የሕይወት እንጀራ

ያልተዋጁ፣ የወደቁ ሰዎች ሁኔታ

ሀ) በእግዚአብሔር ላይ የሰው ልጅ አመጽ – በተጨማሪ ኀጢአት የሚለውን ርዕስ (ክፍል መ1) ይመልከቱ

– የሰው ልጅ አለመታዘዝ፣ ውድቀትና እርግማን – ዘፍ 3፡1-24

– ኀጢአትና ሞት በአዳም በኩል ገባ – ሮሜ 5፡12፤ 1ቆሮ 15፡21-22

– ሁሉ በደለኛ ነው – ሮሜ 3፡23፤ ዘፍ 6፡5፤ 1ነገ 8፡46፤ መዝ 14፡2-3፤ ኢሳ 53፡6፤ 64፡5-7

– ሁሉም መዳን አለባቸው – 1ጢሞ 2፡4፤ ሮሜ 3፤ 23፤ ገላ 3፡22፤ 1ዮሐ 1፡8፤ 5፡19

ለ) ሰው በእግዚአብሔር ቁጣ ስር ወድቋል

ኀጢአትና ሕግ የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል መ2

– የእግዚአብሔርን ሕግ የማይታዘዝ ሁሉ ርጉም ነው – ዘዳ 27፡26

– የሕግ ትዕዛዝ ለሁሉ የተገለጠ ነው – ሮሜ 2፡13-15

– የሕግን ትዕዛዝ ሊጠብቅ የሚችል የለም – ሮሜ 3፡20፤ ገላ 2፡21

– የእግዚአብሔር ቁጣ

– በማያምኑ ላይ – ዮሐ 3፡36

– በፍርድ ቀን – ሮሜ 2፡8

– በማይታዘዙ ላይ – ኤፌ 5፡6፤ ቆላ 3፡6

– ፈሪሃ እግዚአብሔር በሌላቸው ላይ – ሮሜ 1፡18

– የ 666 ምልክትን በተቀበሉ ላይ – ራዕ 14፡9-11

– የዳኑ ከእግዚአብሔር ቁጣ አምልጠዋል – 1ተሰ 5፡9

ሐ) ሰውና ስራ

– ስራ ሃብትና ክብርን ያመጣል – ምሳሌ 10፡4፤ 14፡23፤ 22፡29

– ስንፍና ለድህነት በር ይከፍታል – ምሳሌ 10፡4፤ 14፡23

– በትጋት መስራት በብርቱ ይመከራል – ምሳሌ 13፡4፤ 2ጢሞ 2፡6

– ከውድቀት በፊት

– አዳም ፍጥረትን ይገዛ ነበር – ዘፍ 1፡28

– ኤደን ገነትን ያበጃትና ይጠብቃት ነበር – ዘፍ 2፡15

– ከውድቀት በኋላ

– ስራ መስራት አስቸጋሪ ሆነ – ዘፍ 3፡19፤ 5፡29

– እግዚአብሔርና ኢየሱስ ስራቸውን ይሰራሉ ይፈፅማሉም – የሐ 5፡17፤ 17፡4

– ከድነት በኃላ

– በእጅ መስራት – 1ተሰ 4፡11፤ 2ተሰ 3፡10-12

– የአገልግሎት ሥራ – ኤፌ 4፡12፤ 1ጢሞ 3፡1

– የሚሰሙ፣ ሳያዩ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው – ያዕ 1፡25

– እንደ ሥራችን መጠን እንሸለማለን – 1ጴጥ 1፡17፤ ራዕ 22፡12፤ 1ቆሮ 3፡13-15

– ሥራ ይጠበቅብናል፣ ማረፍ ይጠበቅብናል

– ሕግ ከመሰጠቱ በፊት – ዘፍ 2፡2-3

– ሕግ ከተሰጠ በኃላ – ዘጸ 20፡9-11

መ) ያልተዋጀ ሰው አካላዊና ማሕበራዊ ሁኔታ (በዘፍጥረት መጽሐፍ መነጽር)

– ሃፍረትና በደለኛነት – ዘፍ 3፡7

– በእግዚአብሔር ፊት ፍርሃት – ዘፍ 3፡8፣ 10

– የተበጠሰ ግንኙነት – ዘፍ 3፡12

– የድነት ተስፋ መሰጠት – ዘፍ 3፡15

– ሕመምና ሥራ – ዘፍ 3፡16-19

– የደም መስዋዕት – ዘፍ 3፤ 21፤ 4፡4-5

– በረከት ማጣት – ዘፍ 3፡23-24

– ቁጣና ነፍስ ገዳይነት – ዘፍ 4፡6-8፤ 4፡23-24

– ከእግዚአብሔር መለየት – ዘፍ 4፡14

– በእርጅና መሞት – ዘፍ 5፡5

– አጋንንታዊ ሥራዎች – ዘፍ 6፡1-4

– ክፋትና ግፍ – ዘፍ 6፡5፣ 11

– እግዚአብሔር ኀጢአትን ይቀጣል – ዘፍ 6፡5-7

– ምህረትና ጸጋ – ዘፍ 6፡8-9

– ሥጋ በምግብነት – ዘፍ 9፡3

– የሕዝቦች መከፋፈል – ዘር 11፡1-9

– የተስፋ መሰጠት – ዘፍ 12፡1-3

– ድርቅና በሽታ – ዘፍ 12፡10፣ 17

– ጦርነት – ዘፍ 14፡1-4

– የጸሎት ሃይል – ዘፍ 18፡16-33

– የወሲብ ኢ-ሞራላዊነት – ዘፍ 19፡4-5፣ 33

– የእግዚአብሔር ቅጣት – ዘፍ 19፡24-29

ሠ) የወደቀም እንኳ ቢሆን የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ትልቅ ዋጋ አለው

– ከወፎች ወይም በጎች የበለጠ ዋጋ አለው – መቴ 6፡26፣ 12፡12፣ ሉቃስ 12፡24

– ለመዋጀቱ የተከፈለለት ዋጋ ይህንን ይበልጥ ያሳያል – ዮሐ 3፡16፤ 1ጴጥ 1፡18-19

– የእግዚአብሔር ክብር ተካፋይ ይሆን ዘንድ ተዋጀ – ዕብ 2፡10፤ 2ተሰ 1፡11፣ 12

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading