እግዚአብሔርን ማወቅ

እግዚአብሔር እርሱን በማወቅ እንድናድግ ይሻል፡፡ ከተወለድኩበት ወቅት አንስቶ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አስከተቀበልኩበት ድረስ ባሉት ጊዜያቶች አእምሮዬ አለማዊ በሆኑ አስተሳሰቦችና ልማዶች ተሞልቷል፡፡ እነዚህን እውቀቶቼን፣ ዝንባሌዎቼን፣ እምነቶቼን፣ ስሌቶቼንና ልማዶቼን ቀስ በቀስ እርሱን በማወቅ እውቀት በመተካት፣ ሕይወትን ከእርሱ አቅጣጫ እንድመለከታት ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔራዊ እይታ በእኛ ውስጥ እግዚአብሔራዊ ባሕሪን ይሠራል / A godly perspective produces godly behavior. እግዚአብሔር የውስጥ አስተሳሰቤን እንዲለውጥ ሳልፈቅድለት ከውጭ የሚታዩ ባሕሪዎቼን ለመቀየር በማደርገው ጥረት ደስተኛ አይሆንም፡፡  

ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ ሕብረት እንዲያድግ የምሻ ከሆነ፣ ልክ የትዳር ሕብረትን ለመንከባከብ የሚደረገውን አይነት ጥረት ማድረግና፣ እግዚአብሔርን ከልብ በመፈለግ በደንብ የታሰቡ ምርጫዎችን (conscious choices) መውሰድ ይጠበቅብኛል፡፡

እግዚአብሔር እኔን እና በእኔ ያለመከልከል እንዲሰራ ለእርሱ ግልፅ እና እውነተኛ መሆን ይገባኛል፣ በተጨማሪም ከእርሱ ለመማር ያለኝን ዝንባሌ ላሳየው ይገባል፡፡ ስለ እኔ በቂ እውቀት ያለው እርሱ ብቻ ስለሆነ፣ የእኔ ድርሻ በአስተሳሰቤ ላይ ተገቢውን ለውጥ እንዲያደርግ ፈቃዴን መስጠት ነው፡፡ የወደደውን እንዲያደርግ ስፈቅድለት እኔን የእርሱ ባሕሪ መገለጫ በሆነው በኢየሱስ መልክ ማበጀት ይጀምራል፡፡

እግዚአብሔር፣ ስለእርሱ ብቻ ከማወቅ ተራ ልምምድ ወጥቼ ራሱን በቅርበት እንዳውቀው ይሻል፡፡ ስለ እርሱ ሳይሆን እርሱን እንዳውቀው ይሻል።

«እግዚአብሔራዊ ባሕሪይ፣ የውስጣዊ ለውጥ ተፈጥሮአዊ ውጤት ነው።»

እርሱን በማወቅ ለማደግ ምን ያስፈልገኛል?

  1. አወንታዊ ዝንባሌ (POSITIVE ATTITUDE) ይጠበቅብኛል፡፡

ሀ. እግዚአብሔር ስለ እርሱ ባለኝ እውቀት እንዳድግ እና የልቡን መሻት እንድገነዘብ ይፈልጋል፡፡

ኤር. 9፡23-24 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ ነገር ግን የሚመካ፡- ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፣ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና ይላል እግዚብሔር፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ዮሐ. 17፡3

ሮሜ. 8፡29

ሮሜ. 12፡2

ለ. የነቃ ሕብረት ማድረግ ይጠበቅብኛል፡፡

መዝ. 63፡1 (አ.መ.ት.) እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቆተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማችሥጋዬም አንተን ናፈቀች፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ምሳሌ 2፡1-5

ማቴ. 7፡7-8

1ጴጥ. 2፡2-3

  1. የእግዚአብሔር ቃል ያስፈልገኛል።

የእውነት ምንጭ እኔ ወይም ሌላ ሰው አይደለም፡፡ የእውነት ምንጭ ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹የምደርስባቸው እውነቶች›› ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል አንፃር (በመጽሐፍ ቅዱስ) መፈተሽና መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ. እግዚአብሔር እኔን ከሚለውጥበት መሳሪያ አንዱ ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ የታመነ ነው፡፡

2ጢሞ. 3፡16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 119፡89

1ጴጥ. 1፡25

ማቴ. 24፡35

ዮሐ. 14፡6

ዮሐ. 17፡17

ሮሜ. 15፡4

ኤፌ. 4፡21

2ጢሞ. 3፡16-17

1ዮሐ. 5፡6

ለ. የእግዚአብሔር ቃል፣ በየዕለቱ እንደ ምመገበው ምግብ አስፈላጊዬ ሊሆን ይገባል፡፡

ኢዮብ 23፡12 ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣ የአንደበቱን ቃል ከእለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ፡፡ (አ.መ.ት.)

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ዘዳ. 6፡5-9

ኢዮብ 23፡12

መዝ. 119፡16

መዝ. 119፡103

ማቴ. 4፡4

ሐ. ለማደግ ቃሉን ማስታወስና ማሰላሰል ያስፈልገኛል፡፡

መዝ. 1፡1-3 ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፣ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፣ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 119፡11

መዝ. 119፡97

መዝ. 145፡5

ምሳሌ 22፡17-18

ቆላ. 3፡16

የእግዚአብሔርን ቃል ለማስታወስ የሚረዱ ዘዴዎች፡

ወደመስሪያ ቤትዎ፣ ወደ ትምሕርት ቤትዎ፣ ወይም ገበያ፣ ወዘተ፣ ሲሄዱ አንድ ጥቅስ ለማስታወስ እየሞከሩ ይሂዱ። አልያም ካርድ ላይ ጥቅስ በመፃፍ በግልፅ የሚታይ ቦታ ላይ ይለጥፉ፣ ከዛም ቀኑን በሙሉ ጥቅሱን ያሰላስሉ፡፡

መ. የእግዚአብሔር ቃል በሕይወቴ ውስጥ እንደሚያበራ መብራት ነው፡፡ የልቤን ምስጢሮች ይገልጣል፤ እግዚአብሔር በሚያየኝ መንገድ ራሴን እንዳይ ይረዳኛል፡፡

መዝ. 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርኃን ነው፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 119፡105

መዝ. 119፡130

ሮሜ. 10፡17

ዕብ. 4፡12-13

ሠ. እግዚአብሔር ራሱ የቃሉን መገለጥ ይሰጣል፡፡ ምንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ የቃሉን ክፍሎች ለመረዳት ቢከብደኝም፣ ለእርሱ ታማኝና ግልፅ በሆንኩ መጠን በሚያስፈልገኝ ደረጃ ቃሉን ይገልፅልኛል፡፡

ዘዳ. 29፡29 ምስጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ሉቃስ 24፡45

1ቆሮ. 2፡12-14

2ጴጥ. 3፡15-16

  1. ፀሎት – ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ያስፈልገኛል።

ፀሎት አፅናፈ አለሙን (the universe) ከፈጠረና ከሚቆጣጠር፣ እንዲህ ታላቅ ሆኖ ሳለ ደግሞ ዝርዝርና ትናንሽ በሆኑ የሕይወታችን ክፍሎች ውስጥ ሳይቀር ድርሻ እንዲኖረው ከሚሻ የፍቅር አምላክ ጋር የምናደርገው ጥልቅ ውይይት እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡

እግዚአብሔርን መቅረብም ሆነ ማነጋገር የምችለው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ በኩል መሆኑን ዘወትር በማስታወስ፣ ወደ እርሱ ስቀርብ በታላቅ አክብሮት ሊሆን ይገባል፡፡ የትኛውም መልካም ስራዬ እግዚአብሔር ፊት እንደማያቀርበኝ መረዳት ይኖርብኛል፡፡ የሁሉ ፈጣሪ ወደ ሆነው አምላክ በፀሎት መቅረብን እንደ ታላቅ እድል መቁጠር ይኖርብኛል፡፡

በየትኛውም ውይይት ላይ እንደ ተለመደው፣ መስማት የውይይት ትልቁ ክፍል ነው፡፡ እግዚአብሔር በልቤ ሲናገር ወይም አንድ አዲስ ነገር ሲገልጥልኝ በማሰላሰልና በማድመጥ ጊዜውን መጠቀም ይኖርብኛል፡፡ ዘወትር ከእርሱ አንዳች ነገር እንደ ምንጠብቅ ሆነን (with expectation) እንድንኖር ይወዳል፡፡

እግዚአብሔር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች (priorities) በመፈለግና ሲገልጥልንም በመቀበል መኖር፣ ለእግዚአብሔር ያለንን ክብርና የሚገባውን ትክክለኛ ስፍራ መስጠታችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ትራፊውን ጊዜያችንን፣ ትራፊውን ጉልበታችንን እና ትራፊ የሆነውን ነገራችንን ከመስጠት ልምምድ ወጥተን ምርጥ የምንለውን ነገራችንን ለእርሱ የማቅረብ ልምምድ ውስጥ በመግባት ለእርሱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር እንድናሳየው ይጠብቅብናል፡፡

ሀ. ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ የውይይት (የፀሎት) ጊዜ መጠን- በሚኖረኝ የልብ ዝግጅት፣ ቅድሚያ ስለ ምሰጣቸው ነገሮች ባለኝ እውነተኛ ግምገማ (assessment of my priorities) እና ስለ እርሱ ባለኝ እውቀት መጠን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

መዝ. 5፡3 (አ.መ.ት.) እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምጼን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 37፡7 (አ.መ.ት.) በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤

መዝ. 119፡147 (አ.መ.ት.) ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤

ምሳሌ 3፡5-6 በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
ኢሳ. 50፡4 (አ.መ.ት.)…በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

ለ. ፀሎት፣ እግዚአብሔርን ማድነቅና ማመስገን ያካትታል፡፡

መዝ. 145፡2-3 በየቀኑ ሁሉ እባርክሀለሁ፣ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ እጅግም የተመሰገነ ነው፣ ለታላቅነቱም ፍፃሜ የለውም፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 146፡1-2

ዳን. 6፡10

ኤፌ. 5፡19-20

ፊሊ. 4፡6-7

ቆላ. 4፡2-4

1ተሰ. 5፡16-17

ሐ. ፀሎት መናዘዝ፣ መታረቅን እና ሌሎችን ይቅር ማለትን ያካትታል፡፡

መዝ. 32፡5 ኃጢአቴን ላንተ አስታወቀሁ፣ በደሌንም አልሸፈንሁም፣ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፣ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውክልኝ፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝሙር 66፡18

ምሳሌ 28፡13

ማቴ. 5፡23-24

ማር. 11፡25

ሮሜ. 12፡18

1ዮሐ. 1፡9-10

መ. ፀሎት ልመናዎችን/ምህላ፣ ስለ ግል ፍላጎቶቻችን ጥያቄዎች ማቅረብንም ያካትታል፡፡

ያዕ. 1፡5 ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ማቴ. 6፡5-8

ማቴ. 6፡25-34

ሠ. ፀሎት ምልጃንና ስለሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች መፀለይን ያካትታል፡፡

2ቆሮ. 1፡8-11 በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፣ ወንድሞች ሆይ፣ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ አዎን፣ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፣ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፣ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፣ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፣ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል።

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ኤፌ. 6፡18-20

ቆላ. 4፡12

ረ. ፀሎት ምንም እንኳን የማይቋረጥበማንኛውም ሰአት ልናደርገው የምንችለው ነገር ቢሆንም ለእርሱ የተወሰነ ሰዓት ሊኖረን ይገባል፡፡

መዝ. 55፡17 በማታና በጠዋት በቀትርም እናገራለሁ፣ እጮኸማለሁ፣ ቃሌንም ይሰማኛል፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 119፡62

መዝ. 119፡164

ዳን. 6፡10

ሮሜ. 12፡12

1ተሰ. 5፡17

በ 1ተሰ. 5፡17 ላይ የተሰጠ አስተያየት

‹‹የማያቋርጥ ፀሎት፣ በሚቻል ወቅት ሁሉ የሚደረግ፣ ቀጣይነት ያለው ፀሎት ማለት እንጂ አንድም ጊዜ የማይቆም ማለት አይደለም፡፡ ጳውሎስ ይህንን ጉዳይ ያነሳው ያለ ማቋረጥ ሃሳብን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ፈታኝ በሆነበት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን፣ በተቻለ መጠን ያለማቋረጥ ከእግዚአብሔር ሕብረት ስር የመሆንን አስፈላጊነት ለመግለፅ ነው፡፡››

  1. ለእግዚአብሔር ማሳሰብ

እግዚአብሔር የማያውቀውን ነገር ልንነግረው አንችልም፡፡ ስንፀልይ የምንናደርገው ነገር ቢኖር እርሱ አስቀድሞ የሚያውቀውን ነገር በአንደበታችን ወይም በራሳችን ቃል ለእርሱ መልሶ መናገር ነው፡፡

ይህ ጉዳይ እንድንፀልይ የሚያበረታታን እንጂ ፀሎትን አላስፈላጊ የሚያደርገው አይደለም፡፡ ስለ እኛ እና ስላለንበት ሁኔታ በሚገባ ከሚያውቅ ሰው ጋር ያው የሚያውቀውን ጉዳይ ስናወራ እረፍት ይሰማናል፡፡ የእግዚአብሔር ምላሽ በሰጠነው መረጃ ላይ ሳይሆን እርሱ ስለእኛ ሁኔታ በሚያውቀው ፍፁም እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተደላድለን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ በእኛ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ያለፉ፣ የአሁኑ እና የወደፊቱ ሁኔታዎቻችንን ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡

ኢየሱስ በማቴ. 6፡8 ላይ እንዳለው አባታችን ሁሉን ያውቃል፡፡ እርሱ ሃሳቦቻችንንና ፍላጎቶቻችንን ያውቃል፡፡ መንገዶቻችንን ጠንቅቆ ይረዳቸዋል (መዝ. 139፡3)፡፡ የልባችንን ጭንቀትና ስቃይ ያውቃል፤ የማያቋርጥ ተስፋ መቁረጥ የሚያደርስብንን የስሜት ጉዳትም ይገነዘባል፤ በውስጣችን ያሉ ሁለቱ ተቃራኒ ተፈጥሮዎች በነፍሳችን ላይ የሚያደርጉት ጦርነትም ከእርሱ የተሸሸገ አይደለም፡፡

እንዲህ ከሆነ፣ ካሉብን ችግሮችና ተቃውሞዎች እንዴት እና በየትኛው ሰዓት መውጣት እንዳለብን ለማወቅ እግዚአብሔር ላይ የመታመን አስፈላጊነት አይታያችሁም? ሕይወታችን ሊታነፅ የሚችልበትን የተሻለ መንገድ እኛ ለእግዚአብሔር ልንጠቁም የምንችል ይመስላችኋል? በፍፁም፤ እግዚአብሔርን ምንም ነገር ልናስተምረው አንችልም፡፡ እርሱ ብቻውን እኛን ወደ ክብር የሚያደርሰውን ጎዳና ያውቃል፡፡ ካሉት መንገዶች ሁሉ፣ ለማንነታችን እና በእኛ ውስጥ እርሱ ላስቀመጠው ነገር የሚስማማውን ልዩ መንገድ መርጦልናል፡፡

እግዚአብሔርን እውቀት ልናስገበየው አንችልም፡፡ ልናፈቅረውና ልንደላደልበት ግን እንችላለን፡፡ እርሱ ከኛ የሚጠይቀው ይህንን አንድ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመነሻው የመጨረሻውን ያውቃል፤ ስለዚህ በመካከል በሚፈጠሩ ነገሮች ላይ ሁሉ በእርሱ ልንታመን እንችላለን፡፡

  1. ማጠቃለያ፡- በእግዚአብሔር ላይ ያለኝን መታመን በጨመርኩ መጠን እርሱ ለእኔ ባለው ፍቅር እርግጠኛ እየሆንኩ እሄዳለሁ፡፡ አንዳንዴ ነገሮች ከዚህ አስተሳሰብ ተቃራኒ ቢመስሉም፣ እግዚአብሔር ለእኔ ያለው ሃሳብ በጎና የሚጠቅመኝ ነው፡፡ ከዚህ ሃሳብ በተቃራኒው መሆን ከራሱ ባሕሪ ጋር መጋጨት ይሆናልና፡፡

ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

መዝ. 34፡15

መዝ. 37፡4-5

መዝ. 86፡5

መዝ. 145፡18-19

ኤር. 10፡23

1ዮሐ. 5፡14-15

እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው። (መዝሙር 73፡23-26)

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading