የእግዚአብሔር አባትነት

የእስራኤል ሕዝብ ለአባት የተለየ ክብር አላቸው፡፡ አባት የሚለው ስያሜ ለእስራኤል ሕዝብ ፓትሪያርክ ለነበሩት አብርሃም፣ ይስሃቅና ያዕቆብ ትልቅ ክብር ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል (ሉቃስ 3፡8፤ ዮሐ 8፡39)፡፡ ስለዚህ ስለ ‹‹አባት›› ያልተሳሳተ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡

ሀ) የ ‹‹አባት›› ትርጓሜ

– ‹‹አባት›› ብዙ ጊዜ የአንድ ነገር ምንጭ ወይም ጀማሪ ትርጓሜን ይይዛል፡፡ ያባል በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት – ዘፍ 4፡20 ዮባል በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት – ዘፍ 4፡21

– ‹‹አባት›› ማለት ተፈጥሮዉን ‹‹ለልጆቹ›› የሚያስተላልፍ ማለት ነው፡፡ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ – ኢሳ 64፡8

– ‹‹አባት›› ማለት ስልጣን ያለው ማለት ነው፡፡ – ማር 13፡32

– ምድራዊ ልጆች ሰውነታቸውንና ነፍሳቸው ከወላጆቻቸው ይወስዳሉ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ ‹‹አንድያ ልጅ›› ነው፡፡ የኢየሱስ መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው – ሉቃስ 1፡35፤ ዮሐ 3፡16፤ ቆላ 2፡9

ለ) እግዚአብሔር የሰው ልጆች ሁሉ ‹‹አባት››

– አባታችሁ፣ ፈጣሪያችሁ – ዘዳ 32፡6፤ ሚል 2፡10፤ ዮሐ 1፡18

– የመናፍስት አባት – ዕብ 12፡9

– አባት ለሌላቸው (ድሃ አደግ) አባት – መዝ 68፡5

– እግዚአብሔር አባት ብለን እንድንጠራው ይጠብቅ ነበር – ኤር 3፡19

– የቤተክርስቲያን መሪዎች ክብርን ለመቀበል አባት የሚለውን ስያሜ ሊቀበሉ አይገባቸውም – ማቴ 23፡9

ሐ) እግዚአብሔር የአማኞች ሁሉ አፍቃሪ አባት

– በተጨማሪ ልጅነት የሚለውን ክፍል ይመልከቱ – ክፍል ሠ8

– ከቅድስና ባሕሪው እንካፈል ዘንድ – ዘሌ 20፡8፤ 1ጴጥ 1፡2

– የአማኞች ሁሉ አባት – ሮሜ 4፡11

– ኢየሱስ እግዚአብሔር ‹‹አባታችን›› ብሎ ጠርቷል

– ወደ አባቴና አባታችሁ እመለሳለሁ –

– በሰማይ ያለው አባታችሁ –

– በሰማይ ያለው አባታችሁ መልካም ስጦታን ይሰጣችኋል –

– የማያዳላ አባት –

– በሰማይ ያለ አባታችን –

– ሐዋሪያት አባታችን እያሉ ጠርተውታል

– ‹‹አባ፣ አባት›› ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ – ሮሜ 8፡15፤ ገላ 4፡6

– የአብ ታላቅ ፍቅር – እኛ፣ የእግዚአብሔር ልጆች – 1ዮሐ 3፡1

– ሕብረታችን ከአብ ጋር ነው – 1ዮሐ 1፡3

ሰ) እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት፣ ኢየሱስ አንድያ ልጅ

– ኢየሱስ የሰማይ አባቱን በትክክል ይወክላል – ፊል 2፡5-6፤ ዕብ 1፡3

– መሲህ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ‹‹የዘላለም አባት›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ኢሳ 9፡6

– አብ ለኢየሱስ ሲናገር፡- እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ይላል – መዝ 2፡7፤ ዕብ 1፡5

– አብ ልጁን የአለም አዳኝ አድርጎ ላከው – 1ዮሐ 4፡14

– ኢየሱስ ስለ አባቱ የተናገረው

አባ፣ አባት – ማር 14፡36

አባት ሆይ ፈቃድህ ቢሆን – ሉቃስ 22፡42

አባት ሆይ ይቅር በላቸው – ሉቃስ 23፡34

– እናንት የአባቴ ብሩካን – ማቴ 25፡34

– ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም – ማቴ 11፡27

– እኔና አብ አንድ ነን – ዮሐ 10፡30

– አባት ልጁን ይወዳል – ዮሐ 3፡35

ሸ) እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን እንደመሆኑ መጠን ከእኛ ጋር በብዙ ነገር ተዛምዷል

– ያፈቅረናል – 2ተሰ 2፡16፤ ዮሐ 16፡27

– ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ይሞትልን ዘንድ ልኮልናል (ምህረት) – ገላ 1፡4

– ኢየሱስ ከሙታን መካከል አስነስቶታል (ሕይወትን ሊሰጠን) – ገላ 1፡1

– ይቀጣናል፣ ያርመንማል – ዕብ 12፡5-7፤ ራዕ 3፡19

– በመንፈሳዊ በረከት ይባርከናል – ኤፌ 1፡3

– የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከእርሱ ዘንድ ይመጣል – ሐዋ 2፡33

– እርሱ ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉም የሚኖር ነው – ኤፌ 4፡6

– ክብርን ሁሉ ሊቀበል ይገባዋል – ፊሊ 4፡20፤ ራዕ 7፡12

Leave a Reply

%d bloggers like this: