ሀ) የሕግ፣ የተወሰነ ጊዜ አገልግሎት
– ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ እስኪፈጽም ድረስ ይኖራል – ማቴ 5፡18
– ክርስቶስ ኢየሱስ ሕግን ፈፅሟል – ማቴ 5፡17-18፤ ሉቃስ 24፡44
– በመንፈስ በምንመላለስ በእኛ – ሮሜ 8፡3-5
– ፍቅር ሕግን ይፈጽማል – ሮሜ 13፡8-10፤ ገላ 5፡14፤ ያዕ 2፡8
– አንዱ የሌላውን ሸክም በመሸከም ሕግ ይፈጸማል – ገላ 6፡2
ለ) ድነት በተስፋ (ጸጋና እምነት)
– ሕግ ከመስጠቱ በፊት – በአብርሃም ውስጥ –
– አብርሃም ሕግ እንደፈጸም ሆኖ ተቆጠረለት –
– ሕግ ከተሰጠ በኃላ – በኢየሱስ ውስጥ –
– ሕግ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ይሰራ ነበር – ሉቃስ 16፡16
– ከመጥመቁ ዮሐንስ በኃላ ወንጌል ተሰበከ – ሉቃስ 16፡16
ሐ) የሕጉ ይዘት
– የብሉይ ኪዳን ይዘት
– አስርቱ ትዕዛዛት – ዘጸ 20፡3-17፤ ዘዳ 5፡7-21
– የሌዋዊያን ሕጎች – ዘጸ፤ ዘሌ፤ ዘዳ
– በአዲስ ኪዳን ያለው የሕግ መረዳት
– ታላቂቱ ትዕዛዝ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድ ነው – ማቴ 22፡36-40፤ ሉቃስ 10፡26-27
– ቀጣዩ ታላቅ ትዕዛዝ ደግሞ ሌሎችን እንደራስ አድርጎ መውደድ ነው – ማቴ 22፡39፤ ሉቃስ 10፡27
– የሕግ ዋነኞች – ፍትሕ፣ ምሕረት፣ ታማኝነት – ማቴ 23፡23
– ኢየሱስ ከሕግ በላይ ነው – ዮሐ 8፡5-9፤ ማቴ 12፡8
መ) የሕግ አላማ
– ለኀጢአተኞች ተሰጠ – 1ጢሞ 1፡9
– ሕግ ለተዋጁ ሳይሆን ፈሪሃ እግዚአብሔር ለሌላቸው ተሰጠ – ሮሜ 4፡15
– ሕግ ፊሪሃ እግዚአብሔር በሌላቸው ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ ይገልጣል – ገላ 3፡19
– ሕግ በሰው አምሳል ተገልጧል – ገላ 3፡23
– እምነት ሲመጣ ከሕግ ነፃ ወጥተናል – ገላ 3፡23
– በእግዚአብሔር መንፈስ ከኀጢአት እስራት ነፃ ወጥተናል – ገላ 5፡13-18
– ሕጉ ወደ ፊት ሊመጡ ላሉት ጥላ ነው – ዕብ 10፡1
– የኀጢአት ግንዛቤ (እውቀት) እንዲኖረን ያደርጋል – ሮሜ 3፤ 20፤ 7፡7
– ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ ሞግዚታችን ነው – ገላ 3፡23-29
ረ) የሕጉ ውጤቶች
– ለኀጢአት ኀይል ሰጠው – 1ቆሮ 15፡56
– ያለሕግ ኀጢአት አይቆጠርብንም – ሮሜ 5፡13
– ሰዎች ሕግን መጠበቅ አልቻሉም –
– ፍፁም መታዘዝን ይጠይቃል – ዘዳ 27፡26፤ ገላ 3፡10-11፤ ያዕ 2፡10
– ማንም ሙሉ በሙሉ ሕግን ሊታዘዝ አይችልም – ሮሜ 3፡10
– እስራኤላውያን ሕግን መጠበቅ አልቻሉም – ኢሳ 42፡24፤ ኤር 9፡13፤ ዳን 9፡11
– ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ ሊጸድቁ ይገባል – ሮሜ 3፡19-24
– ከሰው ኀጢአተኝነት የተነሳ ሕግ ሊያድን አልቻለም – ሮሜ 8፡3
– ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ አልቻለም – ዕብ 7፡19፤ ገላ 2፡16
– ለእግዚአብሔር ለመኖር በሕግ በኩል ለሕግ ሞተናል – ገላ 2፡19-21
ሠ) ክርስቶስ ኢየሱስ የሕግ ፍፃሜ ነው
– ሕጉ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ በስራ ላይ ነበር – ሉቃስ 16፡16
– ከመጥምቁ በኃላ ግን ወንጌል መሰበክ ተጀመረ – ሉቃስ 16፡16
– ቤተ ክርስቲያን የሙሴን ሕግ የመጠበቅ ግዴታ የለባትም – ሐዋ 15፡5-12፤ ሮሜ 6፡14
– ይህ ግን የኀጢአት ፈቃድ አይደለም – ሮሜ 6፡15
– ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት ጸድቀናል – ሮሜ 3፤ 28
– ክርስቶስ የሕግን ፍላጎት ፈጽሟል – ማቴ 5፡17
– ክርስቶስ በሞት ሕግን ሻረ – ኤፌ 2፡15-17፤ ሮሜ 10፡3-4
– ክርስቶስ ከሕግ እርግማን ነፃ አወጣን – ገላ 3፡13
ሸ) ከእግዚአብሔር ጋር አዲስ ኪዳን
– አዲሱ ኪዳን (ጸጋና እምነት) የሕጉን ፍላጎት በልባችን ይፈጽማል – ዕብ 8፡10-13፤ 10፡16-17
– ወንጌል የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ረ3