ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት፤ ክፍል 1

ለብዙ መቶ ዓመታት እግዚአብሔር ስለ አዲስ ዘመን የትንቢት መልእክት ተናር ነበር። ይህ አዲስ ዘመን የእግዚአብሔር መሢሕ በጽድቅ የሚገዛበት፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በሕዝቡ ሁሉ ላይ የሚሆንበት ዘመን ነበር። ኢየሱስ መጥቶ በመንፈስ ቅዱስ አመራር በሠራ ጊዜ ይህ ዘመን ደረሰ። አይሁድ የተጠባበቁትም ይህንኑ ነበር። ኢየሱስ የዳዊትን መንግሥት በገሃድ ላቋቋምና የርማን ጦር ሠራዊት ድል ለማድረግ የመጣው መሢሕ እንደሆነ ቆጠሩ። በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ግን ያ ሕልማቸው ከሰመ። ኢየሱስ የመጣው በምድር ላይ ሥጋዊ ንጉሥ ሆኖ ለመግዛት ሳይሆን ይልቁኑ ሰዎችን ከመንፈሳዊ ባርነት ለማዳን ነበር። 

መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ሕይወትና አገልሎት ውስጥ ገቢራን ተሳትና የነበረው ቢሆንም የመጣው እንደተተነበየው አልነበረም። በእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደም። ገር ን ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ሕይወት አይተው የመሰከሩለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ላይ እንደወረድ ተስፋ ሰጠ። የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ወዲያውኑ ቀጥሎ የሚመጣ ነበር። 

ጥያቄ፡- ሁለት ክርስቲያኖች ቡና እየጠጡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ይነጋገሩ ነበር። አንደኛው ሊናገር የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ተግባር ክርስቲያኖች በልሳን እንዲናገሩና የሥጋ ፈውስ እንዲያገኙ ጎድረግ ነው ይል ነበር። ሌላኛው ክርስቲያን ን ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረውን ላማሳየት መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጦ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመለከተ። እስኪ እንተ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንብብ። ማቴ 10፡20፤ ሉቃስ 11፡13፤ ዮሐ 1፡ 33፤ 7፡39፤ 14፡15-27፣ 26-27፤ 16፡5-16፤ 20፡22፤ የሐዋ. 1፡2፥5-8። ሀ) ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው ተስፋ ምን ነበር? ለ) ከላይ በተመለከትናቸው ጥቅሶች ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ተቀጻሚ አማላ ምንድን ነው ብሎ የሚያስተምር ይመስልሃል? ሐ) ለመጀመሪያዎቹ ይነት ክርስቲያኖች እንዴት ትመልስላቸዋለህ? 

የመጥምቁ ዮሐንስ ድምፁ በምድረ በዳ እንዳለ መላክት የመሢሑን የኢየሱስን መምጣት በሚያውጅበት ጊዜ የኢየሱስ የማጥመቅ አገልግሎት በሁላት ነገርች መለያነት ቀርቧል። የመጀመሪያው እሳት ሊሆን ኢየሱስ እንደ መሢሕነቱ የሚያመጣውን ፍርድ የሚያሳይ ነበር። ይህ አገልግሎት ኢየሱስ በመጀመሪያ በመጣበት ጊዜ የተፈጸመ ባይሆንም ጓግም በሚመጣበት ጊዜ ዋናው አገልግሎቱ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ይፈርጓል (ዮሐ 5፡22፥ 27 ተመልከት። 

ሁለተኛው ደጎሞ ኢየሱስ ተከታዮቹን በመንፈስ ቅዱስ ግጥመቁ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በሰው ሁሉ ላይ ይመጣል ከሚለው ትንቢት እኳያ ይህ የኢየሱስ አገልግሎት የጀመረው በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን በሰዎች ላይ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ምድርን ለቅቆ ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት አልነበረም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከአሥራ ሁላቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ስለነበረው ቀንኙነት በወንጌላት የተጠቀሰው በጥቂት ነው። ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር አብሮአቸው በነበረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር እንደሚኖር ተናግሯል (ዮሐ 14፡7)። ኢየሱስ በተጨማሪ እርሱ አብርአቸው እስካለ ድረስ መንፈስ ቅዱስ አብሮአቸው እንደማይኖርም ተናግሯል (ዮሐ 16፡7)። 

ዮሐ 3፡5-8 

ኢየሱስ ሕዝቡን በግልጽ ያገለገለበትን የሦስት ዓመት አገልግሎት ሲጀምር ደቀ መዛሙርቱን ለለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማራቸው እጅግ ጥቂት ነገር ነበር። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ በሕይወቱ ይሠራ ለለነበር በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሕይወቱ ምሳሌ ሆኖ በመኖር አሳያቸው። ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ የአገልግሎት ዘመን ቀልጽ የሆነ ውይይት ያደረገው በዮሐ 3 እንደተጻፈው ኒቆዲሞላ ከተባለ የአይሁድ መምህር ጋር በተገናኘ ጊዜ ነበር። በዚያ ለፍራ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የሚነግረው አዲስ መንፈሳዊ ልደትን ለሰው የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነና እንደ ነፋስም በፀጥታ እንደሚሠራ ነበር። 

ጥያቄ፡- ዮሐ 3፡5-8 አንብብ። ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ስፍራ ያስተምራቸው እውነተች ምን ምን ነበሩ? 

ኢየሱስ፤ ለደቀ መዛሙርቱና ለኒቆዲሞስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማራቸው የመጀመሪያ እውነት ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለማምጣት መንፈስ ቅዱስ የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና ነበር። አንድ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት አካል ለመሆን በመጀመሪያ በውኃ (የሥጋ ልደት) ቀጥሎ ደግሞ ከመንፈስ (መንፈሳዊ ልደት) መወለድ ያስፈልገዋል። መንፈስ ቅዱስ አዲስ ሕይወትን ለማስገኘት በሰው ውስጣዊ ኑባሬ፥ በመንፈሱ ውስጥ መሥራት አለበት። ይህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በሥራው እንደ ነፋስ ፀጥ ያለና ድብቅ (የማይታይ) ሲሆን ነገር ቀን ለውጡ ወይም የሥራው ውጤት በግልጽ ይታያል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ለሰዎች አዲስ ሕይወት የመስጠት አገልግሎቱን በሌላ ትምህርት በሚገባ እንመለከተዋለን። 

ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ ወደ ሰማይ የሚመለስበት ጊዜ እየቀረበ ስለነበር እርሱ በማይኖርበት ጊዜ እንዴት እንደሚቀጥሉ ያዘጋጃቸው ጀመር። ክመሰናበቱ በፊት ካስተማራቸው ዋነኛ እውነቶች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ጉዳይ ነበር። እነዚህን ትምህርቶች በጥንቃቄ ማጥናት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ስለ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ መምጣት የሚገባው ለምን እንደሆነ ቀልጽ ትምህርት ስለሚሰጡ ነው። በእዚህ ትምህርቶች በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ቀጻሚ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ናቸው ብለን ስለምናስባቸው፥ ስለ ፈውስና፡ በልሳናት ስለመናገር፥ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎችና ሌሎችም የተጠቀሰ ምንም ነገር አለመኖሩን ልብ ማለት ጥሩ ነው። ይልቁኑ ኢየሱስ ትኩረት ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር ስላለው ውስጣዊ ቀንኙነት፥ እንዴት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የእርሱን ህልውና እንደሚተካ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ተቀዳሚ ተግባር ለመረጓት ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ለደቀመዛሙርቱ የሰጠውን ትምህርት መገንዘብ ይጠቅማል። 

ስለ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ የሰጠው አብዛኛው ትምህርቱ በዮሐ ከ14-16 ባሉት ምዕራፎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን ይህም ከመሞቱ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በዋነኛነት የሰጠው የመጨረሻ ትምህርት ነው። ስለዚህ ከእነዚህ ሦስት ምዕራፎች ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያተኩሩትን ክፍሎች በጥልቀት እንመለከታለን፡፡ 

ዮሐንስ 14፡15-21 

ጥያቄ፡ ዮሐ 14፡15-21 በጥንቃቄ አንብብ። ሀ) በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ለመንፈስ ቅዱስ የሰጣቸውን የተለያዩ ስሞች ዘርዝር። እነዚህ ላሞች ስለ መንፈስ ቅዱስ ዓላማ ምን ምን ይነግሩናል? ለ) በመንፈስ ቅዱስና በደቀ መዛሙርት መካከል ምን ዓይነት የግንኙነት ለውጥ ሊደረግ ነበር? ሐ) መንፈስ ቅዱስን ላደቀ መዛሙርት የሚሰጥ ማን ነው? መ) መንፈስ ቅዱስ ክደቀ መዛሙርት ጋር የሚያየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? 

በዮሐ 14፡5-21 የሚገኘውን ትምህርት በአጭሩ ለማቅረብ ከሁሉ የተሻለው ዘዴ የተለያዩ ጥያቄዎችን መጠየቅና የዮሐንስ ወንጌል እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ በመመልከት ሳይሆን አይቀርም። 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ላይ የሚመጣው (የሚወርደው) እንዴት ነው? 

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በአብና በወልድ መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ያስተምር ነበር (ዮሐ 14፡9-14)። አብ በወልድ፡ ወልድም በአብ ውስጥ ነበር (ቁጥር 1)። ግንኙነታቸው በጣም የቀረበ ከመሆኑ የተነሣ አንዱ ሲሠራ ሌላውም ይሠራል። ሌላውን ፈጽሞ በማይጨምር መንገድ የተሠራ ሥራ የለም። የወልድ ዓላማ ለአብ ክብርን ማምጣት ነበር (ቁጥር 1)። ይህ እጅግ የቀረበ የጋራ ግንኙነት ኢየሱስ ከደቀመዛሙርት ጋር ለነበረው ንኙነት እንደ ምሳሌ መታየት ያለበት ነበር (ቁጥር 20)። ደቀ ወመዛሙርቱ ኢየሱስ ካደረጋቸው የሚበልጡ ነገሮችን ማድረግ ነበረባቸው (ቁጥር 2)። ይህ እውነት ሊሆን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ ከኖረ ብቻ ነበር። 

በደቀ መዛሙርት ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ለመግላጽ ኢየሱስ ሁለት ዋና ዐረፍተ ነገሮችን ተናግሯል። በመታዘዝ የተደገፈ ፍቅር ለኢየሱስ ማሳየት ነበረባቸው። ኢየሱስ ከዚህ ጥቂት ቆየት ብሎ እንደሚናገረው ለእርሱ ያላቸው ፍቅርና እርስ በርሳቸው በመካከላቸው የሚያሳዩት ፍቅር የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የመሆናችው የመጨረሻ ማረጋገጫ ነው (ዮሐ 15፡12-17፤ 17፡21-23)። ኢየሱስን ከወደዱት ኢየሱስ ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣቸው አብን ይጠይቃል። 

ሁለተኛ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ዋና ምንጭ እግዚአብሔር እብ እንደሆነ እንመለከታለን። ኢየሱስ ለአብ በሚያቀርበው ጥያቄ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ለደቀ መዛሙርት ይሰጣል። ስለዚህ በመጨረሻ የምንላው መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ እንደሚመጣ ነው። 

ለ. ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ሁለት ስሞች ምንና ምን ናቸው? 

1 ሌላው አጽናኝ፡- አብሮአቸው በአካል ሊኖር ለነበረው ኢየሱስ ምትክ እግዚአብሔር አብ ሌላው አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋን ሰጣቸው። በመጀመሪያው መንፈስ ቅዱስ ስም ሁለት ነገሮችን ልብ ማለት እንችላለን። በመጀመሪያ፥ ሌላው የሚለው ቃል ነው። ግሪኮች «ሌላው» የሚለውን ቃል በሁለት መንገድ ይጠቀሙበታል። የመጀመሪያው ቃል ሌላ ፈጽሞ ከመጀመሪያው የተለየ ማለት ሲሆን፥ ሁለተኛው አጠቃቀም ግን ሌላ ተመሳሳይ ነገርን ያመለክታል። በዚህ ስፍራ አገልግሎት ላይ የዋለው ቃል ሁለተኛውን ትርጉም የሚሰጠን ነው። መንፈስ ቅዱስ እንደ መጀመሪያው አጽናኝ ያላ አጽናኝ ነው። ይህ የመጀመረያው አጽናኝ ማን ነው? ላለፉት 3 1/2 ዓመታት ከደ ቀመዛሙርት ጋር የኖረው ጌታቸውና መምህራቸው የሆነው ኢየሱስ ነበር። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስን አገልግሎትና ሥራ ይቀጥላል። መንፈስ ቅዱስ የመጣው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ተክቶ ለመቀጠል ነው። 

ሁለተኛ፥ «አጽናኝ» ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ቃል ከግሪክ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ለመተርጐም እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቃል ነው። አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ቃሉን ወደ እንግሊዝኛ መልሰው ለመጻፍ እየተቸገሩ የግሪኩን ቃል እራሱን በመጠቀም «ጳራቅሊጦስ» የሚሉት ለዚህ ነው። ቃሉ እጅግ ሰፊና በርካታ ትርጉም አለው። «አጽናኝ»፥ «መካሪ»፥ «ረዳት»፥ ∫«ጠበቃ»፥ «አበረታች»፥ «ደጋፊ» ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። ትክክለኛው የቃሉ ትርጉም «በርዳታ ከጎን እንዲቆም የሚጠራ» እንደ ማለት ነው። ከተከሳሽ ጐን በመቆም በሕግ ፊት ለተከሰሰው ወገን የሚከራከር ጓደኛ ወይም የሕግ አማካሪ ማለት ነው። ይሁንና ኢየሱስ የሚለው ከዚህም ይልቃል። መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በመተካት ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ላደ ቀመዛሙርት ያደርግ የነበረውን ነገር ሁሉ ያደርግላቸዋል። በጀልባ ላይ ሳሉ ማዕበል ተነሥቶ ሊሰጥሙ ሲሉ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳዳናቸው ሁሉ ወመንፈስ ቅዱስም በችግሮቻቸው ሁሉ ይረዳቸዋል (ሉቃስ 8፡22-24)። 

መንፈስ ቅዱስ አማላጃቸው በመሆኑ ደቀ መዛሙርት ለራሳቸው መጸለይ በማይችሉበት ሁኔታ ይቃትትላቸዋል (ሮሜ 8፡26-27)። ያስተምራቸዋል፥ ይመራቸዋል፥ ይመክራቸዋል፥ ያጽናናቸዋል፥ ሌሎች ሊተውአቸው ሁልጊዜ የማይከዳ ጓደኛቸው ይሆናል። 

ጥያቄ፡– ሀ) ዛሬም ቢሆን እንደዚህ ዓይነት አጽናኝ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? ለ) ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሕይወትህ የተለማመድከው እንዴት ነው? 

2. የእውነት መንፈስ፡- ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በሚናገርበት ጊዜ እውነትን የሚከብ እንደሆነ መናገሩ የሚገርም ነው። የመንፈስ ቅዱስ ዋና አገልግሎቶች ስላልሆኑት ስለ ኃይልና ስለ ታምራት አልተናገረም። ይልቁኑ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እውነተኛነት ላይ አተኩሯል። ለዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ትኩረት ለመስጠት ዮሐንስ በዮሐ 5፡26 እና 16፡13 ላይ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ስም እንዴት እንደሚደጋግም ልብ በል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት እርሱ መንገድ እውነትና ሕይወት እንደሆነ ነግሮአቸዋል (ዮሐ 14፡6)። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ትቶአቸው ሊሄድ ቀን የሚያስተምራቸው ትክክለኛውንና ስሕተቱን እንዲያውቁ የሚረዳቸው አልነበራቸውም። ስለዚህ በሐሰት ትምህርቶች እንዳይወሰዱ መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆንና ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው ኢየሱስ ተናገር ነበር። 

ጥያቄ፡- ህ) ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች በሐሰት ትምህርቶች የሚወድቁባቸውን መንገዶች ጥቀስ። ለ) የእውነትን መንፈስ ማወቅና እውነትን ከእርሱ መማር ጠቃሚ የሚሆነው ለምንድን ነው? 

ሰ. ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ ባሕርያት ጥቂቶቹን ጥቀስ 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ ለዘላላም ክደቀ መዛሙርት ጋር እንደሚሆን ኢየሱስ ቃል ገብቷል። ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር የቆየው ለ3 12 ዓመት ብቻ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግን በቀረው የሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ከእነርሱ ጋር ይሆናል። በብሉይ ኪዳን ዘመን እንደነበረው ኃጢአት ሊያደርጉ እንኳ ወመንፈስ ቅዱስ ትቷቸው አይሄድም። ይህ የቅርብ ጓደኛ፥ አጽናኝ፥ መምህር፥ መሪና እማላጅ በልባቸው ማደሪያውን በማድረግ በፈተናቸው ሁሉ ሳይለያቸው እጅግ የቀረበ ይሆናል። 

ለ. የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትና ሥራ ከዓለም የተሰወረ ይሆናል። ዓለም ማለትም በኢየሱስ ላመኑ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ሊለማመዱትና ከእርሱ ጋር ኅብረት ሊያደርጉ አይችሉም። ከዚህ በተቃራኒ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥብቅ ኅብረት ይኖራቸዋል። ህልውናውን ያውቃሉ። ይለማመዳሉም። ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር በነበረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በመካክላቸው ነበር። መንፈስ ቅዱስ የተላማመዱት ኢየሱስ በመካከላቸው በነበረ ጊዜ በሕይወቱ ውስጥ የሚያደርገውን በመመልከት ነበር። አሁን ግን ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን በውስጣችሁ ይኖራል አላቸው። እያንዳንዳቸው ህልውናውንና ኃይሉን ሰቀላቸው ይለማመዱታል። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች በመካከላቸው ይመላለስ የነበረውን ኢየሱስን ይተካል። ኢየሱስ የክርስቲያኖች መንፈሳዊ አባት ነበር። እርሱ መካሪያቸው፥ አጽናኛቸውና መሪያቸው ነበር። ነገር ግን ትቶአቸው ወደ ሰማይ መሄዱ ስለነበር በሥጋዊ አካሉ በመካክላቸው የመገኘቱ ነገር አበቃ። በዚህ ምክንያት ወላጆቻቸው እንደሞቱባቸውና ብቻቸውን እንደቀሩ እንዲያስቡ ይጻጻቸዋል። ጉዳዩ ግን እነርሱ እንዳሰቡት አልነበረም። መንፈስ ቅዱስ ወደ ሕይወታቸው ሲመጣ ኢየሱስም ሰልባቸው ይኖራል። በዚህ እንደገና የሥላሴ አካላትን አንድነት እናያለን። በአንድ ሰው ልብ መንፈስ ቅዱስ አለ ማለት በልቡ ኢየሱስ አለ ማለት ነው። በተጨማሪ እግዚአብሔር አብ በልቡ ውስጥ ይኖራል ማለት ነው (ዮሐ 14፡23)። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከላይ የተገለጸው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በብሉይ ኪዳን ከነበረው አሠራሩ ጋር በምን ይለያል? ለ) ከላይ ሳለ መንፈስ ቅዱስ የተገለጡትን ሦስት እውነቶች ክርስቲያን በሕይወቱ እንዲያውቅና እንዲለማመደው የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? 

ዮሐ 14፡23-25 

ጥያቄ፡- የሐ. 14፡23-25 አንብብ። ከእነዚህ ቁጥሮች ስለ መንፈስ ቅዱስ የምናገኛቸው ተጣማሪ እውነቶች ምንድን ናቸው? 

ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ የእስራኤል ንጉሥ የሚሆነው መቼ ነው እያሉ ይገረሙ ነበር። የሮምን መንግሥታት አሸንፎ የዳዊትን ዙፋን በኢየሩሳሌም በመመሥረት የእስራኤል ፖለቲካዊ ንጉሥ መሆኑን የሚያሳየው መቼ እንደሚሆን በጉጉት ይጠባበቁ ነበር። ኢየሱስ ግን የበለጠ ያሳሰበው እርሱ ምድርን ትቶ ከሄደ በኋላ መቀጠል ስለነበረበት የቀድሞ ኅብረታቸው ነው። እርሱ የፈለገው መንፈሳዊ መሪያቸው መሆንን ነበር። ስለዚህ በእርግጥ ከወደዱት የሰጣቸውን ትእዛዛት በመጠበቅ እንዲኖሩ ነገራቸው። ለኢየሱስ ያላን ፍቅር እርሱን ከመታዘዝ ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ደቀ መዛሙርት ለኢየሱስ ያላቸውን ፍቅር በመታዘዝ ሲያረጋግጡ ምን ይሆናል? 

1. እሐዱ ሥሉስ የሆነው አምላክ ይመጣና ስልባቸው ይነግሣል። እግዚአብሔር አብና ወልድ (ቁጥር 23 ላይ ያለውን ብዙ ቁጥር ልብ በል ) ደግሞም መንፈስ ቅዱስ (ቁጥር 17) ሦስቱም በአማኙ ልብ ውስጥ ይኖራሉ። ሁሉም በኢየሱስ ደቀ መዝሙር ልብ ይኖራሉ። ያ ልብ የእግዚአብሔር ማደሪያ ይሆናል። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 6፡19 ላይ የእማኞችን ልብ የእግዚአብሔር «ቤተ መቅደስ» ብሎ ይጠራዋል። 

2. እግዚአብሔር አብ መንፈስ ቅዱስን በኢየሱስ ስም ይልካል። ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ ስም ስናስብ የሚገባን የኢየሱስ አካላዊ መጠሪያ (ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ) የሚለውን ስም ነው። ነገር ግን ይህንን አጠራር አይሁድ የሚረዱት በተለየ መንገድ ነበር። ምክንያቱም እነርሱ የእግዚአብሔርን ስም የሚገነዘቡት ባሕርይውንና ማንነቱን በሙሉ የሚወክል አድርገው ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ስም ስለ መጸለይ ሲናገር የሚያስገነዝበን የጸሎታችን ሥልጣን መሠረቱ የሚመነጨው ከኢየሱስ ሥልጣን፥ ከማንነቱና በእርሱ ለሚያምኑ ከሰጣቸው ሥልጣን መሆኑን ነው። ስለዚህ ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ስም እንደሚላክ ሲናገር መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ወኪል ሆኖ እንደሚመጣ ማመልከቱ ነበር። የኢየሱስ አፈ ቀላጤና ተወካይም እንደሚሆን ያሳያል። 

3. መንፈስ ቅዱስ ለልባቸው የሚሰጠው አገልግሎት ማስተማርንና ማሳሰብን ይጨምራል። ኢየሱስን በመታዘዝና ክብሩን በመግለጽ እንዲኖሩ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ያስተምራቸዋል። ጌታ ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስ እውነትን ሁሉ ያስተምራቸዋል ማለቱ አልነበረም ምክንያቱም ለእኛ ያልተገለጡ በርካታ እውነቶች አሉና (1ኛ ቆሮ. 13፡12)። ይልቁኑ ኢየሱስ ሊያስተምራቸው ሲችል ባለመዘጋጀታቸው የቀሩትን እውነቶች መንፈስ ቅዱስ እንደሚያስተምራቸው ደቀ መዛሙርቱ መታመን ይገባቸው ነበር። በተጨማሪ ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት 3 /2 ዓመታት ያስተማረውን በርካታ እውነቶች ያስታውሳቸዋል። አብዛኛዎቹ ትምህርቶች የሚረሱ ነበሩ። ይሁንና ለእውነት በመታዘዝ መኖር ይችሉ ዘንድ ጌታ ኢየሱስ ያሰተማራቸውን ጠቃሚ እውነቶች በሙሉ መንፈስ ቅዱስ ያስታውሳቸዋል። በአራቱ ወንጌላት በማቴዎስ፥ ማርቆስ፥ ሉቃስና ዮሐንስ ላይ እምነት እንዲያድርብን የሚያደርገው ይህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። እዚህ ወንጌላት መንፈስ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ወቅት የተናገረውንና ያደረገውን ደቀመዛሙርቱ እንዲያስታውሱ በማድረጉ የተገኙ ውጤቶች ናቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሦስት እውነቶች ለክርስቲያኖች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ለ) እዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ብዙ ክርስቲያኖች ዛሬ ስላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በሚናገሩበት ጊዜ ከሚያተኩርበት አገልግሎቶች የሚለየው እንዴት ነው? 

ዮሐ 15፡26-27 

ጥያቄ፡ ዮሐ 15፡26-27 አንብብ። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንማራቸው ተጨማሪ እውነቶች ምን ናቸው? 

ደቀ መዛሙርት የማያምኑ ሰዎች በብዙ ምክንያቶች ስደትን እንደሚያስነሱባቸው መጠበቅ እንዳለባቸው ኢየሱስ በግልጽ አስተምሯል። በመጀመሪያ ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱት ኢየሱስ ክርስቶስን ስለሚጠሉና ኢየሱስን የሚከተል ሁሉ የዚህ ጥላቻቸው ሰለባ ስለሚሆን ነው (ቁጥር 18-20)። በሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱት ከእግዚአብሔር አብ ጋር ኅብረት ስላ ሌላቸው ነው (ቁጥር 21-23)። ሦስተኛ ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱት ኃጢአታቸው ስለሚወቅሳቸው ነው። የኢየሱስ ሕይወትና ሥራ በተለይ ደግሞ የሚፈጽማቸው ተአምራት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ፤ መሐቶው መሆኑን ለማወቅ ለሕዝቡ እንዳልረዳቸው ማየት የሚያስገርም ነው። ተአምራት እውነትን መደገፍ ብቻ እንጂ ሰዎች እውነትን እንዲቀበሉ አያደርጉም። ነገር ግን ስለ ኢየሱስ መሢሕነት ማረጋገጫ የሆኑት ተአምራት ያላመኑትን ሰዎች ጥፋተኝነት ያጐላሉ። ኢየሱስ እርሱ እስከ ተገለጠበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች አልነበሩም ማለቱ አይደለም። አስቀድመውም ኃጢአተኞች ነበሩ። ሆኖም ግን ግልጽ የሆነውን የኢየሱስን ትምህርት ስላላገኙ ኢየሱስን ያዩትንና ለተአምራቱ ምስክሮች የሆኑትን ያህል ጥፋተኞች አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው በግልጥ የምናገኘው ዕድል (ኢየሱስን የማየት ወይም በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ የማደግ ወይም መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ) ሁልጊዜ ታላቅ ኃላፊነትና ታላቅ ፍርድን አጣምሮ ይይዛል። በኢየሱስ ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁድ ኢየሱስን በዓይናቸው ስላዩት፥ በእጆቻቸው ስለዳሰሱትና ተአምራትን ሲያደርግ ስለ ተመለክቱ ጥፋታቸው ትልቅ ነው። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ እንኳ በጥላቻ ሰቀሉት። 

ጥያቄ፡ ስለ ኢየሱስ ፈጽሞ ካልሰሙት የበለጠ ኃላፊነት ውስጥ የሚክቱህና ሊያስፈርዱብህ የሚችሉ የተቀበልኻቸው ልዩ ዕድሎችን ዘርዝር። 

አሁን ቀን ኢየሱስ ወደ አባቱ መሄዱ ነበር። ሰዎች ሁሉ እውነትን እንዲያውቁና ኢየሱስን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ውሳኔ እንዲያደርጉ የኢየሱስ ምስክርነት በሁሉም ስፍራ እንዲቀጥል ማድረግ እንዴት ይቻላል? ይህ ምስክርነት ሊቀጥል የሚችልባቸው ሁለት መንገዶች እንዳሉ ኢየሱስ ተናደአል። የመጀመሪያው መንፈስ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ይመሰክራል። ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አንዱ ለዓለም ስለ ኢየሱስ መናገር ነው። ስለዚህ አገልግሎት ተጨማሪ ነገሮች በሚቀጥለው የዮሐንስ ወንጌል ክፍል እንመለከታለን። 

[ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ዘንድ የተላከው ለራሱ መሆኑን ሲናገር ልብ በል። ቀደም ሲል፥ ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስ ከአብ የተላከው በእርሱ ስም እንደነበር ተናግሯል (ዮሐ 14፡26)። ይህ የሚያሳየን መንፈስ ቅዱስን በመላክ ሥራ እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ የነበራቸውን የቅርብ ግንኙነት ነው። ለዚህ ነው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እማኞች መንፈስ ቅዱስን ለክርስቲያኖች በመላክ አብና ወልድ እንደተሳተፉ የሚናገሩት። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሚወጣ ነው በማለት ታስተምራለች።] 

በሁለተኛ ደረጃ ደቀ መዛሙርት ስለ ኢየሱስ እንደሚመሰክሩ ተጽፏል። ኢየሱስ በዮሐንስ መጥምቁ እጅ ከተጠመቀበት ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ እስከ መስቀል ሞቱ ድረስ ደቀ መዛሙርት ከኢየሱስ ጋር ነበሩ (የሐዋ. 1፡21-22)። የሠራውን በሙሉ ተመልክተዋል። ስለዚህ ለኢየሱስ ተቀዳሚ ምስክሮች ደቀ መዛሙርት ነበሩ። ዮሐንስ ለአብያተ ክርስቲያናት በጻፈው መልእክቱ ኢየሱስን እንዳየውና እንደ ዳሰሰው፥ ስለዚህም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለመመለክር ብቁ እንደሆነ የተናገረው ለዚህ ነበር (1ኛ ዮሐ 1፡1)።  

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈስ ቅዱስ ለአንተም ሆነ ለማያምን ሰው ስለ ኢየሱስ ሲመሠክር ያየኸው እንዴት ነው? ለ) በዮሐንስ መጽሐፍ ውስጥ እስካሁን የተመለከትናቸውን የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ዘርዝር።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.