መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-11 )

ጥያቄ፡- «መንፈስ ቅዱስ እንዳላህና በሕይወትህ በሙላት መኖሩን ለማወቅ በእርግጥ ከፈለግህ በልሳን መናገር አለብህ። ላል አባባል በትናንትናው ትምህርት በመመሥረት እንዴት ምላሽ ትሰጣለህ። 

በ1ኛ ቆሮ. 12፡1-3 ላይ በተሰጣው በትናንትናው ትምህርት ላይ ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማረጋገጫ በልሳናት መናገር ክሚሆን ይልቅ ህልውናው ይበልጥ የሚገለጸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚቀዳጀው ክብር መጠን መሆኑን ጳውሎስ አመልክቷል። ጳውሉላ አሁን ደግሞ በልሳናት መናገር ከስጦታዎች አንዱ ብቻ እንደሆነ መናገሩን ይቀጥላል። መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን በርካታ የተለያዩ ድንቀኛና ድንቀኛ ያልሆኑ ስጦታዎችን ይሰጣል። ሁሉም ያስፈልጋሉ፤ ደግሞም ሁሉም ለክርስቶስ አካል ጥቅም የሚውሉ ናቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) «የተለያዩ» የተባሉትን ነገርች ዘርዝር። ለ) «ተመሳሳይ ናቸው» የተባሉትን ነገሮችም ዘርዝር። ሐህ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተሰጠው ለማን ነው? መ) የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የተሰጠው ለምን ነበር? ሠ) ባለፈው ሳምንት በጀመርካቸው ሁላት ሠንጠረዦችህ ላይ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ዘርዝር። በጹሑፍ ለእያንዳንዱ ስጦታ አጭር መግለጫ ለጥ። ረ) መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሰጠው የሥላሴ አካል የትኛው ነው? ሰ) ማን [የትኛውን ስጦታ እንደሚያገኝ የሚወሰን ማን ነው? 

ቀጥሎ በዚህ ክፍል ውስጥ የተጠቀሱትን ዋና ዋና እውነተች እንገልጻለን። 

1 በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት ምንጩ አሐዱ ሥሉስ የሆነው አምላካዊ ባሕርይ ነው። 

ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት መኖር አለበት ስንል ሁሉም አንድ እይነት መሆን አለበት የሚል የተሳሳተ አሳብ ይይዛሉ። የሚያምኑት ነገር ሙሉ በሙሉ እንድ መሆን አለበት። እንድ ዓይነት ተግባር እንዲኖራቸው ይጠብቃሉ። የቤተ ክርስቲያን ተግባራቸውን አንድ ዓይነት መሆን አለበት ይላሉ። ለምሳሌ አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሁሉም ክርስቲያኖች በልሳን መናገር አለባቸው! ሰው መንፈሳዊ የመሆኑ ምልክት በልሳን መናገሩ ነው የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው። 

በ1ኛ ቆሮ. 12፡4-11 ክፍል ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊነትና መንፈሳዊ ብስለት በአንድነት ውስጥ ያለ የልዩነቶች ውጤት መሆኑን ይናገራል። በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት ቃሎች ያለሟቋረጥ ተደጋግመዋል። እዚህም «ልዩ ልዩ» ና «አንድ» የሚሉ ቃሎች ናቸው። ይህ በግልጽ መሰጠቱን ለመረዳት የሚከተለውን ተመልከት። 

ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው። 

አገልግሎት ልዩ ልዩ ነው ጌታ ግን አንድ ነው። 

አሠራር ልዩ ልዩ ነው እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። 

ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጠውን አጠቃላይ ገለጻ የሚጀምረው በልዩነት ውስጥ ላላ አንድነት ከሁሉ የላቀ ምሳሌ የሆነውን – እግዚአብሔርን በማመልከት ነው። በአንድ በኩል አንድ እግዚአብሔር፡ አንድ ጌታ፥ አንድ መንፈስ አላ። ነገር ግን በዚህ የእግዚአብሔር አንድነት ልዩነት አለ። እዚአብሔር በሦስት ውስጥ ያለ አንድ የሆነ እሑድ ሥሉስ አምላክ ነው። ከዚህ ከአንዱ እግዚአብሔር የተላያዩ ስጦታዎችና አገልግሎቶች ይወጣሉ። እነዚህ ለጦታዎች አገልግሎቶችና አሠራሮች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚናገሩ ሲሆኑ ኋላ ደሞ የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ተብለዋል። አንዱ እግዚአብሔር የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ምንጭ የመሆኑ እውነት እግዚአብሔር የሚሰጠው መንፈሳዊ ስጦታ አንድ ዓይነት ብቻ ነው ማለት አይደለም። በልሳናት የመናገር ስጦታ እግዚአብሔር ሊሰጥ ከሚችላቸው ስጦታዎች አንዱ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ልዩነቶችን የሚወድ ሊሆን የተለያዩ ስጦታዎችን በመስጠት አንድነትን ያበረታታል። በአንድነት መካከል ያላ ይህ ልዩነት እግዚእብሔር ለቤተ ክርስቲያን ያለው ዓላማ ነው። እንዲያውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ብስለት ከሁሉ በላቀ ሁኔታ የሚረጋገጥበት መንገድ የተላያዩ ስጦታዎች ያላቸው የተለያዩ ሰዎች አንዱን እግዚአብሔርን ለማገልገል በአንድነት መሥራታቸው ነው። 

ልዩነቶች ለአንድነት ወይም ለመከፋፈል መሣሪያ ላሆኑ ይችላሉ። ሰይጣን ልዩነቶች ወዳሉባቸው ስፍራዎች በመምጣት ሰዎች ወይም አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፋፈሉ መንገድ መጥረግ ይወዳል። የተለያዩ ዝርያዎች ነገዶች፥ ጾታዎችና ስጦታዎች መኖራቸው ሰይጣን ዓለምንና ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሚጠቀምባቸው ናቸው። የእግዚአብሔር ዕቅድ ቀን ልዩነቶቻችንን በመጠቀም እርስ በርስ መደጋገፍና አንድነትን እንድናጐለብት ነው። ለሰዎች ሌሎች ነገዶች፥ ሌሎች ባሕሎች ሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች ወዘተ…) እንደሚያስፈልጋቸው በማሳየት ሰዎች ፡ በኅብረት ለአንድነት እንዲሠሩ ያደርጋል። በልዩነቶች መካከል ያለው አንድነት እዚአብሔር ላፍጥረትና ለሕዝቡ ያለው ዕቅድ ነው። 

ጥያቄ፡- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩነቶች አንድነትን ሊያግ እንዴት እንዳየህ ምሳሌዎችን ዘርዝር። 

2. የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የተሰጡ ናቸው። 

መንፈሳዊ ስጦታዎች ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚሰጡ አይደሉም። ይልቁኑ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢያንስ አንድ ስጦታ ይሰጠዋል። በልሳናት ይናገሩ የነበሩ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገራቸው የተለዩ የተሻሉና መንፈሳዊ ያደረጋቸው ይመስላቸው ነበር። የራሳቸው ቡድን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበራቸው። በልሳናት የመናገር ስጦታዎች የሌላቸውን ሌሎች ክርስቲያኖችን የበታች አድርገው ይመለክቱ ነበር። ጳውሎላ አበክሮ የተናገረው እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሁሉም እንጂ ላጥቂት ምርጦች ያለ መስጠቱን ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ክርስቲያን ከሌሎች የተለዩ ስጦታዎች ስላሉት ከሌሎች የተሻለ የተመረጠና ልዩ እንደሆነ አድርጐ ራሱን ለሚያቀርብበት መንፈሳዊ ትዕቢት ምንጭ ስፍራ የለም። 

3. የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው። 

አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ያላቸው አስተሳሰብ የተሳሳተ ነበር። መንፈሳዊ ስጦታዎች ለግል ጥቅም ለእያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትና ክብር የተሰጡ አድርገው ይገምቱ ነበር። ለእነርሱ በልሳናት መናገር የአንድ ሰው መንፈሳዊነት የሚታወቅበት በደረት ላይ የሚለጠፍ ምልክት ዓይነት ምልክት ነበር። በተለይ ይህ ችሎታ ያላቸው መንፈሳዊ፥ የሌላቸው ደግሞ መንፈሳዊ ያልሆኑ አድርገው ያስቡ ነበር። 

ግን መንፈሳዊ ስጦታዎች በአጠቃላይ በልሳናት መናገርን ዉር የክርስቲያኑን ማኅበረሰብ በአጠቃላይ ለመጥቀም በመንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ነበሩ። መንፈሳዊ ስጦታዎች አንድን ክርስቲያን ታዋቂ ለማድረግ ወይም የበለጠ መንፈሳዊ ለማድረግ የሚሰጡ አይደሉም። ይልቁኑ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ለመገንባት የሚሰጡ ናቸው። ይህ ማለት ቀን አንዳንድ መንፈሳዊ ላጦታዎች ላግላሰብ ክርስቲያኖች እድገት አይጠቅሙም ማለት አይደለም። ይህ ጥቅስ በራሱ በልሳናት መናገርን ለግል የአምልኮ ጊዜ መጠቀምን አይከለክልም። ሆኖም ግን የለጦታዎች ሁሉ የመጨረሻ ግብ የክርስቶስ አካል የሆኑ ምእመናንን በሙሉ ለመገንባት ነው። 

4.  መንፈሳዊ ስጦታዎች «የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች» ተብለው ይጠራሉ። 

መንፈሳዊ ስጦታዎች የክርስቲያኖች ዋናና ተቀዳሚ ትኩረት አይደሉም። ይል መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙሉ በሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ላይ ልናተኩር ይገባል። ሆኖም ቀን መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው እንዴት ነው? እዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ለመሥራቱ ማረጋገጫው ምንድን ነው? ከማረጋገጥምቹ አንዱ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። ጳውሎስ የሚዘረዝራቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች እያንዳንዳቸው መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች መካክል የሚሠራባቸው መንገዶች ናቸው። ጳውሎላ እያንዳንዱ ሰው ከእዚአብሔር ስጦታን ማግኘቱን እንዲያውቅ የሚፈልግ ቢሆንም በጣም ተፈላጊው ቀን ክርስቲያኖች በሚሠሩት የተለያዩ ስጦታዎች አማካኝነት የእዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ህልውና እንዲገነዘቡ ነው። በቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስን ህልውና አንድ ስጦታ ከሌላው አብዝቶ ሊገልጠው አይችልም። 

5. ስጦታዎችን በሙሉ አካቶ የያዘ ክርስቲያን የለም። 

መንፈስ ቅዱስ በራሱ ሙሉ ሥልጣን ላሚፈልጋቸው ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ያድላል። አንዱን ስጦታ ለአንድ ሰው ሌላውን ስጦታ ደግሞ ለሌላው ሰው ይሰጣል። የጳውሎስ አትኩሮት መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ስጦታዎችን ለተላያዩ ሰዎች እንደሚሰጥ ነው። ለሁሉ ሰው አንድ ዓይነት ስጦታ አይሰጥም። ጳውሎስ በግልጥ ባይናገረውም እንኳ እግዚአብሔር ላአንድ ላሰብ ስጦታዎችን በሙሉ እንደማይሰጥ ያመለክታል። አንድ ሰው ሁሉም መንፈሳዊ ስጦታዎች ካሉት የቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማንም ሰው አያስፈልግም ማለት ነው። ነገር ቀን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ስጦታ – በመመጠን አንዳችን ለሌላችን እንድናስፈልግ ያደርገናል። 

6. መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በብስለት ታድግ ዘንድ የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰጣል። 

መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዴት እንደሚሰጥ ለማስረዳት አውሉላ የተለያዩ ስጦታዎችን ይዘረዝራል። ስለ እነዚህ ስጦታዎች የሚከተሉትን ነገሮች ልብ ማለት አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሙሉ ለመዘርዘር እየሞከረ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ በርካታ የተለያዩ ስጦታዎችን እንደሚሰጥ ለማሳየት ናሙና ብቻ ሊሆን የሚችል ዝርዝር መስጠቱ ነው። ክርስቲያኖች በልሳናት እንደ መናገር ባለ አንድ ስጦታ ላይ በማተኮር መንፈስ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ሌሎች ለጦታዎችን መዘንጋት የለባቸውም። በአዲስ ኪዳን የምናገኛቸው 20 ወይም 21 የተለያዩ ስጦታዎች የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ዝርዝር በሙሉ ያካተቱ ለመሆናቸው ምንም ማስረጃ የለንም። ይልቅ መንፈስ ቅዱስ ለሚሰጣቸው ስጦታዎች ምሳሌ አድርጐ መረዳቱ የተሻለ ነው። 

በሁለተኛ ደረጃ፣ በ1ኛ ቆሮ. 12፡28 ከተሰጠው በተጻራሪ ስየና ር. 12፡4-1 የተዘረዘሩት መንፈሳዊ ስጦታዎች ቅደም ተከተላ በአስፈላጊነታቸው አኳያ ለመሆኑ ምንም አመልካች ነገር አናገኝም። ጳውሎስ ጥበብን የመናገር ስጦታ ከሁሉ የላቀ በልሳናት የመናገር ስጦታ ደግሞ ከሁሉ ያነሰ ነው አይልም። ነገር ግን ጳውሎስ በልሳናት የመናገርንና የተነገረውን የመተርጐም ስጦታ በ1ኛ ቆሮ. 12 በሰጠው የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዝርዝር ላይ በመጨረሻ ማቅረቡ የሚያመላክተው እነዚህ ስጦታዎች በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሚገባ በላይ አትኩረት ተሰጥቷቸው እንደነበር ለመግለጽ ነው። 

በሦስተኛ ደረጃ፣ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በቅርበት በምናጠናበት ወቅት እንዳንዶቹ ስጦታዎች ልዕለ-ተፈጥሮአዊ እንደሆኑ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ ይታወቃል። ለምሳሌ፡= የፈውስ ስጦታና ተአምራታዊ ኃይሎችን መለማመድ የመንፈስ ቅዱስ ግልጽ ማስረጃዎች ተደርገው ይታዩ ይሆናል። ሀኖም ን ሌሎች ስጦታዎች ደግሞ ብዙ የማይታዩና አድናቆት የማይለቡ በመሆናቸው እንደ «ተፈጥሮአዊ ችሎታ» አድርገው ሰዎች ሊያስሏቸው ይችላሉ። የጥበብና የእውቀት ቃል ስጦታዎችል እንደዚህ ዓይነቶቹ ምሳሌዎች ናቸው። ለልውሉላ አንድ መንፈሳዊ ስጦታ ከሌላው የሚበልጥ የሚያንስም አልነበረም። መንፈስ ቅዱስ ድንቀኛ የሚሆኑ ስጦታዎችንም ሆነ ያልሆኑትን የሰጠ ሲሆን ስጦታዎች ሁሉ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አብሮአቸው የመሆኑ ማስረጃዎች ነበሩ። 

በአራተኛ ደረጃ፣ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተለያዩ መንገዶች መመደብ የታወቀና የተለመደ መንገድ ቢሆንም ጳውሎስ ግን ይህን ፍጹም አላደረገም። አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ስጦታዎች በምስት ክፍሎች መመደብ ይወዳሉ። ) የትእዛዝ ወይም የአመራር ላጦታዎች (ጥበብና እውቀትን፥ 2) የኃይል ስጦታዎች (እምነት፥ ፈውስና ተአምራትን ማድረህ፥ እና ) በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ የመናገር ስጦታዎች (ትንቢት፡ ትንቢቶችን መለየት፥ በልሳናት መናገርና፥ በልሳን የተነገሩትን መተርጐም)። ይህ ዓይነት ፍረ ስለ ስጦታዎች ለመረዳትና ለማስተማር ጠቃሚ መንገድ ቢሆንም ጳውሎስ ስጦታዎችን በዚህ መንገድ ለመመደቡ ምንም ማስረጃ የለም። 

ሀ. የጥበብና የእውቀት ቃል 

ክርስቲያን በምድር ላይ በሚኖርበት ጊዜ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ የሳቁት ሁለት ነገሮች ጥበብና እውቀት ናቸው። ኢየሱስ «እውነትም አርነት ያወጣችኋል» (ዮሐ 8፡31-32) እንዳለው እውነትን ማወቅ አለባቸው። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ እግዚአብሔርና የእውነት ሁሉ ምንጭ ስለሆነው ስለ ቃሉ የተወሰነ እውቀት እንዲኖረው የግድ አስፈላጊ ነው። አንድ ክርስቲያን ባገኘው እውቀት ልክ ሕይወቱ የተረጋጋ ይሆናል። 

በተጨማሪ ደግሞ ክርስቲያን በሥራ ቦታ፥ በቤት ወይም በማንኛውም ስፍራ የሚያውቀውን እውቀት በተግባር ላይ የሚያውልበት ዘዴ ወይም ጥበብ ያስፈልገዋል። ጥበብ ከጐደለን እግዚአብሔርን እንድንጠይቀውና እርሱም ሊሰጠን እንደሚችል ተጽፏል። (ያዕ. 1፡5)። ስለዚህ እውቀትና ጥበብ የክርስቲያን ሕይወት መሠረቶች ናቸው። ሆኖም ግን የጥበብና የእውቀት መንፈሳዊ ስጦታዎች ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ከሚያስፈልገው እውቀትና ጥበብ የተለያዩ ናቸው። እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን የሚያሳዩ ልዩ ችሎታዎች ናቸው። 

ጳውሎስ እነዚህን ሁለት ስጦታዎች በመጀመሪያ የገለጸበት ምክንያት ለቆርንቶስ ሰዎች ጥበብና እውቀትን ከፍተኛ ዋጋ ከሚሰጧቸው ነገሮች መካከል ስለሆኑ ይሆናል። የቆርንቶስ ሰዎች በትምህርት በሚገኘው ዓለማዊ እውቀት በጣም የተወሰዱ ነበሩ። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 1፡17-2፡16 ድረስ ባለው ክፍል በላማዊ እውቀትና መለኮታዊ እውቀት መካከል ያለውን ከፍተኛ ልዩነት አሳይቷል። የመንፈሳዊ ጥበብ መልእክት የሚጀምረው ለላ ተሰቀለው ኢየሱስ ከተሰጠው እውነት ላይ ነው። 

ጳውሎስ እነዚህን ሁለት መንፈሳዊ ስጦታዎች ሲጠቅስ ምን ለማለት እንደሆነና በመካከላቸው ያለው ልዩነት ምን እንደሆነም ግልጽ አይደለም። በብሉይ ኪዳን ጥበብ ማለት ዘላለማዊ ብድራትን እየተመለከቱ የመኖር ችሎታ ነበር። ተግባራዊ ነበር። እውቀት ን ይበልጥ የሚያተኩረው በአእምሮ መረዳት ላይ ነው። ሆኖም ቀን ጳውሎል እዚህን ቃላት የለያቸው በዚህ መልክ ለመሆኑ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ምንም ማስረጃ የለም። የቆሮንቶስ ሰዎች ልዩነቱን የተረዱት ቢሆንም ለእኛ ቀን ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። 

እነዚህ ሁለት ስጦታዎች መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላለ ሰው መልእክት የሚሰጥበትና የተቀበለው ሰው መልእክቱን ላጉባኤው የሚያስተላልፍበት አገልሎት ሳይሆኑ አይቀርም። አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህ ስጦታ የሚያተኩረው ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነና ክርስቲያኖች ኢየሱስን በሚያክብር መንገድ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ነው ብለው ያለተምራሉ። እነዚህን ስጦታዎች የሚረዱት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ እውነቶችን በጥልቀት የመረዳትና የተረዱትን እውነት የሰዎችን ሕይወት በሚለውጥ መንገድ ላሌሎች የመግለጽ ችሉታ እንደሆነ አድርገው ነው። ሌሎች ደግሞ ስለ አንድ ሰው ቀልጽ መልእክትን ከእግዚአብሔር መቀበልና ላዚያ ሰው የመንገር ችሎታ አድርገው ይመለከቱታል። ይህ ከነቢያት ስጦታ ጋር እጅግ ተቀራራቢ ያደርገዋል። 

ጥያቄ፡- ቃሉ ዛሬ በኢትዮጵያ እንዴት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት የሆነ አብርሆት ያላቸው የሚመስሉህን በቤተ ክርስቲያንህም ሆነ በኢትዮጵያ (አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ስም ጥቀስ። ለ) የጥበብንና የእውቀትን ቃል የማወጅ መንፈሳዊ ስጦታ ያላቸው ይመስልሃልን? ለምን? 

ጳውሎስ ጥበብን እንደ መንፈሳዊ ስጦታ የጠቀሰበት ብቸኛ ወቅት ይህ ነው። እውቀትን ግን አገልግሎታቸው ከሚያበቃ ስጦታዎች (ትንቢትና፣ በልሳናት መናገር ከመሳሰሉት) ጋር በሌሎች በርካታ ቦታዎችም ጠቅሶታል (1ኛ ቆሮ. ፡2 8-12፤ 14፡16)። 

ለ. የእምነት ስጦታ 

እንደ ጥበብና እውቀት እምነትም የመንፈሳዊ ሕይወት መሠረታዊ ነገር ነው። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንደማይቻል ተጽፎአል (ዕብ. 11፡6)። እምነት የሚያድነውን ጸጋ ስር የሚከፍትልን ነው ኤፌ 28)። በጳ ውሉላ አእምሮ ያለው እምነት ቀን ይህ ዓይነቱ እይደለም። የእምነት ስጦታ ከማመን የተለየ ነው። ክርስቲያኖች ሁሉ እምነት ሊኖራቸው የሚገባ ቢሆንም ክርስቲያኖች ሁሉ ቀን የእምነት ስጦታ አይኖራቸውም። 

የእምነት ስጦታ፥ «ተራራዎችን የሚያንቀሳቅስ፡ ነው (1ኛ ቆሮ. 1፡2)። በሌላ አባባል ልዕለ=ተለምዶአዊ የሆኑ ነገሮችን የሚያደርግ እምነት ነው። እንደገና ጳውሎስ ይህ ስጦታ ምን ማለት እንደሆነ አይገልጽም። ሆኖም ቀን እምነት እግዚአብሔር በአንድ የተለየ ሁኔታ ውስጥ ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚሠራ በመንፈስ ቅዱስ ጽኑ መተማመንን የማግኘት ልዩ ችሎታ ነው። ይህ እምነት ለፈውስና ተአምራትን ለማድረግ ስጦታዎች መሠረት ላመሀኑ የማያሻማ ነገር ነው። የእምነት ስጦታ አንድን ሰው አንድ ነገር ሊሆን እንደሚችል ወይም አዝማሚያ እንዳላው ምንም ዓይነት ሰብዓዊ መረጃ ሳያገኝ ወይም ዒሳው የሚያደርግበት ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ የተስፋ ቃል ሳይኖር እዚአብሔርን እንተማመን የሚያስችል ነው፡ አብርሃም ይስሐቅን ለመሠዋት በሚዘጋጅበት ጊዜ ይስሐቅን እዚአብሔር ሊያስነሣው እንደሚችል ያመነበት እምነቱ ለዚህ ዓይነቱ እምነት አንዱምሳሌ ነው (ዕብ 1፡11-2)። ሌላ ዛሬ ቁልፍ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው ሰው አንዳችም ገንዘብ ሳይኖረው በእንግሊዝ ምድር የሕናት ማሳደጊያ እንዲከፍት እግዚአብሔር እንደፈለገው ያመነው ጆርጅ ሙለር የተባለው እንግሊዛዊ ነው። በየዕለቱ በቤት ውስጥ ምግብ ሳልነበረበት ጊዘ እንካ እዚአብሔር ለእነዚያ ሁሉ ልጆች የሚሆን ምግብ በተአምራት እንደሚሰጥ አምኖ በእግዚአብሔር ተደግፎ ነበር። እግዚአብሔር እምነቱን ያከበረበት እንድም ቀን አልነበረም። 

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ፈጽሞ ሊሆን በማይችል ነገርና ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔርን የመታመን ችሎታ እንዳሳየ የሰማኸው ወይም ያየችው ሁኔታ ካለ ግለጽ። 

ሐ. የፈውስ ስጦታዎች 

አዲስ ኪዳን ፈውስን ለተቀዳጁ ሰዎች ታሪክ የተሞላ ነው። ኢየሱስን፥ ጴጥሮስን ጳውሎስንም እንኳ በመጠቀም እግዚአብሔር ሰዎችን ከበሽታዎቻቸው ፈውሷል። ከበሽታ መፈወስ በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጠበቅ የተለመደ ነገር ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጠው መንፈሳዊ ስጦታዎች አንዱ የፈውስ ስጦታ እንደሆነ መገመት እንችላለን። 

በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር የሥጋ ፈውስን ለልጆቹ በሁለት መንገድ ይሰጥ ነበር። ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጸሎት አማካኝነት ይህን ያደርግ ነበር። የታመመው ሰው የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች በመጥራት እንዲጸልዩለት ማድረግ ነበር። ሽማግሌዎች ይህ በሽታ የመጣው በኃጢአት ምክንያት እንዳልሆነ ሕይወቱን በመመርመር ካረጋገጡ በኋላ ለበሽተኛው በመጸለይ በስፍራው የሚገኘውን ማንኛውንም መድኃኒት ይሰጡት ነበር። (ማስታወሻ በዚያን ዘመን በጣም የሚዘወተረው መድኃኒት ዘይት በመሆኑ እዚህ ላይ የተጠቀሰው መድኃኒትን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።) እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ጸሎት እንደሚሰማና ፈውስን እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል (ያዕ. 5፡14-18 ተመልከት)። በሌላ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ያሉ ሰዎችን በመጠቀም ፈውስን ያውጅ ነበር። «የፈውስ ስጦታ» ማለት ይህ ሲሆን ስታመመ ሰው ላይ ፈውስን ለማምጣት መድኃኒትን ወይም የሠለጠነ የሕክምና ባለሙያን ሳይጠቀሙ ሥጋዊ ፈውስን ለማወጅ የእግዚአብሔር መሣሪያ የመሆን ችሎታ ነው። 

ጳውሎስ ይህን ስጦታ ለመግለጽ የተጠቀመው የነጠላን የፈውስ ስጦታ ሳይሆን የብዙ ቁጥርን ማለትም የፈውስ ስጦታዎችን መሆኑን ማስተዋል ደግሞ አስገራሚ ነው። (ማስታወሻ- ሰብዙ የእንግሊዝኛም ሆነ የአማርኛ ትርጉሞች የሚነበበው የመፈወስ ስጦታ የሚል የነጠላ ቁጥር ሲሆን በግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ን በብዙ ቁጥር ማለትም የፈውሶች ስጦታዎች የሚል ነው።) ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ይህን ስጦታ ለአንድ ሰው በመስጠት ፈውሶችን ሁሉ እርሱ እንዲያከናውን የሚያደርግ ሳይሆን ዛሬ ብዙ የፈውስ ስጦታ ባለቤት ተብዬዎች እንደሚለማመዱት) ችሉታው በተለያዩ ሰዎች መያዙን ነው። ጳውሎላ እየተናገረ ያለው ይህ ስጦታ በቋሚነት ለአንድ ሰው የሚሰጥ ሳይሆን ለተለያዩ ሰዎች በየጊዜውና በየሁኔታው የተለያዩ በሽታዎችን እንዲፈውሱበት የሚሰጥ መሆኑን ነው። እግዚአብሔር አንድን ሰው ከበሽታው ለመፈወስ ሲወስን ያንን ሰው እንዲፈውስ ለአንድ ሌላ ሰው ይህን ችሎታ ወይም ስጦታ በዚያ ልዩ ሁኔታ ውስጥ ይሰጣል። ይህ ችሉታ ከዚያ በኋላ ሊወሰድም ይችላል። አንድን ሰው ከአንድ በሽታ የሚፈውስ ስጦታ የተሰጠው ሰው ሁልጊዜ ሌሎች ሰዎችን ላመፈወስ መሣሪያ ይሆናል ማለት አይደለም። በዚህ መንገድ አገልግሎትን በመጀመር እየዞረ ያገኘውን ሁሉ መፈወስ አለበት ማለትም አይደለም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ዋና አገልግሎቱ መፈወስ ሆኖ በየቤተ ክርስቲያኑ እየዞረ መለኮታዊ ፈዋሽ የሆነ ሰው ለመኖሩ ፍንጭ አናይም። በአዲስ ኪዳን የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ የተፈወሱበት የፈውስ አገልግሎት የሚባል ፕሮግራምም እንደተካሄደ የሚጠቁም አንዳችም ምልክት የለም። ፈውሶች የተካሄዱት ሁልጊዜ በግላሰብ ሕይወት በተናጠል ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከላይ የተመለከትነው ነገር ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ይህን 1 መንፈሳዊ ስጦታ ከሚረዱበትና ከሚለማመዱበት ሁኔታ የሚለየው እንዴት ነው? ለ) ይህ መንፈሳዊ ስጦታ በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ወይም በትምህርት ሲሰጥ የሚያስከትላቸው አደጋዎች ምንድን ናቸው? 

መ. ተአምራትን ማድረግ 

ፈውሶችን የማድረግ ስጦታ ተአምራትን በማድረጎ ውስጥ የሚካተቱ ቢሆኑም እንኳ ተአምራቶችን የማድረግ ስጦታ ሰፊና ሰው ሊገልጸውና ሊረዳው የማይችለውንና የእግዚአብሔር ኃይል የሚገለጥባቸውን ልዕላ ተፈጥሮአዊ ድርጊቶች በሙሉ የሚያካትት ለጦታ ነው። አጋንንትን ማስወጣት አንዱ ምሳሌ ሊሆን ይችላል። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍና መልእክቶች በጥንት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለተደረጉ ተአምራት የሚነግሩን ብዙ ነገርች ባይኖሩም የተላመዱ ነገሮች የነበሩ ይመስላል (ገላ 3፡5 ተመልከት)። ይህ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያተኩረው ወንጌል እንዴት እንደተስፋፋ በመናገር ላይ እንጂ ተአምራት እንዴት እንደተፈጸሙ በመናገር ላይ ስላልሆነ ነው። ትኩረቱ ተአምራትን ማድረሳ ላይ የሆነበት ጊዜ ፈጽሞ የለም። ተአምራት የሚደረገው የሰባኪውን መልእክት ሥልጣን ለማሳየት እንጂ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለማስደነቅ አልነበረም። የቀድሞ ክርስቲያኖች ያስቡት የነበረው ነገር እግዚአብሔር ባለበት በተአምራት ኃይሉን እንደሚያሳይ ነው። 

እንደ ፈውስ ለጦታ ተአምራት የማድረኻ ስጦታም የተጠቀሰው በብዙ ቁጥር ነው። (ማስታወሻ፡ በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስና በብዙ የእንግሊዝና መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች «ለጦታ»ና «ተአምራት» የሚለው ቃል የተጠቀሰው ስነጠላ ቁጥር ሲሆን በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ቀን «ተአምራት። ና «ሥራዎች» ተብሎ በብዙ ቁጥር ነው የተጠቀሰው።) እንደገና ይህ የሚያመለክተው ይህ ስጦታ በየቦታው እየዞረ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ ለአንድ ሰው በቋሚነት የሚሰጥ ያለመሆኑን ነው። ይልቁኑ እግዚአብሔር ተአምራትን ማድረየ ሲፈል ላሰውዬው ተአምራትን የማድረግ ስጦታ ወይም ችሎታን ይሰጣል። መንፈስ ቅዱስ ለአንድ ሰው በፈለገው ጊዜ ተአምራቱን የማድረጎ የረጅም ጊዜ ችሎታ ሊሰጥ እንደሚችል የሚያመለክት አንዳችም ነገር የለም። 

ሠ. የትንቢት ስጦታ 

ጳውሎስ ተአምራዊ ድርጊቶች ከሆኑት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በቃል ወደሚገለጹበት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ይሸጋገራል። ለአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላቀ ሁኔታ ከሚያስፈልጉት ለጦታዎች እንዱ የትንቢት ስጦታ ነበር። ነቢይ ከቤተ ክርስቲያን መሠረቶች አንዱ ነበር (ኤፌ. 2፡19 20)። በ1ኛ ቆሮ. 14፡4-5 የክርስቶስን አካል የሚገነባ በመሆኑ በአምልኮ ፕሮግራሞች ላይ በልሳናት ከመናገር ይልቅ የትንቢት ስጦታ የላቀ ጥቅም እንደነበረው እንመለከታለን። 

በብሉይ ኪዳን ነቢይ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ መልእክትን በመቀበል ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሚናገር ነበር። 

ይህ መላእክት ከእግዚአብሔር በሚገኝ መገለጥ የፍርድን ወይም የድነት (ደኅንነት)ን መልእክት የሚያውጅ ነው። ይህ መልእክት በነቢዩ አካል ውስጥ በሚሆን ያልተለመዱ ለውጦች (ሕሊናን በመሳት ወይም በመንቀጥቀጥ መናገር) ምክንያት የሚመጣ ስለመሆኑ የሚያመለክት አንዳችም ነገር የለም። ከነቢያት መልእክቶች አንዳንዶች የወደፊቱን የሚያመላክቱ ቢሆኑም እንኳ አብዛኛዎቹ የነቢያት መልእክቶች በአጻማቹ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። 

በቀድሞይታ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትንቢት ስጦታ የተካተቱት ነገሮች ምን እንደነበሩ በእርግጠኝነት ማወቅ አስቸጋሪ ነው። ስለ ስጦታው አዲስ ኪዳን ምን እንደሚል በምንመረምርበት ጊዜ ቀን የሚከተሉትን ነገሮች መመልከት እንችላለን። 

ክርስቲያኖች በሙሉ መንፈስ ቅዱስ ስላላቸው ሁሉም የመተንበይ ስጦታ ሊኖራቸው ይችላል (የሐዋ. 2፡17-18)። የትንቢት ስጦታ የተወሰነ ስጦታ ሳይሆን በአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ የታየ ነው (1ኛ ተሰ. 5፡19-22 2ኛ ተሲ 2፡2፤ ሮሜ 2፡6)። የእግዚአብሔርን ቃል ላገወጅ በልዩ ሁኔታ እዚአብሔር የተጠቀመባቸው ታዋቂ ነቢያት የነበሩ ቢሆኑም የትንቢት ስጦታ ለቤተ ክርስቲያን ለነበሩ ሰዎች በብዛት ይገኝ ነበር። 

2 የትንቢት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ ትንቢቱን የሚናገረው ነቢይ እራሱን ይቆጣጠር ነበር። የሚሰጠው መልእክት ብዙ ጊዜ በድንገት በግብታዊነት እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል የማጥናት ውጤት አልነበረም። ሌሎች የሚረዱትና ለጉባኤው በቃል መልእክት የሚተላለፍ ነበር። ዓላማው ሕዝቡን ለማነጽና ለማበረታታት ነው። 

3 የትንቢት ቃል ከእግዚአብሔር ቃል እኩል የታየበት ጊዜ ፈጽሞ አልነበረም። ጳውሎስና ሌሎችም እንደዚህ ዓይነት በቅጽበት የሚመጡት መልእክቶች እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ መፈተን እንዳለባቸው ፍላጎታቸው ነበር (1ኛ ቆሮ. 14፡29፡ 1ኛ ተሰ. 5፡20-2፡ 1ኛ ዮሐ 4፡1)። 

4 ትንቢት «የግል ትንቢት» በመባል የሚታወቁ ጉዳዮች አገልግሎት ላይ ውሉ ያውቅ እንደሆነ ምንም ማስረጃ የለንም። በሰዎች ሕይወት ውስጥ ላላ – የግል ጉዛይ ዝርዝር መመሪያ ለመስጠት በተግባር ላይ የዋለበት ጊዜ ፈጽሞ የላም። ትንቢት የታቀደው ለቤተ ክርስቲያን ምእመናን በሙሉ መመሪያን ለመስጠት ነው። (ማስታወሻ፡- የትንቢት ስጦታን ለመላጽ ሰፊ ጊዜ የምንሰጥበት ትምህርት ወደፊት ይኖረናል።) 

ጥያቄ፡- ሰዎች በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ትንቢትን ከሚረዱበት መንገድ ይህ ተመሳሳይ የሚሆነው ወይም የሚለየው እንዴት ነው? 

ረ. መናፍስትን የመለየት ስጦታ 

በዚህ ስጦታ ትርጉም ላይ ምሁራን ይከራከራሉ። ሁለት መሠረታዊ አሳቦች አሉ። በመጀመሪያ፥ የሚሠሩ የተለያዩ ነገሮች (ተአምራት ማድረ፥ ትምህርት) ከመንፈስ ቅዱስ ወይም ከሌሎች መናፍስት መሆናቸውን የመለየት ችሎታ ነው። ሌሎች መናፍስት የሚለው ሀ) የሚናገረው ሰው መንፈስ ማለትም ሰውዩው ስላሉት አሳቦች፥ ወይም ላ) የሰውዬው የሚል አሳብና ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጡ እውነቶች ድብልቅ ወይም ሐ) በሰውዬው ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ክፉ መናፍስትን ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ የግብጽ ነቢያት የሙሌን ዓይነት ተአምራት ለማድረግ የቻሉ ቢሆንም ኃይል ያገኙት ከሰይጣን እንጂ ከእግዚአብሔር አልነበረም። በሁለተኛ ደረጃ፡ በነቢያቱ፥ በመምህራን ወይም በልሳናት ተናጋሪዎች የተነገረው መልእክት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከእግዚአብሔር የመጣ ወይም ከክፉ መናፍስት የመጣ መሆኑን የመፈተን ነገር ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡29)። ይህ የሚያመለክተው «መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ» የመመርመር ጉዳይ ነው (1ኛ ዮሐ 4፡1)። 

ይህ ስጦታ የሚያመላክተው ለአንድ ሰው የተላለፈው ትንቢት፡ ትምህርት ወይም የልሳን መልእክት ከእግዚአብሔር የመሆኑን ወይም ያለመሆኑን ጉዳይ የመለየት ችሎታ እንደተሰጠው ነው። ትንቢተች በተጠቀሱባቸው በሌሎች ስፍራዎች ጳውሉላ የነቢያት ንግርችን ላለ መፈተን አስፈላጊነት ጠቅሷል (ለምሳሌ 1ኛ ተሰ 5፡20፡-2 1ኛ ቆሮ. 4፡29)። በዘመናት ሁሉ እውነተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያት” ጐን ለጐን አብረዋቸው ይሠሩ ነበር። ልዩነታቸውን በምን እናውቃለን? አንደኛው መንገድ መንፈስ ቅዱስ መናፍስትን የመለየት ስጦታ ያላቸውን ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን መስጠቱ ነው። ይህም ልዩነቱን የማወቅና ከትንቢት ተብዬው ስሕተቶች ሰዎች እንዲጠነቀቁ የማድረጊያ ልዩ ችሎታ ነው። 

ሰ. በልሳናት የመናገር ስጦታ 

ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሙሉ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን” ሆነ ዛሬ ለከፍተኛ ያለመቀባባት ምክንያት የሆነው ይህ ስጦታ ነው ለመንፈስ ቅዱስ ህልውናም ሆነ ሙላት ተናቶሚ ማረጋገመ ነው ተብሎ በሚሰጠው ትምህርት ምክንያት ይህ ስጦታ በዚህ ዘመን ስለ መሥራቱና ስላለመሥራቱ በሚፈጥረው የአመለካከት ልዩነት እጅግ አወዛጋቢ ስጦታ ሆኗል። የዚህ ዘመን የልሳን ንግግር በአዲስ ኪዳን ዘመን መጀመሪያ ላይ ከነበረው ጋር ተመሳሳይ የመሆኑ ነገርም አከራካሪ ጉዳይ ነው። በሐዋርያት ሥራ ላይ ከሆነው የተላየ ላመሆኑ ጥርጥር የለውም። 

በልሳናት ለለ መናገር ጉዳይ እዚህን ምዕራፎች በምናጠናበት ጊዜ የሚከተሉትን ነገሮች ለማየት እንችላለን። 

1. መንፈስ ቅዱስ በልሳን የመናገር ስጦታን ለአንድ ሰው የሚሰጠው+ ቀለሰቡ በመንፈስ ኃይል የሆነ ንግግር ማድረግ እንዲችል ነው (1ኛ ቆር. 12፡7:1-14፡2) 

2. በልሳን የሚናገር ሰው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይም እንደ ሰመመን ሳላ ሁኔታ ውስጥ ገብቶ አይደለም። የራሱን መንፈስ የሚጣጠርና የመናገር ችሎታውንም የሚገዛ ሰመሆኑ በልሳናት መናገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥርዓት መሆን አለበት (1ኛ ር. 14፡27-28)። 

3. በልሳን መናገር ለተናጋሪውም ሆነ ለአዳማጮች በማይገባ ቋንቋ የመናገር ችሎታ ነው (1ኛ ቆሮ. 14፡14፡ 16)። ንግግሩ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይደለም (1ኛ ቆሮ. 14፡2፥ 14 ፥ 28)። ስሚተረጐምበት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የተነገረው ነገር ለሌሎችም ግልጽ ይሆናል። 

የልሳን ንግግር የሰው ቋንቋ ላለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ ጳውሎስ በግልጽ አይናገርም። ዛሬ የሚነገሩ ብዙዎች ልሳኖች የትኛውንም ቋንቋ የማይመስሉ ግልጽ ያልሆኑ ድምጾች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ልሳናት የሰው ቋንቋ እንደሆኑ ጳውሎስ ተረድቶ ነበር ይላሉ። ምክንያቱም ሀ) የግሪኩ ቃል ቋንቋን ስለሚያመለክት፥ ለ) ሊተረጐም ስለሚችልና ሐህ በሐዋ. 2፡5-1 መሠረት የታወቀ ቋንቋ ስለሆነ ነው። ሌሎች ደግሞ ጳውሎስ የሚናገረው በኋላ «የመላእክት ልሳን” (1ኛ ቆሮ. 13፡) ብሎ የጠቀሳቸውን የማይታወቁ ድምጾች ነው ይላሉ። በጉባኤው ካሉ ሰዎች መካከል ልሳናቱን የሚረዱ ሰዎች መኖር እንዳለባቸው ስላመጠበቁ ምንም ፍንጭ የላም። የሰው ቋንቋ ቢሆን ይህን ያደርግ ነበር ይላሉ። 

(ማስታወሻ፡ ስለዚህ ለጦታ በበለጠ ጥልቀት ወደፊት እንመለከታለን።) 

ሸ. በልሳናት የተነገሩትን የመተርጐም ስጦታ 

ይህ መንፈሳዊ ስጦታ ሁልጊዜ በልሳናት ከመናገር ስጦታ ጋር አብሮ የሚሄድና ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። በልሳናት መናገር ለተናጋሪውም ሆነ በጉባኤው ላሉ ሌሎች ሰዎች ግልጽ ስላልሆነ ይህ ስጦታ ተናጋሪውንና ሌሎችን የተነገረውን ነገር እንዲረዱ ያደርጋቸዋል። 

ጳውሎስ ይህን ክፍል የሚያጠቃልለው የእነዚህን ስጦታዎች ዋና ዓላማ አጠር አድርጐ በማቅረብ ነው። የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በቤተ ከርስቲያን ላሉ ሰዎች የሚሰጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አንዱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ሌሎች ስጦታዎችን ወደ ጐን በመተው በአንድ ስጦታ ላይ አትኩሮት ማድረግ የለባቸውም። ስጦታዎችን የተለየና የተሻለ አድርጐ ማቅረብም የላባቸውም። ስጦታዎች በሙሉ እኩል ከመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ናቸው። ስጦታዎች በሙሉ እግዚአብሔር እንደፈቀደና እንደወሰነ የሚሰጡ ናቸው። ይህ ሐረግ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በቤተ ክርስቲያን ላሉ የተለያዩ ሰዎች እርሱ እንደፈቀደ የመስጠቱን ሉዓላዊነት አበክሮ ይናገራል። 

ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚያገኙት ከሌሎች የተሻሉ ወይም መንፈሳዊ በመሆናቸው አይደለም። ይልቁኑ የትኛውን ስጦታ ለየትኛው ክርስቲያን እንደሚሰጥ የሚወሰን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ማንም በሌላው ስጦታ ላይ ሊቀና ወይም ከእግዚአብሔር ስለተቀበለው ስጦታ ሊመካና ሊታበይ አይገባም። 

ይህ እውነት ወደ ቅናትና ወደ ትዕቢት የሚያዘነብለውን ሰብዓዊ ዝንባሌያችንን የሚገድብ ብቻ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ለሚያደርገው እኛ ባለመብት ልንሆን እንደማንችል የሚያስጠነቅቅ ነው። ካሪዝማቲክ የሆኑም ሆኑ ያልሆኑ ክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ጥፋተኞች ናቸው። ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በተለይ ደግሞ ስልሳናት የመናገር ስጦታን እነርሱ እንደሚፈልጉት እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ወይም ፈውስ እንዲሆን ሊያውጁ እግዚአብሔር መፈወስ ግዴታው እንደሆነ የማዘዝ ያህል ነው። ጴንጤቆስጤ ያልሆኑት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ የሚፈልገውን እንዳይሠራ ነቱን በመገደባቸው ጥፋተኛ ናቸው። ለመንፈስ ቅዱስ እንደ እነርሱ እምነት በተወሰነ መንገድ ብቻ መሥራት እንዳለበት አጥብቀው ይናገራሉ። መንፈስ ቅዱስ እነርሱ ከሚጠብቁት መንገድ ውጭ ሲሠራ ይጠራጠራሉ። መንፈስ ቅዱስ አንድ ተአምራዊ የሆነን ነገር እንዲሠራ ወይም ተአምራት መሥራት እንደሌለበት መጠበቅ ስሕተት ነው። መንፈስ ቅዱስ እንደፈለገ የመስጠትና የማድረግ መብቱን እንዳንጋፋ እንጠንቀቅ። 

ጥያቄ፡- ሀ) ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች አንዳንድ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንዳይሠራ የሚወስኑት እንዴት እንደሆነ ምሳሌዎችን ስጥ። ለህ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ አንድ ስጦታን እንዲሰጣቸው ወይም አንድን ነገር እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ እንዲያደርጉ አጥብቀው የሚፈልጉበትን ሁኔታ ለመግለጽ ምሳሌዎችን ጥቀስ። ሐ) ሁለቱም ስሕተት የሆኑት ለምንድን ነው? መ) የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማየት የተሻለው መንገድ ምንድን ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.