2ኛ ቆሮ.4:13-18

ጥያቄ 10. ቁጥር 13ን ሐዋርያው የጠቀሰው ከየት ነው? 

ጥያቄ 11. በቁጥር 13 ላይ የተነገረው የእምነት መንፈስ ምንድነው? 

ጥያቄ 12. በቁጥር 16 ላይ የውጭና የውስጥ ሰውነት ሲል ምንና ምንን ይጠቅሳል? 

ጥያቄ 13. ቁጥር 17ንና 18 በራስህ አማርኛ አብራራ። 

በቁጥር 13 ላይ «አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ» የሚለውን ቃል ሐዋርያው ከመዝሙረ ዳዊት 118(116):1 ላይ ይጠቅሳል። ይህ መዝሙር የተጻፈው እግዚአብሔር ከመከራ ባዳነው ሰው ነው፡፡ የሀሳቡን ዝርዝር ለማየት መዘሙር 115(16)ን በሙሉ አንብብ። የሐዋርያው እምነትና የመዝሙረኛው እምነት አንድ ነበር፤ «ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን»። መዝሙረኛውም ሐዋርያውም ሙታንን በትንሣኤ በሚያነሣ አምላክ እምነታቸውን ጥለው በር። 

ይህ እምነት በትንሣኤ የማመን እምነት መሆኑን ሐዋርያው በቁጥር 14 ላይ ገልጿል። «ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛንም እንዲያነሣን» ሲል የእርሱም የመዝሙረኛውም እምነት እግዚአብሔር የሙታንን ትንሣኤ የሚሰጥ መሆኑን ማምን እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡ ይህ የሐዋርያው በትንሣኤ ማመን የቆሮንቶስም ምእመናን እንደሚካፈሉ ይመሰክርላቸዋል። ስነዚህ ይህ የትንሣኤ እምነት ከአማኝ ወደ አማኝ በምስክርነት ይተላለፋል ማለት ነው። “አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ” ማለቱ መሰከርሁ ማለቱ ነው። የቆሮንቶስም ሰዎች ምስክርነቱን ሰምተው ሙታንን በሚያነሣው አመኑ፡፡ ስለዚህ እነርሱም የትንሣኤ ተስፋ ተካፋዮች ሆኑ። 

ይህ በትንሣኤ ማመን አለመታከትን ወይም ተስፋ አለመቁረጥን ይሰጣል። ቁጥር 16 «ስለዚህም አንታክትም» ይላል። የውጭ ሰውነት ማለቱ በገላ.5፡11-19 እንደተጻፈው «ሥጋ» ማለቱ አይደለም። ሰውነት ሲል ይህን የለበስነውን አካል ማለቱ ነው። እንግዲህ በዚህ ዓለም ስንኖር ሰውነታችን እያረጀና እየወደቀ ይሄዳል። ግን በትንሣኤ ስለምናምን የውስጥ ሰውነታችን እየታደሰ ይሄዳል። የውስጥ ሰውነት ማለትም በመንፈስ ቅዱስ የታደሰችው ነፍሳችን ማለት ነው። በክርስቶስ የሚያምን ሰው የዚህ ዓለም ኑሮው ወደ ማለቁ ባዘነበለ ቁጥር በመንፈሱ እየታደሰ መሄድ አለበት እንጂ በመንፈሱ እየተሸበረ መሄድ የለበትም። ክርስቲያን እውነተኛ ኑሮውን የሚጀምረው ከዚህ ዓለም በኋላ ነው። እንዲያውም ክርስቲያን በዚህ ዓለም መከራ በተቀበለ ቁጥር የሚመጣውን ክብር ማሰብና ይህን የዚህን ዓለም መከራ መናቅ አለበት። ይህን ሃሳብ በቁጥር 17 እና 18 ላይ ዘርዝሮአል። 

ጥያቄ 14. ሀ/ አንድ ክርስቲያን ዓይኑን በማይታየው ነገር ላይ ማቅናት ያለበት ለምንድነው? ለ/ እዚህ የማይታዩት ነገሮች ምንድናቸው? ሐ/ ለጊዜው ብቻ የሚቆዩት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading