መንፈሳዊ ስጦታ (ኤፌሶን 4፡1-16 )

ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ዋና ኃላፊነት ምንድን ነው ብለው ያስባሉ? ለ) መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዋና ኃላፊነት ነው ብሎ የሚያስተምረው ምን ይመስልሃል? 

የመሪዎች · ዋና ኃላፊነት ምንድን ነው? ነገሮች ሁሉ በተገቢ ሁኔታ እንዲሄዱ ቤተ ክርስቲያንን ማስተዳደር ነውን? በኃይልና በሥልጣን ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው መንገር ነውን? ሰዎች ምን ማመን እንዳለባቸው ማስተማር ነውን? ለቤተ ክርስቲያን ራእይንና ምሪትን መስጠት ነውን? ለቀሩት የቤተ ክርስቲያን አባላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሥራዎችን መሥራት ነውን? የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ብዙ ጊዜ የሚያስቡት ዋና ኃላፊነታቸው ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ እንደሆነ ነው። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ኃላፊነቶች አንዳንዶቹ ቢሆኑም እንኳ ዋናዎቹ ቀን አይደሉም። በኤፌ. 4፡1-2 የተጠቀሱትን የመሪነት ስጦታዎች ስናጠና ይህ ዋና ኃላፊነት ምን እንደሆነ እንማራለን። – 

ጥያቄ፡- ኤፌ. 4፡1-16 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ ክርስቲያኖች የሆንን እኛ አሁን እንዴት መመላለስ አለብን ይላል? ለ) የእኛ ባሕርዮች ሆነው ማንም (እኛን ሊለይባቸው የሚችሉ ዝንባሌዎች ምንድን ናቸው? ሐ) በቁ. 3 ላይ የተጠቀሰው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምንድን ነው? መ) በዚህ ክፍል «አንድ» ናቸው ተብለው የተጠቀሱ ነገሮችን ዘርዝር። ሠ) በዚህ ክፍል መሠረት ስጦታዎችን የሚሰጠን ማን ነው? ረ) በዚህ ቦታ የተጠቀሱ የአመራር ወይም የመንፈሳዊ ስጦታዎች አምስት አቋሞችን ዘርዝር። ሰ) [በእነዚህ አቋሞች ላሚበረክተው አገልግሎት ዓላማው ምንድን ነው? ሸ) በቁ. 13 ና 15 ላይ የተገለጹት የእነዚህ ስጦታዎች የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው? ቀ) እነዚህን መንፈሳዊ ስጦታዎች በተገቢው መንገድ መጠቀም ምእመናንን የምንን ከመምሰል ይጠብቃል? ) 

ሮሜ 12፡1-8 በትኩረት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከቤተ ክርስቲያን አባላት አቅጣም የሚያይ ሲሆን የክርስቶስ አካል ጠንካራ ይሆን ዘንድ ስጦታዎች ሁሉ እንዴት በአንድነት እንደሚሠሩ ይናገራል። ሆኖም ግን የኤፌ. 4፡1-16 ትኩረት በቤተ ክርስቲያን የመሪነት ላጦታ ላይ ሆኖ የእነዚህ ስጦታዎችን ተገቢ የሆነ አጠቃቀም ወደ ጠቅላላው ቤተ ክርስቲያን ያመጣዋል። 

የኤፌ. 4፡1-16 መሠረት አሳብ (ዳራ) 

የኤፌሶን መጽሐፍ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ባለው ግንኙነትና በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመናችን የተነሣ ባገኘናቸው በርካታ መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ነው። በክርስቶስ ከሆንን የእግዚአብሔር አብ ብልጽግናዎች ሁሉ የእኛ ናቸው። ከእነዚህ ብልጽግናዎች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ከሆንን አኗኗራችን መለወጥ አለበት። ኤፌ. 4-6 የሚነግረን የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን ነው። 

ኤፌ. 4፡1-6 

ኤፌ. 4፡1-6 ልናጠና የሚከተሉት እውነቶች በትምህርት መልክ ተሰጥተው እናያለን። 

1 ኤፌ. 4፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ላለው ትምህርት መሠረት ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንንና በእግዚአብሔር ክተባረክን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የሚኖር ከሆነ ሕይወታችን መቀየር ያለበት እንዴት ነው? ጳውሎስ የሚናገረው ለተጠራንበት መጠራት የሚገባ ክብር ያለው ኑሮ እንድንኖር ነው። ይህንን እንዴት እናደርጋለን? በተለይ ደግሞ በክርስቶስ አካል በሆኑት መካከል የተለወጥንና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንደሆንን የሚያረጋግጥ ሕይወት እንዴት እንኖራለን? ጳውሎስ አስደናቂ በሚባሉ እንደ ተአምራትና ስልሳናት መናገር ላይ ትኩረት አላደረገም። እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ ሕይወታችንን በሚገባው መንገድ እየኖርን መሆናችንን አያረጋግጡም። ጳውሎስ በቀረው የኤፌሶን ክፍል የሚናገረው ለወንጌል የሚገባ ሕይወት እንዴት መኖር እንዳለብን ነው። 

2. ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለወንጌል የሚገባ ሕይወት መኖር ማለት በተቀዳሚ ሰዎች በሚሠሩት ውጫዊ ተግባራት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ያስተምራሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው በኢየሱስ ባመነበት ቅጽበት እንዳይጠጣ፥ እንዳያጨስ፥ እንዳያመነዝር፥ ከአንድ በላይ ሚስቶች ካሉት ከአንዱ በስተቀር ሌሎችን እንዲተው ወዘተ… ይነገረዋል። እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ ጳውሎስ ሁልጊዜ የሚያስተምረው ለወንጌል የሚገባ ሕይወት መኖር የሚጀመረው ተገቢ የሆነ የተስተካከለ አቋም ወይም ባሕርይ በመያዝ መሆኑን ነው። በኤፌ. 4፡2-3 ጳውሎስ የሚያስተምረን በተገቢ ሁኔታ መኖር ከልብ እንደሚጀምር ነው። ትህትናን፥ ጨዋነትን፥ ትዕግሥትንና ፍቅርን ይጨምራል። በሌላ አባባል እንደ እግዚአብሔር ልጆች ለአዲሱ አቋማችን ተገቢ የሆነን ኑሮ መኖር ማለት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በሕይወታችን አለ ማለት ነው (ገላ. 5፡ 22-23 ተመልከት)። 

መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚያፈራቸው ውስጣዊ ባሕርይዎች ለሌሎች የሚረጋገጡበት ተቀዳሚ መንገድ ምንድን ነው? ከእዚህ ዋና 

መንገዶች አንዱ በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚፈጠረው «አንድነት ነው። ይህ አንድነት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚሠራው ሥራ ቀጥተኛ ውጤት ነው። ጳውሎላ አንድ እንደሆኑ የገለጣቸውን ሰባት የተለያዩ ነገሮች አስተውል። 

አንድ አካል፡- ይህ ጳውሎስ እንድነት ይኖር ዘንድ ፍላጐቱ የነበረበት የክርስቶስ አካል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የተላያዩ የእምነት ክፍሎች (ዲኖሚኔሽኖች) መኖራቸውን የሚከለክል ባይሆንም እንኳ በእግዚአብሔር አእምሮ ያለችው አንድ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት። በመንግሥተ ሰማያት ቃለ ሕይወት፥ ሙሉ ወንጌል፥ መካነ ኢየሱስ ወዘተ… የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት አይኖሩም። የክርስቶስ ኢየሱስ አካል ብቻ ናት የምትኖረው። 

አንድ መንፈስ፡- ይህ በእያንዳንዳችን ሕይወት ለመኖር የመጣው መንፈስ ቅዱስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በተባለች አንድ አካል ውስጥ የሚጨምረን መንፈስ ቅዱስ ነው። 

አንድ ተስፋ፡- የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን በምንሞትበት ጊዜ ሁላችንም ወደ እንድ ሥፍራ ወደ መንግሥተ ሰማያት የመሄዳችን ተስፋ ነው። ክርስቲያኖች በሚሞቱበት ጊዜ የሚሄዱበት የተለያዩ ስፍራዎች የሉም። በምድር ላይ የየትኛይቱም ቤተ ክርስቲያን አካል ቢሆኑም እውነተኛ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደዱም ጠሉ የሚሄዱት ወደ አንድ ስፍራ ነው። ይህ ተስፋ እውነት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለእኛ ባደረገው ሥራ ምክንያት ነው። 

አንድ ጌታ፡- ልናመልከውና ልናከብረው የሚገባው አንድ ጌታ ለእርሱ እራሳችንን በማስገዛት ልንኖርለት የሚገባን እርሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። 

አንድ እምነት፡- ይህ ሁለት ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል። ሁላችንም የጻንንበት ብቸኛ መንገድ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ሊያመለክት ይችላል። ወይም እንድንበት ዘንድ ሁላችንም ልናምነው የሚገባንን አንዱን ወንጌል ሊያመለክት ይችላል። 

አንድ ጥምቀት፡- አንዳንዶች ይህ የሚያመለክተው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ነው ብለው ቢያስቡም እንኳ የኤፌሶን ክርስቲያኖች ሁሉ ባመኑበት ጊዜ የተላማመዱት የውኃ ጥምቀት ሳይሆን አይቀርም። 

አንድ እግዚአብሔር፡- የሁላችንም አባት እግዚአብሔር የነገሮች ሁሉ ዋና ምንጭ ነው። አሕዛብ እንደሚያስተምሩት ብዙ አማልክት የሉንም። እንድ አምላክ ብቻ አለ። 

** ጳውሎስ ሥላሴን የአንድነትና የብዛት ምሳሌ አድርጐ እንዴት እንዴጠቀሰ ልብ በል። ሦስቱንም በተናጠል ቢጠቅሳቸውም ቀን ሁሉም በአንድነት እንደሚሠሩና እርስ በርስ እንደማይለያዩ ግልጽ በሚያደርግ ሁኔታ ነው። 

ኤፌሶን 4፡7-11 

በኤፌ 47-16 ጳውሎስ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያለው አንድነት እንዴት እንደሚጠናከር መለስ ብሎ ይናገራል። በዚህ ስፍራ ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይናገራል። ጳውሎስ ላማሳየት የፈለገው አንድነት ሊኖር የሚችለው በልዩነት ውስጥ መሆኑን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉም አንድ ስጦታን አይሰጥም። የተለያዩ ስጦታዎችን ለእያንዳንዱ ሰው ይሰጣል። አንድነትና ጥንካሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይኖሩ ዘንድ ከተፈለገ ልዩነቶችም መኖር አለባቸው። እንደ ክርስቲያን በሰዎች ሰብዕናና መንፈሳዊ ስጦታዎች መካከል ያሉት ልዩነቶች ለመከፋፈል ሳይfን ለአንድነት ምክንያት እንዲሆኑን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው መማር አለብን። ጳውሎላ በኤፌ. 47 ላይ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የጠቀሳቸውን ቀጥሉ የተዘረዘሩትን መግቢያ ነገሮች አስተውል። 

1 የተሰጠው ለእያንዳንዱ ነው። በዚህ ስፍራ እንደገና የምንመለከተው ነገር በክርስቶስ አካል እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ አንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳለው ነው። ኢየሱስ ለእካሉ ማላትም ለቤተ ክርስቲያን ለመስጠት የሚሻው ስጦታዎች ሁሉ እንዲኖሩን እንዳችን ሌላችንን ስለምንፈልግ ይህን እንድነት እንዲያሳድግ የታለመ ነው። 

2. የተሰጠን በጸጋ ነው። ሠርተን ወይም ለፍተን የምናገኘው አይደለም። ለደኅንነታችን ነፃ የጸጋ ስጦታ እንደሆነ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ነፃ ስጦታ ነው (ኤፌ. 2፡8ን ተመልከት)። 

3 በክርስቶስ የተሰጠን ነው። ሌሎች ክፍሎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ቢናገሩም ጳውሎስ ግን እዚህ ላይ የሚጠቅሰው ክርስቶስን ነው። ይህ የሚያመለክተው በቤተ ክርስቲያን ሥራ ውስጥ መንፈስ ቅዱስና ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን የቅርብ ግንኙነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችን በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጠናል። 

4 ማን የትኛውን ስጦታ እንደሚያገኝ የሚወለን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንደፈለገው የሚያከፋፍል እርሱ ነው። የስጦታዎች ድልድል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አላመሆኑ በአካሉ ውስጥ ምንም ዓይነት የቅናትና የትዕቢት ዝንባሌ እንዳይኖር ያደርጋል። 

እንደሚጠበቀው ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚሰጣቸውን አንዳንድ ስጦታዎች መጥቀሱን ከመቀጠል ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን በተለየ ሁኔታ ተጽዕኖ ሊያደርጉባት የሚችሉትን አምስት ስጦታዎች ብቻ ይጠቅሳል (ኤፌ. 4፡1)። ጳውሎስ እነዚህን አምስት አገልግሎቶች ያቀረበው በመንፈሳዊ ስጦታነት ለመሆኑና ላለመሆኑ አንዳንድ ውዝግቦች (ክርክሮች) አሉ። ሌሎች የአመራር ሥልጣኖች ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የአገልግሎት ቢሮዎች ናቸው ይላሉ። ሆኖም ግን የክርስቶስን አካል ለመገንባት የተሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶች ሳይሆኑ አይቀርም የሚለው ያመዝናል። እነዚህ ቤተ ክርስቲያንን በተለየ አገልግሎት እንዲነቡ መንፈስ ቅዱስ በስጦታ ያበለጸጋቸው ሰዎች ናቸው። 

በዚህ ስፍራ የጳውሎስ ትኩረት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ መሪዎች መዘርዘር አይደለም። (ለምሳሌ ዲያቆናትን ወይም ሽማግሌዎችን ወይም አስተዳዳሪዎችን አልጠቀሰም) ነገር ግን የተወሰኑ የመሪነት ስጦታዎችን መረጠና እነዚህ የመሪነት ስጦታዎች በሚያስገኙት ውጤት ላይ አተኮረ። መሪዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያስፈልጉት ለምንድን ነው? ተቀዳሚ ኃላፊነታቸው ምንድን ነው? ጳውሎስ እንደሚናገረው እነዚህ የመሪነት ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ) እንዲታነፁ፥ እንዲጸኑና አንድ እንዲሆኑ ነው። አስታውሱ ለጳውሎስ የመንፈሳዊ ጽናት ወይም ብስለት ዋናዎቹ ማረጋገጫዎች በአካሉ ውስጥ ያለው አንድነትና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የሆኑትን ፍቅር፥ ሰላም፥ ደስታ፥ የዋህነት፥ ትዕግስት፥ ቸርነት፥ በጐነት፥ እራስን መግዛትና እምነትን መለማመድ ናቸው። 

ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን ሊገነቡ ስለሚችሉ ስጦታዎች ለመናገር አምስት የአመራር ስጦታዎችን በምሳሌነት አቀረበ። የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ ማለትም ሐዋርያት# ነቢያትና ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያንን እየመሠረቱ የሚንቀሳቀሱ ቀጻሚ አገልጋዮች ሊሆኑ የሚቀጥሉት ሁለቱ ማለትም እረኞችና አስተማሪዎች የተመሠረተችን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በእምነት የበሰለች እንድትሆን በቋሚነት የሚሠሩ የቤተ ክርስቲያን መደበኛ መሪዎች ናቸው። አንዲት ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ስፍራ እንድትቆረቆር፥ ወደ ጠንካራ ቤተ ክርስቲያንነት እንድታድግ፥ ደግሞም አንድነቷን አጽንታ ለእግዚአብሔር ሥራ የተዘጋጀች እንድትሆን አምስቱም የመሪነት ስጦታዎች ያስፈልጋሉ። 

1. ሐዋርያት

ሐዋርያ የሚለው ቃል ‹አፖላቶሎስ) ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ‹በሙሉ ሥልጣን እንድን አካል ወክሎ የተላከን ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን በሁላት የተለያዩ መንገዶች አገልግሎት ላይ ውሏል። በመጀመሪያ፥ ጠበብ ባለ መልኩ በአዲስ ኪዳን መጀመሪያ እካባቢ የነበሩ የተላዩ የአመራር አካላትን ብቻ የሚያመለክት ነው። እነዚህ ኢየሱስ የመረጣቸው ከእርሱ ጋር ላሦስት ዓመት የተጓዙና ሞቱን እና ትንሣኤውን የመሰከሩ እሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው። በእነዚህ አሥራ ሁለት ሰዎች ላይ ጳውሎስን መጨመር እንችላለን። ምክንያቱም እራሱን ሁልጊዜ እንደ ልዩ ሐዋርያ የሚቆጥርና የትንሣኤውን ጌታ ያየ በመሆኑ ነው። ከዚያን ጊዜ በኋላ ለነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረት የሆነችውን የቀድሞይቱን ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት ኢየሱስ እምነት የጣለባቸው እነዚህ ሐዋርያት ነበሩ (የሐዋ. 1፡21-22፤ ኤፌ. 2፡20፤ 1ኛ ቆሮ. 9፡1)። 

በሁለተኛ ደረጃ: ‹ሐዋርያየሚለው ቃል ሰፋ ባለ ትርጉሙም አገልግሎት ላይ ውሏል። ወንጌል ባልደረሰባቸው ስፍራዎች የወንጌልን መልእክት እያመጡ አዳዲስ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያቋቁሙ ሰዎችን ለመጥራት አገልግሎት ላይ የዋለ ይመስላል። ጳውሎስ በሮሜ የሚገኙ ቁልፍ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን «ሐዋርያት» ብሎ ጠርቷል (ሮሜ 16፡7)። ይህ ስጦታ ዛሬም ቢሆን ክርስቲያኖች ፈጽሞ ወደሌሉበት የዓለም አካባቢዎች እየሄዱ የምስክርነት አገልግሎት በመጀመር አብያተ ክርስቲያናትን ለመቆርቆር ልዩ ዕድልና ችሎታ ካላቸው ሰዎች አገልግሎት ጋር መወዳደር ይችላል። በ1900ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አገልግሎት የሰጡ የወንጌል መልእክተኞች ኋላ ደግሞ በኢትዮጵያ ዙሪያ በተላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ፈጽሞ ወንጌል ባልደረሰባቸው ቦታዎች ላይ በሺህ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን የቆረቆሩ ኢትዮጵያውያን ወንጌላውያንም ከእነዚሁ መካከል ናቸው። 

ጳውሎስ ሐዋርያትን በመሪዎች ዝርዝር ላይ የመጀመሪያ አድርጐ ሲያስቀምጥ እነዚህን ዓይነት መሪዎችን በአእምሮው ይዞ የነበረ ይመስላል። 

ጥያቄ፡ ሀ) ሰኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሊጠቀሱ የሚችሉ ወንጌልን ወደ አዳዲስ ስፍራዎች ይዘው በመሄድ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን የቆረቆሩ ሰዎችን ስም ዘርዝር። ለ) ከቀድሞ ሐዋርያት ጋር የሚመሳሰሉበት ሁኔታ እንዴት ነው? ሐህ ወንጌል ያልደረሰባቸው የኢትዮጵያና የዓለም ክፍሎችን ጥቀለ። ወንጌልን ያደርሱላቸው ዘንድ [ሐዋርያት የሚያስፈልጓቸው እንዴት ነው? 

2. ነቢያት

በአዲስ ኪዳን ሁለት ዓይነት ነቢያት የነበሩ ይመስላል። የመጀመሪያዎቹ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ አማካይነት መልእክቱን የሚያስተላልፍባቸው ናቸው። የነቢያት ተቀዳሚ አገልግሎት የእግዚአብሔርን ቃል ከእግዚአብሔር በሚያገኙት መገለጥ መሠረት የክርስቲያኖችን ሕይወት በሚገነባ መንገድ ማምጣት ሲሆን ስለ ወደፊቱ መናገርም የአገልግሎታቸው አንዱ አካል እንደሆነ አስታውስ። ይህ ስጦታ በቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን ከነበሩ እጅግ ጠቃሚ ስጦታዎች አንዱ እንደነበር የሚገልጸውን 1ኛ ቆሮ. 14 ስናጠና የበለጠ እንመለከተዋለን። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ነቢያት በመባል የሚጠሩ ልዩ መሪዎች ነበሩ። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የወደፊቱን ነገር ለማመልከት በአዲስ ኪዳን እንደተጠቀሱት እንደ አጋቦስ ያሉ ቁልፍ ሦሳሌዎች አሉን (የሐዋ. 1፡27 28)። ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አብዛኛዎቹ እንደዚህ ዓይነት ተግባር የነበራቸው ይመስላል። ከነቢያት ጥቂቶቹን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መልእክት በጽሑፍ አስቀርተው ለሰዎች ሁሉ እንዲዳረስ ለማድረግ ተጠቅሞባቸዋል። በዚህ ዓይነት ከምንመለክታቸው መካከል ጳውሎስ፥ ጴጥሮስን ዮሐንስና ሌሎችም ይገኛሉ። ክጽሑፎቻቸው አንዳንዶቹ በኋላ አዲስ ኪዳን ሆነዋል። እግዚአብሔር በእነዚህ ሰዎች በኩል ሥልጣን ያለውን ቃሉን ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ለመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ሰጠ። 

ልክ እንደ ሐዋርያት እነዚህ ሁላተኞቹ ዓይነት ነቢያት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት መሠረት ናቸው። የክርስቶስን ሕይወትና ሞት ምክንያት እንዲረዱና እነዚህን እውነቶች የተጻፈ አዲስ ኪዳን ላልነበራቸው ሰዎች ለመግለጽ እግዚአብሔር ሁለተኞቹን ዓይነት ነቢያት ተጠቅሞባቸዋል። በእነርሱ አገልግሎት ዛሬም እንኳ እዲስ ኪዳንን በምናነብበት ጊዜ እንባረካለን። 

ማስታወሻ፡- የእነዚህ የሁላተኛው ዓይነት ነቢያት አገልግሎት ከአዲስ ኪሳን መጻፍ በኋላ አክትሟል። ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር በመጀመሪያዎቹ ዓይነት አተረጓጐም «ነቢያት» ተብለው በሚጠሩ ሰዎች ሊናገር ቢችልም እንኳ መልእክታቸው ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር በእኩልነት የሚወዳደር አይደለም (ራእይ 22፡18-19)። ስለ ነቢይነት ስጦታ 1ኛ ቆሮ. 

14ን ስናጠና የበለጠ እንመለከታለን።) 

3. ወንጌላውያን 

በሦስተኛ ደረጃ የተጠቀሰው የመሪነት ስጦታ ወይም ተግባር ወንጌላዊነት ነው። ልክ እንደ ሐዋርያትና ነቢያት ወንጌላዊም በየአብያተ ክርስቲያናት እየተዘዋወረ የሚያገለግል ነበር። ከክርስቲያኖች ጋር የሚሠራበት ወቅት ያለ ቢሆንም ተቀዳሚ ትኩረቱ ግን ወንጌልን ላልዳኑ ሰዎች ማድረስ ይመስላል። ጥሩ ምሳሌያችን ወንጌልን በመጀመሪያ ለሰማርያ ሰዎች፥ ቀጥሎ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፥ ደግሞም ለአዘቦን ከተማ ያደረሰው ፊልጶስ ነው። በአንድ ቦታ ቆይቶ አይሠራም ነበር። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን የወንጌላዊነት ሥራውን እንዳይተው አስጠንቅቆት ነበር (2ኛ ጢሞ 4፡5)። 

4. እረኞች (መጋቢዎች) 

ጳውሎስ አብያተ ክርስቲያናትን በመቆርቆርና በመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ግንባታ ሥራ ላይ ተጠምደው ከነበሩት መሪዎች ለቤተ ክርስቲያን አባላት የማያቋርጥ ዘላቂ ክብካቤ ወደ ሚያደርጉት መሪያዎች ይመለሳል። ጳውሎስ በዚህ ቦታ የሚጠቅሰው እንድ ወይም ሁለት መሪዎች መሆናቸው እንዳንዶችን ያከራክራል። ጳውሎስ ይናገር የነበረው የምእመናኑን ፍላጐት ይከታተል ስለነበረው መጋቢና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ስለሚያስይዘው አስተማሪ ማለትም ስለ ሁለት ዓይነት መሪዎች ነበርን? ወይስ የሚናገረው መጋቢ አስተማሪ ስለሆነ ምእመናኑን በሚያስፈልጋቸው ነገሮች የሚንከባከባቸውና የሚያስተምራቸው አንድ መሪ ብቻ ነው? ሁለቱም አመለካከቶች ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። 

ምናልባት በሁለቱ ሚናዎች መካከል መጠነኛ ልዩነት ሊኖር ይችላል። ሁለቱ ላጦታዎችም የተለያዩ ናቸው። መጋቢ ምእመናኑን በሚገባ የሚያውቅ ሰው ነው። ተስፋ ሰሚቆርጡበት ጊዜ የሚያበረታታቸው እርሱ ነው። በችግሮቻቸውም ያማክራቸዋል። ከእውነት ርቀው ሲባዝኑ ይገለጻቸዋል። የምእመናንን ፍላጐት ሁሉ ለማገልገል ይጥራል። 

5. አስተማሪዎች 

አስተማሪ የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ የሚያውቅና ሰዎች እግዚአብሔር ከእነርሱ የሚጠብቅባቸውን ነገሮች እንዲያውቁ ብቻ ሳይሆን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሁኔታ መኖርን እስከሚችሉ በተግዳሮት የእግዚአብሔርን እውነቶች የሚያስተላልፍ ነው። 

አንዳንድ ጊዜ መጋቢ የመሆንና አስተማሪ የመሆን ስጦታዎች በአንድ ሰው ውስጥ የሚገለጹ ቢሆኑም እንኳ ብዙ ጊዜ የመሥራትና የቤተ ክርስቲያን አባላትን የማበረታታት ስጦታ ያላቸው ግን የእግዚአብሔርን ቃል በግልጽ ለማስተማር የማይችሉ ሰዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ ስጦታ ያላቸው አስተማሪዎች ሆነው ሰዎችን በማበረታታት ሥራ ለመጠመድ ፈጽሞ የሚቸገሩ አሉ። ሁለቱም ዓይነት መሪዎች ለቤተ ክርስቲያን ጤናማነት የግድ አስፈላጊ ናቸው። 

ጥያቄ፡ የቤተ ክርስቲያንህን ታሪክ ወደ ኋላ መለስ ብለህ አስብ። እነዚህን የመሪነት ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ያየኸው እንዴት ነው? 

ኤፌሶን 4፡12-16 

ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው አንድነት መጻፉን ታስታውሳለህ። በኤፌሶንና በኢትዮጵያ የሚገኙ ክርስቲያኖች እንድ እንዲሆኑ ፍላጐቱ ነበር። ግን ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ተግባራቸው ሁሉ እንድ ይሆናል ማለት ነው? እይደለም ይላል ጳውሎስ። ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ልዩ ስጦታ ሰጥቷል። በክርስቶስ አካል ባላ አንድነት መካከል ልዩነት አለ። ይህ አንድነት መታወቅ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለበት እንዴት ነው? የማን ኃላፊነት ነው? እንዴትስ ይፈጸማል? ጳውሎስ እንደሚያመላክተው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት እንዲኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ስጦታ ያላቸው መሪዎችን ሰጥቷል። አምስት ዓይነት መሪዎችን የጠቀሳ ሲሆን ሦስቱ አብያተ ክርስቲያናትን መቆርቆር ተቀዳሚ ኃላፊነታቸው ነው። ሁለቱ ደግሞ አብያተ ክርስቲያናትን ለመገንባት ኃላፊነት ተሰጥተናቸዋል። 

እነዚህ መሪዎች እግዚአብሔር ባቀደው መንገድ ሲያገለግሉ ምን ይፈጸማል? ሁላችን ‹የእግዚአብሔርን› ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት» እንደርሳለን (ኤፌ. 4፡3)። ሰዎች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚያድጉበት ፍጥነት የተላያየ ቢሆንም ጳውሎላ እዚህ ላይ የሚናገረው ስላተባበረው የክርስቶስ አካል ነው። መሪዎች ኃላፊነታቸውን በሚገባ ሊወጡ ሦስት ነገሮች ይፈጸማሉ። 

1. የእምነት አንድነት ይኖራል። ጳውሎስ ሰዎች ለማመንና ለመዳን ይችሉ ዘንድ ስለሚያሳዩት የውስጥ እምነት መናገሩ አልነበረም። ይልቁኑ ስለ «እምነት» ወይም ለላ «ወንጌል» መናገሩ ነበር። ጳውሎስ እንደተናገረው መሪዎች ኃላፊነታቸውን ሲያሟሉ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን በሙሉ ስለ ወንጌል ምንነት ለላ ክርስትና ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ሰው እንዴት እንደሚድን ወዘተ… ትክክለኛ የጋራ ንዛቤ ይኖራቸዋል። በወንጌል ማዕከል ላይ የጋራ ስምምነት ካለ እንድነት ይኖራል። በወንጌል ማዕከል የጋራ እምነት ከሌለ እውነተኛ አንድነት ሊኖር አይችልም። በዓለም አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመታቀፍ እንድነት ለመፍጠር የሚጥሩ ቤተ ክርስቲያኖች ችግር ይህ ነው። በወንጌል ማዕከል ላይ ሳይስማሙ አንድነትን ይፈልጋሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው የድነት (ደኅንነት) መንገድ በመሆኑ ላይ ሳይሰማው አንድነትን ይፈልጋሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው የድነት (ደኅንነት) መንገድ በመሆኑ ላይ ከተመሠረተ አንድነት በቀር እውነተኛ የክርስቲያኖች አንድነት ሊኖር አይችልም። 

2. ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ አንድነት አለ። ጳውሎስ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶችን ከመረዳት ከኢየሱስ ከርስቶስ ጋር ወደሚሆን የእውነተኛ ግንኙነት ልምምድ ይሸጋገራል። በኢየሱስ ማንነት ላይ የተደረሰ የአእምሮ እውቀት ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ንቃት የሞላበት በልብ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከሚኖር ከሕያው ክርስቶስ ጋር የሚሆን የጠበቀ ግንኙነት ነው። 

3 በመንፈሳዊ ሕይወት የበሰሉ ይሆናሉ። ጳውሎስ ያለ ኃጢአት ይሆናሉ ወይም ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትግሎች ወይም ችግሮች ወደሌለበት ደረጃ ይደርሳሉ ማለቱ አይደለም። ነገር ግን የተረጋጉ፥ ሰይጣንና ዓለም በክርስቲያንና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያመጡትን ውጊያዎች ለመቋቋም የሚችሉ ይሆናሉ ማለቱ ነው። 

ይህ ብስለት በምን ይረጋገጣል? በኤፌ 4፡14-16 ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት ይኖር ዘንድ መሠረት የሚሆኑትን የበሰሉ ክርስቲያኖች ባሕርያት በዝርዝር ያቀርባል። 

1 በእምነታቸው ጽኑ ናቸው። በሚመጡ አዳዲስ ትምህርቶች ተጽዕኖ ሥር አይወድቁም። እውነትን ያውቃሉ፥ እውነትን ይይዛሉ፥ . የሐሰት ትምህርትን ይቋቋማሉ። 

2 እውነትን በፍቅር ለመግለጽ ይችላሉ። ሁላቸውም ክርስቶስን ወደ መምሰል ለማደግ የሚፈልጉ ስለሆኑ የአካሉን አንድነት ለማወክና ወደ ብስለት የሚደረገውን ጉዞ ለማሰናከል የሚመጡ ማናቸውንም ችግሮች ለመጋፈጥ ፈቃደኞች ናቸው። ለሌሎች ሐማትን አይናገሩም። ችግሮችን አይደብቁም። ስሕተትን ፊት ለፊት ይናገራሉ። ሆኖም ግን እውነትን የሚናገሩት ጥፋትን ለማስተካከል በታላመ የተቃውሞ ስሜት አይደለም። 

ለእውነት ያላቸውን ፍላጐት ፍቅር እንዲሰፍን ካላቸው ፍላጐት ጋር ሚዛናዊ እንዲሆን ያደርጉታል። ከእነዚህ ሁለት ነገሮች ማለትም ከእውነትና ከፍቅር አንዱ በቤተ ክርስቲያን ሲጐድል አንድነት አይኖርም፥ ወደ ብለለት የሚያመራ አንድነትም አይኖርም። 

3. እድገት ይኖራል። የክርስቶስ አካል እንደመሆናችን በተናጥልም ሆነ በአንድነት በባሕርያችን ያለማቋረጥ እየመሰለን እንመጣለን። በዚህም ላእርስ በርሳችንም ሆነ ለዓለም ክርስቶስ እንደሚያደርገው እናደርጋለን። እንደምታስታውሰው ይህ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚኖርበት ህግ ነው። መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙሉ ለእኛ የሰጠበት 

ምክንያት ለዚህ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) የመንፈሳዊ ብስለት. አመልካች በሆኑት እነዚህ ጠንካ ነገሮች አኳያ ቤተ ክርስቲያንህ ምን ያህል የበሰለች ትመስላለች? በጣም የበሰላች፥ በክፊል የበሰለች ወይስ ብዙ ያላበሰላች? መላስህን አብራራ። ላ) ቤተ ክርስቲያንህ መንፈሳዊ ብስለት ያላት ትሆን ዘንድ ምን መሆን ያለበት ይመስልሃል? ሐ) የተላያዩ የአመራር መንፈሳዊ ስጦታዎች ለዚህ የብስለት እድገት እንዴት የሚረዱ ይመስልሃል? 

ይህ የብስለት ሂደት የሚፈጸመው ቀን እንዴት ነው? የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሥራውን ሁሉ ሊሠሩት ነውን? አይደለም። በኤፈ 42 ላይ የእነዚህ አምለት ይነት መሪዎች አገልግሎት የሚያተኩረው ሥራውን በመሥራት ላይ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሰዎች ሥራውን ይሠሩ ዘንድ ብቁ በማድረግ ላይ ነው። አንድነትና መንፈሳዊ ብስለት የሚመጣው መሪዎች የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለአገልግሎት ብቁ ሊያደርጉ ብቻ ነው። ይህ ማለት በቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ ለጦታዎችን ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ይጠቀሙበታል ማለት ነው። አንድነትና ብስለት የሚኖረው በዚያን ጊዜ ብቻ ነው። ዛሬ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ደካ የሆኑበት ምክንያት መሪዎች ሥራውን መሥራት ያለባቸው እነርሱ ብቻ እንደሆኑ በማመናቸው ነው። ይህ ዝንባሌ ጥቂቶች ብቻ እንዲሠሩ ሌሎች ቀን ተቀምጠው የሚመለከቱ ያደርጋቸዋል። ይህ ማለት አብዛኛዎቹ የአገልግሎት ለጦታዎች ተግባራዊ ባለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያን እዞችና እግሮች እንደሌሉት ሰው ሽባ ሆናለች ማለት ብቻ ሳይሆን ይህ ብዙ ጊዜ አንድነት ወደ ማጣት ያደርሳል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ አንድነት የሚገልጸው የተላያዩ ስጦታዎችና ችሎታዎች ያሉአቸው ለአንድ ላክ ማለትም ለእግዚአብሔር ክብርና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል ሲሠሩ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) መሪዎች ሁሉን ነገር ለመሥራትና ለመቆጣጠር loመሞከራቸው ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ያሉ ምእመናን በንቃት (እንዳይሳተፉ የተፈጠረውን የአመራር ችግር እንዴት ነው ያየኸው? ላ) ይህ ያመጣውን አንዳንድ አሉታዊ ውጤቶች ላጽ። ሐህ መሪዎች የምእመናንን ሁኔታ በማሻሻል እንዲነሣሡና ለጦታዎቻቸውን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲያውሉ ማድረግ የሚገባቸው ናቸው ትላለህ? 

በዛሬው ትምህርት በቤተ ክርስቲያን የመሪነት ስጦታዎች ላይ እናተኩራለን። ነገር ግን የእነዚህ ስጦታዎች ዓላማና እንዴት አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ ከመናገር ይልቅ ጳውሎስ ያተኮረው የመላው መንፈሳዊ ለጦታዎች የመጨረሻ ግብ ላይ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ አገልግሎት ላይ መዋል ያለባቸው አንድነት ለመመሥረትና መንፈሳዊ ብስለት ለማስገኘት ነው። የመሪነት ስጦታዎች ይህ እንዲሆን ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው። መሪዎች ስጦታዎችን በሙሉ ሰባለንብረትነት ከመያዝና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ለጦታዎችን ሁሉ ክመቆጣጠር ይልቅ ተቀዳሚ ዓላማቸው ሊሆን የሚገባው እያንዳንዱ አባል በቤተ ክርስቲያን ሥራ ውስጥ እንሳተፍና በስጦታውም ሌሎችን እንዲያገለግል መርዳት ነው። እያንዳንዱ አባል ሌሉችን ወደ መንፈሳዊ ብስለት ለማድረስ ባተኮረ ዓላማ ከተጠቀመቶ ውጪአዊ ችግሮች በሐሰት ትምህርት መልክ ወይም በስደት መልክ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲመጡም እንኳ አንድነቷና እድገቷ እያቋርጡም። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከዚህ ትምህርት ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የምናገኛቸውን መመሪያዎች ጥቀስ። ለ) ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ ሌሎችን እንዴት ማስተማር ትችላለህ? ሐ) መሪዎች ሌሉች ምእመናን መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን እንዲጠቀሙ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ለመርዳት ከመሪዎች ጋር እንዴት መሥራት ትችላለህ?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.