የሕይወት እንጀራ

ትንቢተ ኤርምያስ

ሰቆቃወ ኤርምያስ መግቢያ

ክርስቲያኖች ነገሮች ሁሉ ለእነርሱ የጨለሙ በሚመስሉበት ጊዜ ምን ማድረግ አለባቸው? አገራቸው በእርስ በርስ ጦርነት በምትጠፋበትና ምንም ተስፋ የሌለ በሚመስልበት ጊዜ ምን ማድረግ አለባቸው? ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶች በበሽታ፥ በራብ ወይም በሌላ አሳዛኝ መንገድ በሚሞቱበት ጊዜ ምን ማድረግ ይገባቸዋልን? ተስፋ መቁረጥ አለባቸውን? እግዚአብሔርን መውቀስ ይገባቸዋልን? እምነታቸውን መተው አለባቸው? ችግሩን ሸሽተው ለማምለጥ ወደ ሌላ አገር መሰደድ ይገባቸዋል? ቀኖቹ ክፉዎች በሚሆኑበት ጊዜ ክርስቲያኖች አዘውትረው የሚያደርጉአቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው።  የውይይት ጥያቄ፥ እንደዚህ ተሰምቶህ ያውቃልን? ሁኔታውን ግለጽ። የዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶህ የማያውቅ ከሆነ እንደዚህ ተሰምቶአቸው የሚያውቅ ሌሉች ክርስቲያኖችን ታውቃለህን? ለዚህ ስሜታቸው የሰጡት ምላሽ ምን ነበር? ሰቆቃወ ኤርምያስ ከትንቢተ ኤርምያስ ጋር በቅርብ የተያያዘ መጽሐፍ ነው። ይህም የሆነው፥ ሰቆቃወ ኤርምያስ የይሁዳ ሕዝብ ከተማቸው ስትጠፋ በማየት የተሰማቸውን ከፍተኛ የሥቃይ ስሜት በቅኔ የገለጹበት በመሆኑ ነው። እንዲሁም ከሁሉ አብልጠው የሚያፈቅሩትን ነገር ያጡ ክርስቲያኖች ልብ ብዙ ጊዜ ሊሰማው የሚችለውን የሥቃይ ስሜት የሚገልጽ ነው። ለእግዚአብሔር የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎችና በልባቸው የሚፈጠረውን ጥርጣሬ የሚገልጽ ነው። እንዲሁም በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነትና በከፍተኛ ኃዘን ውስጥ የእግዚአብሔርን ምሕረት ለመጠበቅ ፈቃደኛ መሆንንም የሚገልጽ ነው።  የሰቆቃወ ኤርምያስ ስያሜ በዕብራይስጥ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሰቆቃወ ኤርምያስ ከሌሎች አራት መጻሕፍት ጋር በአንድነት ተቀናጅቶ «ጽሑፎች» የሚል ስያሜ ያለው የመጻሕፍት ክፍል መሥርቶ ነበር። እነዚህ አራት መጻሕፍት መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን፥ መጽሐፈ ሩት፥ መጽሐፈ መክብብና መጽሐፈ አስቴር ናቸው። እነዚህ አምስት መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በተወሰኑ ሃይማኖታዊ በዓላት ጊዜ ይነበቡ ነበር። ሰቆቃወ ኤርምያስ ኢየሩሳሌም በ586 ዓ.ዓ. በባቢሎናውያን፥ በ70 ዓ.ም. በሮማውያን እጅ ለወደቀችበት ቀን መታሰቢያ በዓል ዕለት ይነበብ ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ «ሰቆቃወ» የሚለው ቃል በግዕዝ ምን ማለት ነው? የዚህን ቃል ፍች ካላወቅህ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄስን ጠይቅ። ሰቆቃወ ኤርምያስ ከሙሾ ወይም አይሁዳውያን የታወቀ ዐርበኛ በሚሞትበት ጊዜ ከሚያዜሙት ዜማ ጋር ተመሳሳይ ነው። የዚህ ዓይነት መዝሙራት ብዙ ጊዜ የሚጀምሩት «እንዴት» በሚል ቃል ነው (ለምሳሌ፡፡ 2ኛ ሳሙኤል 1፡19፤ ኢሳይያስ 14፡12)። ስለዚህ የዚህ መጽሐፍ የዕብራይስጥ ርእስ «እንዴት» የሚል ነው። የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ርእሶች የልቅሶ ወይም የዋይታ እንጉርጉሮን ያመለክታሉ። ይህም የሚያንጸባርቀው ሰቆቃወ ኤርምያስ የኢየሩሳሌምን መጥፋት ስለሚመለከት ልቅሶ የሚናገር መጽሐፍ መሆኑን ነው።  የሰቆቃወ ኤርምያስ ጸሐፊ የውይይት ጥያቄ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ሰቆቃወ ኤርምያስ የሚለው ርእስ መጽሐፉን የጻፈው ማን ነው ይላል? ሰቆቃወ ኤርምያስ መጀመሪያ ሲጻፍ ስለ ጸሐፊው የሚናገር ነገር አልነበረም። በኋላም የዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ በሴጵቱዋጀንት መጽሐፍ ቅዱስ እንደምናየው ወደ ግሪክ ቋንቋ ሲተረጐም ምሁራን የሰቆቃው ኤርምያስ ጸሐፊም ኤርምያስ እራሱ መሆኑን ጽፈዋል። ስለዚህ በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ርእሱ በኤርምያስ የቀረበ እንጕርጕሮ ነው ይላል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሰቆቃወ ኤርምያስን ማን እንደጻፈው በትክክል አናውቅም። የምናውቀው ነገር ቢኖር የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ማን ይሁን ማንም፥ ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ባጠፉ ጊዜ የነበረ ሰው እንደሆነ ነው። አይሁድም ሆኑ ክርስቲያኖች የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ኤርምያስ እንደሆነ ያምናሉ። ኤርምያስ የኢየሩሳሌምን ጥፋት ያየ ሰው እንደሆነ እናውቃለን። ጸሐፊው ኤርምያስ እንደሆነ እንድናስብ የሚያደርጉትን አንዳንድ ተመሳሳይ ነገሮች በትንቢተ ኤርምያስና በሰቆቃወ ኤርምያስ መካከል ይገኛሉ። ዳሩ ግን አንዳንድ ልዩነቶች ስላሉ፥ ስለ መጽሐፉ ጸሐፊ ማንነት የሚካሄደው የምሁራን ውዝግብ ቀጥሎአል። ስለዚህ ጸሐፊው ኤርምያስ እንደሆነ መገመት ቢቻልም፥ እርግጠኛ መሆን ግን አይቻልም። መጽሐፉ የተጻፈው ኢየሩሳሌም በተደመሰሰችበትና አይሁድ በተማረኩበት በ586 ዓ.ዓ. ሳይሆን አይቀርም።  የሰቆቃወ ኤርምያስ አወቃቀርና አስተዋጽኦ ሰቆቃወ ኤርምያስ አምስት የተለያዩ ግጥሞችን የያዘ ነው። የመጀመሪያዎቹ አራት ግጥሞች አይሁድ እንጕርጕሮውን ወይም ዜማውን ለማጥናት ይረዳቸው ዘንድ የሚጠቀሙበትን የአጻጻፍ ስልት የተከተለ ነው። እያንዳንዱ ጥቅስ ወይም ተከታታይ ጥቅሶች ተከታታይ ፊደላትን ይጠቀማሉ። ለምሳሌ በምዕራፍ አንድና ሁለት የግጥሞቹ 22 ቊጥሮች የሚጀምሩት በአይሁድ የፊደላት ሥርዓት ውስጥ ያሉትን ተከታታይ ፊደላት በመጠቀም ነው። ከመጽሐፉ ጠቅላላ ምዕራፎች ይበልጥ ጠቃሚ በሆነው በምዕራፍ ሦስት እያንዳንዳቸው ሦስት ተከታታይ ቍጥሮች በፊደላቱ ውስጥ ባሉ ተመሳሳይ ፊደል የሚጀምሩ ናቸው።  የሚከተለው የሰቆቃወ ኤርምያስ አስተዋጽኦ ነው፡- 1. በኢየሩሳሌም ላይ ስለደረሰው ችግርና ኃዘን የተሰጠ ገለጻ (ሰቆቃወ ኤርምያስ 1)፥  2. ጌታ በኢየሩሳሌም ላይ ስለ መቆጣቱ የቀረበ ገለጻ (ሰቆቃወ ኤርምያስ 2)፥  3. የግጥሙ ጸሐፊ ስለሆነው ሰው ኃዘንና ተስፋ የቀረበ ገለጻ (ሰቆቃወ ኤርምያስ 3)፥  4. ስለ ኢየሩሳሌም መከበብ የቀረበ ገለጻ (ሰቆቃወ ኤርምያስ 4)፥  5. ስለ ኢየሩሳሌም መመለስ የግጥሙ ጸሐፊ የጸለየው ጸሎት (ሰቆቃወ ኤርምያስ 5)። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

ሰቆቃወ ኤርምያስ መግቢያ Read More »

ኤርምያስ 46-52

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) የመንግሥታት መሪዎች በጽድቅና በቅን ፍርድ ይመሩ ዘንድ የሚያበረታታቸውና ሊገነዘቡት የሚገባቸው ነገር ምንድን ነው? ይህ ነገር ብዙ ጊዜ ይሆናልን? ለ) እግዚአብሔር ለሚፈጽሙት ተግባር ሕዝቦችን ተጠያቂ ሲያደርግ ያየኸው እንዴት ነው? ሐ) እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሲቆጣጠር ያየኸው እንዴት ነው? የብዙ መንግሥታት መሪዎች የተሳሳተ ስሜት ወይም እምነት በእግዚአብሔር ተጠያቂ እንደማይሆኑ ማሰባቸው ነው። ስለ ራሳቸው ኃይል ብቻ ያስባሉ። ይህ ኃይላቸው ብዙ ጊዜ ወደ ምግባረ ብልሹነት፥ ኢፍትሐዊነት የሆነ ውሳኔ ወደ መስጠትና በእግዚአብሔር ላይ በግልጽ ወደ ማመፅ ይመራቸዋል። ዓለማዊ መሪዎች የእግዚአብሔርን ሥራ ለመከልከል፥ አንዳንድ ጊዜም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማጥፋት ይፈልጋሉ። ነገር ግን ተጠያቂነት የለባቸውምን? እግዚአብሔር እነርሱንና ሕዝባቸውን በሞላ ተጠያቂ ያደርጋቸዋልን? እግዚአብሔር የነገሥታት ንጉሥ፥ እንዲሁም የአሕዛብና የመንግሥታት ሁሉ ተቈጣጣሪ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። እነርሱ ቢገነዘቡትም ባይገነዘቡትም እግዚአብሔር ሕዝቦችንና መንግሥታትን ሁሉ ይቈጣጠራል። ሳያውቁት ፈቃዱን የሚፈጽሙ አገልጋዮቹ ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር በእነርሱም ላይ ይፈርዳል። ስለዚህ መንግሥታት፥ ሕዝቦችና ነገሥታት ከፍርዱ ለማምለጥ ለሰዎች ሁሉ ቅን ፍርድ ማድረጋቸው ብልህነት ነው። በኤርምያስ ዘመን የባቢሎን ሕዝብ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነበሩ። ከመንገድ የወጡትን ሕዝቦች ለመቅጣት እግዚአብሔር ተጠቅሞባቸዋል። ዳሩ ግን እግዚአብሔር በእነርሱም ላይ ፈረደባቸውና አጠፋቸው። ሌሎች ሕዝቦች፥ እንደ ነጣቂዎች ያሉት፥ የይሁዳን ሕዝብ ለመበዝበዝ በኢየሩሳሌም ውድቀት ተጠቀሙ። ለጊዜው ጥቅም ስለ ማግኘታቸው ብቻ እንጂ እንደሚፈረድባቸው አላሰቡም። ኤርምያስ ግን በብዙ አሕዛብ ላይ ስለሚሆነው የእግዚአብሔር ፍርድ ተነበየ። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 46-52 አንብብ። ሀ) ኤርምያስ የተነበየባቸውን አሕዛብ ዘርዝር። ለ) በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ የተጠቀሱትን አገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመልከት። እነዚህ የጥንት አገሮች በዚህ ዘመን እነማን ናቸው ወይም የየትኛው መንግሥት አካል ናቸው? ሐ) ስለ እነዚህ አሕዛብ ኤርምያስ የተናገራቸውን ዋና ዋና ትንቢቶች ዘርዝር። መ) ከባቢሎን ውድቀት በኋላ በኤርምያስ ላይ የደረሰውን አሳጥረህ ግለጽ። 1. ኤርምያስ በአሕዛብ ላይ የተናገራቸው ትንቢቶች (ኤር. 46-51) የትንቢተ ኤርምያስ የመጨረሻ ክፍል በይሁዳ ዙሪያ ስለነበሩት ስለ አብዛኛዎቹ አሕዛብ የተነገረ ነው። እነዚህ የአሕዛብ መንግሥታት ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የአይሁዳውያን ታሪካዊ ጠላቶች ሲሆኑ ብዙ ጊዜ ይሁዳን ወይም እስራኤልን ከሚወርር ጠላት ጋር በመተባበር ጥቃት የሚያደርሱ ነበሩ። ብዙዎቹም በ586 ዓ.ዓ. በተፈጸመው የኢየሩሳሌም መደምሰስ ተሳትፈዋል። ሀ. ግብፅ (ኤር. 46) ግብፅ የአይሁድ ሕዝብ የረጅም ጊዜ ጠላት ነበረች። አይሁድን ለ400 ዓመታት በባርነት የገዛችው ግብፅ ነበረች። በአይሁድ ሕዝብ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ሁሉ ዓለምን ይገዛ የነበረው ኃያል መንግሥት የግብፅ መንግሥት ነበር። ስለሆነም አይሁድን በሥልጣናቸው ሥር አድርገው ገዙአቸው። ኃይላቸው በሚደክምበትና የአሦርና የባቢሎን መንግሥታት በሚበረቱበት ጊዜ ግብፅ ይሁዳን እንደምትረዳት ተስፋ በመስጠትና በማግባባት በአሦርና በባቢሎን ላይ እንድታምፅ ትመክራት ነበር። የይሁዳ ነገሥታትም የግብፅን ምክር በመስማት ያምፁ ነበር። ይህም በይሁዳ ላይ የአሦርን ወይም የባቢሎንን ጥቃት ይጋብዝባት ነበር። በዚህ ጊዜ ግብፅ ቃሏን በማጠፍ፥ ይሁዳን ታጋፍጣት ነበር። ግብፅ እንደገና የዓለም ኃያል መንግሥት ለመሆን ብትሻም፥ በባቢሎን ቊጥጥር ሥር እንደምትሆን ኤርምያስ ተነበየ። የግብፅ የክብር ዘመን አልፎአልና ናቡከደነፆር ግብፅን ወርሮ ይይዛል። ለ. ፍልስጥኤም (ኤር. 47) [በዘመናችን ይህ ስፍራ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘው የጋዛ ሰርጥ ነው] የአይሁድ ሕዝብ የረጅም ጊዜ ጠላት የነበረው ሌላው የፍልስጥኤም ሕዝብ ነበር። እንደሚታወሰው በሶምሶን፥ በዔሊ፥ በሳኦልና በዳዊት ዘመን ፍልስጥኤማውያን ያለማቋረጥ ከአይሁድ ጋር ይዋጉ ነበር። ቆይተው ለአይሁድ ቢገዙም፥ ባመቻቸውና ዕድል ባገኙ ጊዜ ሁሉ እያመፁ አይሁድን ለመውጋት ከሌሎች ኃይላት ጋር ይተባበሩ ነበር። ፍልስጤማውያን በይሁዳ ላይ የደረሰውን ጥፋት ግዛታቸውን ለማስፋፋት ተጠቅመውበት ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ እንደሚፈርድና በፍልስጥኤም ላይ ከፍተኛ ጥፋት እንደሚያመጣ ተናገረ። ይህንንም ለመፈም ግብጻውያንን፥ ባቢሎናውያንና ሌሎች መንግሥታትን ተጠቅሟል። ሐ. ሞዓብ (ኤር. 48) [በአሁኑ ጊዜ ይህች አገር ዮርዳኖስ ናት] ይሁዳን ከሙት ባሕር በስተምሥራቅ የምታዋስናት ሌላዋ አገር ሞዓብ ነበረች። በመጀመሪያ፥ ይህ ክልል የሮቤል ነገድ ክልል ነበር። ብዙ ጊዜ ለይሁዳ የተገዛች ብትሆንም ዕድል ባገኘች ቍጥር ይሁዳን ከሚያጠቁ ኃይላት ጋር ትተባበር ነበር። ይሁዳ በባቢሎን እጅ በወደቀች ጊዜ ሞዓባውያን ይህን እንዳደረጉ ጥርጥር የለውም። እግዚአብሔር ግን ይህን ክፋታቸውን ስላሰበ ኢየሩሳሌም ከወደቀች በኋላ ብዙም ሳይቆይ፥ የባቢሎን መንግሥት መጣና የሞዓብን መንግሥት አጠፋ። መ. አሞን (ኤር. 49፡1-6) [የአሁኖቹ ዮርዳኖስና ሶርያ] የአሞን ሕዝብ የሰፈረው ከሞአባውያን በስተ ሰሜን የጋድ ነገድ ክልል በነበረው ስፍራ ነበር። ይህም ሕዝብ ብዙ ጊዜ ለአይሁድ የተገዛ ቢሆንም፥ ዕድሉን ባገኘ ጊዜ ሁሉ ግን ከማመፅ እንዲሁም ይሁዳንና እስራኤልን ለመውጋት ከሚነሡ ሕዝቦች ጋር ከመተባበር ወደኋላ አይልም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ሽንፈትን እንደሚያመጣ ተናገረ። ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌም ከወደቀች ከብዙ ዓመታት በኋላ በአሞን ላይ ወረራ አካሄደ። ሠ. ኤዶምያስ (ኤር. 49፡7-22) [በዛሬዋ ግብፅ ያለው የሲና ወሽመጥ ያለበት ስፍራ ነው] ኤዶምያስ ከሞዓብ በስተደቡብ ትገኝ ነበር። ይህች አገር የዔሳው ዝርያዎች የሚኖሩባት ምድር ስትሆን፥ እነርሱም የአይሁድ ሕዝብ ክፉ ጠላቶች ነበሩ። በማከታተል የአይሁድን ሕዝብ እንደ እሾህ ያለማቋረጥ ይወጉ ነበር። በገደላማ ስፍራዎች ይኖሩ ስለነበር ማንም ሊያጠቃን አይችልም ብለው ያስቡ ነበር። እግዚአብሔር ግን ኤዶምያስን እንደሚደመስስ ተናገረ። በመጀመሪያ ናቡከደነፆር፥ በኋላ ደግሞ ዐረቦች ኤዶምያስን ደመሰሱ። ረ. ሶሪያ (ኤር. 49፡23-27) [የአሁኗ ደማስቆ] በዋና ከተማዋ ስም በደማስቆ የምትጠራው ሶርያ የአይሁድ ሕዝብ ጠላት ነበረች። በኤልያስ ጊዜ ከእስራኤል ጋር እንዴት እንደተዋጉና አንድ ጊዜ ደግሞ በንጉሥ አካዝ አማካይነት ከእስራኤል ጋር በመተባበር ይሁዳን እንደወጉ የሚታወስ ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚቀጣና የደማስቆ ከተማ እንደምትደመሰስ ተናገረ። ይህ በታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተፈጽሟል። ሰ. ዐረቢያ (ኤር. 49፡28-33) ኤርምያስ በዚህ ስፍራ የጠቀሰው ዛሬ ሳውዲ ዐረቢያ ተብላ በምትጠራው አገር ይኖሩ የነበሩትን ሁለት ሕዝቦች ነው። እነርሱም ቄዳርና አሶር ነበሩ። ስለ እነዚህ ሁለት ሕዝቦች የምናውቀው ብዙ ነገር ባይኖርም፥ ብዙ ጊዜ ይሁዳን ይወጉ የነበሩ በርካታ ትንንሽ ሕዝቦች በዐረቢያ ይኖሩ እንደነበር እናውቃለን። እነርሱም ከእግዚአብሔር ፍርድ ለማምለጥ አልቻሉም። እግዚአብሔር እነርሱን ለመቅጣት ናቡከደነፆርን ተጠቅሞበታል። ሸ. ኤላም (ኤር. 49፡34-39) [የአሁኗ ኢራን ናት] የኤላም ሕዝብ ከይሁዳ እጅግ ርቆ የሚገኝ ሕዝብ ነበር። ከኤፍራጥስ ወንዝ ሰሜናዊ ምሥራቅ፥ ከባቢሎን በስተምሥራቅ የምትገኝ ምድር ነበረች። የኤላም አገር በኋላ የታላቁ የሜዶንና ፋርስ መንግሥት አካል ሆና ነበር። የሜዶንና የፋርስ መንግሥት ባቢሎንን በመደምሰስ ዓለምን ለብዙ መቶ ዓመታት ገዝቷል። የኤላም ሕዝቦች ከባቢሎን ጋር በመተባበር ይሁዳን ሳይወጉ አልቀሩም። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱም ላይ ጥፋትን እንደሚያመጣ ተናገረ።  ቀ. ባቢሎን (ኤር. 51፡1-51፡64) [የአሁኗ ኢራቅ ናት] ኤርምያስ ከባድ የፍርድ ቃሉቹን እስከመጨረሻው ድረስ አዘግይቶ ነበር። በአሕዛብ ላይ ስለሚመጡ ፍርዶች በተናገራቸው እጅግ ረጃጅም በሆኑ ትንቢቶቹ ኤርምያስ ስለ ባቢሎን መደምሰስ ተናግሮ ነበር። ይህ ትንቢት በሚነገርበት ጊዜ ባቢሎን በኋያልነቷ ከመጨረሻው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰችና የማትጠፋ ትመስል ነበር። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ታላቅ በመሆኑ ስለ ባቢሎን ሙሉ በሙሉ መውደም አስቀድሞ ተናገረ። የባቢሎን መንግሥት ከ70 ዓመታት ብዙም አልዘለለም። ከዚያም የሜዶንና ፋርስ መንግሥት አሸንፎ አጠፋት። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) የእግዚአብሔር ቃል ስላለው ኃይል ከእነዚህ ምዕራፎች ምን እንማራለን? ለ) እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ የሚቆጣጠር ስለ መሆኑ ምን እንማራለን? ሐ) እነዚህ ምዕራፎች ዛሬስ የሚያበረታቱን እንዴት ነው? 2. ስለ ኢየሩሳሌም ውድቀት የተሰጠ መግለጫ (ኤር. 52) የትንቢተ ኤርምያስ የመጨረሻ ምዕራፍ የኢየሩሳሌም ከተማ የነበረችበትን የመጨረሻ ጥቂት ቀናት ሁኔታ የሚገልጽ ታሪካዊ ክፍል ነው። ኢየሩሳሌምን ለመያዝ ስለተደረገው ከበባ፥ ስለ ኢየሩሳሌም ውድቀት፥ ስለ ከተማይቱ መበዝበዝ፥ ስለ አብዛኞቹ የኢየሩሳሌም መሪዎች መሞት፥ እንዲሁም ስለ ይሁዳ ሕዝብ መማረክ ይገልጻል። ይሁን እንጂ መጽሐፉ ስለ ተስፋ በሚናገር አንድ ማስታወሻ ይጠቃለላል። ከብዙ ዓመታት በፊት ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወስዶ የነበረው ንጉሥ ዮአኪን ከወኅኒ ቤት ተለቀቀ። በምርኮ ምድር እንኳ እግዚአብሔር እየሠራና ሕዝቡን እየባረከ ነበር። ይህ የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያሳየው ከ40 ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ኤርምያስ ሲናገራቸው የነበሩ ትንቢቶች መፈጸማቸውን ነው። ኤርምያስ እውነተኛው የእግዚአብሔር

ኤርምያስ 46-52 Read More »

ኤርምያስ 37-45

አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ሕይወት በመኖሩ ሌሎች ሰዎች ከሚቀበሉት መከራ ያመልጣል ማለት አይደለም። ይልቁንም ድርቅ ወይም ወረርሽኝ ሲኖር የእግዚአብሔር ሕዝብም ብዙ ጊዜ መከራ ይቀበላሉ፤ ደግሞም ይሞታሉ። ኤርምያስ የእግዚአብሔር ነቢይ ቢሆንም እንኳ የኖረው የእግዚአብሔር ፍርድ በይሁዳ ላይ በተፈጸመ ጊዜ በመሆኑ፥ ሌሎች አይሁድ የተቀበሉትን መከራ ተቀብሏል። የምግብ ዕጥረት ሲከሠት ተርቧል፤ አንዳንድ ዘመዶቹ ሞተውበታል፤ ወዘተ። እግዚአብሔር ሌሎች ሰዎች ይቀበሉት ከነበረው መከራ ኤርምያስን አልከለለውም። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ክርስቲያኖች ለጌታ በሚኖሩበት ጊዜ፥ መከራ ሊቀበሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ለ) ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ካለህ ግንዛቤ፥ ሰዎች መከራ እንዲቀበሉ እግዚአብሔር የሚፈቅደው ለምንድን ነው?  ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ በተደረገው ጦርነት ከሌሉች ጋር ከተቀበለው መከራ ሌላ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ አንዳች ፍርሃት ያውጅ ስለነበር፥ በተጨማሪ ሌላ መከራንም ተቀብሏል። ክርስቲያኖች መከራ ሊቀበሉ የሚችሉባቸው የተለያዩ ምክንያቶች ከዚህ ቀጥሉ በዝርዝር ቀርበዋል፡ 1. በሕይወታችን ውስጥ በሚገኙ ኃጢአቶች ምክንያት እኛን ለመቅጣት (ኢዮብ 4፡7-9፤ 8፡20)።  2. በሥርዓት እንድንኖርና አካሄዳችን እንዲስተካከል ለማድረግ (ዘዳግም 8፡3፤ ምሳሌ 3፡11-12)።  3. ልባችንንና ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅርና መታዘዝ ለመፈተን (ዘዳግም 8፡2፤ ኢዮብ 1፡6-12)፥  4. እንደ ድርቅና ሞት ያለ ሥቃይ የምንቀበለው ደግሞ ከአዳምና ከሔዋን ውድቀት በኋላ ኃጢአት በሞላበት ዓለም ውስጥ የምንኖር ሥጋ ለባሾች ስለሆንን ነው (ኢዮብ 5፡6-7፤ መዝ. (14)፡1-4)።  5. የእግዚአብሔር ባሕርይና ዕቅድ ከእኛ የተሰወረ በመሆኑ፥ አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች መከራ የሚቀበሉት ለምን እንደሆነ አናውቅም (ኢዮብ 11፡7፤ መክብብ 3፡1)፥  6. አንዳንድ ጊዜ በሌሎች ፈንታ ወይም ስለ ብዙዎች መከራ ልንቀበል እንችላለን (ዘዳግም 4፡21፤ መዝሙር (106)፡23)፥  7. እግዚአብሔርን በመምሰል እንድናድግ ስለሚረዳን (ያዕቆብ 1፡2-4፤ ሮሜ 5፡3)።  8. ስለ ክርስቶስ ስም ብለን ስለምንሰደድ (ማቴ. 5፡11-12)፡  9. ሌሉች መከራ በሚቀበሉበት ወቅት ልናጽናናቸው እንድንችል (ቆሮንቶስ 1፡3-5) ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 37-45 አንብብ። ሀ) ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቃል በመናገሩ ምክንያት የደረሰበትን መከራ ዘርዝር። ለ) እግዚአብሔር ለኤርምያስ መከራን ባያስቀርለትም እንኳ በስደት ጊዜ እርሱን የጠበቀባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ኤርምያስ 37-45 በ586 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌም ከመውደቋ በፊት ከወደቀች በኋላ በኤርምያስ ሕይወት ውስጥ የተፈጸሙ የተለያዩ ታሪኮች የተመዘገቡበት ክፍል ነው።  1. በኢየሩሳሌም ጦርነት በተካሄደበት ወቅት የተፈጸሙ ክሥተቶች (ኤር. 37-39)።  ኢየሩሳሌም ለበርካታ ወራት በባቢሎናውያን ተከብባ ነበር። በእነዚህ ጊዜያት ኤርምያስ ከባቢሎናውያን ጋር መዋጋት እንደሌለባቸውና ከዚህ ይልቅ ዕርቅ ቢመሠርቱ እንደሚሻል ሕዝቡን ይመክራቸው ነበር። ጦርነቱ በመካሄድ ላይ እያለ የግብፅ ጦር ከባቢሎናውያን ጋር ለመዋጋት በመገሥገሥ ላይ እንደሆነ ተወራ። ይህም ባቢሎናውያን እነርሱን ትተው ከግብፃውያን ጋር ለመዋጋት እንደሚሄዱና ከጥቃት እንደሚድኑ ለሚያስቡ አይሁድ የልብ ልብ ሰጣቸው። ይሁን እንጂ ንጉሥ ሴዴቅያስ ስለዚህ ጉዳይ ኤርምያስን በጠየቀው ጊዜ ጥፋት ጨርሶ የማይቀር እንደሆነ ነገረው። የባቢሎን ጦር በሄደ በጥቂት ቀናት ውስጥ ኤርምያስ ከኢየሩሳሌም ጥቂት ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኝ ወደ ትውልድ መንደሩ ሄደ። ኢየሩሳሌምን ለቅቆ በሚሄድበት ወቅት ከባቢሉን ጦር ጋር ለመቀላቀል የሚሄድ የባቢሎን ሰላይ ተደርጎ በውሸት ተከሰሰና ተያዘ፤ ወደ ወኅኒም ተጣለ። በኋላ ሴዴቅያስ በዘበኞች ጠባቂዎች ግቢ ውስጥ እንዲቆይ አደረገው። ቆይቶ ለባቢሎናውያን እጃቸውን እንዲሰጡ ያቀረበው አሳብ አገርን እንደመካድና በአገር ላይ እንደማመፅ ስለተቆጠረበት፥ ባለሥልጣኖች ኤርምያስ መገደል አለበት ብለው ሰጥሞ እንዲቀር በማለት ጭቃ በሞላበት ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት። ኤርምያስ ከዚህ ጕድጓድ እንዲወጣና በግዞት እንዲቆይ ወደ ዘበኞቹ ጊቢ ተመለሰ። በዚህም ነፍሱ እንድትድን ያደረገው ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ነበር። ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን እጅ እስክትወድቅ ድረስ በግዞት ስፍራ ቆየ። እግዚአብሔር የኤርምያስን ነፍስ ለማዳን ምክንያት ለሆነው አቤሜሌክ ከባቢሎናውያን ጋር በሚደረግ ጦርነት እንደማይሞት ቃል በመግባት ለፈጸመው ድርጊት ብድራት መለሰለት። ከተማዋ በባቢሎን እጁ ከወደቀች በኋላ ናቡከደነፆር የኤርምያስን ሕይወት በማትረፍ ወደ ቤቱ ተመልሶ ከራሱ ሕዝቡ ጋር እንዲኖር ፈቀደለት።  2. ከኢየሩሳሌም ውድቀት በኋላ የተፈጸሙ ድርጊቶች (ኤርምያስ 40-45)  የኢየሩሳሌም ከተማ ስትወድቅ የባቢሎን ጦር አዛዥ ኤርምያስን በነፃ ለቀቀው። ወደሚከበርበትና ጥሩ ኑሮ ወደሚኖርበት ወደ ባቢሎን ሊወስደው ወይም በይሁዳ ውስጥ በፈለገው ስፍራ ሊኖር ምርጫ ሰጠው። ኤርምያስ በይሁዳ ከቀሩ ድሆች ሰዎች ጋር መኖርን መረጠ። ባቢሎናውያን ጎዶልያ የተባለን ሰው በይሁዳ ለቀሩት አይሁድ መሪ አድርገው ሾሙ። ሆኖም በእስማኤል መሪነት ያመፁ ሰዎች ጎዶልያን ገድለው ሸሹ። ሕዝቡም በዚህ ምክንያት ባቢሎናውያን የሚፈጽሙትን ቅጣት እጅግ ፈሩ። ኤርምያስ በይሁዳ ይቆዩ ዘንድ ሕዝቡን ቢመክራቸውም ብዙዎቹ ሳይሰሙት ቀሩ። ኤርምያስን እንደ እስረኛ ይዘው ወደ ግብፅ ሸሹ። እግዚአብሔር በግብፅ የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ እንደሚቀጣና በግብጽ ሕዝብም ላይ ሽንፈትን እንደሚያመጣ ተናገረ። ስለ ኤርምያስ የምናውቀው የመጨረሻው ነገር ይህ ነው። ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፥ አይሁድ ኤርምያስን በድንጋይ ወግረው እንደገደሉት አፈ-ታሪክ ይናገራል። በመሆኑም ዘመኑን ሁሉ በታማኝነት ያገለገለው ነቢይ ታሪክ በዚሁ አበቃ። የእግዚአብሔርን ቃል በግልጽ በመናገሩ ብዙ መከራ ደረሰበት። ይሁን እንጂ እስከሞት ድረስ የታመነ ሆነ። እንደ እውነቱ ከሆነ፥ ኤርምያስ ከብሉይ ኪዳን ታላላቅ የእምነት ጀግኖች ውስጥ አንዱ ነው። የውይይት ጥያቄ፡- ከኤርምያስ ሕይወት ስለ መሪነት የምንማራቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 45 የኤርምያስ ጸሐፊ ለነበረው ለባሮክ የቀረበ አጭር ማበረታቻ ነው። በጊዜ ቅደም ተከተል መሠረት የቀረበ አይደለም። ይህ ምዕራፍ የሚያሳየን ኤርምያስ በስደት ውስጥ እንኳ ሳለ፥ የጸሐፊው የባሮክ ጉዳይ ያሳስበው እንደነበረና ሊያበረታታው እንደፈለገ ነው።  (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

ኤርምያስ 37-45 Read More »

ኤርምያስ 26-36

የእውነትና የወንጌል ጠላቶች ብዙ ጊዜ በሕዝቡ መካከል የሚገኙ የሃይኖት መሪዎች መሆናቸው አሳዛኝ የሆነ እውነታ ነው። ይህ ኢየሱስ በኖረበት ዘመንም እውነት ነበር። ተራ የሆኑ ሰዎችና ኃጢአተኞች ኢየሱስን ሲወዱ፥ ለእግዚአብሔር ቅርብ ነን ይሉ የነበሩ የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ግን ኢየሱስን በመጥላት ሰቅለው ገደሉት። ይህ በኤርምያስ ሕይወትም እውነት ነበር። ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቃል፥ ሊመጣባቸው ስላለው ፍርድ ለሕዝቡ በድፍረት በተናገረ ጊዜ ካህናቱና ነቢያቱ ሊገድሉት ሞከሩ። ለእግዚአብሔር እንደሚናገሩና እውነተኛውን የእግዚአብሔርን አምልኮ እንደሚጠብቁ በአፋቸው ቢናገሩም እንኳ ሕዝቡን ከእውነት በማራቅና እውነት የሚናገሩትን በማሳደድ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሰይጣን መሣሪያዎች ነበሩ። ይህ ነገር ዛሬም ቢሆን ዘውትር የሚታይ ነው። እጅግ ክፉ የምንለው ነቀፋና ትችት የሚገጥመን ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ሳይሆን ከራሳችን ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሊሆን ይችላል። እንዲህ ባለው ጊዜ ዝም ልንልና ሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ልንኖር እንደሚፈልጉት ሆነን ለመኖር እንፈልጋለን። ይህን በማድረጋችንም የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት እናቆምና ለእግዚአብሔር ለመሥራት ለሚፈልጉ ሰዎች ዕንቅፋት መሆን እንጀምራለን። የሌሎች ሰዎችን ነቀፋ መስማትና ከዚያም መማር ያለብን መቼ እንደሆንና ሌሎች ምንም ቢሉ ወይም ቢያስቡ፥ የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና መታዘዝ ያለብን መቼ እንደሆነ ለመለየት ከፍተኛ መንፈሳዊ ብርታትና ጥበብ ያስፈልገናል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) የሃይማኖት መሪዎች አንተን ወይም ቤተ ክርስቲያንህን በቃል ወይም በሌላ አካላዊ ጉዳት በሚያስከትል ሁኔታ እንዴት እንዳሳደዱ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀስ። ይህንን ያደረጉት ለምንድን ነው? ለ) እግዚአብሔርን የሚፈሩ መሪዎች ሳይቀሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለውጥ እንዳይመጣ የተከላከሉባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ሐ) ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እንዲያደርጉት የሚፈልገውን ነገር በሚያውቁበትና ሌሎች መሪዎች ይህን እንዳያደርጉ በሚቃወሟቸው ጊዜ መስጠት የሚገባቸው ትክክለኛ ምላሻቸው ምንድን ነው? ሌሎች መሪዎች በሐሰት በሚከሱን ጊዜ መስጠት የሚገባን ምላሽ ምንድን ነው? በመጀመሪያ፥ ራሳችንን ማዋረድና የሚባለውን ነገር በጥንቃቄ ልንሰማ ያስፈልጋል። ክሱ፥ በአብዛኛው ውሸት ቢሆንም እንኳ ብዙ ጊዜ ግን ውሸት በውስጡ የተወሰነ እውነት ሊኖረው ይችላል። ሌሎች ከሚሉት ውስጥ እውነት የሆነው የትኛው ክፍል ነው? ልንናዘዘውና ልንለውጠው የሚገባ ነገር አለን? ሁለተኛ፥ በቃላት የሚያጠቃንን ሰው መልሶ ከማጥቃትና ለሌሎች ከማማት መፋጠብ ይኖርብናል። ትክክል የሆነውን ነገር ለሌሎች ለማሳየት፥ እግዚአብሔርን መለመን አለብን? ሦስተኛ፥ ስለ እኛ የተሳሳተ ነገር ያወራውን ሰው ሁልጊዜ እንደምንወደው ማረጋገጥ አለብን። የታዘዝነው ጠላቶቻችንን እንድንወድ ነው። ይህም ማለት በበቀልና የሌሎችን መልካም ስም ማጕደፍ የለብንም ማለት ነው። አራተኛ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሕይወታችንን ከመረመርን በኋላ ትክክለኛ ለሆነው ነገር ጸንተን በመቆም፥ የሌሎች አመለካከት ሳያስፈራን ልንኖር ይገባል። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 26-35 አንብብ። ሀ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ኤርምያስ የተጋፈጣቸውን የተለያዩ ስደቶች ዘርዝር። ለ) በኤርምያስ ላይ ስደት ያስከተለው ማን ነበር? ሐ) ኤርምያስ ለአይሁድ ሕዝብ የሰጠው የማበረታቻ ተስፋ ምን ነበር? 1. በኤርምያስ ላይ የደረሰው ግጭት (ኤርምያስ 26-29) ኤርምያስ 26-29 የኤርምያስ መልእክቶች በአይሁድ ሕዝብ፥ በተለይም በሃይማኖትና በፖለቲካ መሪዎች ዘንድ እንዴት ተቀባይነት እንዳልነበራቸው የሚያሳዩ ታሪካዊ ምሳሌዎች ናቸው። ሀ. የኤርምያስ ከካህናትና ከሐሰተኞች ነቢያት ጋር ግጭት (ኤርምያስ 26)  ኤርምያስ ቤተ መቅደሱና የኢየሩሳሌም ቅጥሮች እንደሚደመሰሱ በድፍረት በተናገረ ጊዜ ካህናትና ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡና በአገር ሽማግሌዎች ፊት ከሰሱት። ዳሩ ግን በጊዜው የነበሩት ባለሥልጣናት የኤርምያስን የመከላከያ መልስ ከሰሙ በኃላ ሕዝቡ ኤርምያስን እንዲገድሉ ከመፍቀድ ታቀቡ። ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ኦርዮ የተባለ ሌላ እውነተኛ ነቢይ ለእግዚአብሔር በመታዘዙ ተገደለ። እግዚአብሔር የአንዱን ነቢይ ሕይወት (የኤርምያስን) ሲያተርፍ፥ ሌላውን (ኦርዮ) ደግሞ እንዲሞት መፍቀዱን መመልከት የሚያስገርም ነው። ማን መኖር ግን ደግሞ መሞት እንዳለበት የሚወስነው እግዚአብሔር እራሱ ነው። ሁለቱም ጻድቃን ነበሩ። እግዚአብሔር ሁለቱንም መጠበቅ ይችል ነበር። በዚህ ፋንታ ግን እግዚአብሔር አንዱ ነቢይ እንዲሞት ሌላው ደግሞ እንዲተርፍ አደረገ። ለ. ኤርምያስ ከሐሰተኞች ነቢያት ጋር የነበረው ግጭት (ኤርምያስ 27-29) አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በባቢሎኑ ናቡከደነፆር የባርነት ቀንበር ሥር እንደሚወድቁ በተግባራዊ ምሳሌ ለማሳየት፥ በሬዎች በእርሻ ሥራ ላይ ሲሆኑ የሚጫንባቸውን ቀንበር በራሱ አንገት ላይ አደረገ። ኤርምያስ ሕዝቡ ለባቢሎናውያን ቀንበር በመገዛት በይሁዳ መኖራቸውን እንዲቀጥሉ፥ ይህንን ከተቃወሙ ግን እንደሚሞቱ ወይም በይሁዳ እንደሚማረኩ ነገራቸው። ኤርምያስ የሚናገረው ውሸት እንደሆነና ሕዝቡ ባቢሎንን እንዲቃወሙ የሚገፋፉት ካህናት ሐሰተኞች ነቢያት ስለመሆናቸው ተናገረ። ኤርምያስ፥ እስከ አሁን ድረስ ናቡከደነፆር ያልወሰዳቸው የቤተ መቅደስ ዕቃዎችም ወደ ባቢሎን እንደሚወስዱ ለካህናቱ ነገራቸው። ኤርምያስን ከተቃወሙት ሐሰተኞች ነቢያት አንዱ ሐናንያ ነበር። ሐናንያ ኤርምያስ ያደረገውን የእንጨት ቀንበር በመስበር በሁለት ዓመት ውስጥ ናቡከደነፆር ከቤተ መቅደስ የወሰዳቸው ዕቃዎች በምርኮ ከተወሰደው ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮአኪም ጋር ይመለሳሉ በማለት ተናገረ። ከዚህ በኋላ ኤርምያስ ሊሰበር የማይችል የብረት ቀንበር በአንገቱ ላይ በማድረግ፥ ሊመጣ ያለው የባቢሎን ምርኮ ቀንበር ሊሰብሩት የማይችሉት እንደሆነ አመለከተ። ከዚያም ኤርምያስ በአንድ ዓመት ውስጥ ሐናንያ እንደሚሞት አመለከተ። ይህ ትንቢት ኤርምያስ እንደተናገረ በዓመቱ ውስጥ በመፈጸም፥ ኤርምያስ እውነተኛ ነቢይ እንደሆነ አረጋገጠ። እንደ ሐናንያና ሺሚያ ያሉ ሐሰተኞች ነቢያት ለተማረኩት አይሁድ ከምርኮ ፈጥነው እንደሚመለሱ ስለነገሯቸው በሄዱበት አዲስ ምድር ተረጋግተው አልተቀመጡም ነበር፤ በስደተኝነት ይኖሩ ነበር። ስለዚህ ኤርምያስ በግዞት ላይ ላሉት ሰዎች እግዚአብሔር እነርሱን ወደ ከነዓን ከመመለሱ በፊት የምርኮው ዘመን 70 ዓመት እንደሚወስድ በመጥቀስ ደብዳቤ ጻፈላቸው። እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ስላልተዋቸው አሁንም ለእነርሱ መልካም ዕቅዶች ነበረው። ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በባቢሎን ምድር ተረጋግተው በመቀመጥ በእርሻና በአገሪቱ ንግድ በመሳተፍ፥ የተለመደ ሕይወት መግፋት እንዳለባቸው ነገራቸው። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ ከሃይማኖታዊ መሪዎች ጋር ያደረገውን ትግል ከሚገልጹት ከእነዚህ ምዕራፎች ስለ መሪነት ምን ትምህርት ልንማር እንችላለን? 2. ኤርምያስ ለአይሁድ ያስተላለፈው የማበረታቻ መልእክት (ኤርምያስ 30-33)  አብዛኛዎቹ የኤርምያስ ትንቢቶች ስለሚመጣው የኢየሩሳሌም ጥፋት የሚናገሩ ቢሆኑም፥ ከምርኮው በኋላ ለሚኖሩ አይሁድም የማበረታቻ መልእክት ለማስተላለፍ ይፈልግ ነበር። እግዚአብሔር ጨርሶ እንደማይተዋቸው ኤርምያስ ለሕዝቡ ነገራቸው። ሊቀጣቸው እንጂ ፈጽሞ ሊያጠፋቸው አለማቀዱንም አረጋገጠላቸው። ኤርምያስ «የመከራ ጊዜያት» ተብሎ የሚጠራ እጅግ አስጨናቂ ጊዜ እንደሚኖር ይናገራል። ይህንን የመከራ ጊዜ ምሁራን «የያዕቆብ መከራ» ብለው ይጠሩታል። ይህ ጊዜ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ስለ ሁለት የተለያዩ ጊዜያት የሚናገር ነው። የመጀመሪያው፥ በባቢሎናውያን ስለተፈጸመው የጥፋት ጊዜ ሲሆን፥ ሁለተኛው ግን፥ በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ጥፋት ስለሚደርስበትና በመጨረሻው ዘመን ስለሚቀሰቀስ ሌላ የጦርነት ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡ በእነዚህ ጊዜያት እንዲያልፍ ሲፈቅድም እንኳ ፈጽሞ እንደማያጠፋቸው ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር። ይልቁንም እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል። ከምርኮ ወደ ተስፋይቱ ምድር ይመልሳቸዋል። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ከአይሁድ ፈጽሞ አይወስድባቸውም። እንደገና ታላቅ ደስታና ሐሤት የሚያደርጉበት ዘመን ይመጣል። እስራኤልና ይሁዳ በመባል የተከፈለው የያዕቆብ ቤት እንደገና አንድ ይሆናል። ደግሞም እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን ያደርጋል። ይህ ቃል ኪዳን ለእስራኤል ሁሉ ይሆናል። ይህ ቃል ኪዳን እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰጣቸው ቃል ኪዳን ይበልጣል። የዚህን ቃል ኪዳን ልዩ ተስፋዎች ተመልከት፡- ሀ. ሕጉ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሕዝቦች ሁሉ ልብና አእምሮ ውስጥ ይጻፋል። ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ስለሚያውቁ ስለ እርሱ ማስተማር አያስፈልግም። ሰዎች ሁሉ ውጫዊ በሆኑ ሕግጋት አማካይነት ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ ከመገደድ ይልቅ ከልባቸው የሚታዘዙ ይሆናሉ።  ለ. እውነተኛ የኃጢአት ይቅርታ ይኖራል። ያለፈው ነገር ይረሳና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ይኖራቸዋል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ይህ አዲስ ቃል ኪዳን በኢየሱስ መምጣትና በእርሱ ባመንን ጊዜ በከፊል የተፈጸመው እንዴት ነው? ለ) የዚህ ቃል ኪዳን የተወሰነ ክፍል ገና ወደፊት የምሆነውና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና በሚመለስበት ጊዜ የሚፈጸመው እንዴት ነው? የይሁዳ ከምርኮ መመልስ እርግጠኛ እንደነበር ለማሳየት፥ እግዚአብሔር ኤርምያስን በተወለደበት ምድር መሬት እንዲገዛ ነገረው። ኤርምያስ ሕዝቡ እንደሚማረኩ ቢያውቅም እንኳ ገንዘቡን ለዚህ ዓላማ ማዋሉ፥ ከምርኮ ወደ ይሁዳ ስለ መመለሳቸው በተናገረው ትንቢት ማመኑን የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ ነበር። በኤርምያስ 33 ነቢዩ አንድ ተጨማሪ የተስፋ ቃል ይናገራል። ከዳዊት ግንድ ጻድቅ የሆነ ቍጥቋጥ ወይም ጻድቅ ንጉሥ እንደሚነሣና ይህም ንጉሥ ሕዝቡን ሁሉ

ኤርምያስ 26-36 Read More »

ኤርምያስ 18-25

እግዚአብሔር ከግለሰቦች ጋር እንደሚሠራ ሁሉ፥ በቡድን ከሰዎች ጋር ወይም ከአብያተ ክርስቲያናት ጋርም ይሠራል፤ በሁለቱም ረገድ የራሱ ዓላማዎች አሉ። በግለሰብ ደረጃ፥ ለሁላችንም ያለው ዓላማ ኢየሱስ ክርስቶስን እስክንመስል ድረስ እያንዳንዳችንን መቅረጽ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18)። በአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ ደግሞ የእግዚአብሔር ፍላጎት ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቁ የሆነች ቅድስትና ንጽሕት ሙሽራ እንድትሆን ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2)። በግለሰብ ወይም በአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ፥ እግዚአብሔር በሕይወታችን በሚፈጽመው ሥራ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን የመምሰሉን ሂደት በማፋጠን ረገድ ልንተባበር እንችላለን። ወይም ደግሞ ይህንን ለውጥ በሕይወታችን ልንቃወም እንችላለን፤ ይህ ሲሆን ግን እግዚአብሔር እንደሚፈልገው ያደርገን ዘንድ ዋናውን ሥራ የሚሠራው እርሱ ይሆናል። ይህም እግዚአብሔር መልሶ እኛን ከመሥራቱ በፊት በሕይወታችን ውስጥ ብዙ ችግርና ሥቃይ ጥፋትም ይፈጸማል። እግዚአብሔር ለኤርምያስ ይህንን መመሪያ ለማስረዳት ሸክላ ሠሪን እንዲመለከት ያዘዋል። ሸክላ ሠሪው አንድ ማሰሮ ለመሥራት ሞክሮ ስለተበላሸበት ሙሉ ለሙሉ እንደገና አፍርሶ መሥራት ነበረበት። እግዚአብሔርም እንደዚሁ ይሁዳን ውብ አድርጎ ለመሥራት ፈልጎ ነበር፤ ይሁዳ ግን ፈቃደኛ ሳትሆን ቀረች፤ ስለዚህ በምርኮና በፍርድ እግዚአብሔር ይሁዳን አንድ ቀን እርሱ እንደሚፈልገው እስክትሆን ድረስ ሊሠራት ፈለገ። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስን እስክትመስል ድረስ እግዚአብሔር በሕይወትህ የሚሠራባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ለ) ከቤተ ክርስቲያንህ ቅድስትና የበለጠ ጠቃሚ እንድትሆን እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ የሚሠራባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ሐ) ከዚህ መንፈሳዊ መመሪያ ልንወስዳቸው የሚገባን ማስጠንቀቂያዎች ምንድን ናቸው?  የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 18-25 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ከክፉ ሥራቸው የሚመለሱ ሕዝብ ምን ይሆናሉ አለ? ለ) ክፉ ሥራን የሚሠሩና ከእርሱ የማይመለሱ ሕዝብስ ምን ይሆናሉ? ሐ) በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ምን ይመጣባቸዋል? መ) የተሰበረው ሸክላ ዕቃ የምን ምልክት ነው? ሀ) ጳስኮር በኤርምያስ ምን አደረገ? ረ) ኤርምያስ በእግዚአብሔር ላይ ያቀረበው ስሞታ ምን ነበር? ሰ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የተጠቀሱ ልዩ ልዩ ነገሥታትን ጥቀስ። ሸ) ስለ ዳዊት የዘር ግንድ የተነገረው ትንቢት ምንድን ነው? ቀ) ስለ ሐሰተኛ ነቢያት የተሰጠው ትንቢት ምንድን ነው? በ) ስለ ምርኮው ዘመን ርዝመት የተሰጠው ትንቢት ምንድን ነው?  1. ኤርምያስ በሸክላ ሠሪውና በተሰበረ ጠርሙስ ምልክትነት የሰጠው ስምንተኛ መልእክቱ (ኤርምያስ 18-20) የሸክላ ሠሪነት ተግባር በኢትዮጵያውያን የተጠላ ቢሆንም በአይሁድ ዘንድ ግን የተናቀ አልነበረም። ይልቁንም የተከበረ ሙያ ነበር። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በሸክላ ሠሪ እየተመሰለ የቀረበው ለዚህ ነው። እግዚአብሔር ኤርምያስን ሂድና ሸክላ ሠሪውን ተመልከት አለው። ኤርምያስም ሸክላ ሠሪው አንድ የሸክላ ዕቃ በሚሠራበት ጊዜ ሲበላሽበት፥ የተበላሸውንም ዕቃ በማፈራረስ ከዚያው ሸክላ አዲስ ዕቃ ሲሠራ ተመለከተ። እግዚአብሔር ከዚህ ምልክት እስራኤላውያንን ያስተማራቸው ነገር፥ የመጀመሪያው የሸክላ ዕቃ የሆኑት በኃጢአት ምክንያት ቢበላሹ፥ እነርሱን አፍርሶ ሌላ የሸክላ ዕቃ ለመሥራት እንደሚችል ነበር። ይህ ትምህርት ሌሉችንም ሕዝቦች በሙሉ የሚመለከት ነበር። ከኃጢአቱ ንስሐ የሚገባ ማንኛውም ሕዝብ ይድናል፤ በክፋት ሥራው እየቀጠለ የሚሄድ ሕዝብ ሁሉ ግን ይጠፋል። ይሁዳ በክፋት ሥራው እየቀጠለ ከሚሄድ ሕዝብ መካከል የሚመደብ በመሆኑ፥ እግዚአብሔር ሊያጠፋው ተዘጋጅቶ ነበር። ኤርምያስ የእስራኤልን ሕዝብ መጥፋት ለማመልከት ሌላ ምሳሌያዊ ድርጊት ተጠቅሞ ነበር። ኤርምያስ አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎችን (ሽማግሌዎች) እና ሃይማኖታዊ መሪዎችን (ካህናት) ወደ ሄኖም ሸለቆ ይዞአቸው እንዲሄድ ተነገረው። የሄኖዎ ሸለቆ ከኢየሩሳሌም ቅጥር ክልል ውጭ የሚገኝ ስፍራ ነበር። በዚያ ስፍራ ለበአልና ለሌሎችም አማልክት ሰው እንደ መሥዋዕት ይቀርብላቸው ነበር፡፡ በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር ኤርምያስን ገንቦ እንዲወስድና እንዲሰብር በመንገር፥ የይሁዳ ሕዝብም እንዲሁ እንደሚደመሰሱ አመለከተ። አይሁድ ልጆቻቸውን መሥዋዕት አድርገው ለጣዖት ወይም ለባዕድ አማልክት የሚያቀርቡበት ይህ ስፍራ ከባቢሎን ጋር በሚካሄድ ጦርነት በሚወድቁ ሰዎች ሬሳ ይሞላል። እንዲያውም ወላጆች ልጆቻቸውን እስኪበሉ የሚያደርስ የከፋ ራብ ይሆናል። በኢየሱስ ዘመን ይህ ሸለቆ ቆሻሻ የሚጣልበትና የሚቃጠልበት ሲሆን፥ የገሃነም ምሳሌ ሆኖ ነበር። ኤርምያስ ይህን መልእክት ከተናገረ በኋላ ከካህናት አንዱ የሆነው ጳስኮር ኤርምያስን መታው። ለአንድ ምሽት በላይኛው በብንያም በር ባለው በእግር ግንድ ውስጥ አሳደረው። ይህም ኤርምያስ ከሕዝቡ በኩል ከሚደርሱበት የስደት ዓይነቶች አንዱ ነበር። ኤርምያስ በእግዚአብሔር ላይ በማጉረምረም፥ ባይወለድ ይሻለው እንደነበር ተናገረ። ዝም በማለት ከስደት ለማምለጥ በሞከረ ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ቃል በውስጡ እያቃጠለው የባሰ ስደት ቢያስከትልበትም እንዲናገር ያስገድደው ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) የሌሎች ሰዎችን ፌዝና ቀልድ ወይም ነቀፋ በመፍራት የእግዚአብሔርን ቃል ያለመናገር ስሜት ተሰምቶህ ያውቃልን? ለ) አንድ ክርስቲያን ለኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ እንዲኖርና ያለማቋረጥ ወንጌልን ለሌሎች እንዲያካፍል የሚያደርገው ነገር ምን መሆን አለበት? ሐ) በኤርምያስ ላይ የደረሰው ነገር በተፈጸመ ጊዜ ብትኖር ኖሮ ለኤርምያስ ምን ምክር ትሰጠው ነበር? 2. የኤርምያስ ዘጠነኛ መልእክት የይሁዳን ነገሥታት የሚመለከት ነበር (ኤርምያስ 21፡1-23፡8)።  ኤርምያስ 21 የተፈጸመው ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት በፈጸመ ጊዜ ነበር። ንጉሥ ሴዴቅያስ፥ ኤርምያስ የሚለውን ለመስማት በፈለገ ጊዜ፥ ባቢሎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሊገቡ እንዳለና ንጉሥ ሴዴቅያስና ሕዝቡ እንደሚቀጡ ተናግሮ ነበር። እነዚህ ምዕፍራፎች የተጻፉት ከዳዊት ዘር በርካታ ነገሥታት በነገሡበት ዘመን ነበር። ኤርምያስ ከዳዊት ዘር የሆኑትን ነገሥታት በጽድቅ ባለማስተዳደራቸውና እግዚአብሔር እንደፈለገው ባለመግዛታቸው ገሠጻቸው። እነዚህ ነገሥታት በራሳቸው ብርታትና ጥንካሬ ተማምነው ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ደግሞ በነገሥታቱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅቶ ነበር። ዳሩ ግን አንድ ቀን እግዚአብሔር ከዳዊት ዘር ጻድቅ ቍጥቋጥ ያስነሣል፤ «እግዚአብሔር ጽድቃችን» ተብሎም ይጠራል። እግዚአብሔርን የሚያከብር ዓይነት ንጉሥም ይሆናል። እስራኤልንና ይሁዳንም ነጻ ያወጣል። በእርግጥ ይህ ከዳዊት የዘር ሐረግ ስለሚወጣው የመጨረሻ ንጉሥ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት ነው። 3. የኤርምያስ አሥረኛ መልእክት በይሁዳ ሐሰተኛ ነቢያት ላይ ያነጣጠረ ነበር (ኤርምያስ 23፡9-40)። ኤርምያስ በየሄደበትና የእግዚአብሔርን እውነት በሰበከበት ስፍራ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተልከናል እያሉ ሐሰትን የሚናገሩ የነበሩ በርካታ ሐሰተኞች ነቢያት ነበሩ። በእነዚህ ሐሰተኞች ነቢያት ምክንያት ሕዝቡ መንገዳቸውን እንዲቀይሩ የሚጠይቀውንና ተወዳጅ ያልነበረውን የኤርምያስን መልእክት ከመስማት ታቀቡ። የቃላቸው ሐሰተኛነት ብቻ ሳይሆን ተግባራቸውም ክፉ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሐሰተኞች ነቢያት ላይ ሊፈርድ ተዘጋጅቶ ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ሐሰተኞች ነቢያት ዛሬ የሚሠሩት እንዴት ነው? ለ) ብዙ ክርስቲያኖችን ወደ ስሕተት የሚመሩት እንዴት ነው? ሐ) በእውነተኞችና በሐሰተኞች ነቢያት መካከል ያሉትን ልዩነቶች መነጋገር የምንችልባቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው? መ) የሐሰተኞች ነቢያትን ተጽዕኖ ለመቋቋም የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምን ማድረግ ይችላሉ? 4. የኤርምያስ አሥራ አንደኛ መልእክት የሁለት ቅርጫት በለስ ነበር (ኤርምያስ 24)። ኤርምያስ ሁለት ቅርጫት ሙሉ በለስ ተመለከተ። ይህ ያመለከተው ሁለት ዓይነት የይሁዳ ሕዝብ መኖራቸውን ነበር። ለመብላት መልካም የሆኑ በለስ የሞሉበት ቅርጫት ወደ ምርኮ የሚወሰዱትን ጻድቃን የይሁዳ ሰዎችን ሲያመለክት፥ በምርኮ በሚሆኑበት ምድር እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸውና አንድ ቀን ወደ ገዛ ምድራቸው ወደ ከነዓን እንደሚመልሳቸው የሚናገር ነበር። ለመብላት መልካም ያልሆነ በለስ የሞሉበት ቅርጫት የሚወክለው በከነዓን ምድር የሚቀሩ ወይም ወደ ግብፅ የሚሸሹና እግዚአብሔርን የማይወዱ ሰዎችን ነበር። እግዚአብሔር ተስፋ በሰጣቸው ምድር እንዳይደሰቱ በሰይፍ፥ በራብ፥ በመቅሠፍትና በጥፋት ይፈርድባቸዋል።  5. የኤርምያስ አሥራ ሁለተኛ መልእክት ግዞትና ከምርኮ አገር ስለ መመለስ ነበር (ኤርምያስ 25)።  ይህ መልእክት የተሰጠው ኢየሩሳሌም በባቢሎን እጅ ለመውደቅ በተቃረበችበት በ605 ዓ.ዓ. ነበር። ኤርምያስ ለአይሁድ የተናገረው እርሱን ስላልሰሙት ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋና ሕዝቡም እንደሚማረኩ ነበር። በዚህ ስፍራ ግን የምርኮው ዘመን ለሰባ ዓመት ብቻ እንደሚሆንና ከዚያ በኋላ ምርኮው ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለስ በመናገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሕዝቡን ያበረታታቸዋል። የሰባ ዓመቱ ምርኮ የተጀመረበትን ጊዜ በሚመለከት ምሁራን የተለያየ አሳብ አላቸው። አንዳንዶች ይህ ቊጥር የምርኮውን አጠቃላይ ዘመን የሚወክል ቍጥር ነው ይላሉ። ሌሉች ደግሞ ይህ ቁጥር ትክክለኛ የዓመታት መግለጫ ሆኖ ከ605-539 ዓ.ዓ. ያለውን ጊዜ ማለትም ኢየሩሳሌም ከተደመሰሰችበትና ከዳዊት ዘር የሆነ ንጉሥ መግዛት ካቆመበት ጀምሮ አይሁድ እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ ያለውን የሚያመለክት ነው ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ ይህ 70 ዓመት የሚያመለክተው ቤተ መቅደሱ ከተደመሰሰበት ከ586 ዓ.ዓ. ጀምሮ እንደገና እስከተሠራበት እስከ 516 ዓ.ዓ. ድረስ ያለውን የአይሁድ የሃይማኖት በምርኮ ሥር

ኤርምያስ 18-25 Read More »

ኤርምያስ 7-17

በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው ከፍተኛ አደጋ ስደት አይደለም። የሐሰት ትምህርትም አይደለም። ትልቁ አደጋ ግን ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖትን ቅርጽ ወይም ሥርዓታዊ አምልኮ ብቻ ይዛ መጓዟን፥ መቀበሏንና የሰዎችን ሕይወት የሚለውጥና በሰዎች አኗኗር ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሃይማኖት አለመኖሩ ነው። በኤርምያስ ዘመን የነበሩ አይሁድ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ ማምለካቸውን አልተዉም ነበር። ለእግዚአብሔር የእንስሳ መሥዋዕት ማቅረባቸውን አልተዉም ነበር፤ ነገር ግን ይህ በየጊዜው የሚፈጸሙት ሥርዓት ብቻ ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት አልነበራቸውም። ሕይወታቸው እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ የሚመራ አልነበረም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምልኮአቸውን ለመቀበል አልፈለገም፤ በምትኩ ግን ፍርድ እንደሚያመጣባቸው ተናገረ። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያንህ ወይም በሌላ ቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም ያየኸው እንዴት ነው? አንዳንድ ማስረጃዎች ስጥ፡፡ ለ) ይህ በግል ሕይወትህ ሊፈጸም የሚችለው እንዴት ነው? ሐ) አምልኮህ እውነተኛና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ልታደርጋቸው የምትችላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? መ) ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያንህ አባላት ላይ እንዳይፈጸም ለማድረግ አንተ ወይም የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምን ማድረግ ትችላላችሁ?  የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 7-17 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር የአይሁዶችን አምልኮ ያልተቀበለው ለምንድን ነው? ለ) በዚህ ክፍል ውስጥ የታዩትን የይሁዳ ኃጢአቶች ዘርዝር። ሐ) በዚህ ስፍራ ስለ ይሁዳ መሪዎች የተነገረው ምንድን ነው? መ) ኤርምያስ መንፈሳዊ እውነቶችን ለመግለጥ የተጠቀመባቸውን ምልክቶች ዘርዝር። እነዚህ ምዕራፎች በሚጻፉበት ጊዜ፥ ኢዮስያስ የአይሁድን ሃይማኖት ለማደስ ፈልጎ እንደነበር አስታውስ። ተግባራቸውን ለተወሰኑ ጊዜያት ለመቀየር ችሎ ነበር፤ የሕዝቡ ልብ ግን አልተለወጠም ነበር። ኢዮስያስ ከሞተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሕዝቡ ወደ ሐሰተኛ ሃይማኖቱ ተመለሰ።  1. የኤርምያስ ሦስተኛ መልእክት ስለ አይሁድ አምልኮ መበላሸት የሚናገር ነበር (ኤርምያስ 7፡1-10፡25)። አይሁድ የአምልኮ ሥርዓት እየፈጸሙ ቢመላለሱም እንኳ እግዚአብሔር ደስተኛ አልነበረም። እንደ ብዙዎቻችን ሁሉ በአምልኮ የሚያደርጉትን ነገር በሕይወታቸው ከሚለማመዱት ነገር ለይተውት ነበር። እግዚአብሔር ከአምልኮ ሕይወት ይልቅ በአምልኮ ተግባራት ላይ የበለጠ እንደሚያተኩር ይመስላቸው ነበር፤ ስለዚህ ሕይወታቸው እግዚአብሔርን የሚያስከብር እንዲሆን ምንም ጥረት አያደርጉም ነበር። ከሌሎች ጋር በቅድስናና በፍትሕ አይኖሩም ነበር። የዚህ ዓይነቱ አምልኮ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የሌለው ከንቱ ነበር። አይሁድ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነው ቤተ መቅደስ በመካከላቸው ስለነበር ኤርምያስ የሚናገረው የትንቢት ፍርድ ሊፈጸም ወይም ሊደርስባቸው እንደማይችል አድርገው ያስቡ ነበር፤ ስለዚህ ስለ መልእክቱ ይጠራጠሩ ነበር። ኤርምያስ በመጽሐፈ መሳፍንት ውስጥ እንደተጻፈው፥ በዔሊ ዘመን የመገናኛው ድንኳን እንዲደመሰስና ታቦቱ እንዲማረክ እግዚአብሔር እንዴት እንደፈቀደ ማስታወስ ነበረበት (1ኛ ሳሙኤል 4)። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ይፈርስና ይጠፋ ዘንድ እንደማይፈቅድ በሚያስቡ አንዳንድ ክርስቲያኖች ዘንድ ይህ ተመሳሳይ አመለካከት የሚታየው እንዴት ነው? ለ) የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ስላለ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በኃጢአት ምክንያት አይቀጣም ለሚሉ ክርስቲያኖች እንዴት መልስ ትሰጣለህ? የይሁዳ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስና እርሱንም ለመታዘዝ በተደጋጋሚ እምቢ አሉ። ሐሰተኞች አማልክትን የማምለክ ተግባራቸው የበለጠ ግልጽ እየሆነ መጣ። ፍርድ የሚቀበሉበትን ጊዜ ወሰነ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኤርምያስን ለሕዝቡ ደኅንነት ወይም ከጥፋት ነፃ መውጣት የሚያደርገውን ጸሎት እንዲያቆም ነገረው። ኤርምያስ ባቢሎናውያን ይሁዳን በሚወጉበት ጊዜ ስለሚመጣው ታላቅ ጥፋት ተነበየ። ኤርምያስ ከተመኛቸው ነገሮች አንዱ፡- የተቀረጹ ምስሎችን ማምለክ ምን ያህል የሞኝነት ተግባር እንደሆነ ማስተማር ነበር። የተቀረጹ ምስሎች ሰዎች ከሚያገኟቸው ከማናቸውም ዓይነት ቍሳቁሶች የሠሯቸው ነበሩ፤ ነገር ግን ምንም ኃይል አልነበራቸውም። ከነዚህ ጋር ሲነጻጸር፥ የማይታየው አምላክ እጅግ ታላቅ ኃይል ነበረው። እርሱ ምድርን የፈጠረ ዘላለማዊ ንጉሥ ነው። ስለዚህ ኤርምያስ የተከተሉትን የሞኝነት መንገድ እንዲመለከቱና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ እስራኤላውያንን ያሳስባቸዋል። እነርሱ ግን በሞኝነታቸው ገፉበት፤ የእግዚአብሔርንም ፍርድ በራሳቸው ላይ አመጡ። እግዚአብሔር በአብዛኛው ማንን ጥፋተኛ እንደሚያደርግ አስተውል። ለአብዛኛው ጥፋት ተጠያቂ ያደረጋቸው የይሁዳ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች የሆኑ እረኞችን ነበር። ከእግዚአብሔር ምሪትን ስለማይጠይቁ ምናምንቴዎች ነበሩ። የመጨረሻው ውጤት መንጋው በሙሉ ማለትም የእስራኤላውያን መበታተንና መጥፋት ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ መጥፋት የእስራኤልን ሕዝብ መሪዎች ዋና ተጠያቂዎች ያደረገው ለምን ይመስልሃል? ለ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሆንን ለእኛ ምን ማስጠንቀቂያ ይሆነናል ሐ) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገቢ ያልሆነ አመራር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ጉዳት ሲያስከትል ያየኸው እንዴት ነው? 2. የኤርምያስ አራተኛ መልእክት ይሁዳ ከእግዚአብሔር ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን ስለ ማፍረሷ የሚናገር ነው (ኤርምያስ 11፡1-12፡17)።  እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በሲና ተራራ ላይ የገባውን ቃል ኪዳን የማፍረሳቸው ክስ በብሉይ ኪዳን ነቢያት ልብ ውስጥ መቀመጡ የሚታወስ ነው፤ ስለዚህ ነቢያት ብዙውን ጊዜ በቃል ኪዳኑ ውስጥ የተገለጹት እርግማን መድረሳቸውን ያመለክቱ ነበር። ቃል ኪዳኑን ስላፈረሱ እርግማኑን መጋፈጥ እንደነበረባቸው ኤርምያስ ለሕዝቡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል። እንደገና ኤርምያስ ለሕዝቡ መጸለይ እንደማያስፈልገው ተነግሮት ነበር፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር መልስ አይሰጥም ነበርና ነው። የውይይት ጥያቄ፥ እግዚአብሔር ስለማይመልስልን ዛሬ ልንጸልያቸው የማይገባን ጸሎቶች አሉን? አንዳንድ ምሳሌዎችን ዘርዝር። ኤርምያስ የፍርድ መልእክትን በግልጽ በማወጁ፥ ከሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው። የገዛ ራሱ ነገድና ከትውልድ አገሩ የሆኑ ሰዎች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር (ኤርምያስ 11፡18-23)። ኤርምያስ፥ የይሁዳ ሕዝብ ያዘወትሩት የነበረውን ግልጽ የሆነ ክፉ ድርጊት በመመልከት፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረውን ፍርድ ለምን እንዳላመጣባቸው ይጠይቃል። ክፉዎች የሚከናወንላቸው እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደተዋቸውና ያለ እርሱ ጥበቃም ጥፋቱ እንደማይቀር ለኤርምያስ ነገረው።  3. የኤርምያስ አምስተኛ መልእክት ለምንም የማይረባ የወገብ መታጠቂያና በተቀደደ የወይን አቍማዳ ምልክትነት የተገለጠ ነበር (ኤርምያስ 13)። እግዚአብሔር ሕዝቡ የጥፋት መልእክት እንዲሰሙ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ ለዚያ ጥፋት የሚታይ ምልክት አድርጎ ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ኤርምያስን ይሁዳ እንዴት ዋጋ እንዳጣች ለማሳየት፥ ሁለት ምልክቶችን እንዲያሳይ ኤርምያስን ጠየቀው። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ኤርምያስን ከተልባ እግር የተሠራች ካህናት የሚታጠቋት ዓይነት መታጠቂያ እንዲገዛና እንዲታጠቅ አዘዘው። ይህች መታጠቂያ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ የእግዚአብሔር ካህናት መሆን እንደነበረባቸው የምታስታውሳቸው ነበር (ዘጸአት 19፡6 ተመልከት)። ይህችን መታጠቂያ ወደ ጴራክ ወስዶ እንዲሸሽጋት ተነገረው። ይህች ስፍራ በመቶ የሚቈጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቃ ከኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ነበረች። ይህ የአሦራውያንና የባቢሎናውያን ክፉ ተጽዕኖ የሚመጣበትን አቅጣጫ የሚያሳይ ነበር። ከብዙ ቀናት በኋላ ኤርምያስ የተበላሸችውን መታጠቂያ ለሕዝቡ እንዲያሳይ ተነገረው። ይህም የእግዚአብሔር ሕዝብ በምድራቸው እያሉ በአሕዛብ ተፅዕኖ መበላሸታቸውን ብቻ ሳይሆን ወደፊትም በምርኮ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ እንደሚበላሹ የሚያሳይ ነበር። በዚህ ጊዜ ለእግዚአብሔር ያላቸው ጠቀሜታ ያከትማል። ሁለተኛው ምልክት በወይን የተሞላ አቁማዳ ነበር። በጥንት ዘመን በኅብረተሰቡ ዘንድ ከሚታወቁ ክፉ ነገሮች መካከል አንዱ ሰካራምነት ነበር። ብዙ መሪዎች ሰካራሞች በመሆናቸው ይመኩ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በተለይ መሪዎችን ለየት ባለ መንገድ ሰካራሞች ያደርጋቸዋል። በቍጣው መዓት እንዲሰከሩ ሲያደርግ በእነርሱ መዘጋጀቱን ያሳያል። ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነው ይህ ፍርድ በከፊል የጠላት ወረራ በሚመጣበት ጊዜ፥ ሕዝቡ የሰከሩ በመምሰል ጠላቶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ለይተው መናገር እስከማይችሉ መድረሳቸው ነው።። ከዚያም ኤርምያስ ግልጽ በሆነ መንገድ ስለሚመጣው ምርኮ ተነበየ። ንጉሡና የንግሥቲቱም እናት ሳይቀሩ ከሰሜን በሚመጡት በባቢሎናውያን እንደሚማረኩ ተናገረ።  4. የኤርምያስ ስድስተኛ መልእክት ስለሚመጣው ድርቅ የተነገረ ነበር (ኤርምያስ 14፡1-15፡21)። በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ በሕዝቡ ላይ ስለሚደርሱ ሦስት ዐበይት የጥፋት ምንጮች በተደጋጋሚ እናነባለን። በዝናብ ዕጥረት ምክንያት የተከሠተ ድርቅ ነበር። ምግብ ባለመኖሩ ምክንያት ደግሞ ራብ ነበር። ራብ የድርቅ ወይም ሰብል ሁሉ የሚደመሰስበትና የእርሻ ሥራ የሚቆምበት የጦርነትም ውጤት ሊሆን ይችላል። በመጨረሻ ሰይፍ ነበር፤ ይኸው ሰይፍ በጠላት ውጊያ የሚመጣ ጥፋት ነበር። እግዚአብሔር ለኤርምያስ የፍርዱ ቀን ስለደረሰ፥ ስለ ሕዝቡ ነፃ መውጣት መጸለይ እንደሌለበት ለሦስተኛ ጊዜ ይነግረዋል። በዚያን ወቅት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ታላላቅ የጸሎት ሰዎች በመሆናቸው የሚታወቁት ሁለቱ ሰዎች ማለትም እስራኤላውያን በሲና ተራራ ፈጽመው እንዳይጠፉ የማለደው ሙሴና ሕዝቡ ንጉሥ እንዲነግሥላቸው በጠየቁ ጊዜ ሊጸልይላቸው ቃል የገባው ሳሙኤል እንኳ ለሕዝቡ ቢማልዱ፥ እግዚአብሔር አይሰማቸውም ነበር። ኤርምያስ ሊመጣ ስላለው ጥፋት የተሰማውን ኀዘን ይገልጻል። ዓይኖቹ እንባ አዝለው፥ ልቡም ተሰብሮ ነበር፤ ይህም ሆኖ

ኤርምያስ 7-17 Read More »

ኤርምያስ 1-6

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) አንተ ባለህበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው መሪ የሚሆነው እንዴት ነው? የሚመረጠውስ እንዴት ነው? ለ) አንድ ሰው የቤተ ክርስቲያን መጋቢ፥ ሽማግሌ ወይም ወንጌላዊ ለመሆን ሊኖሩት የሚገቡ የተለያዩ መመዘኛዎችን ዘርዝር። አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ሊኖረው ከሚገባ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ፡- የሚሠራው ሥራ እግዚአብሔር ሊያደርገው የሚፈልገው ነገር ለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት። ይህን ማረጋገጥ ብዙ ጊዜ «የእግዚአብሔር ጥሪ» ብለን እንጠራዋለን። የቤተ ክርስቲያን መሪ የሚሠራው ሥራ እግዚአብሔር እንዲሠራ የሚፈልገው ጉዳይ መሆኑን፥ እግዚአብሔር በሰጠው ስጦታ እንደሚሠራና ሥራውንም የሚያከናውነው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑን ማወቁ አስፈላጊ ነው። የሚያሳዝነው ግን ከመሪዎቻችን መካከል አብዛኛዎቹ ለመምራት በእግዚአብሔር ስለ መጠራታቸው ምንም የሚሰማቸው ነገር የለም። ለመሪነት የምትሾማቸው ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች ነው የሚያስቡት። በቤተ ክርስቲያን አመለካከት የመሪነት ብቃት ዋና መመዘኛ ሆኖ የሚቀርበው ሰውዬው ከትክክለኛ ትውልድ መምጣቱ፥ ከፍተኛ ትምህርት ያለው መሆኑ ወይም መሪ ለመሆን ያለው ትክክለኛ ማኅበራዊ ከበሬታ ነው። አንዳንድ ቦታ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክብር ለማግኘት ወይም ሥራ ለመቀጠር የሚያስችል ስለሆነ መሪ ለመሆን ይፈልጋሉ። አንድ መሪ የሚያደርገው ነገር እግዚአብሔር እንዲያደርገው የመረጠውን ተግባር ስለመሆኑ በጥልቀት የማይሰማው ከሆነ በአመራሩ ላይ ወዲያውኑ ችግሮች ይፈጠራሉ። በስግብግብነትና በራስ ወድነት ሀብትና ክብርን ለማካበት ሲል ይመራል። አንድ የተሻለ ሥራ በተሻለ ክፍያ በሚያገኝበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የአመራር ተግባር ይተዋል። አንድ ሰው እግዚአብሔር እንደጠራው ይህ ውስጣዊ ግንዛቤ ከሌለው፥ በስደት ጊዜ ጸንቶ ከመቆም፥ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣውን አብዛኛውን ስደት ከመቀበልና አመራሩን ከመቀጠል የመሪነት ሥራውን ይተዋል። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የነበሩትን ነቢያት ለነቢይነት አገልግሎት የጠራቸው ግልጽ በሆነ ሁኔታ ነበር። እነርሱ መርጠው የገቡበት አልነበረም። እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ነቢያትን ለመጥራት ትልልቅ ራእዮችን ይሰጥ ነበር (ለምሳሌ፡- ኢሳይያስ፥ ሕዝቅኤል)። ብዙውን ጊዜ ግን የነቢያት ጥሪ ቀላል ነበር። እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑትን ሰዎች ለመጥራት የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀም ነበር። ዋናው ነገር እግዚአብሔር አንድን ሰው መጥራቱ ሳይሆን፥ ቤተ ክርስቲያንና ሰውዩው ራሱ፥ እግዚአብሔር ለዚያ አገልግሎት እንደጠራው መረዳታቸው ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር ሳይጠራቸው ወይም ስጦታ ሳይኖራቸው በቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ በሚቀመጡበት ጊዜ ምን ዓይነት ችግሮች ተፈጥረው አይተሃል? ለ) ቤተ ክርስቲያንህ የተሻሉ መሪዎችን ለመምረጥ ምን ማድረግ የምትችል ይመስልሃል? ኤርምያስ የአገልግሎት ጥሪውን የተቀበለው በወጣትነቱ ነው፤ ይሁንና በጥሪው ለ40 ዓመታት አገልግሎት ዘመኑ ተመርቶበታል፤ የደረሰበትንም ስደት እንዲቋቋም ረድቶታል። የውይይት ጥያቄ፥ ከእግዚአብሔር ጥሪ አለህን? ከእግዚአብሔር ጥሪ አለኝ ካልክ፥ አንድ የተለየ ነገር ታደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራህ የተረዳህበትን መንገድ ግለጽ። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 1-6 አንብብ። ሀ) የኤርምያስን ጥሪ ግለጽ። ለ) በኤርምያስ ምዕራፍ 1 የምትመለከታቸው ሁለት ራእዮች ምን ይመስሉሃል? ሐ) እስራኤላውያን በጥፋተኛነት የተከሰሱባቸውን የተለያዩ ኃጢአቶች ዘርዝር። መ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ተለይተው የተጠቀሱት የመሪዎች ኃጢአቶች ምንድን ናቸው? 1. የኤርምያስ ጥሪ (ኤር. 1) ኤርምያስ እግዚአብሔር እንደጠራው ያውቅ ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ እግዚአብሔር ኤርምያስን ለነቢይነት የመረጠው ገና በማኅፀን ሳለ መሆኑን ነግሮት ነበር። ኤርምያስ እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ ገና ወጣት ስለነበረ ለመሪነት እንደማይበቃ አስቦ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በማለት፥ እድሜ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እንደገና አረጋገጠለት። ኃይል የሚመጣው ከኤርምያስ እድሜ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ከመናገሩ ነበር። የመንግሥታትን መደምሰስ የመተንበይ ችሎታ ለኤርምያስ የሰጠው ያ የእግዚአብሔር ቃል ነበር። በኃጢአታቸው ምክንያት በይሁዳ ሕዝብ ላይ ፍርድ የሚመጣበት ጊዜ መኖሩን ገና ከጅምሩ እግዚአብሔር ለኤርምያስ ነግሮት ነበር። እንዲሁም የሰው ተቃውሞ የሚገጥመው ቢሆንም እንኳ እግዚእብሔር እንጂ ሰውን መፍራት እንደሌለበት ኤርምያስን አስጠንቅቆት ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ብዙውን ጊዜ መሪዎች ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩባቸውን መንገዶች ግለጽ። ለ) ይህ ነገር በአንተ ሕይወት የደረሰው እንዴት ነበር? እግዚአብሔር ለኤርምያስ ለመልእክቱ ምልክት የሚሆኑት ሁለት ራእዮች ሰጥቶት ነበር፤ እነርሱም፡- ሀ. ስለ ለውዝ ዛፍ በትር ያየው፡- በዕብራይስጥ የለውዝ በትርና «መጠበቅ» የሚሉት ቃላት አንድ ዓይነት ይመስላሉ። የዚህ ራእይ ትርጕም እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ይጠብቃል፤ እርሱ አልተኛም ማለት ነው። እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ፍርድን ለማምጣት ቀርቦ ነበርና እግዚአብሔር እንደተናገረው ይፈጸም ዘንድ ቃሉ ይጠብቃል ማለት ነው።  ለ. በሰሜን አቅጣጫ ስላየው የሚፈላ ድስት ራእይ፡- ይህ ራእይ የሚያመለክተው በባቢሎን አማካይነት ስለሚመጣው የሰሜን ሠራዊት ጦርነት ነበር። እግዚአብሔር ይሁዳን ያጠቁ ዘንድ አሕዛብን እያንቀሳቀሰ ነበር። እግዚአብሔር በወሰነ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ፍርድ የሆነው ድስት በኃጢአታቸው ምክንያት የይሁዳን ሕዝብ ለመቅጣት ይፈስሳል።  2. የኤርምያስ የመጀመሪያ መልእክት፡- የይሁዳ ሕዝብ እምነት ማጣት (ኤርምያስ 2፡1-3፡5) የመረጣቸውን እግዚአብሔርን ያለ አንዳች ምክንያት እንደተዉት ኤርምያስ ለሕዝቡ ነገራቸው። በሞኝነታቸው ሌሉችን የድንጋይና የእንጨት አማልክት በመምረጥ የጣዖት አምልኮ ያዘወትሩ ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ፍርድን ለማምጣት ወሰነ።  3. የኤርምያስ ሁለተኛ መልእክት፡- ተመለሱ ወይም የእግዚአብሔርን ፍርድ ተቀበሉ (ኤርምያስ 3፡6-6፡30) ይሁዳም ልክ እንደ እስራኤል ስለሆነች እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ተመሳሳይ ፍርድ ሊያመጣ ተዘጋጅቶ ነበር። ይሁን እንጂ ይሁዳ ለባለዋ እንዳልታመነች ሚስት ለእግዚአብሔር ያላትን ታማኝነት የተወች ቢሆንም፥ ሕዝቡ ንስሐ ቢገቡና መንገዳቸውን ቢለውጡ እግዚአብሔር ይሁዳን ይቅር ለማለት አሁንም ፈቃደኛ ነበር። ቢመለሱና መንገዳቸውን ቢለውጡ፥ እግዚአብሔር ተገቢ የሆኑ እረኞችን (መሪዎች) ይሰጣቸዋል። ኢየሩሳሌምና ይሁዳም ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣሉ። ንስሐ ካልገቡና ካልተመለሱ ግን ምድሪቱን ሙሉ በሙሉ የሚደመስስ ኃይል ከሰሜን ይመጣል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ከእነዚህ የኤርምያስ መጽሐፍ ምዕራፎች ምን ማስጠንቀቂያዎችን መውሰድ እንችላለን? ለ) ቤተ ክርስቲያንህን ስለ ኃጢአትና ኃጢአት ስለሚያስከትላቸው ነገሮች፥ እንዲሁም ስለ ንስሐ አስፈላጊነት ለማስተማር እነዚህን ምዕራፎች እንዴት ትጠቀምባቸዋለህ? (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

ኤርምያስ 1-6 Read More »

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ፣ ዋና ዋና ትምሕርቶች እና ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ ትንቢተ ኤርምያስ የተጻፈው ስለ ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ነበር፤ አንደኛ፡- የይሁዳ ሕዝብ ለምን እንደተማረኩ ለመግለጽ ነበር። ይህ ክፍል እግዚአብሔር ለሕዝቡ የነበረውን የመጨረሻ መልእክት የሚነግረን ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ራሱ ለመመለስ የሞከረበት፥ ሕዝቡ በእግዚአብሔርና በሕጉ ላይ በማመፃቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ነገር በማሳየት የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ሁሉ የምናይበት ነው። ሕዝቡ የነበረበትን መንፈሳዊ ሁኔታ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አሻፈረኝ ማለታቸውንና በዚህ ምክንያት የደረሰባቸውን የምርኮ ፍርድ ያሳያል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ሰዎች እግዚአብሔር ለምን እንደሚቀጣቸው ማወቅ ያለባቸው ለምንድን ነው? ለ) ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያንህ የሚከናወነው እንዴት ነው? የትንቢተ ኤርምያስ ሁለተኛ ዓላማ የነቢዩ ኤርምያስን ሕይወትና ያለፈበትን ትግል ማሳየት ነበር። የኤርምያስ ሕይወት ተቀባይነት በማይገኝበት መሃከል የታማኝነት አመራር ምሳሌ ይሆን ዘንድ ቀርቧል። ኤርምያስ ሥራው ምንም ለውጥ የሚያመጣ በማይመስልበት ሁኔታ እንኳ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ የሚኖር ሰው ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። እግዚአብሔርን እንከተላለን በሚሉ ሰዎች አማካይነት ስደትና ተቃውሞ ቢገጥመውም እንኳ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ቆረጠ። ይህም ማለት ኤርምያስ አልታገለም፤ አገልግሎቱን ለማቋረጥ አልፈለገም ማለት አይደለም። ኤርምያስ እግዚአብሔርን በፍጹም ተጠራጥሮ አያውቅም ማለትም አይደለም። በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ እነዚህን ትግሎች እናያለን፤ ነገር ግን ኤርምያስ ለራሱ የሚመቸውን ነገር በመምረጥ የተጠራበትን አገልግሉት አላቋረጠም። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ይህንን ትምህርት በሕይወታችን መማር የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? ለ) በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርምያስን ዓይነት ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸው አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በምሳሌነት ጥቀስ። ኤርምያስ ብዙ ሚስዮናውያንና ወንጌላውያን ከሙስሊሞችና ለማመን ፈቃደኞች ካልሆኑ ሰዎች ጋር በሚሠሩበት ጊዜ ለሚገጥሟቸው ችግሮች ጥሩ ምሳሌ ነው። ብዙ ሚሲዮናውያን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ በአንድ አካባቢ ሠርተው አንድም ሰው እንኳ ወደ ክርስቶስ ሳያመጡ አልፈዋል። እነዚህ ሰዎች አልሠመረላቸውም ማለት ነውን? ለዚህ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት እንፈተን ይሆናል። እግዚአብሔር ግን እንዲሠሩ ያዘዛቸውን ነገሮች በታማኝነት እስከሠሩ ድረስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ አሉታዊ ነው። በእግዚአብሔር አመለካከት ታላቅነት ማለት በአገልግሎታችን የተዋጣልን ለመሆን መቻል ነው በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ መጠመድ የለብንም። በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ትምህርቶች 1. ኤርምያስ ስለ እግዚአብሔር ብዙ ያስተምረናል። እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ እንደሚቆጣጠርና እርሱ የመጨረሻው ባለሥልጣን እንደሆነ ያስተምረናል። እግዚአብሔር የሕያዋን ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው (ኤርምያስ 32፡27፤ 48:15፤ 51፡57)። እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይችላል፤ (ኤርምያስ 32፡17)። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው፤ ነገር ግን ኃጢአት የሚያደርጉትን ሁሉ የሚቀጣ አምላክም ነው (ኤርምያስ 32፡18)። እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ እንደየሥራቸው ይከፍላቸዋል። የዓለምን ሕዝቦች ሁሉ የሚቆጣጠርና በላያቸው ላይ ፍርድን የሚያመጣው እግዚአብሔር ነው (ኤርምያስ 5፡15፤ 46-5)። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትና ባሕርይ ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖራቸው የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ለ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ያሉት አባላት በሙሉ ስለ እግዚአብሔር እውነተኛውን ነገር እንዲያውቁ ስለ ባሕርዩ ልታስተምር የምትችልባቸውን መንገዶች ዘርዝር። 2. ትንቢተ ኤርምያስ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን በሚመለከት ስላለው መመሪያ ያስተምረናል (ኤርምያስ 18፡7-11)። የትንቢተ ኤርምያስ የመጨረሻ ክፍል (46-51) በይሁዳ ላይ ጥቃት በፈጸሙ መንግሥታት ላይ ስለሚመጣ ፍርድ የሚናገር ነው። እግዚአብሔር በራሱ ሕዝብ ላይ ስላደረሱት ነገር ፈረደባቸው። አንዳንዶቹ ትንቢቶች ወዲያውኑ ሲፈጸሙ እናያለን፤ ሌሎች ደግሞ ለመፈጸም ብዙ ዓመታት ወስደዋል። አሕዛብ የሚፈረድባቸው መቼ እንደሆነ የሚወስነው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ በላይ ስለሆነ ደግሞ ሕዝቦች ያንን ፍርድ ሊቋቋሙት አይችሉም። አንድ ሕዝብ ክፉ ከሆነ እግዚአብሔር ይፈርድበታል። ነገር ግን አንድ ሕዝብ መልካም ከሆነ ወይም ከክፉ ሥራው ንስሐ ከገባ፥ እግዚአብሔር ያንን ሕዝብ ያድናል። እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ስለሆነ ስለፈጸሙት ክፉ ተግባር ይፈርድባቸዋል። ብዙ ጊዜ መንግሥታትና ሕዝቦች ክፉ እየሠሩ ያልተቀጡ ቢመስልም፥ እግዚአብሔር ግን በራሱ ጊዜ ይቀጣቸዋል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በዓለማችን ላይ ጨቋኝ በሆኑ መንግሥታት ሥር ለሚኖሩ በርካታ ክርስቲያኖች ይህ ጉዳይ ማበረታቻ የሚሆነው እንዴት ነው? ለ) መንግሥት ክፉና ጨካኝ በሚሆንበት ወቅት ክርስቲያኖች ምን ማድረግ አለባቸው? 3. ትንቢተ ኤርምያስ ስለ ሐሰተኞች አስተማሪዎችና ነቢያት ብዙ ነገር ይናገራል (ኤርምያስ 14፡11-16፤ 23፡9-40፤ 28፡1-17)። የኤርምያስ ቀንደኛ ጠላቶች የዘመኑ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ። ካህናቱ ኤርምያስን ብዙ ጊዜ ይቃወሙትና ንጉሡ እንዲገድለው ይጠይቁ ነበር፤ ዳሩ ግን ከእነዚህም የሚብሰው በእግዚአብሔር ስም እናስተምራለን እያሉ ሕዝቡን ወደ ክሕደት ይመሩ የነበሩ የሐሰተኞች ነቢያት ጉዳይ ነበር። ኤርምያስ ሊመጣ ስላለው ጥፋት ለሕዝቡ በመንገር ንስሐ እንዲገቡ በሚያስተምርበት ጊዜ ሐሰተኞች ነቢያት ግን ሕዝቡ በግማሽ ልቡ በሚፈጽመው አምልኮ እንዲቀጥል በማበረታታት እግዚአብሔር ብልጽግና፣ ሰላምና በጠላቶቻቸውም ላይ ድልን እንደሚሰጣቸው እንደተናገረ አድርገው ያቀርቡ ነበር። እነዚህ ሐሰተኞች ነቢያት ብዙ ከመሆናቸውም መልእክታቸውም ምንም ሕዝቡን እምብዛም የማያስጨንቅና በቀላሉ ተቀባይነት የነበረው በመሆኑ፥ ኤርምያስ ራሱ እንደ ሐሰተኛ ነቢይ ተቆጥሮ ነበር፤ መልእክቱንም የሚሰማው አልነበረም። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሐሰተኞች ነቢያት አሉን? መልስህን አብራራ። ለ) እነዚህ ሐሰተኞች ነቢያት የሚሠሩት እንዴት ነው? ሐ) መልእክታቸው በብዙ ሰዎች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነት የሚያገኘው ለምንድን ነው? መ) የእነዚህ ሐሰተኞች ነቢያት መልእክት የሚያስከትለውን መዘዝ ለመገደብ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምን ማድረግ ይችላሉ? 4. ኤርምያስ የባቢሎን ምርኮ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በትክከል ተንብዮ ነበር፤ ይህም 70 ዓመታት ነበር (ኤርምያስ 29፡10)። (70ውን የምርኮ ዓመታት በሚመለከት ቀደም ሲል ያሰፈርነውን በሁለት የተለያዩ መንገዶች የተሰጠ ማስታወሻ ተመልከት።) ባለመታዘዛቸው ምክንያት እግዚአብሔር ሕዝቡን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት አልፈለገም። በከፍተኛ ደረጃ የቀጣቸው ቢሆንም እንኳ ከቅጣቱ ጊዜ በኋላ ግን የምሕረትና የይቅርታ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደገዛ ምድራቸው ለመመልስ ተስፋ ሰጠ። ኤርምያስ እስራኤል የምትመለስበትንና አሕዛብ በእግዚአብሔር የሚሸነፉበትን፥ እንዲሁም አይሁድ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በመፈጸም የሚኖሩበትን የመጨረሻ ዘመን አሻግሮ በመመልከት ተናግሯል። አይሁድ እስከ አሁን ድረስ በብዙ መንገድ በእግዚአብሔር ቅጣት ሥር ናቸው። ከአይሁድ ብዙዎች ወደ አገራቸው የተመለሱ ቢሆንም፥ ሌሉች እጅግ ብዙዎች ደግሞ በአሕዛብ መካከል ተበትነው ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንድ ቀን እግዚአብሔር እስራኤልን ዳግም በማነጹ እዛው በአሕዛብና በአይሁድ ላይ ይነግሣል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ኤርምያስ 31፡31-34 አንብብ። በአዲሱ ቃል ኪዳን ውስጥ የተካተቱ ተስፋዎች ምንድን ናቸው? ለ) አዲሱ ቃል ኪዳን ከቀድሞው ቃል ኪዳን የሚለየው እንዴት ነው?  5. ኤርምያስ አዲስ ኪዳን የተመሠረተበትን አዲስ ቃል ኪዳን ያስተዋውቀናል። አዲሱንና የብሉይ ቃል ኪዳንን ብናወዳድር አንዳንድ ዐበይት ልዩነቶችን እንመለከታለን። ብሉይ ቃል ኪዳን የተመሠረተው በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ባለ የጋራ ስምምነት ላይ ነው። ቃል ኪዳኑ የተፈጸመው በስምምነት መልክ ሲሆን፥ እንዲታዘዙት እግዚአብሔር ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ነበር። ለሕጉ በሚሰጡት ምላሽ መሠረት በረከትና መርገም ይከተላቸው ነበር። ይሁን እንጂ አዲስ ኪዳን በስምምነት መልክ አልነበረም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠው ተስፋ ነበር። እግዚአብሔር በሕይወታቸው ውስጥ እንዲሠራ ሕጉ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን፥ በሰዎች ልብ ውስጥ መጻፍ ነበረበት። ይህም ሕጉን የበለጠ እንዲያውቁትና እንዲታዘዙት የሚያደርግ ነው። ነገር ግን አዲሱ ቃል ኪዳን በብዙ መንገድ ሙሉ በሙሉ አዲስ አልነበረም። ሕግን (ኤርምያስ 31፡33) የፓልስጢናን ምድር (ኤርምያስ 32፡36-44) እንዲሁም የዳዊትን ሥርወ-መንግሥት (ኤርምያስ 33፡15-26) ይጨምር ነበር። ይህም ማለት አዲሱ ቃል ኪዳን በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር፥ ቀጥሉም ከዳዊት ጋር ያደረጋቸው የሁለት ቃል ኪዳኖች ቅጥያ ነው ማለት ነው። በቀድሞውና በአዲሱ ቃል ኪዳን መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት፡- በአሮጌው ቃል ኪዳን ውስጥ ከግብ ለማድረስ ፈጽሞ የማይቻለውን ጉዳይ በአዲሱ ቃል ኪዳን ውስጥ ግን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሕግጋት ለመፈጸም መቻሉ ነው። ሁኔታዎቹ ከግቡ የሚደርሱት መንፈስ ቅዱስ ትክክለኞች የሆኑትን የእግዚአብሔር መመዘኛዎች ለመፈጸም የሚያስችል ኃይል ስለሚሰጥ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ክርስቲያን ከሆንክ ጀምሮ ሕይወትህ እንዴት ነው የተለወጠው? ለ) በሕይወትህ እንድትቀደስና የእግዚአብሔርን ሕግ ለመፈጸም እንድትችል መንፈስ ቅዱስ ሊረዳህ በመሥራት ላይ ያለው እንዴት ነው? ትንቢተ ኤርምያስ ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት ትንቢተ ኤርምያስ እንደ ትንቢተ ኢሳይያስ ከአዲስ ኪዳን ጋር በቅርብ

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ፣ ዋና ዋና ትምሕርቶች እና ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት Read More »

የትንቢተ ኤርምያስ መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ታላቅ ክርስቲያን፥ የተዋጣለት ወንጌላዊ ወይም ሰባኪ፥ በአገልግሎቱና በግል ሕይወቱ ሁልጊዜ የሚከናወንለት ይመስልሃልን? መልስህን አብራራ። ለ) ክርስቲያኖች ከሆኑ ሕይወት እጅግ ቀላል እንደሚሆንላቸው፥ እግዚአብሔር ከበሽታ እንደሚጠብቃቸው፥ ሥራ እንደሚያገኙና ሀብታሞች እንደሚሆኑ አድርገው የሚያስቡ የምታውቃቸው ሰዎች አሉን? ይህ ነገር ሁልጊዜ እውን የሚሆን ይመስልሃል? ሐ) በመንፈሳዊ ሕይወቱ የበሰለ ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም ወይም እግዚአብሔርን አይጠራጠርም ብለህ ታስባለህን? መልስህን አብራራ። በብሉይ ኪዳን ውስጥ እጅግ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ ትንቢተ ኤርምያስ ነው፤ ስለዚህ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ዐበይት መጻሕፍት መካከል እንደ አንዱ አድርገው እንደሚቈጥሩት እናምናለን። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በመጽሐፉ ውስጥ ምን እንደሚያስተምር ለማየት ትንቢተ ኤርምያስን ሲያነቡ ወይም ሲያጠኑ አይታዩም። ትንቢተ ኤርምያስ ለብዙዎቻችን የተደበቀ መጽሐፍ ነው። ስለሆነም እግዚአብሔር እንድናውቃቸው የሚፈልጋቸው በርካታ ጠቃሚ እውነቶች መጽሐፉን ባለማጥናታችን ተሰውረውብን ይኖራሉ። በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ የነቢዪ ኤርምያስን ታሪክና የተናገራቸውን ትንቢቶች እናገኛለን። በብሉይ ኪዳን ከሚገኙ ነቢያት ሁሉ ስለ ሕይወቱ፥ ስላ አሳለፈው ትግል፥ ስለ ጥርጣሬውና ስለ ደረሰበት ስደት ይበልጥ በዝርዝር የተናገረ ኤርምያስ ነው። የኤርምያስን ሕይወት በምናጠናበት ጊዜ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ስለሚኖር ታላቅነትና በመንፈሳዊ ሕይወቱ ስለበሰለ ክርስቲያን ምንነት የሚኖሩን በርካታ አሳቦች ፈተና ይገጥማቸዋል። ኤርምያስ በእግዚአብሔር አመለካከት ታላቅ ሰው ነበር፤ ነገር ግን ብዙዎቻችን ኤርምያስ ጽኑ እምነት የሌለውና ታላቅ ሊባል የማይችል ሰው እንደሆነ ልናስብ እንችላለን፡- ታላላቅ ሊባሉ የሚችሉ ወንጌላውያንና ሰባኪዎች፥ ብዙ ነፍሳትን ለጌታ የሚማርኩና ሁልጊዜ ደስተኞች ሆነው እንዲሁም ሰምሮላቸው የሚኖሩ ሰዎች እንደሆኑ የማሰብ ዝንባሌ አለን። ይህ ግን ሁልጊዜ እውነት አይደለም። እግዚአብሔር ታላቅነታችንን የሚለካው ወደ ጌታ ባመጣናቸው በርካታ ሰዎች ምክንያት፥ ወይም ሰዎች በእኛ ደስ በመሰኘታቸው አይደለም። ታላቅነታችን የሚለካው እጅግ አስቸጋሪና አስጨናቂ በሆኑና እግዚአብሔርን ሳይቀር እንድንጠራጠር በሚጋብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ለእግዚአብሔር በሚኖረን ታማኝነት ነው። የኤርምያስን ሕይወት በሚገባ ብንመለከት የሚከተሉትን ነገሮች ለማየት እንችላለን፡- 1. የኤርምያስ የስብከት አገልግሉት በሙሉ ከንቱ ይመስል ነበር። በሚያስተምረው ትምህርት የሚለወጡ ሰዎችን ማግኘት አልቻለም ነበር። ሕዝቡ ከክፋታቸው ተመልሰው በጽድቅ መንገድ ይመላለሱ ዘንድ ሊመራቸው አልቻለም። ይሁን እንጂ ኤርምያስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲናገር የሰጠውን መልእክት በታላቅ ብርታት ይናገር ነበር። መልእክቱ የማስጠንቀቂያና የፍርድ መልእክት ነበር። መልእክቱ ሰዎች ሊሰሙት የማይፈልጉት ዓይነት ቢሆንም እንኳ ኤርምያስ ለሕዝቡ ያመጣውን የእግዚአብሔርን መልእክት በታማኝነት ተናገረ። በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ያሰኘው ይህ ታማኝነቱ ነበር።  2. የኤርምያስ ሕይወት በታላቅ መከራ፥ በስደትና በብቸኝነት የተሞላ ነበር። ኤርምያስ ሚስት ለማግባት የነበረው መብት በእግዚአብሔር ታግዶ ነበር። አብዛኛው የአገልግሎት ዘመኑ ሊያገለግላቸው በሞከረ ሰዎች በኩል በሚነሣበት ስደት የተሞላ ነበር። ይህ ነገር ኤርምያስን ብዙ ጊዜ በእጅጉ ተስፋ ያስቆርጠው ነበር። ስለ ሕዝቡ ኃጢአትና ዓመፅ ያውቅ ስለነበር በሕዝቡ ላይ ስለሚመጣው ጥፋት በማልቀሱ ምክንያት «አልቃሻው ነቢይ» ይባል ነበር (ለምሳሌ፡- ኤርምያስ 13፡17)። ኤርምያስ ብቸኝነት በእጅጉ ስላጠቃው ባይወለድ ይሻለው እንደነበር ሲመኝ እናገኘዋለን (ኤርምያስ 20፡13-18)። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔርን በመጠራጠር ይጠይቀው ነበር። ኤርምያስ ከእግዚአብሔር ዕቅድና ዓላማ ጋር ታግሏል፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ጥሪ ታማኝ ሆኖአል። እንዲሁም ታላቅ ስደትን ስላስከተለበትና ማንም ሰው ስለማይሰማው አገልግሎቱ ከንቱ የሆነ ቢመስልም የእግዚአብሔርን ቃል ተናግሯል። 3. ኤርምያስ በግል የነበረበት ትግል ከእግዚአብሒርና ከሌሎችም ጋር እውነተኛና ግልጽ ነበር። በሰዎች ፊት «ቅዱስ» በመምሰል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያካሂደው የነበረውን ውስጣዊ ትግል ለመሰወር አልሞከረም። ይልቁንም በእግዚአብሔር ፊት ነበር። ታግሎ በሚጐዳበት ጊዜም ለእግዚአብሔር ይናገር ነበር። ያደረገውንም ትግል በመጽሐፉ ውስጥ መዝግቦታል። በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ስላለው ትግል በእግዚአብሔርና በሌሎች ፊት ግልጽ መሆን የታላቅነት እንጂ የደካማነት ምልክት አይደለም። ቅዱስ የመምሰል ግብዝነትን ከማሳየት የመታቀብና ፍጹም ታማኝነትን የማሳየት ምልክት ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ብዙ ጊዜ ስለተዋጣለት የእግዚአብሔር ሰው ካለን አስተሳሰብ የኤርምያስ ሕይወት የሚለየው እንዴት ነው? ለ) አንዳንድ ጊዜ አገልግሎትህ ከንቱ እንደሆነ በማሰብ፥ የእግዚአብሔርን ዕቅድና ዓላማ በጥርጣሬ የጠየቅከበትን መንገድ ግለጽ። ሐ) ከኤርምያስ ሕይወት ስለ መሪነት ምን እንማራለን? የትንቢተ ኤርምያስ ጸሐፊ ትንቢተ ኤርምያስን የጻፈው የኬልቅያስ ልጅ ኤርምያስ ራሱ ነው። ኤርምያስ ያደገው የይሁዳ ዋና ከተማ ከሆነችው ከኢየሩሳሌም 5 ኪሎ ሜትር ያህል ወጣ ብላ በምትገኝ ዓናቶት በተባለች ትንሽ ከተማ ነበር። ወላጆቹ ከካህኑ ከአሮን የዘር ግንድ የመጡ ስለነበሩ ኤርምያስ ካህን ነበር። ኤርምያስ የተወለደው እግዚአብሔርን ይፈሩ ከነበሩ የአይሁድ ነገሥታት የመጨረሻው ኢዮስያስ በተወለደበት ዘመን ገደማ በ650 ዓ.ዓ. ነበር። ኢዮስያስ በይሁዳ ሁሉ የመንፈሳዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ከጀመረ (628 ዓ.ዓ.) ከአንድ ዓመት በኋላ (በ627 ዓ.ዓ.) ኤርምያስ የነቢይነት ጥሪውን ከእግዚአብሔር ተቀበለ። እግዚአብሔር መሪዎችን ወደ አገልግሎት ለመጥራት የሚጠቀምበት ዘዴ አንድ ዓይነት አይደለም፤ ነገር ግን ኤርምያስ ለሕዝቡ የእግዚአብሔር ቃል አቀባይ ሆኖ እንዲያገለግል በእግዚአብሔር መጠራቱን ያውቅ ነበር። ኤርምያስ ነቢይ ለመሆን ብቁ እንዳይደለ ቢሰማውም እንኳ እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን መፍራት እንደሌለበት በመናገር፥ እግዚአብሔር ጥሪውን አረጋገጠለት። መልእክቱም የመልካም ተስፋ ቃል ኪዳን ያዘለ ሳይሆን የጥፋትና የፍርድ መልእክት እንደሆነ አስጠነቀቀው። ሕዝቡም መልእክቱን እንደማይሰሙና ኤርምያስን እንደሚቃወሙት በመንገር አስጠነቀቀው፤ ዳሩ ግን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለሚሆን፥ ሕዝቡ ቢቃወሙትም እንደማያሸንፉት ተስፋ ሰጠው። የውይይት ጥያቄ፥ ኤርምያስ 1 አንብብ። ሀ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሁሉ በኤርምያስ ጥሪ ውስጥ የሚገኙትን ትምህርቶች ማስታወስና መታዘዝ የሚያስፈልጋቸው እንዴት ነው? ለ) ከእግዚአብሔር የተቀበልከው ምን ጥሪ አለህ? እግዚአብሔር በሕይወትህ እንድታከናውነው የሚፈልገው ምንድን ነው? ንጉሥ ኢዮስያስ በይሁዳ ባካሄደው መንፈሳዊ ተሐድሶ ውስጥ የኤርምያስ ድርሻ ምን እንደነበር የምናውቀው ነገር የለም። ኤርምያስ የተቀረጹ ምስሎች ሁሉ እየተደመሰሱ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚካሄድ አምልኮ ሲታደስ በተመለከተ ጊዜ እጅግ እንደተደሰተ መገመት እንችላለን። ከዚያ በኋላ ግን ንጉሥ ኢዮስያስ በጦርነት በተገደለ ጊዜ ኤርምያስ እጅግ እንዳዘነ እንመለከታለን (2ኛ ዜና 35፡25 ተመልከት)። ኤርምያስ ስለ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ መጥፋት የተነበየውና ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ አጥብቆ መለመን የጀመረው ከኢዮስያስ ሞት በኋላ ነበር። ሕዝቡ አሻፈረኝ ብለው ወደ ጣዖት አምልኮ በተመለሱ ጊዜ ከእግዚአብሔር የሚመጣው ጥፋት የማይቀር መሆኑን ኤርምያስ አወቀ። ኤርምያስ ስለ ሕዝቡ እንዲጸልይ እንኳ እግዚአብሔር አልፈቀደም ነበር (ኤርምያስ 7፡16፤ 11፡14)። ኤርምያስ ሕዝቡ ሊጠፉ እንደቀረበ በመናገር መሪዎች እጃቸውን ለባቢሎናውያን እንዲሰጡ መጠየቅ ሲጀምር የተለያየ ጥቃትና ስደት ደረሰበት። የኤርምያስ የቅርብ ወዳጅ፥ መልእክቱን የጻፈለት ጸሐፊው ባሮክ ነበር። የትንቢቱን የመጀመሪያ ቅጅ ንጉሡ አቃጠለው (ኤርምያስ 36፡1-28)። ኤርምያስ ትንቢቶቹን እንደገና ጻፋቸው። ኢየሩሳሌም ከተደመሰሰችና ሕዝቡ ተማርከው ከሄዱ በኋላ እንኳ አይሁድ በይሁዳ እንዲሰፍሩና ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖሩ የሚመክራቸውን ኤርምያስን መስማት እምቢ አሉ። ይልቁንም ኤርምያስን አፍነው ወደ ግብፅ ወሰዱት። የአይሁድ አፈ ታሪክ እንደሚናገረው፥ ኤርምያስን በግብጽ ምድር በድንጋይ ወግረው የገደሉት አይሁድ ናቸው (ዕብራውያን 11፡37)።  የኤርምያስ የነቢይነት አገልግሎት የተጀመረው በ626 ዓ.ዓ. ሲሆን፥ የተጠቃለለው ደግሞ ከ586 ዓ.ዓ. በኋላ ነው። ይህ ማለት ኤርምያስ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለገለው ከ40 ዓመታት በላይ ነው ማለት ነው። የኤርምያስ ሕይወት በሁለት ዐበይት ባሕርያት ሊለይ ይችላል፤ የመጀመሪያው፥ ርኅራኄ ነው። የኤርምያስ መልእክት የጥፋት መልእክት የነበረ ቢሆንም፥ በደረሰበት ስደት ምክንያት መራር አልሆነም ወይም የሕዝቡን ሥቃይና መከራ አይቶ ርኅራኄ አልጐደለውም ነበር። ኤርምያስ አልቃሻው ነቢይ በመባል ይታወቅ እንደነበር ቀደም ሲል ጠቅሰናል፤ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ በመጽሐፉ ውስጥ በአጠቃላይ የሕዝቡን ኃጢአትና የሚደርስባቸውን ጥፋት በሚመለከት ስለ ውስጣዊ ሥቃዩና ኃዘኑ ማንበብ ስለሚቻል ነው። (ለምሳሌ፡- ኤርምያስ 8፡21-9፡1)። እንደ እውነቱ ከሆነ ከኢየሩሳሌም መደምሰስ በኋላ ኤርምያስ የጻፈው ሰቆቃወ ኤርምያስ ለሕዝቡ ያለቀሰው ልቅሶ ወይም ሙሾ የተመዘገበበት ነው። የውይይት ጥያቄ፥ የሚከተሉትን ጥቅሶች በመመልከት ኤርምያስ የተጋፈጣቸውን ችግሮች ዘርዝር፡- ኤርምያስ 16፡1-4፤ 20፡1-3፤ 26፡11-15፤ 28፡10-11፤ 36፡19፥ 26፤ 37፡11-15፤ 38፡5-6። ሁለተኛ፥ ኤርምያስ በጣም ድፍረትና ብርታታ የነበረው ሰው ነበር። ብዙ ጊዜ ተስፋ የቆረጠ ቢሆንም፥ የነቢይነት አገልግሉቱን ግን አቋርጦ አያውቅም። ኤርምያስ ከሌሎቹ ነቢያት ሁሉ የላቀ ስደት የደረሰበት ነቢይ ነበር። በቤተ መቅደስ ተይዞ ለአንድ ምሽት በሰንሰለት ታስሮአል። ስለ ቤተ መቅደሱ መደምሰስ በተናገረ

የትንቢተ ኤርምያስ መግቢያ Read More »