የዮሐንስ ወንጌል መዋቅር እና አስተዋጽኦ

፩. የዮሐንስ ወንጌል መዋቅር

በትምህርት ቤት ጥሩ ጽሑፍ ለማዘጋጀት መግቢያውን፥ ፍሬ ነገሩንና መደምደሚያውን በሚገባ ማዋቀር እንዳለብን አስተማሪዎቻችን ይነግሩናል። የዮሐንስ ወንጌልም በዚህ መንገድ የተዘጋጀ ነው።

  1. መግቢያ (ዮሐ 1፡1-18)። የነገረ መለኮት ምሑር የሆነው ዮሐንስ፥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እያስተማረ ነበር። በመሆኑም በመግቢያው ላይ ቃል የተባለው ኢየሱስ ከዘላለም ዘመናት በፊት ከእግዚአብሔር አብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ወደ ነበረበት ጊዜ ይወስደናል። አስደናቂው ሁኔታ ይህ ዘላለማዊ አምላክ ሥጋን በመልበስ በፍጥረቱ መካከል እንደ ሰው ኖረ።

ዮሐንስ የኢየሱስን ሕይወት ያጠቃለለው በጥቂት ዐረፍተ ነገሮች ነው። የእርሱ ወደሆኑት፣ ማለትም ወደ አይሁዶች ወይም ወደ ሰዎች ሁሉ ቢመጣም፣ እንደ አምላካቸው አውቀው አልተቀበሉትም። ነገር ግን የክርስቶስን አምላክነት ተረድተው በእምነት የተከተሉት ጥቂት ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን በቅተዋል።

  1. ፍሬ ነገር፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞትና ትንሣኤ (ዮሐ 1፡19-20፡31)። ዮሐንስ መጽሐፉን የጻፈበት ዓላማ ሰዎች ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ አምነው እንዲቀበሉት መሆኑን ገልጾአል። በዮሐ 1፡10-19፡42 ላይ ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶችንና ትምህርቶችን አቅርቧል። ከዚያም ዮሐንስ ዋንኛ የመረጃ አካሉን ከ13-20፡31 ይቀጥላል። ይህ ክፍል ኢየሱስ በሞቱ እንዴት እንደ ከበረ የሚያመለክት በመሆኑ፣ ምሑራን «የክብር መጽሐፍ» ብለው ይጠሩታል።
  2. መደምደሚያ፤ ጴጥሮስ የኢየሱስን ይቅርታ ተቀበለ (ዮሐ 21)። ጴጥሮስና ዮሐንስ የቅርብ ጓደኛሞች ነበሩ። ብዙውን ጊዜ በወንጌላትም ሆነ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ፥ ለምሳሌ ያህል፣ የሐዋ. 3) አብረው ተጠቅሰዋል። በዚህ ክፍል ዮሐንስ፥ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ የከዳውን ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ በመጥራት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪ እንዲሆን እንዳበረታታው ያስረዳል። በዚህ ታሪክ፣ ዮሐንስ አንዳንድ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ዮሐንስ ከመሞቱ በፊት ይመለሳል በማለት የተናገሩትን የተሳሳተ አሳብ ተቃውሟል።

፪. የዮሐንስ ወንጌል አስተዋጽኦ

  1. መግቢያ፤ (ዮሐ ፡1-18)
  2. የኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎት፣ የኢየሱስ ምልክቶችና ይፋዊ ትምህርቶች (ዮሐ 1፡19-12፡50)

ሀ. የመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት (ዮሐ 1፡19–34)

ለ. ኢየሱስ በመጀመሪያ ከጥቂት ደቀ መዛሙርት ጋር ተገናኘ (ዮሐ 1፡35-51)

ሐ. የኢየሱስ የመጀመሪያው ምልክት፤ ውኃን ወደ ወይን ጠጅ መለወጥ (ዮሐ 2፡1-11)

መ. ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን አጸዳ (ዮሐ 2፡12-25)

ሠ. ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር እንደ ተነጋገረ (ዮሐ 3)

ረ. ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር ተነጋገረ (ዮሐ 4፡1-42)

ሰ. የኢየሱስ ሁለተኛው ምልክት፡- ኢየሱስ የሹሙን ልጅ ፈወሰ (ዮሐ 4፡43-54)

ሸ. የኢየሱስ ሦስተኛው ምልክት፡- ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አንድ በሽተኛ መፈወሱና ለለ ራሱ ያቀረበው ትምህርት (ዮሐ 5) ቀ. የኢየሱስ አራተኛውና አምስተኛው ምልክት፡- ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ፤ በውኃ ላይ ተራመደ፥ አስተማረ ዮሐ 6)

በ. ኢየሱስ በመገናኛው ድንኳን በዓል ላይ አስተማረ ዮሐ 7-8)

ተ. የኢየሱስ ስድስተኛው ምልክት፡- ኢየሱስ ዐይነ ስውሩን ፈወሰ፥ አስተማረ (ዮሐ 9)

ቸ. መልካሙ እረኛ ኢየሱስ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ተከራከረ (ዮሐ 10)

ኀ. የኢየሱስ ሰባተኛው ምልክት፡- ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፥ አስተማረ (ዮሐ 11)

ነ. ኢየሱስ ለመጭው ሞቱ ሲዘጋጅ፡- በድል ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱና በማርያም መቀባቱ (ዮሐ 12)

  1. የኢየሱስ ይፋዊ ያልሆነ አገልግሎት፡- ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አስተማረ (ዮሐ 13-17)

ሀ. ኢየሱስ ፋሲካን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በላ (ዮሐ 13)

ለ. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመጭው ሞቱ አዘጋጀ (ዮሐ 14-16)

ሐ. ኢየሱስ ለራሱና ለደቀ መዛሙርቱ ወደ እግዚአብሔር አብ ጸለየ (ዮሐ 17)

  1. የኢየሱስ መታሰር፡- መመርመርና የጴጥሮስ ክህደት ዮሐ 18)
  2. ኢየሱስ ለዓለም ኃጢአት እንደ ፋሲካ በግ ሞተ (ዮሐ 19)
  3. የኢየሱስ ትንሣኤ (ዮሐ 20)
  4. ኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን አገለገለ (ዮሐ 21)

ሀ. ኢየሱስ 153 ዓዎችን በማስገኘት የፈጸመው ተአምር (ዮሐ 21፡1-14)

ለ. ኢየሱስ ጴጥሮስን ለተልዕኮ አሰማራ (ዮሐ 21፡15-25)

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

Leave a Reply

%d bloggers like this: