የመጽሐፍ ቅዱስ ውድድር መመሪያ

ጠቃሚ መረጃዎች፡

 • ማንኛውም ሰው በጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል።
 • የውድድሩ ዋነኛ ግብ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ለመጥናት አንዳችን ሌላችንን ማበረታታት ቢሆንም በውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው አንድ ግለሰብ ከአዘጋጁ የተዘጋጀለትን ሽልማት ይቀበላል።
 • ውድድሩ እንደ ተሳታፊዎቹ ጥንካሬ 4 ሳምንትና ከዛ በላይ ሊፈጅ ይችላል።
 • ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ ዘግይተው የሚቀላቀሉ ተሳታፊዎች በውድድሩ መሳተፍ ያሚችሉ ቢሆንም ያለፋቸው የውድድሩ ክፍል ውጤት ከቀሪው ክፍል ጋር አይደምርላቸውም። ይህም ውጤታቸውን አነስተኛ እንዲሆን ያደርገዋል። ስለዚህ ውድድሩን አለማቋረጥም ሆነ በተሰጠው የጊዜ ገዳብ ስርቶ መመልስ ለአሸናፊነት ከሚያበቁ ነገሮች መካከል መሆናቸው የታወቀ ይሁን።
 • እያንዳንዱን ጥያቄና መልስ ሰርቶ ለመላክ ቢያንስ የአንድ ሳምንት ጊዜ ይኖራል። የጊዜ ገደቡ ከጥያቄው መለቀቅ ጋር ተያይዞ የሚገለጽ ይሆናል።
 • ጥያቄዎቹን ሰርተው ከላኩ በኋላ በድግሚ ሰርቶ መላክ ቢቻልም ለውድድሩ የሚያዘው ውጤት ግን በመጀመሪያ የተላከው ብቻ ይሆናል።
 • አንድ ግለሰብ በተለያዩ የኢ-ሜይል አድራሻዎች በመጠቀም በአንድ ውድድር ላይ መሳተፍ አይችልም።
 • በውድድሩ ላይ የሚኖርዎትን ማንኛውንም ጥያቄ በሚከተለው የ ኢ-ሜይል አድራሻ ቢልኩልን በተቻልን ፍጥነት ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል፣ tsegaewnet@gmail.com
 • የውድድሩን ጥያቄዎች በ ፌስ ቡክ ፔጅ (https://www.facebook.com/tesegaewnet/) ወይም በቫይበር ግሩፑ ስር ወይም በዚሁ ዌብ ሳይት ላይ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን (ይህን ሊንክ ይጫኑ) ሊያገኙ ይችላሉ።
 • ጥያቄዎቹ ሲለቀቁ እንዳያመልጥዎ ወይም ዘግይቶ እንዳይደርስዎ ይረዳዎ ዘንድ የሚከተለው ድረ-ገጽ (website) (https://ethiopiansite.com/) ላይ በመሄድ እና የኢ-ሜይል አድራሻዎን ከድረ-ገጹ የፊት ገጽ ግርጌ ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ሳጥን ውስጥ በማስገባትና “ድረ-ገጹን ይከታተሉ” የሚለውን ሰማያዊ ቁልፍ በመጫን የድረ-ገጹ ተከታታይ (follower) እንዲሆኑ በአክብሮት እጋብዛለሁ። ይህን ሲያደርጉ፣ የውድድር ጥያቄዎቹና ሌሎች አዳዲስ ጽሁፎች በድረ-ገጹ ላይ በሚለቀቁበት ጊዜ ሁሉ በኢ-ሜል አድራሻዎ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል።
 • ከመጀመሪያው ዙር በተለየ ሁኔታ በዚህ ውድድር ላይ በመጨረሻ ላይ ከሚገለጸው አሸናፊ ስም በቀር የማንም ተወዳዳሪ ስም በይፋ አይገለጽም። የተሳታፊዎች ስምም ሆነ የ ኢ-ሜይል አድራሻ በሚስጥር የሚጠበቅ ይሆናል። ስለዚህ በጥያቄና መልሱ ላይ ትክክለኛ ስምዎን መግለጽ ካልፈለጉ የብእር ስምዎን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ነገር ግን አንዴ ይህን ስም መጠቀም ከጀመሩ በኋላ መቀየር አይፈቀድም። የኢ-ሜይል አድራሻዎ ግን ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ።

መልካም የውድድርና ቃሉን የማጥናት ጊዜ ይሁንልን።
አዳነው ዲሮ ዳባ
የውድድሩ አዘጋጅ

1 thought on “የመጽሐፍ ቅዱስ ውድድር መመሪያ”

Leave a Reply

%d