ታላቂቱ አሜሪካ ወዴት እያመራች ይሆን???

በአሁኑ ሰአት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገቦች ታሪካዊ እውነቶች መሆናቸውን የሚያምኑ አሜሪካውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየቀነሰ መሄዱን አንድ የቀርብ ጊዜ ጥናት አመልክቷል። ለአብነት ያህል አሁን ምዕራባውያኑ ያሚያከብሩትን የገና በአል ብቻ እንኳን ብንወስድ፣ በ 2014 ኢየሱስ ከድንግል ማሪያም መወለዱን የሚያምኑት አሜሪካዊያን ቁጥር 73% የነበረ ሲሆን አሁን በምንሸኘው አመት (2017) ግን ይህ ቁጥር በ 7% ቀንሶ ታሪኩን አሜን ብለው ያሚቀበሉት ዜጎቿ 66% ደርሷል። ኢየሱስ ክርስቶስ በግርግም መወለዱን ያምኑ የነበሩት አሜሪካውያኑ ቁጥርም ከ 81% በ 2014 ወደ 75% (2017) መውረዱን ጥናቱ ይጠቁማል። ሰበአ ሰገል ኢያሱስን ለማግኘት በምስራቅ ኮከብ መመራታቸውን ያሚያምኑቱ ደግሞ ከ 75% በ 2014 ወደ 68% (2017) ወርዷል። የክርስቲያን አገር እንደሆነች በሚነገርላት ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ዛሬ ላይ፣ ማለትም በ2017፣ የእግዚአብሔር መልአክ የኢየሱስን ልደት ለእረኞች ማብሰሩን ያሚያምኑት ዜጎቿ ቁጥር 65% ያህሉ ብቻ ናቸው። ይህ ቁጥር በ 2014፣ 74% እንደነበር ጥናቱ አብሮ አመልክቷል።

ለመሆኑ የኢያሱስን የልደት ታሪክ ምን ያህል ያውቁታል? ካዚህ በታች ያለውን መመዘኛ በመስራት ራስዎን ይፈትሹ:-

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.