የመንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመምራት አገልግሎት

ጥያቄ፡- ሀ) ከእግዚአብሔር ጋር በአንድ ቤት ውስጥ የምንኖር ቢሆን ኖሮ ኑሮአችን ምን ይመስል ነበር? ለህ ተግባራችንና አኗኗራችን እንዴት ይላወጥ ነበር? ሐ) 1ኛ ቆሮ. 3፡16፥ 6፡19 ተመልከት። ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖረው በምን ዓይነት መንገድ ነው? 

በፈለግነው ሰዓት በፊቱ ለመቅረብና የፈለግነውን ለመጠየቅ ቀጠሮ ሳያስፈልገን በአንድ ንጉሥ ቤት ውስጥ እንደምንኖር አድርገን እናስብ። የዓለም ሁሉ ንጉሥ ጓደኛችን ፥ አማካሪያችንና፥ የሚወድደን አሳታችን መሆኑን በዓይነ ሕሊናችን እንመልከት። የንጉሥ ሥልጣን በጨመረ ቁጥር ያለን ጥቅምም ይጨምራል። 

በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደሚኖር ክርስቲያን ይህ የምንጠቀመው መብታችን ነው። በልባችን ህልውናውን በመሠረተው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፥ እግዚአብሔር አብ በልባችን ይኖራል። እካላችን አሁን ማደሪያው፥ ቤተ መቅደሱ ሆኗል። ልባችን ዙፋኑ ሆኗል። በምንፈልገው በቀኑ በማንኛውም ሰዓት ወደ እርሱ ልንቀርበውና የምንፈልገውን ሁሉ ልንጠይቀው እንችላለን። ለእኛ እርሱ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ሊያደርግልን ሙሉ ኃይል አለው። አንዳችም የሚያቅተው ነገር የላም። ከጠላቶቻችን የትኛውም ቢሆን ከእርሱ የሚበልጥ ኃይል የለውም። እኛ ልጆቹ ስለሆንን መንግሥቱንና ብልጽግናውን ሁሉ እንወርሳለን። 

አስደናቂ የሆነ መብት ልናገኝ የቻልነው እንዴት ነው? የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። ይህ ኃጢአተኛ የሆነ ድንኳን አካላችንን እንጽቶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያደርገናል። ይህ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጥ በሚጨምረን ወቅት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ከሚፈጠረው አዲስ ግንኙነት የሚመነጭ ነው። 

በትምህርት 6 በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመንን መንፈስ ቅዱስ አስደናቂ ሥራውን በሕይወታችን እንደሚጀምር ተምረናል። ይህን ሥራ በተለያዩ ሰርካታ መንገዶች መግለጽ ይችላል። ድነናል፥ ተዋጅተናል፥ ነጽተናል፥ ታትመናል፥ ደግሞም ሕይወታችንን መኖሪያ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶናል። ነገር ግን በሕይወታችን የተፈጸመውን ለመግለጽ ደንበኛው መንገድ፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት ምን እየተፈጸመ እንዳለ ማየቱ ነው። በመጀመሪያ፥ ልክ እንደ ዳንን «በክርስቶስ አካል» ውስጥ እንመራለን። መንፈሳዊ በረከቶቻችን ሁሉ የተገኙት «በክርስቶስ» ውስጥ ነው። 

ጥያቄ፡– ኤፌ. 1፡3–2፡22 አንብብ። ሀ) «በእርሱ» ወይም «በክርስቶስ» የሚለው ቃል ስንት ጊዜ ተጠቅሷል? ለ) በክርስቶስ በመሆናችን የእኛ የሚሆኑትን በረከቶች ጥቀስ። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ በአቋም በክርስቶስ ውስጥ ከሆንንበት ቅጽበት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን መልክ የምንመስልበትን ለውጥ ማከናወን ይጀምራል። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን መሥራት ይጀምራል (ሮሜ 8፡29፤ ፊልጵ. 3፡21)። በብዙ መንገዶች ክርስቶስን መምሰል እንጀምራለን። በመጀመሪያ፥ በባሕርይ ክርስቶስን እንመስላለን። የበለጠ ቅዱስ ፥ ጻድቅ፥ አፍቃሪና ታማኝ እንሆናለን። በሁለተኛ ደረጃ ፥ በተግባራችን የበለጠ ክርስቶስን እንመስላለን። በክርስቶስ አካል ውስጥ ላሉ ሌሎች ወገኖቻችንና በመንፈሳዊ ስጦታዎቻችን አማካኝነት ደግሞ በዓለም ላሉት የምናደርጋቸው ነገሮች ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ያደረጋቸው ናቸው። ሦስተኛ፥ ለዓለም ክርስቶስን የምንወክል እንሆናለን። እንደ ክርስቶስ አምባሳደር የእርሱ አፈ ቀላጤዎች እንሆናላን (2ኛ ቆሮ. 3፡18፤ 5፡18-20)። 

ሦስተኛ፡ መንፈስ ቅዱስ በመጨረሻ ፍጹም፥ የበሰልንና ኢየሱስ ክርስቶስን በሁሉ መንገድ የምንመስል በምንሆንበት ሂደት ውስጥ ያሳልፈናል። ሂደቱ ወደ ሚጠናቀቅበት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስደናል። በመስተዋት አምሳላችንን እንደምናይ ስመንግሥተ ሰማያት ኢየሱስ ክርስቶስን እንመስላለን። 

ጥያቄ፡– ትምህርት 6ን ተመልከትና አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያምን መንፈስ ቅዱስ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ነገሮች ዝርዝር። 

በትምህርት 6 አንድ ሰው በክርስቶስ አምኖ የእግዚአብሔር ልጅ በሚሆንበት ጊዜ መፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ስለሚሠራቸው በርካታ የተለያዩ ሥራዎች አጥንተናል። የመንፈስ ቅዱስ አንዱ አገልግሎት (ማጥመቅ፣ እንደሆነም ተመልክተናል። ይህ የውኃ ጥምቀት አይደለም። ይልቁኑ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው። መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ክርስቲያን ማደሪያው በማድረግ የክርስቶስ አካል ወደ ሆነችው የዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የሚጨምርበት አገልግሎት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በተለያዩ የክርስቲያን ቡድኖች ጽኑ ክርክርን ያስነሣ ለመሆኑ ባለፉት ሁለት ትምህርቶቻችን ተመልክተነዋል። መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ሁሉ ለአንዴና ለሁልጊዜ በክርስቶስ አካል ውስጥ የመጨመር አገልግሎቱን ስናይ ከአዲስ ኪዳን መረጃ ዎች አንፃር እውነትነቱ የበለጠ የሚያመዝን ነው። ከዚህ በተነጻጻሪ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አገልግሎት ግን እራሳቸውን በሰጡ ክርስቲያኖች ሕይወት መንፈስ ቅዱስ የበላይነት የሚወስድበትና ለእምልኮና ለአገልግሎት ኃይልን እንዲለብሱ የሚያደርግበት ተደጋጋሚ ድርጊት ነው። 

(ማስታወሻ፡- ክርስቲያኖች የሚሰባሰቡበት ሕንፃ፥ በሚለውና ከየትኛውም ክፍለ እምነት ኢየሱስን እንደ አዳኛቸው በትክክል የተቀሰሉ ክርስቲያኖች፥ የክርስቶስ አካል በሆነችው ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታቅፈው በአካባቢያቸው የሚመሠርቱት ኅብረት በመባል በሚሰጠው የቤተ ክርስቲያን ትርጉም መካከል ያለውን ልዩነት በአእምሮአችን መያዝ ጠቃሚ ነው። በአዲስ ኪዳን (ቤተ ክርስቲያን› የሚለው ቃል ሁልጊዜ የሚያመላክተው ክፍለ እምነታዊ መሠረታቸው ሳይታሰብ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎችን ሁሉ ነው።) 

በዚህ ሳምንት መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን እየመሰሉ እንዲሄዱ በሚያደርግበት የመለወጥ ሂደት ውስጥ ከሚሰጣቸው የተላያዩ አገልግሎቶች በኦንዳንዶቹ ላይ እናተኩራለን። 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። የሐዋ. 8፡29፥ 10፡19፥ 11፡12፥ 15፡28፥ 16፡6፥ 20፡22፤ ሮሜ 8፡14፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡10። ሀ) በእያንዳንዱ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰውን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተናገር። ላ) ይህ አገልግሎት ምን ምን እንደሚያጠቃልል አጭር መግለጫ ስጥ። ሐ) ይህን አገልግሎት በሕይወትህ ውስጥ ያስመሰከርኸው እንዴት ነው? 5ኛ ጥያቄ፡- ሀ) አንዲት ውብ ወጣት እንደተዋወቅህና ልታገባት እንዳሰብክ ገምት። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑንና አለመሆኑን በምን ታውቃለህ? ለ) ሰዎች ብዙ ጊዜ ላሕይወታቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉባቸውን ሌሎች ሁኔታዎች ጥቀስ። ሐ) ክርስቲያኖች (የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ ነገሮች ጥቀስ። 

በታሪክ ሁሉ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለሕዝቡ ገልጿል። በብሉይ ኪዳን ዘመን አንዳንድ ጊዜ ላሰዎች ሕልሞችንና ራእዮችን ይሰጥ ነበር፥ ነቢያትን ይልክ ነበር፥ ለሰዎች በቀጥታ ወይም በተጻፈው ቃሉ አማካይነት ይናገር ነበር። ኢየሱስ ቆይቶ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ ለመኖር በሚመጣበት ወቀት ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ ሰጣቸው (ዮሐ 16፡13)። ክጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ እግዚአብሔር ለልጆቹ በሕይወታቸው ውስጥ የሚኖረውን መንፈሱን ሰጥቶአቸዋል። የእግዚአብሔርን ልጆች ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ መምራት የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ኃላፊነት ነው። 

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ሰዎች የመራበትን የተለያዩ መገዶች ያሳየናል። ለምሳሌ፡- መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ በቀጥታ በመናገር ትእዛዝን ሰጥቶታል (የሐዋ. 8፡29)። የተናገረው በሚሰማ ድምፅ ይሁን እይሁን አናውቅም። ይህ በመንፈስ ቅዱስ ለተሞላው ሰው የሚገባው ሰልብ ውስጥ በፀጥታ የተነገረ የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ሊሆን ይችላል። መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስ ምን ማድረግ እንዳለበት ራእይን በማሳየትና በራእዩ ውስጥ ድምፅን በማሰማት ነገረው (የሐዋ. 10፡9-19)። በኢየሩሳሌም የነበሩ መሪዎች የብሉይ ኪዳን ሕግን በመጠበቅና በአሕዛብ ድነት (ደኅንነት) መካከል ስላለው ግንኙነት በሚከራከሩበት ወቅት በንግግራቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ መገኘቱንና ወደ ትክክለኛ ውሳኔም እንደ መራቸው ተገነዘቡ። ይህን እንዴት እንዳወቁ እርግጠኞች አይደለንም፤ ምናልባት ግን መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው በፈጠረው የመንፈስና የአእምሮ አንድነት ሊሆን ይችላል (የሐዋ. 15፡28)። ጳውሎስ በአንዳንድ የእስያ ክፍሎች ወንጌልን ሊሰብክ አስቦ በተዘጋጀበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደ ከለከላው ተጽፎአል (የሐዋ. 16፡6)። መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አንድ ቦታ እንዳይሄድ በምን መንገድ እንደ ገለጸለት እናውቅም። ምናልባትም ከዚያ ቀጥሎ እንዳየው ዓይነት ስራእይ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ሁኔታዎች ትክክል ስላልነበሩ ወደዚያ ስፍራ መሄዱን እግዚአብሔር እንዳልፈቀደ ጳውሎስ ተረድቶት ይሆናል። ምናልባትም እግዚአብሔር ለልቡ ተናግሮት ይሆናል። በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት በምን መንገድ መሄድ እንዳለባቸው በእግዚአብሔር ቃል እማካኝነት ይናገራቸው ነበር (የሐዋ. 1፡16-22)። ነቢያትንም በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞባቸዋል (የሐዋ. 11፡27-28)። 

ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች አንዱ «የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት አውቃለሁ?» የሚለው ነው። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ «መንገዴ ይህ ነው በዚህ ተመላለስ» የሚል ድምፅ እንዲያሰማን እንመኛለን። እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ሊያደርግ ይችላል፤ ግን ብዙ ጊዜ አይደለም። ታዲያ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ የሚያሳውቀው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ፈቃድ ስንልስ ምን ማለታችን ነው? 

ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ስንነጋገር ስለ ሦስት ነገሮች መናገራችን ነው። በመጀመሪያ፥ ነገሮችን ሁሉ የሚቆጣጠርና የሚመራ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድ ስለ መኖሩ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው በምድር ላይ የሚፈጸሙ ነገሮች ሁሉ ፍቅርና ጥበብ በተሞላው በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ናቸው። እግዚአብሔር ሳያውቀውና ሳይቆጣጠረው በምድር ላይ የሚፈጻም አንዳችም ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር ዓላማትንና የሰውን ልጅ ታሪክ በሙላት እርሱ ወደ ወሰነው ፍጻሜ ይመራቸዋል። ይህ ፍጻሜ በራእይ መጽሐፍ ተገልጧል። እግዚአብሔር ኃጢአትን ባያመጣም እንኳ ሰይጣን ኃጢአትን ከመሥራቱ በፊት፥ አዳምና ሔዋን ኃጢአትን ከማድረጋቸው በፊት ያውቅ ነበር። ወይም እኛ ኃጢአትን ከማድረጋችን በፊት ምን እንደሚከተል ያውቃል። ኃጢአትን ይቆጣጠራል። የኃጢአትን ውጤት ይወስናል። ኃጢአትንና ፍሬዎቹን እኛን ሊያስተምረንና ክርስቶስን እንድንመስል ሊያደርግ ይጠቀምበታል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር አጠቃላይ ዕቅድ የሚነግረን ብዙ ነገር ቢኖርም እግዚአብሔር ፈቃዱን በመፈጸም በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ እንዴት እንደሚሠራ ከእኛ የተሰወረ ምሥጢር ነው (ምሳ. 21፡1፤ ዳን 4፡35፤ ኢሳ. 45፡1-3፤ 3፥ 21-25፤ ሮሜ 9፡19፤ ኤፌ. 1፡11 ተመልከት)። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ የእግዚአብሔር የሥነ ምግባር ፈቃድ አለ። እነዚህ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰጣቸው እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚጠብቅና እንዴት መኖር እንዳለብን የሚገልጹና ተለይተው የሚታወቁ ትእዛዛት ናቸው። እነዚህ የሥነ ምግባር ሕጐች እንዴት መኖር እንዳለብን ግልጽ ትእዛዛትንና አጠቃላይ መመሪያዎችን የሚሰጡ ሲሆን በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብን ግን አይናገሩም (ሮሜ 2፡18፤ 1ኛ ተሰ 5፡18፤ 4፡3፤ 2ኛ ቆሮ. 6፡14)። ለምሳሌ፡- ከማያምኑ ጋር መጋባት እንደሌለብን ተጽፏል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የትኛዋን ክርስቲያን ልጃ ገረድ ወይም ክርስቲያን ወንድም ግባት እንዳለብን አይናገርም። በሁሉም ሁኔታዎች እግዚአብሔር በጥቅሉ ከእኛ የሚፈልገውን እንጂ ዝርዝሩን እንድናውቅ መጽሐፍ ቅዱስ አይረዳንም። መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ስሕተት ነው ብሎ ያስቀመጠውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድን ነው ብለን መጠየቅ የለብንም። 

በሦስተኛ ደረጃ ፥ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን በግል የሆነ ፈቃድ አለው። እነዚህ ፈቃዶች እግዚአብሔር በምድር ላይ ከማንም ለይቶ እያንዳንዳችን እንድናደርጋቸው የሚሰጠን ነገሮች ናቸው። ለእያንዳንዳችን ሕይወት ይህን ፈቃድ ደረጃ በደረጃ መግለጹ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። ይህንን ለማድረግ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማል (ቆላ. 1፡9፤ 4፡12፤ ሮሜ 12፡2፤ ኤፌ. 6፡6፤ ምሳ. 3፡5-6፤ መዝ. [32]፡8)። ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ገጽታ ይህ ሲሆን በተለይ ደግሞ በሕይወታችን እንደ ጋብቻ ያሉ ትላልቅ ውሳኔዎችን ለመወሰን በምንዘጋጅበት ጊዜ የሚገጥመን ነው። 

ስለዚህ ለለ ሦስተኛው ዓይነት ‹የእግዚአብሔር ፈቃድ› ሁለት የተለያዩ ግንዛቤዎች አሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ያላቸው አስተሳሰብ በጣም ጠባብ ነው። እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ ለአንድ ሰው ያለው ፈቃድ አንድ ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። ለምሳሌ፡ እግዚአብሔር ለአንድ ሰው እንዲያገባ የመረጠለት የትዳር ጓደኛ አንድ ሰው ብቻ ነው ይላሉ። በዓለም ላይ ካሉ ሰዎች መካከል የተመረጠለትን ሰው ለማወቅ መንፈስ ቅዱስን ማድመጥ የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ነው። ከላይ የተገለጠው አመለካከት አንድ ክርስቲያን አብዛኛውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ለማወቅ በሚጣጣርበት ወቅት አንዳንድ ጊዜ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ይከተዋል። እግዚአብሔር ለእኔ የሰጠው ሰው በእውነት ይህ ይሆንን? ወይስ ተሳስቼ ይሆንን? ይህን እጅግ የጠበበ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብልት በቀረው ዘመኔ ከእግዚአብሔር ፍጹም ምርጫ ተላይቼ የምኖረው እንዴት ነው? እነዚህና የመሳሰሉ ሌሎች ጥርጣሬዎች አእምሮውን ያስጨንቁታል። 

ሌሎች ክርስቲያኖች ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በስፋት ማየትን ይመርጣሉ። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ላልጆቹ ሊያደርጉት የሚገባቸውን ነገር ነጥሎ ያመለክታቸዋል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለሕዝቡ የሚገልጥበት ልማዳዊ መንገድ ሳይሆን ልዩ መንገድ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ሰፊ መመሪያዎችን በመስጠት ለእነዚህ መመሪያዎች ታዛዥ ሆነን እንድንመላለስ ነው የሚጠይቀን ይላሉ። የእግዚአብሔር ፈቃድ በአንድ ውሳኔ ላይ የማያፈናፍንና የተገደበ አይደለም። ለምሳሌ፡- ክርስቲያን እንደ መሆናችን ሌላ ክርስቲያንን ማግባት እንድንችል እግዚእብሔር ምሪትን ሰጥቶናል። የትኛዋን ክርስቲያን ማግባት እንዳለብን እግዚአብሔር አብዛኛውን ምርጫ ለእኛ ለባለቤቶቹ ትቶአል። በባሕርያቸውና በሕይወት ዓላማቸው ከእኛ ጋር የሚስማሙትን መርጠን ማግባት የምንችልበትን እእምሮ እግዚአብሔር ሰጥተናል። ማንን እናግባ? የት እንኑር? ምን እንማር? 

ምን ዓይነት ሥራ እንፈልግ? ወዘተ… ለሚሉ አብዛኛው የሕይወት ጉዳዮችና ለምንደርስባቸው ውሳኔዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረተ-ሰፊ መመሪያ አኳያ እግዚአብሔር ነፃነት ሰጥቶናል። 

ይህ አመለካከት የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመግለጥ እኛን የሚመራበት አራት ዋና መመሪያዎች እንዳሉ ነው። 

1. የእግዚአብሔር ቃል ላለንባቸው ሁኔታዎች እቅጣጫ የሚሰጡ የተወሰኑ የሥነ ምግባር ሕጐች (ለምሳሌ፡- በሐሰት አትመስክር) ወይም ግልጽ መመሪያዎች ስላሉ አማኞች የእግዚአብሔርን ትእዛዞች መጠበቅ አለባቸው። 

2. መጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ወይም መመሪያ በማይሰጥባቸው አካባቢዎች አማኙ የራሱን ምርጫ ሊወስንና በውሳኔውም ኃላፊነቱን ሊወለድና ተግባራዊ ሊያደርግ ነፃ ነው። በእግዚአብሔር የሥነ ምግባር ሕ1 ሥር የሚደረጉ ውሳኔዎች ሁሉ ተቀባይነት አላቸው። 

3. የእግዚአብሔርን የሥነ ምግባር ሕግጋት የማይሽሩ ውሳኔዎችን በተመለከተ እግዚአብሔርን ለማስደሰት ከሚመነጭ ፍላጐት ጥበብ የሞላባቸውን ውሳኔዎች ለማድረግ መሻት አለብን። እግዚአብሔር የሚገደው ምን እንደምንመርጥ ብቻ ሳይሆን ከትክክለኛ አቋም በመነሣት፥ ለትክክለኛ ምክንያት ትክክለኛ ውሳኔ እንድንሰጥ ነው። 

4 ክርስቲያን በውሳኔዎቹ ሁሉ በሕቡዕ ለሚሠራው ሉዓላዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ በትሕትና እራሱን የማስገዛት እቋም ሊኖረው ይገባል። 

ጥያቄ፡– ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት አመለካከቶች የትኛውን ትመርጣለህ? ለምን? 

መጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት የሚያደርገው በመጀመሪያዎቹ ሁለት የእግዚአብሔር ፈቃድ ዓይነቶች ማለትም በሉዓላዊ የእግዚአብሔር ፈቃድና በሥነ ምግባራዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ነው። እግዚአብሔር በተወሰኑ ሁኔታዎች ለአማኞች የማያሻሙ መመሪያዎችን የሚሰጥ ቢሆንም፥ ይህ በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ለሚሰጠን አመራር እንደ ምሳሌ ሳይሆን ልዩ ተደርጐ ነው መታየት ያለበት። እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የሕይወት ጉዳያችን ላይ ያለውን ፈቃድ በነፍስ ወከፍ ለማወቅ ከመጣር ይልቅ ለእግዚአብሔር ሥነ ምግባራዊ ፈቃድ ታዝዞ መኖር ላይ ማተኮር አለብን። 

ሁለቱም አመለካከቶች የሚያስኬዱ ቢሆኑም እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ፈቃዱን የሚገልጠው አጠቃላይ መመሪያ በመስጠት መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ የሚያመለክት ይመስላል። እነዚህ መመሪያዎች የትኞቹ እንደሆኑ ማወቅና ለእነርሱ በመታዘዝ መኖር የእኛ ኃላፊነት ነው። የትኛውንም አመለካከት በአቋም ደረጃ ብንይዝ የእግዚአብሔርን ‹ፍጹም› ፈቃድ እንዳናጣ መስጋት የለብንም። ፈቃዱን እንድናውቅና በዚያ እንድንኖር ከእኛ የበለጠ ስለ እኛ እግዚእብሔር ያስባል። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይገልጥልናል እንጂ አይሰውረውም። ብዙ ጊዜ ችግራችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያለማወቅ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ያለመታዘዛችን ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) እግዚእብሔር በግልጽ እየተናገርህ ማድረግ ያቃተህን ነገሮች በዝርዝር ጻፍ። ለ) እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዴት እንዳስታወቅህ ግላጽ። 

በአንድ ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅ እንችላለን? የመንፈስ ቅዱስን ምሪትና እርሱን ማድመጥ መማር አለብን። ብዙ የተለያዩ የመናገሪያ መንገዶችን ሊጠቀም ስለሚችል እግዚአብሔር ሲናገረን ድምፁን ለመስማት ንቁ መሆን አለብን። ብዙ ጊዜ ሁኔታዎች አሳሳች ናቸው። ሰዎች የተሳሳተ ምክር ሊሰጡን ይችላሉ። ውስጣዊ አሳሳችንን ሁሉ ማወቅ እጅግ ከባድ ነው። እግዚአብሔር ግን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንደሚናገረንና እንደሚመራኝ ቃል ገብቶልናል። ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው? የሚጠቀመው መንገድስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ሊናገረን እያዳመጥን መሆናችንን እንዴት እናውቃለን? እግዚአብሔር እኛን የሚናገርባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። በንቃት ከተከታተልነው ሲናገር ልናደምጠው እንችላለን። ቀጥሎ አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን እንዴት እንደሚሰማና ፈቃዱን እንደሚያውቅ የሚረዱ አሳቦችን እንመለከታለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) 1ኛ ቆሮ. 2፡6-16፤ 2ኛ ጴጥ. 20-21ን አንብብ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጻፍና ከዚያም በክርስቲያኖች እንዲታወቅ ለማድረግ መንፈስ ቅዱስ ያለውን ሚና ስለሚገልጹት ጥቅሶች እነዚህ ቃላት ምን ያሳያሉ? ለ) መንፈስ ቅዱስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ጸሐፊዎች በመምራት ስለተጫወተው ሚና በትምህርት 3 የተማርነውን ትምህርት ከልስ። 

1. እግዚአብሔር የሚናገርበትና እኛም ፍቃዱን የምናውቅበት ተቀዳሚ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በትምህርት ዎላት በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አንዱ በተለያዩ ሰዎች ልብ ውስጥ በመሥራት የሚጽፉት ነገር የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ እንዲወጣ መምራት እንደ ነበር ተመልክተናል። የግለሰቦች ማንነትና የአጻጻፍ ስልታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛው ደራሲ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ በተደጋጋሚ ያሳየናል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰብዓውያን ደራሲያን ውጤት ብቻ አይደለም። ይልቁኑ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ሁለት ደራሲዎች አሉት ማለት እንችላለን። በመጀመሪያ፥ ሰብዓዊው ደራሲ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ በተደጋጋሚ ዳዊት መዝሙር እንደ ጻፈ፥ ሙሌ ወይም ጳውሎስ ደግሞ የየራሳቸውን መጻሕፍት እንደ ጻፉ የሚናገረው ለዚህ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፥ መለኮታዊው ደራሲ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ጸሐፊ እርሱ የሚፈልጋቸውን አሳቦች እንዲያስተላልፍና እሳቦቹንም ለመግለጽ የሚመርጣቸውን ቃላት እንዲጠቀም በመቆጣጠር መርቶእል። 

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን መጻፍ የመንፈስ ቅዱስ ብቸኛ ሥራ አልነበረም። በዘመናት ሁሉ ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ዋነኛው ራሱ በጻፈው ቃል ውስጥ ያሉትን መንፈሳዊ እውነቶች ሰዎች መረዳታቸውን ማረጋገጥ ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል ለሰዎች ግልጽ የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት (አብርሆት› ተብሎ ይጠራል። ጳውሎስ ሲናገር የእግዚአብሔር ነገር ክርስቲያን ላልሆኑ ሰዎች የተሰወረ ነው ይላል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ግልጽ ያደርግላቸዋል (1ኛ ቆሮ. 2፡6-16)። 

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ነገሮች ግልጽ የሚያደርግልን እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ልንገነዘበው የሚገባን መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ከመነሻው የተጻፈበትን ትርጉም እንደማይቃረን ነው። በብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ልብ በሚሠራበት ወቅት የሰጠው ትርጉም ለዛሬው ዘመን ትርጉም መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ‹ሰምና ወርቅ› በመቁጠር ከገሃድ ትርጉም በስተጀርባ ያለውን ስውር ትርጉም የምንፈልግ ከሆነ አደጋ ላይ እንወድቃላን። መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመተርጐምና መንፈስ ቅዱስ ምን ለማለት እንደ ፈለገ በትክክል ለመረዳት የአተረጓጐምና የሥነ መግባቢያ ሕግጋትን በሙሉ መጠቀም አለብን። ከቃሎቹ በስተጀርባ የተደበቀ ትርጉም የምንፈልግ ከሆነ አተረጓጐማችን ትክክል ስለመሆኑ የምንረዳበት መንገድ የለም። ስለዚህ ትርጉሙን በነሲብ እየገትን ነው ማለት ነው። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ከማያምኑ ሰዎች የተሰወረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉት ቃሎች ወይም ትርጉማቸው አለመሆኑን መረዳት ይገባናል። አንድ የማያምን ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ የተጻፈውን ቃል ትርጉም ለመረዳት ይችላል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የሰውዬውን ዓይን ካልከፈተ በቀር ከሰውዬው የሚሰወረው ነገር ሀ) እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ ባለው አጠቃላይ ዓላማ ውስጥ እነዚያ ቃሎች እንዴት እንደሚሠሩ፥ ለ) የሚያነበው ቃል ከሕይወቱ ጋር እንዴት እንደሚዛመድና ሐ) ለቃሉ የመገዛትና በሕይወቱ ተግባራዊ የማድረግ ችሎታ ነው። 

ሆኖም ግን ለክርስቲያኖች እነዚህ ሁኔታዎች ፈጽሞ የተለዩ ናቸው። በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በእርሱ የተጻፈውን ቃል ወስዶ ስለ እግዚአብሔር ዓላማዎችና መንፈሳዊ መመሪያዎች ለእግዚአብሔር ሕዝብ ማስተማር የሚፈልገውን ክርስቲያኖች እንዲረዱ ያግዛቸዋል። መንፈስ ቅዱስ እነዚህ መመሪያዎች እንዴት በሕይወቱ ተፈጻሚነት እንደሚያገኙ ለማሳየት፥ ከዚያም ሕይወቱ እንዲለወጥ እውነቶቹን ከሕይወቱ ጋር እንዲያዛምድ ለመርዳት በአማኙ ልብ ውስጥም ይናገራል። እነዚህን እውነቶች መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርግ ግን ክርስቲያኖች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ማጥናት ይጠበቅባቸዋል። 

መንፈስ ቅዱስን ለመስማትና በሕይወታችን ፈቃዱ ምን እንደሆነ ለመረዳት ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ የገለጠውን ለማወቅ ማጥናት ይጠበቅብናል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ ያለአንዳች ጥያቄ የምንረዳበት ዋና ምንጣችን ነው። በጥበብ የተሞሉ ውሳኔዎችን እንድናደርግ የሚያስችሉንን ዋና መመሪያዎች እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቀምጦልናል። የእግዚአብሔርን ቃል ላማጥናት በቂ ጊዜ ሳንወስድ ቀርተን ደካማ ውሳኔዎችን ብናደርግ ጥፋቱ የእኛ እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ማቴ. 10፡26-39፤ የሐዋ. 20፡26-35፤ ሮሜ 1፡1-16፤ ኤፌ. 5፡7-21፤ 1ኛ ተሰ. 4፡1-12 5፡16-18፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡13-16። ሀ) እግዚአብሔር ፈቃዱ እንደሆኑ የገለጣቸውን ነገሮች ዘርዝር። ለ) እነዚህ ነገሮች ሕይወታችንን የምንመራባቸው መሠረታዊ መመሪያዎች የሚሆኑት በምን መንገድ ነው? ሐ) የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድትገነዘብ የሚያደርጉህ ሌሉች መመሪያዎች የትኞቹ ናቸው? 

መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ግልጽና የማያሻማ ምሪት የሚሰጠን እንዴት ነው? የእግዚአብሔርን ቃል በምናጠናበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አንድን ጥቅስ ወደ አእምሮአችን ያመጣል። ይህ ጥቅስ ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ ያነበብነው ሊሆን ይችላል። እያነበብነው እያለ መንፈስ ቅዱስ ጥቅሱን ልዩ ያደርግልናል። እግዚአብሔር ይህን ጥቅስ የሚጠቀመው እንድ እንድናውቀውና በተግባር እንድንተረጉመው የሚፈልገው ነገር በመኖሩ መሆኑን እንገነዘባለን። ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጠቀም መንፈስ ቅዱስ «ልታድግበት የሚያስፈልግህ የሕይወት ክፍል ይህ ነው» ሊለን ይችላል። ወይም እያለፍህ ባለህበት በዚህ ሁኔታ እንድታደርገው የምፈልገው ነገር ይህ ነው ሊለን ይችላል። የእግዚአብሔርን ትርጉም በማቻቻል ሳይለወጥ እንድታደርገው የሚፈልገው ነገር ይህ ነው ሊለን ይችላል። የእግዚአብሔርን ቃል ትርጉም ሳናመቻዎች መንፈስ ቅዱስ በግልጽ ይመራናል። 

ሆኖም ግን ለእኛ የእግዚአብሔር ፈቃድ ናቸው ብለን የምንገምታቸውንና ነገር ግን ያይደሉትን አሳቦች በውስጡ በመጨመር እነርሱን በመደገፍ እንዲያመለክተን በማድረግ ያለአግባብ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳንጠቀምበት መጠንቀቅ አለብን። ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እንናገራቸው ዓይኖቻቸውን ጨፍነው መጽሐፍ ቅዱስን በመክፈትና ጣታቸውን አንድ ጥቅስ ላይ በማሳረፍ የጨፈኑትን ዓይኖቻቸውን ይከፍታሉ። ከዚያም በጣታችው የነኩትን ጥቅስ በማንበብ እግዚአብሔር እነርሱን ለመምራት የሰጣቸው እንደሆነ አድርገው ይወስዱታል። በዚህ መንገድ ምሪት ለማግኘት ስለ ሞከረ አንድ ክርስቲያን የሚነገር ታሪክ አለ። በመጀመሪያ ሙከራው መጽሐፍ ቅዱሱን ሲገልጥ «ይሁዳ ታንቆ ሞተ። የሚል ጥቅስ ያገኛል። ይህ በሚገባ ግልጽ ስላልሆነለት ሌላ ሙከራ አደረገ። ለሁለተኛ ጊዜ ጣቱ ያረፈበት ቃል «ሂድና እንዲሁ አድርግ» የሚል ነበር። ስለዚህ ያ ክርስቲያን እራሱን እንዲገድል እግዚአብሔር የፈለገ መሰለው። የእግዚአብሔርን ቃል ያለሟቋረጥ ማንበብ ልባችን በመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ቅኝት ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በመጠቀም መሥራት የሚገባንን ይነግረናል። 

ጥያቄ፡- መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በሕይወትህ የሚፈልገው ነገር ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም የተናገረበትን ሁኔታ ግለጽ። 

2. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እኛን የሚናገርበት ሁለተኛ መንገድ በልባችን የውስጥ ማንነታችንን በፀጥታ በመቀስቀስ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ የሚሆነው በምንጸልይበትና እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲያሳየን በምንጠይቅበት ጊዜ ነው። እየጸለይን ሕልሞቻችንና ዕቅዶቻችንን ለእግዚአብሔር ስናስረክብ እግዚአብሔር ልባችንና አእምሮአችን በአንድ ነገር ላይ እንዲያተኩርና ሌላውን እንዲተው ያደርገዋል። ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር እንድናደርገው የሚፈልገውን ነገር ሳናደርግ ስንቀር በልባችን ያላው ውስጣዊ ሰላም ይወሰድብንና አንድ ስሕተት እንዳለ ይሰማናል። ወይም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ስናደርግ ደግሞ ስለ ውሳኔያችን ጥልቀት የሰላም ስሜት ይሰጠናል። እራሳችንን ለእግዚአብሔር ከሰጠን፥ በትሕትና በጸሎት ወደ እርሱ ከቀረብን፥ የሚያስከፍላን ዋጋ የፈለገውን ያህል ቢሆንም እንኳ አድርጉ የሚላንን ነገር ሁሉ ለማድረግ ከቆረጥን፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ልባችንንና አእምሮአችንን ይመራል። እግዚአብሔር ፈቃዱን እስከፈለነው ድረስ ከእኛ አይሸሽግም። 

በሌሎች ጊዜያት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ባላሰብነው ሁኔታ ሲናገረን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን ጠንካራ ስሜት ይሰማናል። አንዳንድ ጊዜ አንድ ችግር ውስጥ ያላን ወዳጅ እንድንጎበኝ፥ ወይም ለማናውቀው ሰው እንድንመሰክር፥ ወይም በኋላ በችግር ውስጥ እንደነበረ ለምንረዳው እሩቅ ላለ ሰው እንድንጸልይ ሊሆን ይችላል። ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አሳቦችን ወደ አእምሮአችን ያመጣል። ይህ እርሱ ለእኛ የሚናገርበት መንገድ ነው። ይህ እግዚአብሔርን የማድመጥ ችሎታ ልምድ ይጠይቃል። በጥድፊያ ሆነን መንፈስ ቅዱስን ማድመጥ እንችልም። ስግብግብ ፍላጎታችንን እያሳደድን መንፈስ ቅዱስን ማድመጥ አንችልም። ነገር ግን «ባሪያህ ይሰማልና ተናገር» የሚል ዝንባሌ ሊኖረን የእግዚአብሔር መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ይገናኝና ወደ ፈቃዱ ይመራናል። 

ጥያቄ፡- እግዚአብሔር በዚህ መንገድ የተናገረህ እንዴት ነው? አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀስ። 

3. እግዚአብሔር ሰውን የሚናገርበት ሦስተኛ መንገድ በሌላ ሰው በኩል መናገር ነው። ትላልቅ ውሳኔዎችን ማድረግ በሚያስፈልግበት ወቅት የእግዚአብሔርን ወንድና ሴት ልጆችን ምክር መጠየቅ አለብን። እግዚአብሔር ጥበብንና ምክርን ሁሉ በሰዎች ውስጥ አድርጓል። ስለዚህ እንዲህ ካሉት ጥልቅ እውቀት ልናገኝ እንችላለን። የሚያውቁንና የምናምናቸውን ወንድና ሴት የእግዚአብሔር ሰዎችን ምክር መጠየቅ አለብን። የሚያውቁንና የምናምናቸውን ወንድና ሴት የእግዚአብሔር ሰዎች ሳናማክር በሕይወት ውስጥ ዐቢይ ውሳኔ ማድረግ የለብንም። 

ሌሎች በምክራቸው የሚሰጡንን አምላካዊ ጥሰብ ከመጠቀም ይልቅ እግዚአብሔር ለእኛ ለማለት የፈለገውን ነገር በቀጥታ ለአንድ ሰው በመንገር ያ ሰው መልእክቱን እንዲያስተላልፍልን የሚያደርግበት ጊዜያትም እሉ። ይህ «የመገለጥ ቃል» በመባል ይታወቃል። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ለሌላ ሰው ሊናገርና (ከእነዚህ መንገዶች የትኛውንም ተጠቅሞ) ያ ሰው ወደ እኛ 

መጥቶ ሊነግረን ይችላል። 

እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመግለጥ ይህን መንገድ አሁንም ይጠቀማል ወይስ አይጠቀምም በሚል አሳብ በመለያየት ክርስቲያኖች ይከራከራሉ። የቀድሞ ነቢያትን በተናገረበት መንገድ አሁንም ይናገር እንደሆነና እንዳልሆነና የአሳብ ልዩነት ያሳያሉ። በዚህ መንገድ የሚናገርስ ከሆነ መልእክቱ የተጻፈውን ቃል ያህል ሥልጣን አለውን? «የመገለጥ ቃል» ከተባለው የሚመጣው መልእክት ከእግዚአብሔር መሆንና ያለመሆኑ በምን ይረጋገጣል? እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ ለመግለጥ ሌሎች ሰዎችን እንደሚጠቀም ባምንም ቃሎቹ ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ሥልጣን ያላቸው አይደሉም። የሚሉት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ሁልጊዜ ማረጋገጥ አለብን። የሚያሳዝነው ነገር ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በዚህ መንገድ እንደተናገራቸው በመጥቀስ የትዳር ጓደኛን በግድ ለማግኘት ሲሞክሩ ወይም መንፈስ ቅዱስ ከሚፈልገው ነገር ይልቅ እራሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ሲያደርጉ መመልከታችን ነው። ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልእክት ብቻ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከመወሰን መጠንቀቅ አለብን። ከላይ የተጠቀሱት ሌሎች መንገዶች ሁሉ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ እንደሚፈልግ ለመወሰን እንደ ሚዛን ሊያገለግሉ ይገባል። (ማስታወሻ፡- ወደፊት ባሉን ትምህርቶች «የመገለጥ ወይም የትንቢት ስጦታን» በሰፊው እንመለከታለን።) 

ጥያቄ፡- በሕይወትህ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችል የሌላን ሰው መንፈሳዊ ምክር እግዚአብሔር የተጠቀመበት እንዴት ነው? አንዳንድ ምሳሌዎችን ስጥ። 

4. እግዚአብሔር እኛን ለመምራት አንዳንድ ጊዜ ልዕለ-ተፈጥሮዊ (ተአምራዊ) መንገዶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ፡- እግዚአብሔር በሚሰማ ድምፅ፥ በራእይ፥ በሕልም በመላእክት ወዘተ… ሊናገረን ይችላል። ይህ እግዚእብሔር እኛን የሚመራበት ልማዳዊ መንገድ ስላይደለ ለእያንዳንዱ ውሳኔያችን በዚህ መልክ ይመራናል ብለን መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር እኛን ሰሚመራባቸው በተቀሩት መንገዶች ላይ አትኩሮት ማድረግ ይገባናል። እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባት ልዩ የሆነ መንገድ ተጠቅሞ ግልጽ ምሪት የሚሰጠን ከሆነ እሰየው ነው። 

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ከዳር እስከ ዳር መንፈስ ቅዱስ ላሕዝቡ መልእክቱን ለማስተላለፍ ሕልሞችንና ራእዮችን ተጠቅሟል። ለምሳሌ፡- በሐዋ. 10 ላይ ጴጥሮስ በእንድ ራእይ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲገለጥለት እንመለከታለን። በተላይ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል አንብበው በቀላሉ እግዚአብሔር ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ ለመረዳት በማይችሉባቸው ላፍራዎች እግዚአብሔር ሕልሞችንና ራእዮችን ይጠቀማል። ሆኖም ግን እያንዳንዱ ሕልምና ራእይ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ከማሰብ ልንጠነቀቅ ይገባል። 

በየዕለቱ የምናየው ተፈጥሮአዊ የሆነ ሕልም አለ። አልፎ አልፎ አንዳንድ ሰዎች የሚያዩትን በዚያም በኩል እግዚአብሔር ለእነርሱ የሚናገርባቸው ልዕለ-ተፈጥሮአዊ የሆኑ ሕልሞች አሉ። ማንኛውም ሰው እግዚአብሔር በዚህ ተናገረኝ ብሎ የሚያመጣቸውን ሕልሞች በጥንቃቄ መመዘን አለብን። ማንኛውም ሰው ያየውን ራእይ በእግዚአብሔር ቃል በመፈተን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ይስማማ እንደሆነ መመልከት አለብን። አንዳንድ ጊዜ የሕልሞቹ ትርጉም ምን እንደሆነ መረዳት ቀላል አይሆንም። ነገር ግን ሕልሙ የተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ከሆነ እንድንረዳው ብቻ ሳይሆን ይህ ሕልም ከእግዚአብሔር መሆኑን ሌሎችም አምነው እንዲቀበሉ በልባቸው ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመከተል መሠረት አድርገን የምንከተለው ሕልሞችን ብቻ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። የተሰጠን ሕልም ወይም ራእይ ከእግዚአብሔር መሆኑን አምነው ይቀበሉ እንደሆነ የእግዚአብሔር ሰዎችን፥ ማለትም ወዳጆቻችንን፥ መጋቢያችንን ወዘተ… በመጠየቅ ማረጋገጥ አለብን። እነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች ሕልሙ ወይም ራእዩ ከእግዚአብሔር ስለመሆኑ ከፍተኛ ጥርጣሬ ካላቸው ተከታዩን እርምጃ ለመውሰድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ክርስቲያኖች ከዚህ ቀደም ሕልሞች ወይም ራእዮችን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት የእግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆኑ ነገሮችን ፈጽመዋል። እግዚአብሔር ይህን መንገድ ዛሬም የሚጠቀምበት ሊሆን ቢችልም እንኳ መልእክቱ ሁልጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስና እግዚአብሐር ሰሚናገርባቸው ሌሎች መንገዶች አማካኝነት መረጋገጥ አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረን ጋር ከተቃረነ ውሸት ነው። እግዚአብሔር በአሳቡ እርስ በርስ አይጋጭም። 

5. ምን ማድረግ ትፈልጋለህ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የተፈቀዱ ፍላጎቶች ሲኖሩን እነዚህን ፍላጎቶች በውስጣችን ያደረገ ማን ነው? ብዙውን ጊዜ ከልዩ ስጦታዎቻችን፥ ችሎታዎቻችንና ፍላጎታችን ጋር ያስቀመጠን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር በመገዛት እየኖርን፥ ለእርሱ ለመኖር አጥብቀን እየተጋንና እየታዘዝነው ፍላጐቶቻችን የሚቀጥሉ ከሆነ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመሆኑ ምልክት ነው። በሌላ በኩል ግን አንድን ነገር የምናደርገው ከትክክለኛ ውስጣዊ ዓላማ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልገናል። የምናደርገው ነገር ለእግዚአብሔር ወይስ ለራሳችን ክብር ነው? ብለን መጠየቅ አለብን። አንድን ነገር ለራሳችን ጥቅም ወይም ንጹሕ ላልሆነ ውስጣዊ ዓላማ ስንሻ ብዙ ጊዜ የመጨረሻ ነገራችን እግዚአብሔር የማይፈልጋቸው ነገሮች ላይ መውደቅ ይሆናል። 

6. የእግዚአብሔርን አቅጣጫ ለመወሰን በዙሪያህ የሚደረጉ ነገሮችን ተመልከት። ክርስቲያን፥ በሕይወቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ማናቸውም ነገሮች በአጋጣሚ ወይም በዕድል እንዳልሆኑ ያውቃል። እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ ይቆጣጠራል። ስለዚህ በሚያጋጥሙን ነገሮች ሁሉ ፡ እግዚአብሔር የበላይ ተቆጣጣሪ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ይመራን ዘንድ በሮችን በመዝጋት ወይም በመክፈት ሁኔታዎችን ይጠቀምባቸዋል። በሕይወታችን እግዚአብሔር አንድ ነገር ፈቃዱ እንዳልሆነ ለማሳየት በሮችን የሚዘጋበት ወይዎ ፈቃዱ ስለሆነ እንድንገባባቸው ለግመልክት ያልተጠበቁ የአገልግሎት ወይም የሥራ በሮችን የሚከፍትበት ብዙ ጊዜያት አሉ። 

አንድ ነገር የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ወይም አይሁን ለመወሰን ብዙ ጊዜ ሁኔታዎችን መረዳት ከባድ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማዕክላዊ ስፍራ ከያዝሁ በማደርገው ደስ ይለኛል ነገሮችም ቀላል ይሆኑልኛል ብለው ያስባሉ። አንዳንድ ጊዜ ደስ የሚያሰኙ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ አመልካች ናቸው። ሁልጊዜ ግን አይደለም። ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገር ታዝዞ ነበር፤ ብዙ ሳይቆይ ግን ተይዞ በወኅኒ ተጣለ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየተከተለ ተደበደበ፥ መርከቡ ተሰበረች፥ ተራስ፥ ደኻየ፥ ወዘተ… (2ኛ ቆሮ. 1፡23-33) ። 

የእግዚአብሔር ፈቃድ ብቸኛ አመልካቾች ሁኔታዎች መሆን የለባቸውም። እግዚአብሔር ፈቃዱን ለእኛ ክሚገልጥባቸው ሌሎች መንገዶች ጋር ሚዛናዊ መጣጣም ሊኖራቸው ይገባል። አንዳንድ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለየት መጠቀም የሚወዱት እግዚአብሔርን መፈተን ነው። ከዚያም የሚከሰተውን ውጤት የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርገው ይቆጥሩታል። ጌዴዎን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የበግ ፀጉር ባዘቶን እንደ ምልክት ሲጠይቅ ያደረገው ይህንን ነው (መሳ. 6፡36-40)። መንፈስ ቅዱስ አሁን በእኛ ውስጥ ሆኖ እየመራን እያላ፥ ፈቃዱን ለማወቅ እንዲህ ዓይነት ዘዴ በመጠቀም እግዚአብሔርን መፈተን አስፈላጊ ነው ወይ? በማለት አንዳንድ ክርስቲያኖች ይከራከራሉ። ይህን መንገድ ከመጠቀም የሚያግደን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ የለንም። ሆኖም ግን ይህን ምልክት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በተሳሳተ መንገድ እንዳንገነዘብ መጠንቀቅ አለብን። ይህ መንገድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከምናውቅባቸው ሌሎች መንገዶች ጋር መጣጣም አለበት። እግዚአብሔር በጸጋው ፈቅዶ የጌዴዎንን ጥያቄ መለሰ። የእርሱን ምሳሌነት መከተል ግን አስፈላጊ አይደለም። የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል በእጃችን ስለሆነ ፈቃዱን ከዚያ ማግኘት እንችላለን። የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናውቅ እግዚአብሔር የሰጠን ሌሎች የተለመዱ መንገዶች አሉ። 

7. የመረዳት ችሎታህን ተጠቀም። የምናደርገው ነገር ለአእምሮአችን ስሜት የማይሰጥ ከሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን በጥንቃቄ ማረጋገጥ አለብን። መጽሐፈ ምሳሌ የተጻፈው በአእምሮአዊ እውቀት ስሜት የሚሰጥ ነገር እንድናደርግና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንድንኖር ነው። ጠቢብ ሰው ፈሪሃ እግዚአብሔር የሞላበት ላዛ ያዳበረ ሰው ነው። ለዛ ላበስ የሆነ አእምሮአዊ እውቀት ብዙ ጊዜ ጠቃሚ መሣሪያ ቢሆንም እንኳ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁልጊዜ በትክክል የሚመራን አይደለም። የእምነት ኑሮ ብዙ ጊዜ አእምሮአችን እንድናደርግ ከሚነግረን በላይ ያራምደናል። የእግዚአብሔር መንገድና አሳቡ እንደ እኛ አይደለም (ኢሳ. 55፡8-9)። ታላቅ የሆነ ውስጣዊ መልእክትን እግዚአብሔር ካልሰጠህ በአእምሮአዊ እውቀት ስሜት የሚሰጠውን ነገር መከተል ትችላለህ። 

ጥያቄ፡- ሀ) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደተናገረህና ምሪትን እንደሰጠህ ያረጋገጥክባቸውን አንዳንድ ሁኔታዎች ግለጥ። ከላይ ከተጠቀሱት መንገዶች የተጠቀመው የትኛውን ነበር? ለ) እግዚአብሔር እንዴት ሰውን እንደሚናገርና እንደሚመራ ከላይ የተጠቀሱትን የተለያዩ መንገዶች በአጭሩ ግላጽ። እነዚህን መንገዶች አንድን ሰው እንድታገባ የእግዚአብሔር ፈቃድ 

መሆኑን ለማረጋገጥ እንዴት ትጠቀምባቸዋለህ? 

እግዚአብሔር ለሰው በብዙ መንገዶች ይናገራል። ለአንድ ሰው በአንድ መንገድ ላሌላው ሰው ደግሞ ፈጽሞ በተለየ መንገድ ይናገራል። አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር እየመራቸው እንደሆነ በጣም ይሰማቸዋል። ለሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር በጸጥታ ይናገራል። አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ውሳኔ ማድረግ ስንፈልግ እግዚአብሔር የሚፈልገውን እያደረግን እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ እንችልም። በዉላማ እንደምንደናበር ይሰማናል። ነገር ግን እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ያለንን እምነት እንድንጨምር ይህን ሁኔታ ይጠቀምበታል። ኋላም ወደዚህ ጫላማ ዘመን መለስ ብለን ስንመለከት እግዚአብሔር እና በወሰንነው ውሳኔ እየመራን እንደነበር እናውቃለን። 

በመጨረሻ አንዳንድ የምክር አሳቦች ቀጥለው ተዘርዝረዋል። 

1. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ከሚገባ በላይ አትጨነቅ። ይልቁኑ የእግዚአብሔር ሰው ለመሆን ብቻ ትጋ። የጸሎት ሕይወትህንና መጽሐፍ ቅዱስ የማጥናት ልማድህን አዳብር። ተቀዳሚው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በነገር ሁሉ እርሱን ለማክበር በመሻት እግዚአብሔርን በመታዘዝና በፍጹም መሰጠት መመላለስ ነው። ይህን ስታደርግ እግዚአብሔር እንደሚመራህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንድታደርገው የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ እንተ ከምትጨነቀው በላይ እርሱ ያስባል። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ከመጨነቅ ይልቅ ትኩረትህ የእግዚአብሔር ሰው በመሆንህ ላይ ይሁን። 

2. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ተጣጣር። በሕይወትህ ውስጥ ዋናው ግህ ባሕርይውን ማወቅና መንገዶቹን መማር ይሁን። እስራኤላውያን በምድረ በዳ በሚንከራተቱበት ወቅት ሙሴ በእግዚአብሔር አመራር በመተማመን ተስፋ በማድረግ እንዲህ አለ «… እነሆ እንተይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፡ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን እገንህ አልኸኝ። አሁን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ እውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አላው» ሙሴ በመቀጠል «እባክህ ክብርህን አሳየኝ» አለ። (ዘጸእ 33፡12-13፥ 18)። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እራሱን ለሙሴ ገላጣላት። ሙሴ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ፈቃዱ የበለጠ በተረዳ መጠን በእግዚአብሔር ፈቃድ እየተራመደ ለመሆኑ የበለጠ እየተማመነ ይሄድ ነበር። በሕይወታችን ውሳኔ በመስጠት ጉዳይ እርግጠኛ ሳንሆን እየቀረን የምንጨነቀው እግዚአብሔርንና መንገዶቹን በማናውቅበት ወቅት ነው። 

3. የእግዚአብሔር የተገለጠ ፈቃድ የሆኑትን ግልጽ ትእዛዛቱን ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን እጥና። ምንም ዋጋ ቢያስከፍሉም ለእነዚህ ትእዛዛት ለመገዛት ወስን። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የገለጠልህን ፈቃድ ግላጽ። ፈቃዱን የማትጠብቅና በዐመፅ የምትኖር ከሆንህ በእንድ ሁኔታ ውስጥ የሚኖረውን ልዩ ፈቃዱን እንዲያሳውቅህ እግዚአብሔርን ልትጠባበቀው አትችልም። 

4 ሕይወትህ በንጽሕና መጠበቁን አረጋግጥ። የምታውቀውን ማንኛውንም ኃጢአት ተናዘዝ። የቅድስና ሕይወት የማትኖር ከሆነ፥ ኃጢአት በሕይወትህ ካላ፥ የስስታምነት ወይም ያለመታዘዝ መንፈስ ካለህ፥ እግዚአብሔር እይመራህም። የራስህን መንገድ እየተከተልክ ሳለህ እንድትሰናከልና እንድትወድቅ ይተውሃል። በዚህም በንስሐ እንድትመለስና የራስህን ሳይሆን የእግዚአብሔርን መንገዶች እንድትፈልግ ያደርግሃል።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: