ድነት፣ ደኅንነት፣ መዳን – (Salvation)

ተፈጥሮአዊ (አካላዊ) ልደት ወደዚህ ምድር የምንቀላቀልበት ደጃፍ እንደሆነ ሁሉ፣ ዳግም ልደትም (መንፈሳዊ ልደት) ወደ መንፈሳዊው አለም የምንቀላቀልበት ደጃፍ ነው፡፡ የዚህ ትምህርት አላማ አዲስ አማኝ ጌታን ሲያገኝ (ሲቀበል) በሕይወቱ የሚከናወኑ ጥቂት ነገሮችን ማብራራት ነው፡፡ ከዚህ ስር ከተጠቀሱት በተጨማሪ ከድነት ጋር በተያያዘ ሊቀርቡ የሚችሉ ሌሎች በርካታ መርሆዎች እና እውነቶች እንዳሉ መዘንጋት የለብንም፡፡

  1. ምህረትና ፀጋ

‹‹ምህረት›› = ሊደርስብኝ የሚገባ ነገር፣ ሳይደርስብኝ ሲቀር ማለት ነው።

‹‹ፀጋ›› = የማይገባኝ ነገር ሲሰጠኝ ማለት ነው።

የእነዚህን ቃላት ትርጉም ለመረዳት ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር ምክንያት የትራፊክ ፖሊስ የሚሰጠውን የቅጣት ወረቀት (Speeding Ticket) በምሳሌነት እንመልከት፡፡

‹‹ፍትህ›› – በትራፊክ ፖሊሱ ተይዘው የክስ ወረቀት ከተሰጥዎ ፍትህ አግኝተዋል ማለት ነው።

‹‹ምህረት›› – በትራፊክ ፖሊሱ ተይዘው ነገር ግን የክስ ወረቀት ካልተሰጥዎ ምህረትን ተቀብለዋል ማለት ነው።

‹‹ፀጋ›› – በትራፊክ ፖሊሱ ተይዘው፣ የክስ ወረቀት ከተሰጥዎ፣ ነገር ግን ቅጣትዎን የትራፊክ ፖሊሱ ከከፈለልዎ ጸጋን አግኝተዋል ማለት ነው።

  1. ከመዳኔ በፊት በእግዚአብሔር ፊት ምን እመስል እንደነበረ እና እግዚአብሔር ምን እንዳደረገልኝ ጳውሎስ ከዚህ በታች ባሉ ጥቅሶች ውስጥ የሚያብራራውን ተመልከት፡፡

ሮሜ. 3፡10-12 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፡- ፃድቅ የለም፣ አንድስ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፣ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ የለም፡፡

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ሮሜ. 5፡6-10

ኤፌ. 2፡1-9   

ኤፌ. 2፡12  

ኤፌ. 4፡17-19  

  1. የእግዚአብሔር፣ ልጁን በእኛ ፈንታ የመተካት መርህ ወይም የክርስቶስ ቤዛነት

ሀ. የእግዚአብሔር ጸጋ፣ አዳምና ሔዋን ባለመታዘት እግዚአብሔርን በበደሉበት ወቅት ተገልጧል፡፡

ዘፍጥረት 2፡15-17

አዳምና ሔዋን አንድ ሕግ ተሰጣቸው፤ እርሱንም አልታዘዙም፡፡ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ሞከሩ (ይህ የበለስ ቅጠሎችን ሰፍተው በመልበሳቸው ተመስሏል፡፡) እርስ በእርሳቸው ተካሰሱ፡፡ ለአመጻቸውም የሚገባቸውን አገኙ፤ ይህ ፍትህ ይባላል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር የማይገባቸውን ነገር ሰጣቸው፤ ይህ ደግሞ ፀጋ ይባላል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያዘጋጀው እንስሳ በእነርሱ ፈንታ በመታረዱ ተመስሏል፡፡ ምንም በደል የሌለበት እንስሳ በእነርሱ ኃጢአት ምክንያት ታርዷል፡፡ የዚህ እንስሳ መታረድ፣ ኋላ ለሚመጣውና ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአት ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ለሚሰጠው ለኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ምሳሌው ነበር፡፡

ለ. ፋሲካ – ሌላው የክርስቶስ በእኛ ምትክ/ቤዛ መሆን ምሳሌ

ዘጸአት 12፡1-30

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ዮሐ. 1፡29

1ቆሮ. 5፡7

እስራኤላውያን በግብፅ የባርነት ቀንበር ስር ነበሩ፡፡ ጠቦት በእነርሱ ምትክ ታረደ፡፡ የጠቦቱ ደም ባለበት ቤት ላይ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርድ ይከለከል ነበር፡፡ ጌታ ደሙን በመቃኖቹ ላይ እና በጉበኑ ላይ ሲመለከት «ፍርድ በዚህ ቤት ላይ አስቀድሞ ሆኗል ይላል፡፡››

ሐ. የኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በእኛ ፈንታ›› መሞት ወይም ቤዛ መሆን፣ እግዚአብሔር ለእኛ ያዘጋጀው የድነት መንገድ ነው፡፡

ኢሳ. 53፡4-6 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

2ቆሮ. 5፡21

ገላ. 3፡13

1ጴጥ. 3፡18

  1. የዳንኩት ከፍቅሩ የተነሳ እንጂ ስለሚገባኝ አይደለም (NOT BECAUSE I AM DESERVING)፡፡

ቲቶ 3፡3-7 እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፣ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፣ የምንጣላ፣ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፣ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፣ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።

በተጨማሪ ተከታዮቹን ጥቅሶች ይመልከቱ፡-

ዮሐ. 6፡37  

ዮሐ. 6፡44

ሮሜ. 3፡10-12

ሮሜ. 4፡4-8

ኤፌ. 1፡3-8  

  1. በ ‹‹ክርስትና›› እና በ ‹‹ሐይማኖት›› መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?

‹‹ሐይማኖት›› በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖርህ አንተ ራስህ አንድ ነገር ማድረግ ትችላለህ ብሎ ሲያስተምር፣ ‹‹ክርስትና›› ግን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖርህ የሚያደርግህ ክርስቶስ በአንተ ፈንታ የሰራልህ የመስቀል ስራ ብቻ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡

ዮሐ. 14፡6 እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም

ሐዋ. 4፡12 መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና

  1. ኢየሱስ ስለ ድነት የሰጠው ጠቅለል ያለ ምልከታ (ዮሐ 5፡24)፤ ይህ ጥቅስ በቃላችን ልንይዘው የሚገባ ታላቅ ጥቅስ ነው)

(ኢየሱስ እንዲህ አለ)፣ ‹‹እውነት እውነት እላች“ለው፣ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading