የሕይወት እንጀራ

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ከሁለት ቀናት በፊት አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ስለፈጸሙት ኃጢአት ተምረናል። ይህ የአዳምና የሔዋን ኃጢአት በእነርሱ ላይ ብቻ ተወስኖ አልቀረም። ከእነርሱ በኋላ የመጣውን የሰው ዘር ሁሉ ኃጢአታቸው በክሎአል። ለመሆኑ ከአዳምና ከሔዋን የተገኙትን የሰው ዘሮች ሁሉ የእነርሱ ኃጢአት እንዴት ሊበክላቸው ቻለ? ይህ የሆነው በሁለት መንገዶች ነው። በመጀመሪያ ነገር፥ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ሁሉ በደለኞች ሆነዋል። ሁለተኛ ደግሞ፥ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ስኃጢአት የተበከለ ተፈጥሮ ተላብሰዋል። ዛሬ ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ በደለኞች ስለመሆናቸው እናጠናለን። በሚመጣው ሳምንት ደግሞ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከመሥራታቸው የተነሣ ሰዎች ሁሉ በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኞች ስለመሆናቸው እንማራለን። 

2. የአዳም ኃጢአት በሰዎች ሁሉ ላይ ሞትን አመጣ። 

ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡12 አንብቡ። ሀ) ኃጢአት እንዴት ወደ ዓለም ገባ? ለ) ኃጢአት ወደ ዓለም በገባ ጊዜ፥ ምን ወደ ዓለም አብሮት ገባ? ሐ) ሰዎች ሁሉ በምን ምክንያት ይሞታሉ? 

ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡13-14 አንብቡ። ሀ) ሐዋርያው ጳውሎስ፥ «ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቆጠርም ሲል ምን ማለቱ ነበር? ለ) ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ሞት በማን ላይ ነገሠ? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 4፡15 አንብቡ። ሀ) ሕግ ምንን ያመጣል? ለ) ሕግ ከሌለ ምን ሌላ ነገር የለም? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡5 አንብቡ። ሀ) በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ምን መጣ? ለ) ሮሜ 5፡16 አንብብ። ኩነኔ ከየት መጣ? ሐ) ሮሜ 5፡17 አንብብ። በአንድ ሰው በአዳም መተላለፍ የተነሣ ምን ሊመጣ ቻለ? መ) ሮሜ 5፡18 አንብብ። አዳም በሠራው አንድ የመተላለፍ ኃጢአት ምን ውጤት መጣ? 

በሮሜ 5፡12-21 ድረስ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች ስለ ዘላለማዊ ደኅንነታቸው እርግጠኛች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስተምራል። እንደዚሁም እማኛች ስለ ዘላለማዊ ደኅንነታቸው እርግጠኞች መሆናቸውን ለማሳየት ሐዋርያው በአዳምና በክርስቶስ መካከል ስላለው ሁኔታ በማነጻጸር ይጠቅሳል። ከአዳም በተወለዱት ሁሉ ላይ ሞት እንደ መጣ ሁሉ፣ በእምነት በክርስቶስ ለሆኑት ሁሉ ዘላለማዊ ሕይወት መጣ በማለት ጽፎአል። እንዲሁም በሮሜ 5፡12 አዳም በበደለ ጊዜ ኃጢአትን ወደ ዓለም አመጣ፥ ከዚያም የኃጢአት ዋጋ የሆነውን ሞትንም ወደ ዓለም እንዲመጣ አደረገ በማለት ይገልጻል። ስለሆነም ኃጢአት ከመኖሩ በፊት ሞት አልነበረም፡ የኃጢአት ጅማሬ የሞት ጅማሬ ሆነ። አዳም ኃጢአት ከመሥራቱ የተነሣ ሞት ብቻ አልመጣበትም። አዳም በመበደሉ ምክንያት ሞት በሰዎች ሁሉ ላይ መጣ። ምክንያቱም አዳም ስለ በደለ ሁሉም በድለዋል ወይም ኃጢአትን ሠርተዋል። 

ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉም ኃጢአትን ሠሩ» ሲል ሁሉም በግሪ በሠሩት ኃጢአታቸው ምክንያት ይሞታሉ ማለቱ ነበር? አይደለም፥ እዳ። ኃጢአትን በመሥራቱ ሁሉም ይሞታሉ ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው በአንድ በኩል አዳም ከበደሉ የተነሣ ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል ስለዚህ ሁሉም የኃጢአት ዋጋ በሆነው ሞት ይቀጣሉ። ሐዋርያው ጳውሎ ከአዳም ኃጢአት የተነሣ ሁሉም ኃጢአተኞች ስለሆኑ መሞት አለባቸው ያላበት ሦስት ምክንያቶች አሉት። 

1) ሮሜ 5፡12 ሰዎች በየግላቸው በሚሠሩት ኃጢአት ምክንያት ይሞታሉ አይልም። ምክንያቱም ሰዎች ሁሉ በግል ኃጢአታቸው መሞታቸው እውነት ስላልሆነ ነው። ሕፃናት በግላቸው የሚፈጽሙት ኃጢአት ባይኖርም፥ ይሞታሉ። 

2) ጳውሎስ በሮሜ 5፡13-14 ላይ ሲናገር፥ በግል ኃጢአት ባልሠሩት ሰዎች ላይ እንኳን ሞት ሥልጣን አገኘ ይላል። ይህም በአዳምና በሙሴ መካከል ባሉት ዘመናት ሆነ። እንዴዚሁ በቁጥር 3 ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ ሕጉን እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ዓለም በኃጢአት ተሞልታ እንደ ነበረች ያስረዳል። ሆኖም ያ ኃጢአት አይቆጠርም ነበር። ሕግ በሌለባት ኃጢአት እንደ ኃጢአት አይቆጠርም ብሎ ሲል ምን ማለቱ ነው? ሮሜ 4፡15 ላይ ያለው ቃል በሮሜ 5፡13 ላይ የተጻፈውን ጥቅስ ለማብራራት ይረዳናል። ሮሜ 4፡15 የሚነግረን ሕግ በሌለበት መተላለፍም ሆነ ቅጣት አለመኖሩን ነው። ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነው። መተላለፍ ሁልጊዜም መተላለፍ ነው። ነገር ግን የሚተላለፈው ሕግ ከሌለ አንድ ሰው ሕግ ተላለፈ ሊባል አይችልም። ሕግ እስካልተሰጠ ድረስ አንድ ሰው ሕግ አፈረሰ ተብሎ ሊቀጣ አይችልም። 

በእርግጥ እግዚአብሔር በአዳምና በሙለ ዘመን መካከል ለኖሩ ሰዎች አንዳንድ ትእዛዛትን ሰጥቶአቸዋል። ለምሳሌ ያህል፥ ደም ያለበትን ሥጋ እንዳይበሉና ሰውን እንዳይገድሉ አዝዞአቸው ነበር (ዘፍጥ. 9፡4-6)። በተማሪ እያንዳንዱ ሰው በልቡ ውስጥ የተጻፈ ሕግ አለው (ሮሜ 2፡5)። ይህን ሕግን ሲተላለፉ መቀጣት ነበረባቸው (ሮሜ 2፡12)። ነገር ግን ከአዳም እስከ ሙሴ በነበረው ዘመን ገና ሕግ ተጽፎ ስላልተሰጠ እግዚአብሔር የሚፈቅዳቸውንም ሆነ የሚጠላቸውን ነገሮች በውል ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ነበር። በዚያን ዘመን ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ለይቶ ለመገንዘብ የሚያስችል መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረም። እግዚአብሔር ገና ሕጉን በመዘርዘር ጽፎ አልሰጠም ነበር። ሆኖም የሙሴን ሕግ ጽፎ ከሰጠ ወዲያ ፈቃዱ ግልጽ ሆነ። ከዚያም በኋላ ሰው ሁሉ ለሚሠራው ኃጢአት ሰበብ ማቅረብ የማይችልበትና ኃላፊነትን የሚሸከምበት ጊዜ መጣ። ሰዎች ኃጢአትን ሲፈጽሙ ሕግን ማፍረሳቸው ስለሆነ ቅጣታቸውም ሞት ሆነ። ይሁን እንጂ በአዳምና በሙሉ መካከል በነበረው ረጅም ዘመን የኖሩት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ግልጽ የሆነ ሕግ ያላፈረሱትም ሳይቀሩ ሁሉም ሞቱ። ታዲያ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ግልጽ የሆነ ሕግ ካልተላለፉ በምን ምክንያት ሞቱ? እንዲሁም በግላቸው ካልበደሉስ በምን ሰበብ እንዲሞቱ ሆኑ? ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት አላም በፈጸመው ኃጢአት እነርሱም በደለኞች ስለሆኑ፥ የኃጢአትን ቅጣት ሞትን እንዲቀበሉ ተፈረደባቸው። ስለዚህ ከአዳም የውርስ ኃጢአት የተነሣ በአዳምና በሙሴ ዘመን መካከል የነበሩ ሰዎች እንዲሞቱ ሆነዋል። ይህ እንግዲህ በግልጽ የሚያስረዳን፥ ለዘመናት የኖሩትና የሚኖሩት የሰው ልጆች ሁሉ በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአተኞችና በደለኞች መደረጋቸውን ነው። 

3) በሮሜ 5፡15-18 ባለው ክፍል ሐዋርያው ጳውሎስ አራት ጊዜ ደጋግሞ ሞት በአዳም ኃጢአት ምክንያት ወደ ሰዎች ሁሉ ዘንድ መጣ ይላል። ሰዎች ራሳቸው በፈጸሙት ኃጢአት የተነሣ ሞት መጣባቸው አይልም። እርሱ በግልጽ የሚለው አዳም በፈጸመው አንድ ኃጢአት ሰበብ ሞት በሰዎች ሁሉ ላይ መምጣቱን ነው። እንዲሁም በሮሜ 5፡5 ውስጥ በአንድ ሰው በአዳም በደል ብዙዎች ይሞታሉ ይላል። በሮሜ 5፡16 ውስጥ አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ ኩነኔ መጥቷል ይላል። ይህም አንድ ሰው የተባለው አዳም ነው። በሮሜ 5፡17 ውስጥ በአንዱ በአዳም በደል ሞት ነገሠ ይላል። እንዲሁም በሮሜ 5፡18 ውስጥ ይደግምና በአንዱ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ ይገልጻል። 

በዚህ ክፍል በቁጥር 18 ላይ የአንዱ የክርስቶስ የጽድቅ ሥራ ብዙዎችን ነፃ አድርጎ፥ «ሕይወትን ይሰጣል» ስለሚል ይህ ጥቅስ ሰዎች ሁሉ እንደሚድኑ ይናገራል ብለው አንዳንድ ሰዎች ሊያስቡ ይችሉ ይሆናል። ሐዋርያው ግን የሚናገረው ከአዳም ዘር የሆኑት ኃጢአትን ወርሰው በመወለድ አዳማውያን እንደሆኑ ሁሉ በእምነት በክርስቶስ ስለሆኑት ነው። በዚህም ሐዋርያው የክርስቶስ ወገንና የአዳም ወገን ስለሆኑት መናገሩ ነው። ከሮሜ 3፡21 – 4፡25 ድረስ ባለ ክፍል ጳውሎስ አንድ ሰው የክርስቶስ ለመሆን በእርሱ ማመን ይኖርበታል ይላል። ጳውሎስ ቀደም ሲል ስለዚህ ነጥብ ደህና አድርጎ ያብራር በመሆኑ እዚህ ላይ አልደገመውም። ሐዋርያው ጳውሎስ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ማስገንዘብ የፈለገው ቁም ነገር በልደት አዳማውያን የሆኑት የሞት ሥቃይን እንደሚቀበሉ ሁሉ፥ እንዲሁም ይህን ነጥብ የበለጠ ግልጽ በማድረግ የአዳም የኃጢአት ውጤት ሰዎች ሁሉ የዚያን ኃጢአት መቀጫ ሰሞት እንደሚከፍሉ ያስተምራል። 

ስለዚህ በሮሜ 5፡12 ውስጥ ጳውሎስ የሚናገረው አዳም ኃጢአት ባደረገ ጊዜ ከእርሱ ዘር የሚወለዱት ሁሉ ማለትም የሰው ዘር የሆኑ ሁሉ ከእርሱ ጋር ኃጢአትን መፈጸማቸውን ነው። ስለሆነም ከአዳም ኃጢአት የተነሣ ሁሉም በድለዋል። በዚህ በአዳም ኃጢአት ምክንያት እያንዳንዱ ሰው የኃጢአት ቅጣት የሆነውን ሞትን ይቀበላል። 

2. አዳም ሰዎችን ሁሉ የሚወክል በመሆኑ፥ የእርሱ ኃጢአት ሞትን አመጣ። 

ለመሆኑ አዳም የሠራው ኃጢአት እንዴት አድርጎ የሰውን ዘር ሁሉ ሊነካ ቻለ? አዳም የሰውን ዘር ሁሉ ይወክላል። እርሱ ኃጢአትን ባደረገ ጊዜ ምርጫውን ለራሱ ብቻ መወሰኑ አልነበረም። የእርሱ ምርግ ለተቀሩት የሰው ዘሮችም ሁሉ የተደረገ ነበር። ለዚህ የሚሆን ጥሩ ምሳሌ በዲሞክራሲያዊ መንግሥት ውስጥ ያለው ሁኔታ ነው። ዲሞክራሲያውያን በሆኑ አገሮች የሚገኙ ሕዝቦች እነርሱን በምክር ቤት ውስጥ የሚወክሉዋቸውን ሰዎች ይመርጣሉ። በዚያ ሕግ ውስጥ የተመረጡት ወኪሎች ምርግ ሁሉ ለዚህ ሥልጣን የመረጣቸው ሕዝብ ምርግ ሆኖ ይወሰዳል። ሕዝቡን የሚወክሉት ሰዎች የሚፈጽሙት ምርግ ሁሉ ሕዝቡ ራሱ እንደ ፈጸመው ይታሰባል። ሕዝቡ ወኪላቶው በሚያደርገው መልካም ተግባር ሊጠቀም፥ በመጥፎው ተግባር ደግሞ ይጎዳበታል። በዚሁ መሠረት፥ እንግዲህ አዳም የሰው ዘር ሁሉ ወካይ ነበር፥ እርሱ ኃጢአትን ለመሥራት ባደረገው ምርጥ ምክንያት ሰዎች ሁሉ እንዲሠቃዩ ሆነ፡፡ 

ጥያቄ፡– ሰአዳም ኃጢአት ምክንያት ሁላችንም መቀጣታችን ፍትሐዊ አይደለም የሚል ሰው ቢያጋጥማችሁ ምን መልስ ትሰጡታላችሁ? 

ጥያቄ፡– ሀ) ሮሜ 2፡6 አንብብ፡ የእግዚአብሔር ፍርድ በምን ላይ ይመሠረታል? ለ) ሮሜ 33 አንብብ፡ ኃጢአትን የሠራ ማን ነው? 

ምናልባት አዳም ከሠራው ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ መሠቃየታቸው ፍትሐዊ ላይመስል ይችል ይሆናል። ሆኖም የሕይወት አብዛኛው ጎኗ ይህን ይመስላል። ብዙ ጊዜ ሰዎች ሌሎች በፈጸሙት ለሕተት ይሠቃያሉ፡ ለምሳሌ ያህል፥ የአንድ አገር መሪ የሆነ ሰው አጉል ውሳኔ ሲያሳልፍ፡ የዚያ አገር ሰዎች ሁሉ በውሳኔው ይሠቃያሉ። እንዲሁም በእግር ኳስ ወይም በቅርዓት ካለ ቀጥሚያ ላይ አንድ ተጫዋች ስሕተት ወይም ጥፋት ሲሠራ፥ ቡድኑ እንዳለ ይቀጣል። ከዚህም በስተቀር ማንም ሰው በዔድን ገነት አትክልት ስፍራ ቢሆን ኖሮ፥ እንደ አዳም አልሳሳትም ነበር ሊል አይችልም። ማንም ሰው በዔድን ገነት ውስጥ እንደ አጻም ቢኖር ኖሮ፥ ልክ እንደ እርሱ ሊሳሳት በቻለ ነበር። ማንኛችንም እንደ አዳም አንሳሳትም ነበር ብለን በድፍረት ለመናገር አንችልም። በመጨረሻም፥ ጳውሎስ በሮሜ 2፡6 እና በ3፡28 ውስጥ እያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው በእግዚአብሔር ፊት ፍርዱን ይቀበላል፥ እያንዳንዱም ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፎአል፥ በግልም እግዚአብሔርን በድሎአልና ይላል። እያንዳንዱ ሰው ወንድ ወይም ለት በግላቸው ለሚሠሩት ኃጢአት ቅጣታቸውን ይቀበላሉ። 

ምናልባት አዳም በግሉ በሠራው ኃጢአት ሁላችን መቀጣታችን አግባብ አይደለም የሚሉ ሰዎች ቢያጋጥሙዋችሁ በርሜ 5፡12-21 የተጻፈውን የማብራሪያ ቃል ንገሯቸው። ልክ በአዳም ኃጢአት ምክንያት ሰዎች በደለኞች እንደሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ጸጋ በመቀበል በክርስቶስ የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ። እንደዚሁም በአዳም ምክንያት ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች እንደሆኑ ሁሉ በክርስቶስ አማካይነት የጽድቁ ተካፋዮች ይሆናሉ። በኢየሱስ እና በመስቀል ሞቱ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን መሆናችን ታውጇል፣ የዘላለምን ሕይወትም እንቀበላለን። 

ጥያቄ፡– ወንጌልን ለሌሎች ጋር ለመካፈል የዛሬው ትምህርት ምን ያህል ቀለቅሶአችኋል? 

አዳም ከሠራው ኃጢአት የተነሣ ሁሉም ሰው በድሎአል። ነገር ግን ከክርስቶስ የጽድቅ ሕይወት፥ ሞትና ትንሣኤ የተነሣ ሁሉም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ተብሎ ሊታወጅ ይችላል። ይህ እንግዲህ ለሴሎች ወንጌልን ለማስተማርና አብረናቸው ለመካፈል በኃይል ሊቀሰቅሰን የሚችል ሁኔታ ነው። ለሠሩት ኃጢአት ቅጣት ሞትን መቀበል የሚገባቸው ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎችም ቢሆኑ በኢየሱስ ክርስቶስ በነፃ የሚሰጠውን የዘላለም ሕይወት ማግኘት ይችላሉ። ታዲያ በመጀመሪያ የክርስቶስን መልእክት መስማት ይኖርባቸዋል። ይህንንም የኃጢአታቸው ፈውስ የሆነ መልእክት ሰምተው እንዲድኑ ወደ እነርሱ ማድረስ የእኛ ኃላፊነት ነው። 

አንድ የጎሣ መሪ የራሱን ሰዎች በተወሰነ አካባቢ አስፍሮአቸዋል እንበል። ይህ መሪ የአካባቢው ውኃ ለሰው አገልግሎት የማይሆን መሆኑን አላወቀም ነበር። እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ከዚህ ውኃ ሲጠጡ ልጆቹ ሕይወታቸውን ለችግርና ለሥቃይ በሚያጋልጥ አካለ ስንኩልነት ይወለዳሉ። በዚህ አካባቢ ለብዙ ዓመታት የሚውለዱ ሕፃናት አካለ ስንኩላን ይሆናሉ። በዚህ ስፍራ አንድ ሐኪም መጥቶ ሆስፒታል ሲያቋቁም ገምቱ:: ይህ ሐኪም ወደ እርሱ የሚመጡትን አካለ ስንኩል ሕፃናትን እየተቀበለ በቀዶ ሕክምና ያቃናላቸዋል እንበል። በአቅራቢያው ያሉ ወላጆች ፈጥነው ስለዚህ የፈውስ ዕድል ሰምተው በጉጉት ይጠቀሙበታል። ከዚህም የተነሣ ልጆቻቸውን ወደ ሆስፒታሉ በማምጣት አካለ ስንኩልነታቸው በሕክምና ይሻሻላል። ይህም ልጆቻቸው የተስተካከለና ጤናማ ሕይወት እንዲኖሩ አስቻላቸው። ዳሩ ግን ደግሞ ከዚህ ሆስፒታልና ሠፈር ርቀው የሚኖሩ ችግሩ ያለባቸው ወላጆች ስለዚህ የፈውስ ሕክምና አልሰሙ ይሆናል። ታዲያ በሆስፒታሉ ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ምን እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል? መልሱ ግልጽ ነው። ፈጥነው ሄደው ለእነርሱና ለልጆቻቸው ያገኙትን የፈውስ ወሬ ለሩቆቹ መንገርና ራሳቸውም አካለ ስንኩላን ልጆቻቸውም ሕክምናውን ቶሎ መጥተው እንዲያገኙ ማድረግ ነው። እንግዲህ የአዳም ኃጢአት ጤናማ ያልሆነ ውኃ ባለበት ስፍራ ሰዎቹን ለማስፈር ይህ የጥንት ዘመን የጎሣ መሪ ያደረገውን ውሳኔ ይመስላል። የዚህ ጎሣ መሪ ውሳኔ በጎሣው ተከታታይ ትውልድ ሁሉ ላይ ባስከተለው ችግር አካለ ስንኩላን የሆኑ ልጆች እንዲወለዱና ሰው እንዲሠቃይ እንዳደረገ ሁሉ፥ አዳም የሠራው ኃጢአትም የኃጢአት ባለ ዕዳ ሆነን እንድንወለድና እንድንሞት አደረገን። ሆኖም ግን ያ ሐኪም አካለ ስንኩላን ለሆኑ ሕፃናት ሁሉ ከልደታቸው ተያይዞ ለመጣው ሥቃይና የጤና ጉድለት ፈውስን እንደ ሰጠ ሁሉ፥ ክርስቶስም ከኃጢአት ዕዳና ቅጣት እንድንድን ደኅንነትንና ዘላለማዊ ሕይወትን ሰጠን። ክርስቶስን የተቀበልን ሁላችን ከልደት ጀምሮ ከነበረባቸው አካለ ጎዶሎነት ሲፈወሱ አይተው የተደሰቱትን ወላጆች እንመስላለን። ልክ እነዚያ በሆስፒታሉ አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ መንደርተኞች ስለ ሆስፒታሉ ወሬ ላልሰሙት የጎሣ ወገኖቻቸው ሄደው የመንገር ኃላፊነት እንደ ነበረባቸው ሁሉ፥ እኛም ክርስቶስ የሚሰጠውን ደኅንነት ለሰው ዘር ሁሉ ለማብሠር ታላቅ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading