“ኢየሱስ የ ‹‹እግዚአብሔር ልጅ›› አይደለም፡፡”

አንድ ሙስሊም ስለ ክርስትና ሃይማኖት ከሚረዳቸው የተሳሳቱ ግንዛቤዎች መካከል በመጀመሪያ ስፍራ ላይ የሚቀመጠው እግዚአብሔር ሚስት እንዳለውና እርሷም ኢየሱስ የሚባል ልጅ እነዳስገኘችለት የሚያስተምር ሃይማኖት እንደሆነ ማሰቡ ነው፡፡ እንተ ግን እንደክርስቲያን ‹‹ይህ ተራ ነገር ነው! መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ አይነቱን አጸያፊ ነገር አያስተምርም፡፡›› ትል ይሆናል፡፡ እስቲ፣ የራሱን ቅዱስ መጽሐፍ ቃል በቃል እያነበበ፣ ለሚገጥሙት እንግዳ ትምህርቶች ትርጉም ለማግኘት በሚጥር አንድ ሙስሊም ፈንታ ራስህን አስቀምጥና ይህንን ጉዳይ ለመረዳት ሞክር፡፡ ሙስሊሞች ከክርስቲያን መስካሪዎች እጅ ከሚቀበሏቸው ጽሑፎች መካከል የዮሐንስ 3፣16 መልዕክት ያለባቸው ጽሑፎች ይጠፋሉ ብለን አንገምትም፡፡ ለበርካታ ክርስቲያኖች ይህ ጥቅስ የወንጌልን ጭብጥ ከሚወክሉ ጥቅሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሙስሊሙ ግን፣ ከዚህ የተለየ አሳብ ነው የሚያነብበት፡፡ አይኖቹ ‹‹አንድያ ልጁን ሰጠን›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ላይ ሲደርሱ፣ ‹‹ምን እግዚአብሔር ልጅ አለውን ይህ አጸያፊ ነገር ነው! እግዚአብሔር ልጅ አለው ማለት ሚስትም አለው ማለት አይደለምን? ይህንን አሳብ ፈጣሪ ይገስፀው!›› ማለቱ አይቀርም፡፡ ከዛም፣ በመጸየፍና ፅሁፉን በመጣል ዳግመኛ እንዲህ አይነቱን ‹‹የክህደት ትምህርት›› ላለመስማት ለራሱ ይምላል! 

በርካታ ሙስሊሞች ከልጅነታቸው ዘመን አንስቶ እግዚአብሔር አንድ ነው፣ ሌላ አጋር የለውም፣ ሴት ወዳጅም የለውም፣ እርሱ አይወለድም፣ ሌሎች አማልክትንም አይወልድም በሚሉት ትምህርቶች ተኮትኩተው እንደ ሚያድጉ መገንዘብ ይኖርብል፡፡ እስቲ እነዚህን ጥቅሶች እንመልከት፡-

  •  (እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነዉ፤ ለርሱ ሚስት የሌለችዉ ሲኾን እንዴት ለርሱ ልጅ ይኖረዋል ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፤ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቁ ነው፡፡ ይኻችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ ተገዙት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡

ሱረቱ አል-አንዓም (6)፡101-102 

How can he have a son when He hah no consort? He created all things, and hath full knowledge of all things. That is God, your Lord! There is no God by the, the Create or of all things. 

  • በል፡- እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፣ አልተወለደምም፡፡ ለርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡

ሱረቱ አል-ኢኸላስ (112)፡1-4

Say: He is God, the One and only; God the Eternal, Absolute; He begetteth not, nor is He begotten; And there is none like unto Him.

እርግጥ ነው ምንም ያህል አንዳንድ ሙስሊሞችን የሚያስከፋ ቢሆንም ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለውን ስያሜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልንሰርዘው አንችልም፡፡ ነገር ግን አባባሉን ስንጠቀም ሙስሊም ወዳጆቻችን ለሚያሳዩት ያልተጠበቀ ምላሽ ትዕግስት ሊኖረን ይገባል፡፡ አንተም ብትሆን እግዚአብሔር ወንድ ልጅ የወለደችለት ሴት ወዳጅ አለችው የሚለውን የስህተት ትምህርት በብርቱ ትቃወማለህና!

ታዲያ እንዴት ነው እንዲህ አይነቱን ስሜት የሚኮረኩር ጉዳይ አንስተህ ከሙስሊም ወዳጅህ ጋር ልትወያይ የምትችለው በመጀመሪያ ደረጃ ለሙስሊም ወዳጅህ ይህ ስያሜ በሰው የአኗኗር ስርአት አንጻር መመንዘር እንደ ሌለበት ልታብራራለት ይገባሃል፡፡ እግዚአብሔር ልጅ አለው ማለት እንደ ሰው ሰርዐት ሴት ከሆነች አማልክት ጋር ወዳጅነት ፈጥሯል ማለት እንዳልሆነ አስረዳው፡፡ በነገራችን ላይ፣ ይህ ስያሜ ብዙ ነገር ማለት ሊሆን የሚችል ተምሳሌታዊ ወይም ውስጠ ወይራዊ ገለጻ ነው፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለው ስያሜ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ልዩ ግንኙነት የሚገልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ በቀላሉ ሙስሊም ወዳጅህን፣ ‹‹በቁርአን መሰረት የኢየሱስ እውነተኛ አባት ማን ነው›› ብለህ ጥያቄ አንሳ፡፡ ምናልባት፣ ቁርአን ኢየሱስ በተአምራት ከድንግል ማርያም እንደ ተወለደና በዚህም ምክንያት ምድራዊ አባት እንደ ሌለው የሚያስተምረውን ትምህርት ያውቅ ይሆናል፡፡ እናም፣ በዚህ መነሻነት ያለምንም ግርታ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለው ስያሜ ኢየሱስ ከወንድ ዘር ያልተገኘ መሆኑን ለመግልጽ ጥቅም ላይ እንደዋለ ይረዳል፡፡ እርሱ በቀጥታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ነውና፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለውን ስያሜ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል (ስልጣን) ተወካይና ወራሽ እንደሆነ ሊያመለክትም ይችላል፡፡ እግዚአብሔር፣ ኢየሱስ በግዛቱ ላይ ሁሉ እንዲሰለጥን ስልጣንን እንደ ሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ንጉሥ ለልዑል ሥልጣንን እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ለወራሹና ልዑሉ ኢየሱስ፣ ሥልጣንን ሰጥቶታል፡፡ እንግዲህ ያስተውሉ፣ የንጉሱና የልዑሉ ግንኙነት የአባትና የልጅ ግንኙነት ነው፡፡ እንደ ‹‹እግዚአብሔር ልጅ›› ኢየሱስ የእግዚአብሔር ወኪል እና የታላቅ ስልጣኑ እና ኃይሉ ወራሽ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለው ስያሜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከኢየሱስ መሲህነት ጋር በተያያዘ መልኩ ተገጿል፡፡ እንደ መሲህ፣ ወይም እንደተቀባ ሰው፣ ኢየሱስ የጨለማ ኃይላትን ለመገርሰስና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከክፉ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት እንደ ታላቅ ገዢ መምጣት ነበረበት፡፡ እዚህ ላይ ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ የተናገረውን ምስክርነት ልብ ይሉዋል፣ ‹‹አንተ ክርስቶስ (የተቀባ) የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፡፡››

በርካታ ክርስቲያኖች የክርስቶስን መለኮታዊነት ለማጉላት በስብከቶቻቸውና በጽሑፎቻቸው መካከል ያለማቋረጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን መግለጽ ይወዳሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተሻለ መንገድ የኢየሱስን መለኮታዊነት ማስተላለፍ የምንችልበት መንገድ አለ፤ እርሱም ኢየሱስ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› መሆኑን አስረግጦ በማስረዳት ነው፡፡ ይህ ስያሜ ከዚያኛው ይልቅ ለሙስሊሞች ተቀባይነት ያለው ማዕረግ ነው፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ራሱ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ቃል ይለዋልና፡፡ በተጨማሪም በርካታ ሙስሊሞች የእግዚአብሔር ቃል የማይፈጠር መሆኑን ይስማማሉ፡፡ ይህም ማለት ይህ የእግዚአብሔር ቃል መለኮታዊ ማንነት አለው ማለት ነው፡፡ 

ከሙስሊም ሕዝቦች ጋር በሚኖርህ የመጀመሪያ ውይይት ወቅት ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለውን ስያሜ አትጠቀም፡፡ ኢየሱስን ለመግለጽ የሚያስችሉህ ሌሎች በርካታ ስያሜዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለልህና፡፡ የሐዋሪያትን ስብከት በምናገኝበት የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ›› የሚለውን ስያሜ አንድ ግዜ ብቻ ተጠቅሶ እናገኘዋለን (9፡20)፡፡ ስያሜው ተጠቅሶበት ካለው ክፍል አውድ የምንረዳውም ቢሆን ስያሜው መለኮታዊነቱን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ሳይሆን ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረውን የኢየሱስን የመሲህነት ማእረግ ለመናገር ነው (9፡22)፡፡ የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ ስለ ኢየሱስ ለመናገር የሚጠቀምባቸውን ስያሜዎችና ማዕረጎች ልብ ይበሉ፡-  

  • ጌታና መሲህ (2፡36)፣ እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእሥራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።
  • ብላቴና (አገልጋይ) (3፡13)፣ የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፣ የአባቶቻችን አምላክ፣ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው። 
  • ቅዱስና ጻድቅ (3፡14)፣ እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፣
  • የሕይወት ራስ (የሕይወት መገኛ) (3፡15)፣ የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፣ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን።
  • ቅዱስ ብላቴና (አገልጋይ) (4፡27-28)፣ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእሥራኤል ሕዝብ ጋር፣ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፣ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ። 
  • ራስና አዳኝ (5፡31)፣ ይህን እግዚአብሔር፣ ለእሥራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
  • የሰው ልጅ (7፡56)፣ እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።
  • የሁሉ ጌታ (10፡36)፣ የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እሥራኤል ልጆች ላከ።
  • በሕያዋንና ሙታን ላይ የሚፈርድ (10፡42)፣ ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።
  • አዳኝ (13፡23)፣ ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእሥራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።
  • ክርስቶስ (18፡5) ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።

ኢየሱስን ለሙስሊም ወዳጅህ በምታስተዋውቅበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠውን ታላቅ ኃይልና ስልጣን አጉልተህ ተናገር፡፡ ነፍሱን ለሰው ዘር ቤዛ አድርጎ ለመስጠት የመጣ የእግዚአብሔር ቅዱስ አገልጋይ እንደሆነ ተናገር፡፡ በዓለሙ ሁሉ ላይ ሰላምን ለመመለስ አንድ ቀን ዳግመኛ የሚመጣ የሰላም አለቃ እንደሆነ ተናገር፡፡ አለሙን ከኃጢአት እርግማን እና ከሰይጣን ሥራ ሊታደግ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ አዳኝ እንደሆነ ተርክለት፡፡ ሰዎች በእርሱ ሥራ በኩል ዘላለማዊ ሕይወትን የሚወርሱበት ቅዱስና ጻድቅ መሆኑንም መስክር!

Leave a Reply

%d bloggers like this: