የሕይወት እንጀራ

“ቁርአን የመጣው መጽሐፍ ቅዱስን ለመተካት ነው፡፡”

በርካታ ሙስሊሞች፣ የሙስሊሞች ቅዱስ መጽሐፍ የሆነው ቁርአን፣ የአይሁድንና ክርስቲያኖችን ቅዱሳት መጻሕፍት ሊተካ እንደመጣ ያስባሉ፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የሚያቀርቡት እነዚህ መጻሕፍት ተበላሽተዋል፣ ተለውጠዋል፣ ጊዜ አልፎባቸዋል ወይም ጠፍተዋል የሚል ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ ቁርአኑ እነዚህን ምክንያቶች በውስጡ አላካተተም፣ አያውቃቸውምም፡፡ እንዳውም ቁርአን የቀደሙትን መገለጦች [ማለትም ኦሪትና ወንጌልን] ለማረጋገጥና ለማጽደቅ እንደተላከ ይናገራል፡፡ አንድ ነገር እውነተኛነቱ ዳግም መረጋገጥ ካስፈለገው ደግሞ የነገሩን እጅግ አስፈላጊነት ያሳያል፡፡ በተለይ አረጋጋጩ እግዚአብሔር ሲሆንማ ነገሩ እንዴት እጅግ አስፈላጊ ይሆን! ከዚህ በታች የተገለጹትን ጥቅሶች ልብ ይበሉ፤ በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት ቁርአን የቀደሙትን መገለጦች ለማረም፣ ለመተካት፣ ለመሰረዝ፣ ወይም ለማሻሻል ሳይሆን ለማረጋገጥ/ለማጽደቅ መምጣቱን ያበሥራል፡፡ 

  • ከእናንተ ጋር ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ሆኖ ባውረድኩትም (ቁርአን) እመኑ፤…

 ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡41

And believe in what I reveal, confirming the revelation which is with you….

  • ከነሱም ጋር ያለውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የሆነ መጽሐፍ [ቁርአን] ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ፣ …

 ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡89

And when there comes to them a Book (Qur’an) from God, confirming what is with them …… 

  • … እርሱ [ቁርአን] ከእነርሱ ጋር ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ እውነተኛ ሲሆን ይክዳሉ፤ …

 ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡91

… yet they reject all besides, even if it (Qur’an) be truth confirming what is with them.

  • እነርሱ ጋርም ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የሆነ መልክተኛ [ሙሐመድ] ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ …

 ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡101

And when there came to them an apostle (Muhammad) from God Confirming what was with them ….

  • ከበፊቱም የሙሳ [የሙሴ] መጽሐፍ መሪና ፀጋ ሊሆን አለ፣ ይህም [ቁርአኑ] እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ ሲሆን (የፊቶቹን መጻሕፍት) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፣ …

 ሱረቱ አል-አሕቃፍ (46)፡12 

And before this (Qur’an) was the Book of Moses as a guide and a mercy; and this book (Qur’an) confirms (it) in the Arabic tongue.

  • … ይህም ያወረድነው [ቁርአን] የሆነ ብሩክ፣ ያንንም በፊቱ የነበረውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፣ …

 ሱረቱ አል-አንዓም (6)፡92

And this is a book (Qur’an) which We have sent down, bringing blessings, and confirming (the revelation) which came before it.

  • ወደ አንተም [ወደ ሙሐመድ] መጽሐፉን [ቁርአኑን] ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በእውነት አወረድን፣ …

 ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡48 

To thee (Muhammad) We sent the scripture (Qur’an) in truth confirming the scripture that came before it, and guarding it in safety.

ዛሬ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተካተው የምናገኛቸውንና ከቁርአኑ በፊት የነበሩትን መገለጦች [ብሉይና አዲስ ኪዳን] እንደ እዚህ እጅግ አስፈላጊዎች ያደርጋቸው ነገር ምንድን ነው? ለምንድን ነው ቁርአን – የእኔ መምጣት እነርሱን ለማረጋገጥና ለመጠበቅ ነው – የሚለው ለእነዚህ ጥያቄዎች ቁርአን ራሱ ምላሽ አለው፡፡ ቁርአን፣ እነዚህ የቀድሞ መገለጦች [ብሉይና አዲስ ኪዳን] ለሰው ልጆች በሙሉ እንደ ማስጠንቀቂያ፣ እንደ የልብ ብርኃን፣ እንደ ፀጋ፣ እንደ ምሪት እና እንደ መብራት ሆነው እንደተላኩ ይናገራል፡፡ ደግሞም እርግጥ ነው፣ ይህ ብቸኛ ብርኃን ነው አለሙን ከኃጢአት ጨለማ ወደ አስደናቂው salvation/ድነት እና የዘላለም ሕይወት መንገድ ሊመራ የሚችለው፡፡ የቁርአኑን ማረጋገጫዎች ከዚህ በታች እንመለከታለን፡- 

  • ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍትን የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፍን (ቁርአንን) ባንተ ላይ [በሙሐመድ ላይ] ከፋፍሎ በውነት አወረደ፡፡ ተውራትና [ኦሪትንና] ኢንጂልንም [ወንጌልን] አውርዷል፡፡ [ከቁርአን] በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)፣ 

ሱረቱ አሊ-ዒምራን (3)፡3፣4

And He sent down the Law (of Moses) and the Gospel (of Jesus) before this (the Qur’an) as a guide to mankind.

  • እኛ ተውራትን [ኦሪትን] በውስጥዎ መምሪያና ብርሃን [guidance & light] ያለበት ስትሆን አወረድን …

ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡44

It was We who revealed the Law (to Moses); therein was guidance and light.

  • በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን [የማርያምን] ልጅ ዒሳ [ኢየሱስ] ከተወራት [ከኦሪት] በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን አስከተልን፤ ኢንጂልንም [ወንጌልንም] በውስጡ ቀጥታና ብርሃን [guidance & light] ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆቹም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው፡፡

ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡46

We sent him (Jesus) the Gospel; therein was guidance and light.

  • የፊተኞቹን የክፍል ዘመናት ሕዝቦችም ከአጠፋን በኋላ፣ ለሰዎችም የልብ ብርሃን [insight] መሪም [guidance] እዝነትም [mercy] ሲሆን ይገሰጹ ዘንድ ለሙሳ [ለሙሴ] መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡

ሱረቱ አል-ቀሶስ (28)፡43

We did reveal to Moses the book after We had destroyed the earlier generation, (to give) insight to men, and guidance and mercy, that they might receive admonition.

ሙስሊሞች፣ ከላይ በቁርአኑ የተመሰከረላቸው መልዕክቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት አሳቦች ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን እንዲረዱ አግዛቸው፡፡ በእርግጥም እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ምልክቶች ናቸው፤ መሆናቸውንም በእምነት ልንቀበል ይገባል፡፡ ቁርአኑ ማስጠንቀቂያየልብ ብርኃንፀጋምሪት እና መብራት እያለ የሚጠራቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት በእምነት በማይቀበሉ ላይ የሚያስተላልፈውን ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክቶች እስቲ አብረን እንመልከት፡-

  • … እነዚያ በአላህ ታአምራቶች [ምልክቶች] የካዱ ለነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፣ አላህም አሸነፊ የመበቀል ባለቤት ነው፡፡

ሱረቱ አሊ-ዒምራን (3)፡4

Then those who reject faith in the Signs of God will suffer the severest penalty, and God is exalted in might, Lord of retribution. 

  • ወደነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልክተኞቻችንን በርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉት (አታይምን) ወደፊትም ያውቃሉ፡፡ እንዛዝላዎቹና ስንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በርሷ) ይጎተታሉ፡፡ በገሀነም ውስጥ (ይጎተታሉ)፣ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ፡፡

ሱረቱ አል-ሙእሚን (40)፡70-72
Those who reject the Book and the (revelation) with which We sent Our apostles: but soon shall they know,—when the yokes (shall be) round their necks, and the chains; they shall be dragged along in the boiling fetid fluid; then in the Fire shall they be burned.

_____________________________________

 መጽሐፍ የሚለው ቃል ኦሪትን እና/ወይም ወንጌልን የሚወክል ሲሆን እነሱ እየተባሉ የሚጠሩት ደግሞ አይሁድ እና/ወይም ክርስቲያኖች ናቸው፡፡

Salvation/ድነት = ይህ የእንግሊዘኛ ቃል በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹መዳን፣ ድኅነት› ተብል የተተረጎመ ሲሆን በተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎች ደግሞ ‹ደኅንነት› የሚሌ ፍቺ ተሰጥቶት እንመለከታለን፡፡ የቃሉ ትርጓሜ ከአንድ ጎጂ ነገር መጠበቅን፣ መከለልን እና ነጻ መውጣትን የሚያመለክት ሲሆን፣ የቃሉ መንፈሳዊ ትርጉም ደግሞ ከኃጢአት ሃይል እና የዘላለም ሞት ከሆነው ከኃጢአት ቅጣት ማምለጥን ያመለክታል (ሮሜ 6፡23)፡፡ በጥቅሉ ቃሉ ከመንፈሳዊ ሞት ወይም፣ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ለዘለአለም በሲኦል/ገሃነም ከመኖር ነጻ መውጣትን፣ መትረፍን፣ መቤዠትን የኃጢአት ስርየት/ይቅርታ ማግኘትን፣ ያመለክታል፡፡ አንድ ሰው ሲድን ለሃጢአቱ ይቅርታን ያገኛል፤ እንዲሁም ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆናል (ሮሜ 8፡30)፡፡ ይህን ድኅነት ለማግኘት የሚሻ ሰው ሊከተል የሚችለው መንገድ አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ለሰው ልጆች ኃጢአት ምትክ ሆኖ በፈቃዱ ለመስቀል ሞት ታዛዥ በሆነው በጌታችንንና በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ማመን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በስፋት ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡

 ‹ኦሪት› = ሙሴ እንደ ጻፋቸው የሚነገሩ የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ አምስት ቅዱሳት መጻሕፍት (ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘጸአት፣ ኦሪት ዘሌዋዊያን፣ ኦሪት ዘኁልቁና ኦሪት ዘዳግም) ናቸው፡፡

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading