የሰው አፈጣጠር

ሀ) የሰው አፈጣጠር

– በእግዚአብሔር አብ – ዘፍ 1፡27፤ ኢሳ 45፡11-12

– በኢየሱስ ክርስቶስ – ዮሐ 1፡1-5፤ ቆላ 1፡13-16

– በመንፈስ ቅዱስ – ኢዮብ 33፡4

– በስድስተኛው ቀን – ዘፍ 1፡26-27

– በሌላ ቦታ ሳይሆን፣ በምድር ላይ – ዘዳ 4፡32፤ መዝ 104፡30፡ኢሳ 45፡12

– አካሉ ከምድር አፈር – 2፡7፤ ኢዮብ 33፡6

– መንፈሱ ደግሞ ከእግዚአብሔር እስትንፋስ – ዘፍ 2፡7፤ መክ 12፡7

– ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው – ዘፍ 1፤ 27፤ 5፡1-2

– ሴት የወንድ የበታች አይደለችም፤ በዘፍ 2፡20 ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ‹‹ረዳት›› የሚለው ቃል በ መዝ 33፡20 ላይ የእግዚአብሔርን ማንነት ለመግለፅ ጥቅም ላይ ከዋለው ‹‹ረዳት›› የሚለው ቃል ጋር አንድ ነው፡፡

– እጅግ መልካም ነበር – ዘፍ 1፡31፤ መዝ 139፡14

– ከነፃ ፈቃድ ጋር ተፈጠረ – ዘፍ 2፡16፣ 17፤ ኢያሱ 24፡15

ለ) ሰው ምድራዊና መንፈሳዊ ነው

– ሰው ከምድር ጋር የሚያዛምደው አካል አለው – ዘፍ 2፤ 7፤ መክ 12፡7

– ሰው መንፈሳዊ ማንነትም አለው፣ የእግዚአብሔር የእስትንፋሱ ሕይወት – ዘፍ 2፤ 7፤ መክ 12፡7

– ‹‹ነፍስ›› ተብሎ ተጠርቷል – ማቴ 10፡28

– ‹‹መንፈስ›› ተብሎ ተጠርቷል – ሐዋ 7፡59

– ‹‹መንፈስ›› እና ‹‹ነፍስ›› እና ‹‹ሥጋ›› ተብሎ ተጠርቷል – 1ተሰ 5፤ 23

– የማይሞተው (መንፈሳዊ) አካሉ በሥጋ ውስጥ ይኖራል – 2ቆሮ 5፡6፣ 8

– መንፈስ ሲለይ አካላዊ ሞት ይሆናል – ያዕ 2፡26

– መንፈስ ሲመለስ ደግሞ አካል ሕያው ይሆናል – ሉቃስ 8፡55

– ከአካላዊ ሞት በኋላ መንፈስ ሕያው ሆኖ ይቀጥላል – ማቴ 22፡32

– በነፍስ በመንፈስ መካከል ልዩነት ለመፍጠር አዳጋች ነው

– አንድ እንደሆነ ያህል ጥቅም ላይ ውሎ እናገኛለን – 1ሳሙ 1፡15፤ ኢዮብ 7፡11፤ ኢሳ 26፡9

– የእግዚአብሔር ቃል በሁለቱ መካከል እንደሚለይ ተፅፏል – ዕብ 4፡12

– የነፍሳችን መዳን ድነት ይባላል – 1ጴጥ 1፡8-9፤ ያዕ 1፡21፤ ዕብ 10፡39

– አለበለዚያ ነፍሳችን ትጠፋለች – ማቴ 10፡28፤ ሐዋ 3፡22-23

– መንፈሳችን ወደሰራት ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለች – መክ 12፡7

– አካላችንን መመልከት ይቻላል፡፡ ነፍስና መንፈሳችን ግን አይታዩም፡፡ መንፈሳችን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን ሕይወት ነው፡፡ ነፍሳችን ስብዕናችንና ባሕሪያችን ነው – ማንነታችንና የምንሆነው።

ሐ) ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ

– ሰው በእግዚአብሔር መልክ (አምሳል) ተፈጠረ – ዘፍ 1፡26-27፤ 5፡1-2

– ስለዚህ የሰውን ነፍስ ማጥፋትና እርግማን አልተፈቀደለትም – ዘፍ 9፡6፤ ያዕ 3፡9-10

– ወንድና ሴት ሁለቱም በእግዚአብሔር መልክ (አምሳል) ተፈጠሩ – ዘፍ 1፡27፤ 5፡2

– መመሳሰላችን አካላዊ አይደለም – እግዚአብሔር መንፈስ ነውና – ዮሐ 4፡24

– መመሳሰላችን በጽድቅ፣ ቅድስናና እውነት ነው – ኤፌ 4፡21-24

– መመሳሰላችን በሥነ ምግባራዊ እውቀት ነው – ቆላ 3፤ 10

– መመሳሰላችን በመምራት (በምድር ላይ) ስልጣን ነው – ዘፍ 1፡26

መ) የጠፋውና የታደሰው የሰው የእግዚአብሔር አምሳል

– ከሰው ልጅ ውድቀት (አመጽ) በኃላ

– ልጆች በኃጢአተኛ ወላጆቻቸው አምሳል መወለድ ጀመሩ – ዘፍ 5፡3

– የኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምድር መምጣት

– በሰው አምሳል – ሮሜ 8፡3፤ ፊል 2፡7-8

– በፍፁም እግዚአብሔር አምሳል – 2ቆሮ 4፡4፤ ቆላ 1፡15፤ ዕብ 1፡3-4

– ሰዎች በኢየሱስ ከተዋጁ በኃላ

– የኢየሱስን መልክ እንድንመስል ታድሰናል – ቆላ 3፡10

– የኢየሱስን መልክ እንድንመስል አስቀድመን ተወስነናል – ሮሜ 8፡29

– በትንሳኤው ወቅት

– አማኞች የእሱን መልክ ይመስላሉ – መዝ 17፡15፤ 1ቆሮ 15፡49

– ሀጥአን የተናቀ መልክ ይኖራቸዋል – መዝ 73፡20

ሠ) የሰው ዘር ሁሉ መነሻው አንድ ነው

– የሰው ዘር ሁሉ ከአንድ ወገን ተፈጠረ – ሐዋ 17፡26-29

– አንዲት ሴት የሕያዋን ሁሉ የመጀመሪያ እናት ናት – ዘፍ 3፡20

– ከጥፋት ውኃ በኋላ የሰው ዘር ከኖህ ዘር መጣ – ዘፍ 9፡18-19

ረ) ሰው በምድር ላይ ያለው ስልጣን

– በምድር ላይ ካሉ ፍጥረታት ሁሉ የበላይ ነው – ማቴ 6፡26፤ 12፡12

– ፍጥረታትን ይገዛል – ዘፍ 1፡28፤ መዝ 8፡1-9

– ተክሎችን ለምግብነት ይጠቀማል – ዘፍ 1፡29

– እንስሳትን ለምግብነት ይጠቀማል – ዘፍ 9፡1-3

– የተቤዠ ሰው በአለምና በመላእክት ላይ ይፈርዳል – 1ቆሮ 6፡2-3

Leave a Reply

%d bloggers like this: