የሕይወት እንጀራ

“መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል – የቁጥር ልዩነቶች፡፡”

አንዳንድ ሙስሊሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኙ የቁጥር ልዩነቶች ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ዋጋ ለማሳጣት ይሞክራሉ፡፡ በፍጥነት የሚያነሱት መከራከሪያ አሳብ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እዉነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ፣ እግዚአብሔር ፍፁም ስለሆነ ምንም አይነት የቁጥር ልዩነት በመጽሐፉ ውስጥ ሊኖር ባልተገባ ነበር የሚል ነው፡፡ አውነት ነው፣ እግዚአብሔር ፍፁም ነው፡፡ ሰዎች ግን አይደሉም፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያለምንም ሕፀፅ ለሰው ልጆች የገለጣቸዉ እግዚአብሔር ቢሆንም እነዚህን መጻሕፍት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገሩ የገለበጣቸው/የጻፋቸው ግን የሰው እጆች ነበሩ፡፡ ሰዎች ደግሞ ፍፁሞች ስላልሆኑ በሥራዎቻቸው ውስጥ ስህተቶችን ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ስህተቶች የገልባጮች ስህተቶች እንላቸዋለን፤ ምክንያቱም እነዚህ ስህተቶች መጻሕፍቱን በስፋት በማሰራጨት አድካሚና አሰልቺ ሥራ ወቅት የተሰሩ ስህተቶች የመሆን እድላቸው ሰፊ ነውና፡፡ የሚከተለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የዚህ አይነቱን ስህተት ለአብነት ያሳያል፡፡ 

  • ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞች፣ ሀያ ሺህም እግረኞች ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለመቶ ሰረገላ ብቻ አስቀረ።

2ሳሙኤል 8፡4

  • ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፣ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፣ ሀያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊት ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቆረጠ።

1ዜና 18፡4

የመጀመሪያው ጥቅስ ዳዊት 1700 ፈረሰኞችን ከእርሱ ጋር ወሰደ ሲል ሁለተኛዉ ጥቅስ ደግሞ 7000 ፈረሰኞችን ወሰደ ይላል፡፡ በብሉይ ኪዳን እንዲህ አይነቶቹ ስህተቶች በሌሎች ቦታዎችም ላይ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በርካታዎቹ የእብራይስጥ የቁጥር ፊደላት እርስ በእርስ የቀረበ ምስስሎሽ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በግልበጣ ወቅት አንዱን ቁጥር በሌላው የመተካት ወይም አንዱን ፊደል የመዘንጋት አደጋ በቀላሉ ሊኖር ይችላል፡፡

እንደ እነዚህ አይነቶቹ ስህተቶች በመጀመሪያዎቹ (original) የቅዱሳት መጻሕፍቱ ቅጂ ውስጥ ይኖራሉ ተብሎ ግን አይታመንም፡፡ ስህተቶቹ ታላቅ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ የዶክተሪን ትምህርቶች እንደማያውኩም ሙስሊሙ ሊረዳዉ ይገባል፡፡ በነገራችን ላይ ተመሳሳይ የሆነ የቁጥር ልዩነት በቁርአኑ ዉስጥም ይገኛል፡፡ እስቲ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያስተዉሉ፡-

  • ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደርሱ ይወጣል፣ (ይመለሳል)፡፡ 

ሱረቱ አል-ሰጅዳህ (32)፡5

…in the end will (all affairs) go up to Him (God) on a Day, the space whereof will be (as) a thousand years of your reckoning.

  • መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ዉስጥ ወደርሱ ያርጋሉ፣ (ይወጣሉ)፡፡

ሱረቱ አል-መዓሪጅ (70)፡4

The angels and the Spirit ascend unto Him (God) in a day, the measure whereof is (as) fifty thousand years.

የመጀመሪያው ጥቅስ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ልኬት እንደ 1000 አመታት እንደሆነና ሌላው ጥቅስ ደግሞ አንድ ቀንን ከ50000 አመታት ጋር እኩል እንደሚያደርገው እናነባለን፡፡ እንደዚህ አይነት የቁጥር ልዩነት በቁርአን ውስጥ መገኘቱ በቁርአን ትምህርት መሠረት አላህ መሃሪ፣ የሚራራ እና በማንኛውም ሰአት ሊምር የተዘጋጀ ነው የሚለውን መልዕክት ዋጋ ሊያሳጣው አይችልም፡፡ በተመሳሳይ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታየው የ 6300 ፈረሰኞች ልዩነት እግዚአብሔር በመሲሁ ኢየሱስ በኩል የገለጸውን ምህረትና ርህራሄ፣ በእርሱም በኩል የሚገኘውን ቤዛነትና የኃጢአት ይቅርታ ዋጋ ሊያሳጣው ፈፅሞ አይችልም!

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading