እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ መሆኑ ፀሎትን አላስፈላጊ አያደርገውም ወይ?

እግዚአብሔር የማያውቀውን ነገር ልንነግረው አንችልም፡፡ ስንፀልይ የምንናደርገው ነገር ቢኖር እርሱ አስቀድሞ የሚያውቀውን ነገር በቃላችን መደርደር ነው፡፡

ይህ ጉዳይ እንድንፀልይ የሚያበረታታን እንጂ ፀሎትን አላስፈላጊ የሚያደርገው አይደለም፡፡ ስለ እኛ እና ስላለንበት ሁኔታ በሚገባ ከሚያውቅ ሰው ጋር ያው የሚያውቀውን ጉዳይ ስናወራ እረፍት ይሰማናል፡፡ የእግዚአብሔር ምላሽ በሰጠነው መረጃ ላይ ሳይሆን እርሱ ስለእኛ ሁኔታ በሚያውቀው ፍፁም እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተደላድለን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ በእኛ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ያለፉ፣ የአሁን እና የወደፊት ሁኔታዎቻችንን ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡

ኢየሱስ በማቴ. 6፡8 ላይ እንዳለው አባታችን ሁሉን ያውቃል፡፡ እርሱ ሃሳቦቻችንንና ፍላጎቶቻችንን ያውቃል፡፡ መንገዶቻችንን ጠንቅቆ ይረዳቸዋል (መዝ. 139፡3)፡፡ የልባችንን ጭንቀትና ስቃይ ይረዳል፤ የማያቋርጥ ተስፋ መቁረጥ የሚያደርስብንን የስሜት ጉዳትም ያውቃል፤ በውስጣችን ያሉ ሁለቱ ተቃራኒ ተፈጥሮዎች (አዳማዊው እና አዲሱ ሰው) በነፍሳችን ላይ የሚያደርጉት ጦርነትም ከእርሱ የተሸሸገ አይደለም፡፡

እንዲህ ከሆነ፣ ካሉብን ችግሮችና ተቃውሞዎች እንዴት እና በየትኛው ሰዓት መውጣት እንዳለብን ለማወቅ እግዚአብሔር ላይ የመታመን አስፈላጊነት አይታያችሁም?  ሕይወታችን ሊታነፅ የሚችልበትን የተሻለ መንገድ እኛ ለእግዚአብሔር ልንጠቁም የምንችል ይመስላችኋል? በፍፁም፣ እግዚአብሔርን ምንም ነገር ልናስተምረው አንችልም፡፡ እርሱ ብቻውን እኛን ወደ ክብር የሚያደርሰውን ጎዳና ያውቃል፡፡ ካሉት መንገዶች ሁሉ፣ ለማንነታችንና በእኛ ውስጥ እርሱ ላስቀመጠው ነገር የሚስማማውን ልዩ መንገድ መርጦልናል፡፡  

እግዚአብሔርን እውቀት ልናስገበየው አንችልም፡፡ ልናፈቅረውና ልንደላደልበት ግን እንችላለን፡፡ እርሱ ከኛ የሚጠይቀው ይህንን አንድ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመነሻው የመጨረሻውን ያውቃል፤ ስለዚህ በመካከል በሚፈጠሩ ነገሮች ላይ ሁሉ በእርሱ ልንታመን እንችላለን፡፡

በእግዚአብሔር ላይ ያለኝን መታመን በጨመርኩ መጠን እርሱ ለእኔ ባለው ፍቅር እርግጠኛ እየሆንኩ እሄዳለሁ፡፡ አንዳንዴ ነገሮች ከዚህ አስተሳሰብ ተቃራኒ ቢመስሉም፣ እግዚአብሔር ለእኔ ያለው ሃሳብ በጎና የሚጠቅመኝ ነው፡፡

መዝ. 34፡15 የእግዚአብሔር አይኖች ወደ ፃድቃን፣ ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና፡፡

መዝ. 37፡4-5 በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሀል፡፡ መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፤ በእርሱም ታመን እርሱም ያደርግልሀል፡፡

መዝ. 86፡5 አቤቱ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፣ ምህረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና፡፡

መዝ. 145፡18-19 እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡ ለሚፈሩት ምኞቶቻቸውን ያደርጋል፣ ልመናቸውንም ይሰማል፣ ያድናቸዋልም፡፡

ኤር. 10፡23 አቤቱ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም፡፡

1ዮሐ. 5፡14-15 በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል፡፡ የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ፣ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደተቀበልን እናውቃለን፡፡

እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው። (መዝሙር 73፡23-26)

 

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading