የማርቆስ ወንጌል መዋቅርና አስተዋጽኦ

I. የማርቆስ ወንጌል መዋቅር

የማርቆስ መጽሐፍ ጴጥሮስ ስለ ክርስቶስ መሢሕነት በሰጠው ምስክርነት ላይ ያማከለ ይመስላል (ማር. 8፡29)። የቀረቡት ተአምራት ሁሉ፥ ሰዎች ክርስቶስ መሢሑ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲገነዘቡ የታሰቡ ናቸው። ከጴጥሮስ ምስክርነት በኋላ፥ የማርቆስ ወንጌል በመጭው የክርስቶስ ስቅለት ላይ ያተኩራል። ከመጽሐፉ ግማሽ ያህሉ ስለ ክርስቶስ የመጨረሻ ሳምንትና የመስቀል ላይ ሞት ይዘግባል።

ሌላው የመጽሐፉ መዋቅር መልክዐ ምድራዊ አቅጣጫ የተከለ ይመስላል። የመጽሐፉ የመጨረሻ አጋማሽ ክርስቶስ በሰሜን ፍልስጥኤም፥ ማለትም በገሊላና አካባቢዋ ባካሄደው አገልግሎት ላይ ሲያተኩር (ማር. 1-8፡30)። ሁለተኛው አጋማሽ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ባካሄደው አገልግሎትና በሞቱ ላይ ያተኩራል (ማር 8፡31-16፡20)።

II. የማርቆስ ወንጌል አስተዋጽኦ

የማርቆስ ወንጌልን አስተዋጽኦ በብዙ መንገዶች መመልከት ይቻላል። የሚከተለው አንድ መንገድ ነው።

1. የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለይፋዊ አገልግሎት መዘጋጀት (ማር. 1፡1-5)

2. ኢየሱስ በገሊላና በሰሜን የእግዚአብሔር ልጅነቱን ማሳየቱ (ማር. 1፡16-8፡26)

ሀ. ኢየሱስ አገልግሎቱን በገሊላ መጀመሩ (ማር. 1፡16-3፡6)

ለ ኢየሱስ በገሊላ ያካሄደው የኋለኛው አገልግሎት (ማር. 3፡7-6፡29)

ሐ ኢየሱስ አገልግሎቱን ከገሊላ ውጭ ማስፋፋቱ (ማር. 6፡30-8፡26)

3. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስ መሢሑ፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተገነዘቡ (ማር. 8፡27-30)

4. ኢየሱስ ለመሞት ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ (ማር. 8፡31-10፡52)

5. የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ማገልገሉ (ማር. 11፡1-13፡37)

6. ኢየሱስ በስቅላት መሞትና መነሣቱ (ማር. 14-16)

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

4 thoughts on “የማርቆስ ወንጌል መዋቅርና አስተዋጽኦ”

Leave a Reply

%d bloggers like this: