መንፈሳዊ ስጦታ (ሮሜ 12፡1-8)

ጥያቄ፡- ሮሜ 12፡1-8 በጥንቃቄ አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው መሥዋዕት ወይም መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባር ምን ዓይነት ነው? ለ) መለወጥ ያላበት የእኛነታችን ክፍል የትኛው ነው? የመላወጡስ ውጤት ምንድን ነው? ሐ) እራሳችንን ከሌሎች ጋር እያወዳደርን በምናይበት ጊዜ ራሳችንን እንዴት መመልከት እንዳለብን ጳውሎስ የሰጠን ማስጠንቀቂያ 

ምንድን ነው? መ) ለእያንዳንዱ ሰው ‹የእምነትን መጠን› የሚሰጠው ማን ነው? ሠ) ቤተ ክርስቲያን ከአንድ አካል ጋር የምትመሳሰለው እንዴት ነው? ረ) በዚህ ስፍራ የተጠቀሱት ስጦታዎች ምን ያህል ናቸው? ሰ) በስጦታዎች መካከል ካለው ልዩነትና ከስጦታዎች አጠቃቀም በዚህ ክፍል ልንማር የምንችላቸው ጠቃሚ እውነቶች ምንድን ናቸው? 

የሮሜ 12፡1-8 መሠረት 

የሮሜ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለድነት (ደኅንነት) ያለው ዕቅድ በአጭሩ የቀረበበት ነው። በዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ጳውሎስ ዓለም ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ምክንያት ጥፋተኛ መሆኑን አሳውቋል። ማንኛውም ሰው የሚድንበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ በእምነት ወደ ክርስቶስ በመመለስ እንጂ የእርሱን ጽድቅ በመፈለግ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ የራሱን መንገድ በመፈለግ እንዳልሆነ አስረድቶአል። የሮሜ መጽሐፍ ከሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝብ የሰጠው የብሉይ ኪዳን ሕግ ከአዲሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ማለትም ክርስቲያኖች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ማጤን ነው። ጳውሎስ ሲናገር የብሉይ ኪዳን ሕግ መልካምና እግዚአብሔር የተጠቀመበት ቢሆንም እንኳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከእንግዲህ በኋላ አስፈላጊ አይደለም ይላል። ታዲያ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን የተለማመዱትና (ለምሳሌ የአሣማ ሥጋን የማይበሉ) የራሳቸው ባሕል ያላቸው ክርስቲያን አይሁዶች፥ በአብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን ሕግጋት ሥር ከማይተዳደሩት (ለምሳሌ የአሣማ ሥጋን ከሚበሉት) የአሕዛብ ክርስቲያኖች ጋር አብረው የሚኖሩት እንዴት ነው? 

(ሮሜ 12-16 ለዚህ ተግባራዊ ችግር መልስ በመስጠት ላይ ያተኩራል። 

ሮሜ 12፡1-2 

ሮሜ 12፡1-2 ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ጨምሮ ሌሎች ትምህርቶቹን ሁሉ የመሠረተበትን አጠቃላይ የመከራከሪያ አሳብ የሚያቀርብበት ክፍል ነው። በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ ሲናገር ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ አትኩሮት ማድረግ አለባቸው ይላል። የአይሁድ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የተላየ ታሪካዊ መሠረት ካላቸው ከአሕዛብ ጋር ተስማምተው ለመኖር ፈቃደኛ የሚሆኑት የሚያድናቸው ባሕላቸው ቅርሳቸው ወይም የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን መጠበቃቸው ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት መሆኑን ከተነገዘቡ ብቻ ነው። የዳንንና ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ያለን ማንኛችንም አብረን መኖር የምንችልበት መሠረት የእግዚአብሔር ምሕረት ነው። ከተለያየ ብሔር መውጣታችንን ለመክፋፈላችን ምክንያት ካደረግን መሠረታዊውን እውነት ዘንግተናል ማለት ነው። ከየትኛውም ባሕል ወይም ነገድ እንውጣ፥ ምንም ያህል ድሃ ወይም ሀብታም ብንሆን፥ ወንድም ሆነ ሌት እንሁን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እኩል እንቀርባለን (ገላ. 3፡28-29)። በዚያ ያለነው ክምሕረቱ የተነሣ ብቻ ነው። በክርስቲያኖች መካከል ስለ መንፈስ ቅዱስ እንኳ የሚደረግ የቃላት ጦርነት በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ከማተኮር ይልቅ በትዕቢት በራስ ጽድቅ በማጉላት ላይ ያነጣጠረ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) በኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ የሚጋጩባቸውን ነገሮች በምሳሌነት ዘርዝር። ለ) በሚጋጩበት ጊዜ ያዳናቸውን የእግዚአብሔር ምሕረት የረሱ መሆኑን ይህ እንዴት ያሳያል? 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ጳውሎላ የሚነግረን ኃጢአተኞች ሳለን እግዚአብሔር ስላደረገው ምሕረት ስናስብ ከእኛ ዘንድ የሚጠብቀው ምላሽ ሰውነታችንን የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጐ ማቅረብ መሆኑን ነው። መሥዋዕቶች ምን እንደሆኑ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ያውቁ ነበር። በብሉይ ኪዳን ሥርዓት አምልኮና አሕዛብ የአምልኮተ ጣዖት ሥርዓት መሥዋዕቶች የተለመዱ ነበር። በመሥዋዕት ውስጥ ሁልጊዜ የእንስሳት ሞት አላ ማለት ይቻላል ሰዎች በቀድሞ ዘመን እንስሳትን መሥዋዕት ያቀርቡ የነበረ ቢሆንም፥ ጳውሎስ ግን በቤተ ክርስቲያን እዲስ ዓይነት መሥዋዕት መኖሩን ገለጸ። ይህም እራሳችንን መልስን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማድረግ ነው። ለመሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ እንደሚሞት እንሞታለን ማለት አይደለም። ይልቁኑ ይህ ሥዕላዊ እገላላጽ ነው። በሮማ 6 ጳውሎስ የሚያስተምረው ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንደምንኖር ነው። ጳውሎስ ይህንኑ አባባል በሮሜ 12 ላይ በመጠቀም የሚያስተላልፍልን መልእክት፥ ስለ እኛ ለተደረገው የእግዚአብሔር ምሕረት ተመጣጣኝ ምላሽ የሚሆነው እራሳችንን ለእግዚአብሔር መልሰን ማስረከብ መሆኑን ነው። ለራሳችን የላዊ ፈቃድ መሞት አለብን። በሌላ ስፍራ ጳውሎስ በዋጋ ተገዝተናል ይላል (1ኛ ቆሮ. 6፡20)። እራሳችንን መሥዋዕት አድርገን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ያለ ምንም ቅደመ-ሁኔታ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንሰጣለን ማለት ነው። አንተ ገዝተኻኛል እኔ የአንተ ነኝ በእኔ የምትፈልገውን – እድርግ። ወደ ፈልክበት ላከኝ ማለታችን ነው ዕቅዳችንን፥ ሕልማችንንና ፍላጐታችንን ሁሉ ለእርሱ ሰጠን ማለት ነው። 

ጳውሎስ እንደሚናገረው እራሳችንን ሕያውና ቅዱስ መሥዋዕት አድርጐ የማቅረብ ዝንባሌ «መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባር» ነው። የአምልኮአችን፥ የዝማሬአችን፥ የስብከታችን፥ አሥራትን የመስጠታችንና መንፈሳዊ ስጦታዎችን የመጠቀማችን መሠረቱ በሙሉ እራሳችንን መሥዋዕት አድርጐ የማቅረብ ዝንባሌ መሆን አለበት። እራሳችንን ለመስጠት ካልፈለግን የምናደርጋቸው ማናቸውም ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እያገኝም። ድምጻችን እስኪዘጋ ድረስ ብንዘምርም እንኳ መላ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እስካልሰጠን ድረስ ቃላትን መለፍለፍ ብቻ ይሆናል። እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ያለንን ገንዘብ ሁሉ ብንሰጥም እንኳ መላ ሕይወታችንን ካልሰጠነው የምናደርገው ሁሉ ከንቱ ነው። 1ኛ ቆሮ. እንደሚያስተምረን የፍቅር መንፈስ ሊሰፍን ይገባል። ይህ የሚሆነው ደግሞ እራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ ብቻ ነው። 

በሦስተኛ ደረጃ፥ ጳውሎስ የሚለው ከእግዚአብሔርና ከእኛ እጅግ ከሚለዩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን እእምሮአችን መለወጥ አለበት። ክርስቲያኖች ከመሆናችን በፊት እናስባቸው የነበሩ ነገሮች፥ ለእኛ እጅግ ጠቃሚ የነበሩ ነገሮች፥ ይቆጣጠሩን የነበሩን ባሕላዊ ነገሮች ሁሉ አሁን መለወጥ አለባቸው። አስተሳሰባችንን የምንቀይረው እግዚአብሐር የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለማድረግ በመፍቀድ ነው። እግዚአብሔር እንድናስባቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች ስናስብ፥ እግዚአብሔር አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ነገሮች ስናደርግ ያኔ እግዚአብሔር እንዴት እንድንመላለስ እንደሚፈልግ እናውቃለን። በሌላ አባባል ጳውሎስ እንዳለው «የእግዚአብሔርን ፈቃድ» እናውቃለን። ይህንን ስናደርግ የእግዚአብሔር መንገድና፥ «ፈቃድ መልካም ፍጹምና ደስ የሚያሰኝ» የመሆኑን እውነታ እንለማመዳለን (ሮሜ 12፡2)። 

ጳውሎስ በዚህ ቦታ ባይናገረውም እንኳ ሌሎች ክፍሎችን የምናጠና ብንሆን እራሳችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አስተሳሰባችንንና ተግባራችንን መቀየር ስሰብአዊ ጥረት ብቻ ሊደረግ እንደማይቻል የተረዳን መሆኑን ማየት እንችል ነበር። ይልቁኑ ይህ በውስጣችን የሚሠራው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። 

ጥያቄ፡– ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት ነገሮች ብናስታውስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ስምምነት የሚኖረው እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ነው? 

ሮሜ 12፡3-8 

ጳውሎስን ያሳሰበው ነገር አስተሳሰባችን የተለየ መሆን እንደሚገባው ብቻ አልነበረም። አእምሮአችን መታደስ ያለበት ተግባራችንም እንዲለወጥ ነው። ተግባራችን በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ውስጥ የሚኖረንን የእርስ በርስ ግንኙነት ይወስናል። ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በታደሰ አእምሮ ቁጥጥር ሥር ከመኖር፥ ሰውነቱን ሕያው መሥዋዕት አድርጐ ከማቅረብ ጋር በጥብቅ ያቆራኘዋል። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚከተሉትን እውነቶች ልብ በል። 

1. መንፈሳዊ ሕይወቱና እግዚአብሔር የሰጠውን መንፈሳዊ ስጦታዎች ማወቅ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው። ጳውሎስ ለክርስቲያኖች ሲናገር «እንደ ባለ አእምሮ ስለማሰብ» ተናግሯል። የዚህ ክፍል ቀዳሚ መልእክት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች አጠቃቀም ጉዳይ ነው። ይህ ዐረፍተ ነገር የሚያሳየን ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ሁለት በተለያየ አቅጣጫ የከረሩ አሳቦች መኖራቸውን ነው። የመጀመሪያው፥ የትዕቢት አሳብ ነው። በመታበይ ስለ ራሳችን በምናስብበት ጊዜ ለመገምገሚያ የምንጠቀመው የተሳሳተ መመዘኛን ነው። እራሳችንን ከሌሎች ከእኛ የባሱ ናቸው ብለን ከምናስባቸው ጋር እናወዳድራለን። በልባችን ትዕቢት በሚኖርበት ጊዜ የበላይነት ስሜት ያድርብናል። እኔ ወንድ ነኝ አንቺ ለት ነሽ ስለዚህ ከአንቺ እሻላለሁ። እኔ ከተማረ ቤተሰብ ሆንህ አንተ ከወዛደር ቤተሰብ ነህ። እኔ ከምርጥ ጐሳ ነኝ፤ እንተ የባሪያ ጐሳ ነህ። በዓለምም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ፀብን የሚጋብዙ እንደነዚህ ዓይነት ዝንባሌዎች ሁሉ የሚመነጩት ክትዕቢት በሚወጣ እኔ እበልጥ እንተ ታንስ ባይነት ነው። ለላ ራሳችን ባላን በትዕቢት የተሞላ ግምት ሰዎች ሲያፋጥጡን ቁጡና ቀናተኞች ሆነን እንታያለን። ይህም ወደ ፀብና ክፍፍል ይመራናል። 

መንፈሳዊ አቋማችንን በመመልከት እራሳችንን ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በማወዳደር ከእነርሱ የተሻልን እንደሆንን ካሰብን መንፈሳዊ ትዕቢት ይዞናል ማለት ነው። ወይም ስጦታዎችንንና ችሎታችንን ከሌሎች ጋር ስናወዳድር ወደ ትዕቢት ውስጥ እንገባለን። ከእከሌና ከእከሌ በተሻለ ሁኔታ ለማስተማር እችላለሁ የሚለው ብዙ ጊዜ በአእምሮኦችን ብልጭ የሚል አሳብ ነው። ማወዳደር ስንጀምር፥ እኛ ከሌሎች እንደምንቫል እራሳችንን በማሳመን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እናደርጋለን። በርካታ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መምራትን ሲለማመዱና ከሌሎች በጣም የተሻሉ በመሆናቸው ያላ እነርሱ ቤተ ክርስቲያን ልትሠራው አትችልም ብለው የሚያስቡትን ሲሠሩ በወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ። 

እራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ጋር ከማወዳደር ይልቅ የእግዚአብሔርን የመጨረሻ መመዘኛ መጠቀም አለብን። (አስታውስ እግዚአብሔር «እኔ ቅቶስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ» ብሏል) እራሳችንን እግዚአብሔር ከሚፈልግብን ካፍጹም ቅድስና ጋር ስናወዳድር በተገቢ ትሕትና እንኖራለን። ልንመካበትና ልንኮራበት የምንችለው አንዳችም ነገር እንደሌለ እንነዘባለን። ይህ ደግሞ ከሌሎች ጋር በሰላምና በስምምነት ወደ መኖር ይመራናል። 

ሁለተኛው፥ ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በሌላኛው ጽንፍ አክርረው ይሄዳሉ። ስለ ራሳቸው እጅግ ዝቅ ያለ አስተሳሰብ ስላላቸው ለእግዚአብሔር አንድም ነገር የሚያደርጉ እይመስላቸውም። የተለያዩ አስደናቂ ስጦታ ያላቸውን ሰዎች በመመልከት ይቀናሉ። ‹እንደ እከሌና እከሌ ለመስበክ አልችልም፤ ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን አልጠቅምም› ማለት የአስተሳሰባቸው ዘይቤ ነው። ይህ አስተሳሰብ በተለይ ጎልቶ የሚታየው በባሕላቸው ወንዶችን እንዲያገለግሉ እንደተፈጠሩ አድርገው በሚያስቡ ሴቶች ዘንድ ሊሆን የራሳቸው መንፈሳዊ ስጦታዎችና ችሎታዎች እንዳሏቸው በእነዚህም እግዚአብሔርን ማገልገል እንደሚችሉ አይገነዘቡም። 

ጥያቄ፡- ስለ ራሳቸው ከላይ የተመለከትናቸውን ሁለት የከረሩ አስተሳሰቦች በመያዝ ሰለሚሰቃዩ (የምታውቃቸውን) ክርስቲያኖች ምሳሌ ስጥ። 

2. ጳውሉላ ሁላችንም ለክርስቶስ የምናስፈልግ መሆናችንን እንድንገነዘብ ይፈልጋል። ልንጫወታቸው የሚገቡ ጠቃሚ ሚናዎች አሉን። ስጦታዎችን አጠቃልላን የያዝን ማናችንም ላላሌለን ልንታበይ አንችልም። እያንዳንዳችን ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልግ ቢያንስ አንድ ስጦታ አለን። ወደ ራሳችን ሕይወት በመመልከት ደካማና ብርቱ ጐናችንን ማጤን አለብን። እምነትንና የአገልግሎት ችሎታን የሰጠን እግዚአብሔር መሆኑን ተገንዝበን የራሳችንን ስጦታዎችና ችሉታዎች ለይተን በማወቅ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም አገልግሎት ላይ ማዋል አለብን። 

እያንዳንዱ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለማስረዳት ጳውሎስ በክርስቶስ አካል ማለትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ክርስቲያኖች ከሥጋዊ አካል ጋር ያወዳድራቸዋል። ሰውነት ለጠነኛ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያስፈልጉ ብዙ ክፍሎች (ጆሮዎች፥ ዓይኖች፡ አፍንግ) አሉት። እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል ልዩ የሆነ የራሱ የሥራ ድርሻ አለው። ሁሉም አንድ ዓይነት ሥራ ለመሥራት ቢሞክሩ፥ ለምሳሌ ሁሉም ዓይን ቢሆኑ አካል በሚገባ ሊሠራ አይችልም ነበር። ደግሞም እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል በሥራው እርስ በርስ የተያያዘ ነው። ዓይኖች ባይኖሩ እጆች በሚገባ አይሠሩም ነበር። ምክንያቱም የሚይዙትን ስለማያውቁ ነው። በክርስቶስም አካል ውስጥ እንዲሁ ነው። መንፈስ ቅዱስ ለተለያዩ ሰዎች በሚሰጣቸው የተለያዩ ስጦታዎቻቸው ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው የተያያዙ ናቸው፤ ለመንፈሳዊ ጤንነትም አንዱ ለሌላው አስፈላጊ ነው። የሚያሳዝነው እውነት ግን ብዙ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ስጦታዎችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለመጠቀማቸው ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት፥ ቃሉን መስማትና መዘመር ብቻ ያረካቸዋል። ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አያገለግሉም። በውጤቱም ቤተ ክርስቲያን የተዛባ አስተዳደግ ያላት ትሆናለች። በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ካልተጠቀሙ ቤተ ክርስቲያን በጤንነት ሥራዋን ልትሠራ አትችልም። 

3 መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የሚሰጥ ቢሆንም ለሁሉም የሚሰጠው ስጦታ ደረጃ ው እኩል አይደለም። ጳውሎስ «እንደ ተሰጠን ጸጋ መጠን የተለያዩ ስጦታዎች አሉን» ይላል። ለምሳሌ መንፈስ ቅዱስ የማስተማርን ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተለያዩ ሰዎች ይሰጣል። ሆኖም ግን ሁሉም አስተማሪዎች እኩል የማስተማር ችሎታ አይኖራቸውም። አንዱ ከሌላው እጅግ ይሻላል። ነገር ግን የትኛውን ችሎታ በምን መጠን ማን ማግኘት እንዳለበት የሚወስን እግዚአብሔር ስለሆነ ባሉን ስጦታዎች እንዳንታበይ ወይም ሌሎች ባላቸው ትላልቅ ስጦታዎች እንዳንቀና መጠንቀቅ አለብን። 

4. ስጦታችንን የምንጠቀምበት ዝንባሌ የለጦታችንን ያህል አስፈላጊና ልንጠነቀቅበት የሚገባ ነው። ትንቢት በእምነት መነገር አለበት። ስጦታ በችሮታ ወይም በለጋስነት መደረግ አለበት። አመራር በትጋት መሆን አለበት። ምሕረት ማድረግ ደግሞ በደስታ መሆን አለበት። ብዙ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን ይጠቀሙበታል። የአጠቃቀማቸው የልብ ዝንባሌ ግን ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያስከብር አይደለም። በኋላ በ1ኛ ቆሮ. 13 እንደምናየው (እንደ ተአምራት ያሉ ትላልቅ ተግባራት ያለ ትክክለኛ ዝንባሌ (ያለ ፍቅር) ከተደረጉ ከንቱ ናቸው። 

5. ጳውሎስ የክርስቶስ አካል በሙላት በሚገባ እንድትሠራ የሚያስፈልጉ አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ምሳሌ ያቀርባል። ቀጥሎ የምናቀርበው እያንዳንዱን ስጦታ በአጭሩ ብቻ ነው። ወደፊት በምንመለከታቸው ትምህርቶች የስጦታዎችን ትርጉሞች በዝርዝር እናያለን። 

ሀ. ትንቢት መናገር፡- ትንቢት የመናገር ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ በተሰጠ መገለጥ ላይ ተመርኩዞ የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ነው። ትንቢትን የመናገር ስጦታ ዓላማው ቤተ ክርስቲያንን ለማበረታታትና ለማነጽ ነው። ይህ ስጦታ ብዙ ጊዜ ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮች መናገርን እንደሚይዝ ብናስብም ይህ የትርጉሙ እንድ ክፍል ብቻ ነው። ትንቢት ስለ ወደፊት ሁኔታዎች ገላጭ የሚሆንበት ጊዜ አላ (ለምሳሌ የሐዋ. 11፡28፤ 21፡10-11)። ብዙ ጊዜ ቀን በአንድ ሁኔታ ውስጥ እግዚእብሔር ያላውን ፈቃድ ለመግለጥ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ መልእክትን ማወጅ ነው (ለምሳሌ 1ኛ ቆሮ. 14፡29፤ የሐዋ. 13፡1-2)። አንዳንድ ክርስቲያኖች በዚህ ቦታ (ትንቢት› የሚለው ቃል የተገላጻ ው እጅግ ሰፋ ባለ ሁኔታ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ማንኛውንም ሰው፥ በማንኛውም ጊዜ ለአምልኮ የተሰበሰቡ አማኞች ክርስቶስን እንዲመስሉ ለማበረታታትና ለማሳመን የሚያመጣውን መልእክት ያጠቃልላል ይላሉ። ይህ ስጦታ በአንደኛ ደረጃ መጠቀሱ በላ ውሎስ አእምሮ ከሁሉ የላቀው መንፈሳዊ ስጦታ እርሱ 

መሆኑንና እማኞች ለእምልኮ ሲሰበሰቡ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት የሚረጋገጥበት ዋነኛው መንገድ ይኸው መሆኑን ለማሳየት ነው ብለው አንዳንዶች ያስተምራሉ። ይህን ስጦታ «እንደ እምነቱ መጠን ይናገር» ሲል ጳውሎስ ምን ማለቱ እንደሆነ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። ይህ እሳብ በሁለት የተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ ይሰጠዋል። የመጀመሪያው በትንቢት ተናጋሪው ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ያለውን የእምነት መጠን ማላት ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ የሚላው ይህ ስጦታ ያላቸው ክርስቲያኖች የተላያዩ ትንቢት የመናገር ችሎታዎች እንዳሏቸውና ስጦታው ያለው ማንኛውም ሰው ደግሞ የራሱን ችሎታ ከሌሎች ጋር ሳያነፃፅር መጠቀም እንዳለበት ነው። በሁለተኛው አመለካከት ላቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትንቢት ከእምነት ማለትም ከወንጌል መልእክት ጋር የሚሄድ መሆን አለበት ማለት ሲሆን ይህም መልእክት ጳውሎስ በሮሜ መጽሐፉ ያስተማረው ነው። በዚህ ስፍራ በቤተ ክርስቲያን የሚነገሩ ትንቢቶች ትክክል ስለመሆናቸው የክርስቶስ አካል በሆነችው በቤተ ክርስቲያን መመዘንና መረጋገጥ እንዳለበት ጳውሎስ በ1ኛ ተሰ. 5፡20-21 እንዳደረገው ክርስቲያኖችን ማሳሰቡ ሊሆን ይችላል። ትንቢቶች የሚመዘኑት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማወዳደር ነው። ላአካሉ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ክርስቲያኖች የሚያውቁት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ክገለጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚገኘው መለኮታዊ እውነት ጋር ሊስማማ ነው። 

ለ. ማገልገል (አገልግሎት)፡- ይህ ሌሉች የቤተ ክርስቲያን አባላትን በማገልገል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሥራት ችሎታን የሚያመላክት ነው። ሌሎችን በማገልገል ፍላጐት ላይ ተመሥርተ በሎሌነት መንፈስ የሚደረግ መሆን አለበት። 

ሐ ማስተማር፡- ይህ ስእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚገኘውን እውነት በግልጽና በትክክል የመግለጥ ችሉታ ሲሆን ዓላማውም ሰዎች እግዚአብሔርንና ቃሉን በሚገባ እንዲረዱና እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ መኖር እንዲችሉ ማድረግ ነው። 

መ. መምከር፡- ተስፋ የቆረጡ ክርስቲያኖች ተስፋቸውን እንደገና በማደስ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ የማበረታታት ችሎታ ነው። ተስፋ የቆረጠን ሰው ስሜት እንደገና የማንሣትና ደስተኛ እንዲሆን የማድረግ ተግባርን . ያካትታል። 

ሠ. መስጠት፡- መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን የሚለውጥበት አንዱ መንገድ በልግስና እንዲሰጡ በማድረግ ነው። ገንዘብ ሁሉ የሚመጣው ከእግዚአብሔር መሆኑንና በእርሱም ሌሎችን እንዲረዱበት እግዚአብሔር እንደሚፈልግ በመገንዘብ ግላዊ ቁሳዊ ብልጽግና ከመፈለግ ይልቅ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ይረዱበታል። እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከሁሉ የላቀውን እንደሰጠን በነፃ ነትና በልግስና ለሌሎች መስጠት አለብን። 

ረ. መግዛት፡- ይህ ቃል በመንፈስ ቅዱስና በ ሕዝቡ ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት ተመርጠው ስለሚያገለግሉት ሽማግሌዎች ይናገራል። ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሥር ሆነው ቤተ ክርስቲያንን በጥንቃቄ፥ ደግሞም በትጋት ይመሩ ዘንድ ይጠበቅባቸዋል። 

ሰ. ምሕረትን ማድረግ፡- ምሕረት ማድረግ ማለት እርዳታ የማይገባቸውን ሰዎች መርዳት ማለት ነው። ይህ ስጦታ የታመሙትን፥ ድሆችን፥ በዕድሜ የገፉትንና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የመርዳት ችሎታ ነው። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎችን እን ደ ሸክም ከማየትና በቅሬታ ከመርዳት ይልቅ በደስታ መንፈስ ሊደረግ ይገባል ። 

አንዳንዶቹ ላጦታዎች ክርስቲያኖች ላአምልኮ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ስጦታዎቻቸውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የሚያመለክቱ ናቸው። (ለምሳሌ- ትንቢት መናገር፥ ማስተማርና መምከር።) ሌሎች ስጦታዎች ደግሞ የሚያመለክቱት በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ለላ መርዳት ነው (ምሳሌ፡- መስጠትና ምሕረት ማድረግ)። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ የተለያዩ ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያስፈልጉት ለምንድን ነው? ለ) ከእነዚህ ስጦታዎች አንዳንዶቹ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማይገኙበት ጊዜ ምን ይከሰታል? ሐ) እነዚህ ስጦታዎች የእያንዳንዳቸው በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ እንዴት እየሠሩ እንደሆነ ምሳሌዎችን ስጥ። መ) በሮማ 12፡ 1-8 ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሰጡትን አንዳንድ ዋና ዋና መመሪያዎች ዝርዝር። ሠ) ከእነዚህ ስጦታዎች {አንዱ አለህን? ከሆነ እንዴት እየተጠቀምክበት እንደሆነ መግለጫ ስጥ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.