የሉቃስ ወንጌል አወቃቀር እና አስተዋጽኦ

፩. የሉቃስ መጽሐፍ አወቃቀር

የሉቃስ ወንጌል በአራት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል።

ሀ. የኢየሱስ ልደትና የልጅነት ጊዜ (ሉቃስ 1-2)

ለ. የኢየሱስ አገልግሎት በገሊላ (ሉቃስ 3፡1-9፡50)

ሐ. የኢየሱስ አገልግሎት ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ (ሉቃስ 9፡51–19፡27)

መ. የኢየሱስ አገልግሎት በኢየሩሳሌም (ሉቃስ 19፡28-24፡53)

፪. የሉቃስ መጽሐፍ አስተዋጽኦ

1. የሉቃስ ወንጌል መግቢያ (ሉቃስ 1፡1-4)

2. ኢየሱስ በምድር ላይ ላለው አገልግሎት ያደረገው ዝግጅት (ሉቃስ 1፡5-4፡13)

ሀ. የመጥምቁ ዮሐንስና የኢየሱስ መወለድና የልጅነት ጊዜ (ሉቃስ 1፡5-2፡52)

ለ. የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት (ሉቃስ 3፡1-20)

ሐ. የኢየሱስ መጠመቅና በመንፈስ ቅዱስ መሞላት (ሉቃስ 3፡21–4፡13)

3. የኢየሱስ አገልግሎት በገሊላ (ሉቃስ 4፡14-9፡9)

ሀ. ኢየሱስ መልካሙን የምሥራች ዐወጀ (ሉቃስ 4፡14–5፡16)

ለ. ኢየሱስ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ተጋጨ (ሉቃስ 5፡17-6፡11)

ሒ ኢየሱስ ለድሆች መልካሙን የምሥራች ዐወጀ (ሉቃስ 6፡12-8፡3)

መ. ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ገለጠ (ሉቃስ 8፡4-9፡50)

4. ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ (ሉቃስ 9፡51-19፡28)

ሀ. ኢየሱስ በይሁዳ አገለገለ (ሉቃስ 9፡51-13፡21)

ለ ኢየሱስ በጲሪያና አካባቢዋ አገለገለ (ሉቃስ 13፡22-19፡27)

5. የኢየሱስ የመጨረሻው አገልግሎት በኢየሩሳሌም (ሉቃስ 19፡28-24፡53)

ሀ. የኢየሱስ አገልግሎት ከስቅለቱ በፊት (ሉቃስ 19፡28–22፡46)

ሊ የኢየሱስ መያዝ፣ መመርመርና መሰቀል (ሉቃስ 22፡47-23፡56)

ሐ. የኢየሱስ ትንሣኤና ዕርገት (ሉቃስ 24)

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading