተናገረው ዘፍ 22፡13-14

– ያህዌ- ራፋ እግዚአብሔር ይፈውሳል እግዚአብሔር ለሚሰሙትና ለሚታዘዙት ቃል ሲገባ ዘጸ 15፡26

– ያህዌህ- ንሲ እግዚአብሔር አላማችን (ሰንደቃችን) ነው ሙሴ አማሌቃዊያንን ድል ባደረገ ጊዜ የተናገረው ዘጸ 17፡15

– ያህዌ- ሰላም እግዚአብሔር ሰላማችን ነው ጌዴዎን የተናገረው መሳ 6፡24

– ያህዊ- ራ-አህ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ሕብረት መዝ 23፡1

– ያህዌ-ጽድቄኑ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው እግዚአብሔር ወደምድር በሚመጣበት ጊዜ የሚጠራበት ስያሜ ኤር 23

– ያህዌ -ሻማህ እግዚአብሔር በዚያ አለ የእግዚአብሔር ከተማ ስም ሕዝ 48፡35

– ያህዌ- ሳቦት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እግዚአብሔር የባቢሎናዊያንን ሠራዊት በደመሰሰ ጊዜ ኤር 28፡2

– ያህዌ- መቅደሽ እግዚአብሔር ቀዳሽ ለተቀደ ሕዝብ የተቀደሰ ሰንበት እንደምልክት ዘጸ 31፡13

ለ) ኤሎሂም ወይም ኤል፡ ብርቱ የሆነ

– ኤል ኤሊዩን – ልዑል እግዚአብሔር

መልከ ጼደቅ አብርሃምን ሲገናኘው ዘፍ 14፡18፣ 19 እዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ባለቤት እንደሆነ ተገልጻጿል የአስራት ስጦታ ለመጀመሪያ የተጠቀሰበት ስፍራ ነው ዘፍ 14፡20

– ኤል ኤሊዮን – ሉሲፈር  (በልዑል) እመሰላለሁ ብሎ ተናገረ ኢሳ 14፡14

– ኤል-ሻዳይ ብርታትን የሚሰጥ -አብርሃም በ99 አመቱ የልጅ ተስፋ ተሰጠው ዘፍ 17፡1

– ኤል- ኦላም ዘላለማዊው -አብርሃም ከፍልስጤማዊያን ጋር ስምምነት አደረገ ዘፍ 21፡33

– ኤል ጊቦር ብርቱዉ /ሃያሉ/ ስለሚመጣው መሲህ ትንቢት ኢሳ 9፡6 ከዚህ በተጨማሪ ድንቅ መካር (መካሪ) የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተሰኝቷል ኢሳ 9፡6

ሐ) አዶናይ ጌታ /አለቃ/

አብርሃም ስለልጅ እጦት መሚያጉረመንምበት ጊዜ- ዘፍ 15፡2

መ) እኔ አኔ ነኝ ወይም እኔ ነኝ ዘጸ 3፡14

ሙሴ፣ እግዚአብሔርን ለእስራኤላዊያን ምን ብሎ ማስተዋወቅ እንዳለበት ግራ በተጋባበት ጊዜ ዘጸ 3፡13

ሠ) ቀናተኛ ዘጸ 34፡14

እግዚአብሔር የጣኦት አምልኮን ይቃወማል

ረ) አባት ክፍል ለ7 ይመልከቱ

ሰ) ኢየሱስ (አዳኝ) ክፍል ለ8፣ ለ9፣ ለ10፣ ለ11 ይመልከቱ

ሸ) መንፈስ ቅዱስ ክፍል ለ12፣ ለ13 ይመልከቱ

Leave a Reply

%d bloggers like this: