በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስፍራ

በአንድ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ ቆሞ መንገዱ ወደ የት እንደሚወስድ ለመናገር መሞከር እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ወደፊት ለማየት የምንችለው ጥቂት እርምጃ ዎች ብቻ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ከተራራ ጫፍ ላይ ቆመን የአንድን መንገድ አቅጣጫ ብናጠና ያ መንገድ ወደ የት እንደሚወለደን መመልከት እጅግ ቀላል ነው። ስለ መንፈስ ቅዱስ በምናደርገው ጥናት ወደ የት እንደምንሄድ ለመረዳት ትምህርታችን ወደ የት እንደሚወስደን በአጭሩ መረዳት ያስፈልገናል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥናታችንን የምንጀምረው የምንመለከታቸውን ዋና ዋና እውነቶች በሰፊው በመቃኘት ይሆናል። ይህም የጥናት መጽሐፋችን እንዴት እንደተዋቀረ ለመመልከት ያግዘናል። 

«መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?» የሚል ጥያቄ እናነሣለን። እካላዊ ህልውና የሌለው ኃይል ብቻ ነውን? ወይስ ሕያው የሆነ አካል ያለው ህልውና የሥላሴ ሦስተኛው አካል ነው? ቀጥላን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን፥ በአራቱ ወንጌላት በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የታየውና በሐዋርያት ሥራ የሚያስተምረውን በአጭሩ እንቃኛለን። ሰማያቋርጥ ተከታታይነት እየተገለጠ እንደሚመጣ ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስን እየቀጠልን ስናነብ ስለ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ እየተማርን እንሄዳለን። ከዚያ በመቀጠል የመንፈስ ቅዱስን አገልግሎት ከፋፍለን እንመለከተዋለን። ክርስቲያኖች ባልሆኑ ሰዎች መካከል እንኳ ስላለው ተግባር እናያለን። እያንዳንዱን የዳነውን ሰው ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወዳለ ግንኙነት እንዴት እንደሚመራው እንመለከታለን። ቀጥለን አንድን ክርስቲያን ክርስቶስን ወደ መምሰል እንዲያድግ በሕይወቱ የሚሠራበትን፥ ክርስቶስ እያንዳንዳችን እንድንሠራ የሚፈልጋቸውን ነገሮች፥ በክርስቲያን ውስጥና በክርስቲያን አማካኝነትየሚሠራበትን በርካታ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች እንመለከታለን። ከዚያ በመቀጠል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በተለይ ደግሞ በቤተ ክርስቱያን ውስጥ የተለያዩ ውዝግቦች የሚያስነሡትን ማለትም ሰልሳን የመናገር፥ የፈውስና የትንቢት ስጦታዎችን እንመለከታለን። ጥናታችንን የምናጠቃልለው በየዕለቱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዴት መመላለስ እንደምንችል በመመልከት ይሆናል። 

ጥያቄ፡– ያለፈውን አንቀጽ አንብብ። በዚህ መጽሐፍ በምንመለከታቸው እያንዳንዱ ዋና ርእሶች እግዚአብሔር እንዲያስተምርህ ጸልይ። 

ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ሥራዎች በሙሉ እንዴት አስፈላጊና ጠቃሚ እንደሆነ እንመለከታለን። ዛሬ በዓለም ላይ መንፈስ ቅዱስ ስላለው ሁለት ዋና ተግባራት በአጭሩ እንጠቅሳለን። 

ጥያቄ፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ ላታስብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው አሳብ ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ ምን ይመስላል? ምን ለመሥራት ይሞክራል? 

እንደ ክርስቲያኖች አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችን ስለ እግዚአብሔር እብና ደኅንነታችንን ስለዋጀው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነትና ምን እንደሚሠራ ለማሰብ የምንወለደው ጊዜ በጣም አነስተኛ ነው። ይህም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ስጥንቃቄ ብናጠና በእያንዳንዱ የእዲስ ኪዳን ገጽ ላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ እናነባለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ተቀዳሚ አትኩሮት ባይሆንም እንኳ ለላ መንፈስ ቅዱስ የተጠቀሱ እውነቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ትምህርቶች ሁሉ ጋር እጅግ ክመጣመራቸው የተነሣ መንፈስ ቅዱስ እግዚእብሔር በሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ውስጥ ገቢራዊ ተሳትፎ አለው። 

ለምሳሌ፡- በአዲስ አበባ የምትኖር ሆነህ አንድ ቆንጆ ባለ 10 ፎቅ ሕንነ ተመላክትህ እንበል። – ይህን ሕንፃ ማን ሠራው? ከየት ተገኘ? እንዴት ህልውና ሊያገኝ ቻለ? ሕንፃውን እንደገነቡ የምናስባቸው በርካታ የተለያዩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ሕንፃውን በአእምሮው በመቅረጽ ስሕንፃው ሥራ መጨረሻ መካተት አለባቸው ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በሙሉ ጨምሮ ሕንፃውን በወረቀት ላይ ያሰፈረው የንድፍ መሐንዲሱ (አርክቴክቱ) ይኖራል። ባንድፍ መሐንዲሱ የተሠራው ነገር በሙሉ በታሰበው መንገድ በሥራ ላይ መዋሉን የሚያረጋግጥ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ይኖራል። በመጨረሻ ሥራውን በመሥራት ሕንፃው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርጉት ግንበኞች፥ አናፂዎች የኤሌክትሪክ ሠራተኞች ወዘተ… ይኖራሉ። 

ይህ መግለጫ ሥላሴዎች እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዴት እብረው እንደሚሠሩ ለማሳየት ጥሩ ምሳሌ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በቅርበት ስንመረምር ማናቸውንም ዋና የሚባሉ ተግባራት ሥላሴ አብረው እንደሚሠሩት ያሳየናል። እግዚአብሔር አብ እንደ ንድፍ አውጪው መሐንዲስ ሆኖ ምን እንደሚፈጸም ይወስናል። እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር አብ ዕቅድ ይፈጸም ዘንድ የበላይ ተቆጣጣሪ ሆኖ እንደሚመለከተው ተቋራጭ ነው። መንፈስ ቅዱስን ደግሞ የእግዚአብሔር አብና የእግዚአብሔር ወልድን ዓላማና ዕቅድ ወደ እውነታ የሚተረጉም የሕንፃው ሠራተኛ ሆኖ እንመለከተዋለን። መንፈስ ቅዱስ ለሕንፃው ሥራ እንደ ተቆጣጣሪ በመሆን በሠራተኞች ማለትም በእግዚአብሔር ልጆች አማካኝነት የሚያከናውናቸው ሌሎች የእግዚአብሔር ሥራዎችም አሉ። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 1፡1-2 እና ቆላ. 1፡16-17፤ ሉቃስ 1፡35 እና ዮሐ 3፡16፤ ዮሐ 6፡35-40 እና ቲቶ 3፡3-7። እነዚህ ጥቅሶች ሥላሴዎች አንድ ነገር በመፈጸም እብረው እንዴት እንደሚሠሩ ምን ያሳዩናል? 

የሥላሴ አካላት በሙሉ ያልተሳተፉበት የእግዚአብሔር ሥራ ምናልባት አይኖር ይሆናል። ክሥላሴ አካላት አንዳቸው ለአንድ ሥራ ተቀዳሚ ኃላፊነት የሚወስዱ ቢሆንም እንኳ (ለምሳሌ ለኃጢአታችን የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው) የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ሁሉ በአንድነት ስናጣምራቸው የቀሩትም የሥላሴ አካላት እንደተሳተፉበት እናየላን። 

ሥላሴዎች የእግዚአብሔርን ዕቅዶች ለመፈጸም እንዴት እንደ ሠሩ ሦስት ምሳሌዎችን እንመልከት። 

1. የመፍጠር ሥራ፡- መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ጊዜ እንደምንመለከተው እያንዳንዱ የሥላሴ አካል በመፍጠር ሥራ ተካፍሏል። በዘፍ 1፡1 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን እንዲፈጠረ ተገልጾልናል። በቆላ. 1፡16-17 ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንመለከታለን። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም በመዘጋጀት በውኃ ላይ እንደ ርግብ ሰፍፎ እንደነበር ተነግሮናል (ዘፍ 1፡2)። 

2. የክርስቶስ መወለድ፡ ዮሐ 3፡16 እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስን ወደዚህች ምድር እንደላከው ይነግረናል። ነገር ግን ዘላለማዊ ልጁ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በተአምራዊ መንገድ የሰው ሥጋ ይለብስ ዘንድ ድንግል ማርያም እንድትፀንስ ያደረገው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናነባለን (ሉቃስ 1፡35)። 

3. የአማኝ ድነት (ድነት (ደኅንነት))፡– ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን የሰጠን የትኛው የሥላሴ አካል ነው? ሦስቱም ናቸው። እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተካፋይ ነበሩ። እግዚአብሔር አብ፤ የሚያምኑትን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደሰጠ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ አንዳቸውም እንዳይጠፉ እንደሚጠብቃቸው (ዮሐ 6፡35-40) ተጽፎአል። ነገር ግን ከኃጢአት ያጠባንና ያነጻን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተነግሮናል (ቲቶ 3፡3-7)። 

እያንዳንዱ የሕይወታችን ክፍል የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ማኅተም አለው። የፈጠረን፥ ያበጃጀንና እከላዊ ህልውናችንን የዕጣን ቤተሰባችንን፥ እገራችንን፥ ዜግነታችንን ወዘተ… የመረጠ እርሱ ነው (መዝ (139) በእድገታችን ወቅት እየተከባከበን እርሱ የሚፈልገውን ዓይነት ሰው እንድንሆን የሕይወታችንን ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ያደራጀልን መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 5፡16)። በኃጢአት ሞቶ ወደ ነበረው ልባችን መጥቶ በመሥራት ክርስቶስ ለደኅንነታችን ያደረገውን ጥሪ እንድንሰማ ያደረገ በዚህም በኢየሱስ እንድናምን ልባችንን ያነሣሣና የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ ያስቻለንም መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 5፡26፤ 16፡6~1)። ኃጢአትን እንድናሸንፍ በየዕለቱ የሚያስፈልገንን ኃይል የሚሰጠን፥ (ሮሜ 8፡13) ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናገለግል ስጦታዎችን የሚሰጠን፥ ክርስቶስን ወደ መምሰል እንድንለወጥ የሚረዳንና እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ወደ መንግሥተ ሰማየት እስከሚወስደን ድረስ የሚጠብቀን እራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁን የያዝነውን እኛነታችንን ያበጀው ከሥላሴ አካላት አንዱ የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። አመስኑት! እወቁት! 

ጥያቄ፡– ከእግዚአብሔር የተቀበልካቸውን በረከቶችህን ዘርዝር። ይህን ፍቅር ያሳዩህንና በረከቶችህን የሰጡህን እያንዳንዱን የሥላሴ አካላት ለማመስገን ጊዜ ውሰድ። 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.