ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈበት ጊዜና ቦታ

ብዙዎቹ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መቼና የት እንደ ተጻፉ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምሑራን በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተጠቀሱትን ነገሮች በማገናዘብ ጊዜውን ለመገመት እንዲረዳቸው መጽሐፉን ይመረምራሉ። ይህም በኮሚኒዝም ዘመን የተጻፈ መጽሐፍ፥ ስደት በሌለበት ጊዜ ከተጻፈው የተለየ አሳብ ከሚያስተላልፉበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ነው።

1ኛ የውይይት ጥያቄ፡- በኮሚኒዝም ዘመን የተጻፉ መጻሕፍት፥ ቤተ ክርስቲያን ችግሮችን በምትጋፈጥበት በአሁኑ ጊዜ ከተጻፉ መጻሕፍት የሚለዩት በምንድን ነው? ለ) ይህ የወንጌላት ጸሐፊዎች ቤተ ክርስቲያን በዘመኑ ለምንቋቋማቸው ችግሮች መፍትሔ የሚሰጡትን ታሪኮችና ትምህርቶች እንደ መረጡ ለመገንዘብ የሚረዳን እንዴት ነው?

ቀደም ሲል እንደጠቀስነው ሁሉ ምሑራን የመጀመሪያውን ወንጌል ማን እንደ ጻፈውና መቼ እንደ ጻፈው ይከራከራሉ። አንዳንድ ምሑራን ማቴዎስ በመጀመሪያ የተጻፈ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ እንደሆነ ይናገራሉ። ማቴዎስ በአይሁዶች ላይ ስላተኮረ፥ መጽሐፉ ቤተ ክርስቲያን ወደ አሕዛብ አገሮች ከመስፋፋቷ በፊት ሳይጻፍ እንዳልቀረ ያስረዳል። ስለሆነም መጽሐፉ ከ50-55 ዓም. ባለው ጊዜ እንደ ተጻፈ ይገምታሉ። ማቴዎስ የማርቆስን ወንጌል ከመረጃ ምንጮቹ አንዱ አድርጎ እንደ ተጠቀመ ሲናገሩ፥ ሌሎች ምሑራን ግን መጽሐፉ ከ55-65 ዓ.ም. ባለው ጊዜ እንደ ተጻፈ ይናገራሉ። የማቴዎስ ወንጌል አይሁዶች ከ66-70 ዓ.ም. በሮም ላይ ከማመጻቸው በፊት በ60 ዓ.ም. ኣካባቢ የተጻፈ ይመስላል።

ምንም እንኳ ማቴዎስ ወንጌሉን በሚጽፍበት ጊዜ የት እንደ ነበረ ለማወቅ የምንችልበት መንገድ ባይኖርም፥ ምናልባትም በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም። መጽሐፉ ከሌሎቹ ወንጌላት ሁሉ የበለጠ የአይሁዳዊነት ጠረን ስላለበት፥ አብዛኞቹ ምሑራን በኢየሩሳሌም ውስጥ እንደ ተጻፈ ያስባሉ። ሌሎች ግን ከሶሪያዊቷ አንጾኪያ እንደ ተጻፈ ይናገራሉ።

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ አይ ኤም ከታተመውና የዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው)

1 thought on “ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈበት ጊዜና ቦታ”

Leave a Reply

%d bloggers like this: