የዮሐንስ ራእይ መዋቅር እና አስተዋጽኦ

፩. የዮሐንስ ራእይ መዋቅር 

የውይይት ጥያቄ፡– ራእይ 1፡19 እንብብ። እግዚአብሔር ለዮሐንስ ራእዩ የሚሸፍናቸውን ሦስት ክፍለ ጊዜያት ነግሮታል። እነዚህን ክፍለ ጊዜያት ዘርዝር።

የዮሐንስ ራእይ በጥሩ ሁኔታ የተዋቀረ መጽሐፍ ነው። የዮሐንስ ራእይ ሦስት መሠረታዊ ክፍሎች አሉት።

 1. መግቢያና ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት የተላኩ ደብዳቤዎች (ራእይ 1-3)። ራእይ 1፡19 ዮሐንስ ስለ አሁኑ ጊዜ የተመለከተውን ከራሱ እይታ አንጻር መጠየቁን ያስረዳል። ዮሐንስ 7 ደብዳቤዎችን በእስያ ውስጥ ለሚገኙ 7 አብያተ ክርስቲያናት ይጽፋል። ዮሐንስ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ታላቁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እየተመለከታቸው መሆኑን በመግለጽ ያስጠነቅቃቸዋል። ዮሐንስ የአብያተ ክርስቲያናቱን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ለይቶ ያውቅ ነበር። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጤነኛ ያልሆኑትን አብያተ ክርስቲያናት ያስጠነቅቃቸዋል። ለጌታ ጸንተው የቆሙትን ደግሞ ያበረታታቸዋል።
 2. ክርስቶስ እስኪመለስ ድረስ የዓለም ታሪክ ምን እንደሚመስል (በራእይ 4-19)። በራእይ 1፡19፥ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ ይሆን ዘንድ ስላለውም ይጽፋል። እነዚህ ምዕራፎች ኢየሱስ ክርስቶስ የታሪክን ቁጥጥር ከእግዚአብሔር አብ መቀበሉን ያሳያሉ። የዚህ የወደፊት እይታ ማዕከላዊ ትኩረት በሦስት ፍርዶች (ማኅተም፥ መለኮት፥ ጽዋ) እና በሦስት አካላት (ሰይጣን፥ ሐሳዊ መሢሕ፥ ሐሰተኛ ነቢይ) ላይ ያነጣጠረ ነው። እነዚህም ከታሪክ መጨረሻ ላይ የሚከሰቱ ናቸው።

ምሁራን እነዚህን ሦስት ዓይነት ፍርዶች ታሪክን በቅደም ተከተል በመግለጽ መጀመሪያ የማኅተምን ፍርድ፥ ቀጥሎ የመለከት ፍርድና በ3ኛ ደረጃ የጽዋ ፍርድ የሚያስተናግዱ ወይም ሦስቱም ፍርዶች በተመሳሳይ ጊዜ የሚካሄዱ ስለመሆናቸው ይከራከራሉ። ሦስቱ ፍርዶች በቅደም ተከተል የሚካሄዱ ከሆነ፥ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ፍርዶች ወቅት ሰባተኛው ፍርድ ሁለተኞቹን ተከታታይ ፍርዶች ያስጀምራል። ሰባተኛው ፍርድ በዝርዝር የተገለጸው በጽዋ ፍርዶች ውስጥ ብቻ ነው።

ወይም ደግሞ እነዚህ ሦስት የፍርድ ዓይነቶች በተመሳሳይ ጊዜ የሚፈጸሙ ሊሆኑ ይችላሉ። የማኅተም ፍርዶች ስለመጨረሻው ዘመን ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ። የመለከት ፍርዶችና የጽዋ ፍርዶች ከፍርዱ ክፍል ጊዜ በመጨረሻው ክፍል ለሚሰሙት የእግዚአብሔር ፍርዶች ዝርዝር ሃሳቦችን ያቀርባሉ። ሦስቱም ፍርዶች የሚጠቃለሉት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ነው።

 1. የክርስቶስ መንገሥና አዲሱ ሰማይና ምድር (ራእይ 20-22)፡፡ ዮሐንስ የመጨረሻውን ዘመን በመጽሐፍ ውስጥ ገልጾታል። ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ምድራዊ መንግሥት ቢገልጽም፥ የበለጠ አጽንኦት የሰጠው ሁሉም አዲስ ስለሚሆንበት የዘላለም መንግሥት ነው። በዚህ መንግሥት ውስጥ እግዚአብሔር ከሰው ጋር አብሮ የሚኖር ሲሆን፥ ክፋትም ሆነ ሥቃይ አይታሰብም።

(ማስታወሻ፡ ዮሐንስ መጽሐፉን ያደራጀባቸው ልዩ መንገዶች አንዱ ተያያዥነት ያሏቸውን ራእዮች ሌሎች ተያያዥነት የሌላቸው ራእዮች እንዲያቋርጡ በማድረግ ነው። ከዚያም ተመልሶ የተቋረጡትን ተከታታይ ራእዮች ያሟላና ወደ ሌሎች ተከታታይ ራእዮች ያልፋል። ምሁራን እነዚህን ማቋረጫዎች የእረፍት ጊዜ ሲሉ ይጠሯቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ6ኛው ማኅተም ፍርድ መጨረሻ ላይ (ራእይ 6፡17) ዮሐንስ ወደ 7ኛው ማኅተም ከመመለሱ በፊት ሁለት ሌሎች ራእዮችን ያቀርባል (ራእይ 7፡1-8፡1)። እነዚህ ቅንፎች ወይም የእረፍት ጊዜዎች በራእይ 10፡1-11፡14 ውስጥም ይገኛሉ።) 

፪. የዮሐንስ ራእይ አስተዋጽኦ 

 1. መግቢያ (ራእይ 1፡1-8) 
 2. ክርስቶስ በእስያ ለሚገኙ 7 አብያተ ክርስቲያናት ያስተላለፈው መልእክት (ራእይ 1፡9-3፡22) 

ሀ. መልእክቱን ለአብያተ ክርስቲያናት የሚያስተላልፈው የክርስቶስ ራእይ (ራእይ 1፡9-20) 

ለ. ለ 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት የተላኩ መልእክቶች (ራእይ 2-3) 

 1. እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ የሚታይበት ራእይ (ራእይ 4-5)

ሀ. የእግዚአብሔር አብ ራእይ (ራእይ 4)

ለ. አንበሳና በ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ (ራእይ 5) 

 1. የ7ቱ ማኅተም ፍርዶች (ራእይ 6፡1-8፡1)

ሀ. 6 የማኅተም ፍርዶች (ራእይ 6) 

ለ. ቅንፍ (ራእይ 7፡1-8፡1)

 1. የ144 ሺህ ሰዎች መታተም (ራእይ 7፡1-8)
 2. በሰማይ ያሉ እጅግ ብዙ ሰዎች (ራእይ 7፡9-17) 

ሐ. 7ኛው ማኅተም (ራእይ 8፡1) 

 1. 7 የመለከት ፍርዶች (ራእይ 8፡2-11፡19)

ሀ. የ6 መለከት ፍርዶች (ራእይ 8፡2-9፡21) 

ለ. የእረፍት ጊዜ (ራእይ 10፡1-11፡14)

 1. መላኩና ትንሿ የመጽሐፍ ጥቅልል (ራእይ 10)
 2. ሁለቱ ምስክሮች (ራእይ 11፡1-14) 

ሐ. 7ኛው የመለከት ፍርድ (ራእይ 11፡15-19) 

 1. መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ተሳታፊዎች (ራእይ 12-14)

ሀ. በሴቲቱ እና በዘንዶው መካከል የተካሄደ ጦርነት (ራእይ 12) 

ለ. ከባህር የወጣው አውሬ (ራእይ 13፡1-10) 

ሐ. ከመሬት የወጣው አውሬ (ራእይ 13፡11-14)

መ. በጉና 144 ሺህ ሰዎች (ራእይ 14፡1-5)

ሠ. መላእክት ምድርን በፍርድ ሲያጭዱ (ራእይ 14፡6-20) 

 1. የጽዋ ፍርዶች (ራእይ 15–16) 
 2. የባቢሎን ውድመት (ራእይ 17-18) 
 3. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት (ራእይ 19)
 4. አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር (ራእይ 21፡1-22፡6) 
 5. የክርስቶስ የሺህ ዓመት አገዛዝ (ራእይ 20፡1-15) 
 6. ማጠቃለያ፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተስፋ (ራእይ 22፡7-20)

የውይይት ጥያቄ፡- የዮሐንስ ራእይን መዋቅርና አስተዋጽኦ አጥና። ይህ ዮሐንስ መጽሐፉን እንዴት እንዳደራጀ ለመረዳት ያስችለናል። 

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

Leave a Reply

%d bloggers like this: