ቤተ ክርስቲያን በሚለው ፅንሰ አሳብ ውስጥ የሚካተተው ምንድነው?

እንዳንድ ክርስቲያኖች የሥነ-መለኮት ሰዎች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት ግራ የተጋቡ ይመስላሉ። ብዙ አማኞች ስለ ቤተ ክርስቲያን ያላቸው እውቀት፥ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትገኝበትን አካባቢ ከማወቅና የአምልኮ ቦታችን ነው ብሎ ከመናገር የሚዘል አይደለም። የሥነ-መለኮት ሰዎች፣ ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረች በሚለው መሠረታዊ ነጥብ ላይ ግራ ተጋብተውና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር፥ ግብና እንቅስቃሴዋ የተለያየ አሳብ ይዘው እናገኛቸዋለን። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በብዙዎች ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ከእንግዲህ የምትሰጠው ጥቅም የለም፤ እሷ የምትሰጠውን አገልግሎት ሌሎች ድርጅቶች ሊሠሩት ይችላሉ የሚል አመለካከት አለ። 

በስሕተት ለተሞላ ለዚህ አመለካከት የሚሰጠው መልስ፥ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሚሠራውን ሥራ አላቋረጠም የሚል ይሆናል። የቱንም ያህል በስሕተት ብትወድቅና ዓለማዊ ብትሆን፥ ክርስቶስ አሁንም በቤተ ክርስቲያን ሊሠራ ይፈልጋል (ራእይ 2-3)፤ እግዚአብሔር ለሥራ የመረጣቸው ሁለት ድርጅቶች፥ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ናቸው። ይህ ሲባል ግን እግዚአብሔር እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች ድርጅቶች አይጠቀምም ማለት ሳይሆኑ የመጀመሪያ ዓላማዎቹን ለማከናወን የሚጠቀምባት ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ለማጠናከር ነው። ቤተ ክርስቲያንን ስንተው የእግዚአብሔርን ድርጅት መተዋችን ነው (1ኛ ጢሞ. 3፡15)። 

ቤተ ክርስቲያን ብለን የተረጎምነው የግሪክ ቃል ከሁለት ቃላት የተውጣጣ ሲሆን ትርጉሙ “የተጠሩ” ማለት ነው። ጐባኤ ወይም ስብሰባ ማለትም ይሆናል። የማን ጉባኤ? የሚለውም ጥያቄ መልስ ይሻል። ስለሆነም ጕባኤ የሚለው ቃል እንደ ሌሎቹ ጠቃሚ ቃላት ሁሉ ሊብራራ ይገባል። 1. አንዳንድ ጊዜ (በአዲስ ኪዳን እንኳን) የአንድ ከተማ ጉባኤ ስንል፥ ለተወሰነ ዓላማ የተጠራ የሕዝብ ስብሰባ ማለት ይሆናል (ሐዋ. 19፡32፥ 39፣ 41)፣ 2. በአንድ ወቅት ደግሞ፥ በበረሃ የተደረገን የአይሁድ ሕዝብ ጉባኤ በማስመልከት ተጽፏል (ሐዋ. 7፡38)፤ 3. ብዙ ጊዜም በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ክርስቲያኖችን ለማመልከት አገልግሏል (1ኛ ቆሮ. 1፡2፤ 1ኛ ተሰ. 1፡1፤ ራእይ 1፡11 እና ሌሎችም) 4. በመጨረሻም “ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ቃል “ሁሉን አቀፍ የሆነች ቤተ ክርስቲያን” የሚል ትርጉም ተሰጥቶት ይገኛል። ይህም በሁሉም ዘመናት የነበሩ የሰው ዘሮችን በሙሉ የሚያካትቱ አማኞችን ማለት ሲሆን “የክርስቶስ አካል” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው (ማቴ. 16፡18፤ ኤፌ. 1፡22-23፤ 3፡10፥ 21፤ 5፡23፥ 25፣ 27፥ 29፥ 32፤ ቈላ. 1፡18፤ ዕብ. 12፡23) መሆኑን ያመለክታል። 

ሲጠቃለል “ቤተ ከርስቲያን” የሚለው ቃል ሰዎች የሚሰበሰቡበት ቤት ሳይሆን፥ ለጉባኤ የተጠሩ ሰዎች እንደማለት ነበር። የጉባኤው ዓይነት ቃሉ ከሚገኝበት ምንባብ ይዘት የሚታወቅ ይሆናል። የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከላይ 3ኛውና በ4ኛው ተራ ቁጥር የተጠቀሱትን ብቻ ያካትታል።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.