ማቴዎስ 15፡1-39

ማቴዎስ በክርስቶስና የሃይማኖት መሪዎች መካከል ወደነበረው ግጭት እየተመላለሰ ይናገራል። ቀደም ሲል ሰንበትን በመጠበቁ ጉዳዩ ላይ የተጋጩ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ ስለ ሥርዓታዊ ንጽሕና ተከራከሩ። የብሉይ ኪዳን ካህናት ለእግዚአብሔር መሥዋዕቶችን ከማቅረባቸው በፊት እጆቻቸውን የመታጠብ ግዴታ ስለነበረባቸው (ዘጸ 30፡17-20)፥ ፈሪሳውያን አይሁዶች ሁሉ ከየትኛውም ሃይማኖታዊ ተግባር በፊት መታጠብ እንዳለባቸው አስተማሩ። ይህም ለምግብ ከመጸለይና ከመመገብ በፊት እጅ መታጠብን ይጨምር ነበር። ፈሪሳውያን፥ አይሁዶች እግዚአብሔርን ለምግቡ አመስግነው መብላት ከመጀመራቸው በፊት በተወሰነ መንገድ መታጠብ እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር።

የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጠቀሱትንና ክርስቲያኖች ለእውነተኛ መንፈሳዊነት ጠቃሚዎች ናቸው የሚሏቸውን አንዳንድ ልምምዶች ዘርዝር። ለምላሉ፥ በጸሎት ጊዜ ዓይንን መጨፈን፥ ፊልም አለማየት የመሳሰሉትን። ለ) ምንም እንኳ እነዚህ ባሕላዊ ልምምዶች ቢሆኑም፥ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል እኩል ሊያዩዋቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች ዓለጽ፡፡

ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት እነዚህን የመታጠብ ባሕሎች እያከበሩ ኣለመሆናቸውን ሲገልጹ፥ ክርስቶስ ደግሞ ለሕዝቡ ስለ እውነተኛ መንፈሳዊ ንጽሕና አስተማረ፥ እንዲሁም ክርስቶስ ለፈሪሳውያን በሚከተለው መንገድ ምላሽ ሰጥቷል።

ሀ. በሰው ሠራሽ ደንቦች ላይ በማተኮር፥ ፈሪሳውያን ብዙውን ጊዜ እውነተኞቹን የእግዚአብሔር ሕግጋት ይተላለፉ ነበር። የራሳቸውን የራስ ወዳድነት ዓላማዎች ለማሳካት፥ ሕጉን በመሣሪያነት ይጠቀሙ ነበር። ለምሳሌ፥ ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ላለመስጠት ገንዘባቸው «ቁርባን» እንደሆነ ይናገሩ ነበር። ይህም “ለእዚአብሔር ሊሰጥ የተለየ” የሚል ፍች ያለው የኣይሁዶች ቃል ነበር። ይህን ማለታቸው ግን ገንዘብን ለራሳቸው ፍላጎት ከመጠቀም አላገዳቸውም ነበር። ነገር ገን ለሌሎች፥ በተለይም ለወላጆቻቸው ገንዘብ ላለመስጠት ማመኻኛ ሆኗቸዋል።

ሊ ሰዎችን መንፈሳዊ በሚያስመስሉ ደንቦች ላይ ማተኮሩ፥ እጅግ መንፈሳዊ የሆነውን ነገር ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸውን ቀንኙነትና ሌሎችን መውደድ እንዳይመለከቱ ዓይኖቻቸውን አሳውሮታል። ሰዎች መንፈሳዊነትንና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግን እንደ ማበረታታት፥ በውጫዊ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርገዋል።

ሒ በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት አንድን ሰው የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው ነው። የምንበላው ምግብ እያረከሰንም፡፡ በልባችን ውስጥ ያለውና በአፋችን በኩል የሚወጣው ግን ሰውን በእግዚአብሔር ፊት ያረክሰዋል። የኃጢአት ምንጩ ሰዎች የሚለብሱት፥ የሚበሉት ወይም የሚጠጡት ነገር አይደለም። የኃጢአት ምንጭ ክፉ ልብ ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚቃረኑ ውጫዊ ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት፥ ከክፉ ልብ ነው። ይህም የምንበላው ምግብ (ለምሳሌ፥ የሙስሊሞች ምግብ) እንደማያረክሰን ያሳያል።ይህ ባሕላችን ይህ ጥሩ ነው ያ መጥፎ ነው ብሎ በሚያስተምረን ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው።

መ. ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩትን ወገኖች ለመቃወም እንዳይፈሩ አስጠንቅቋቸዋል። ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ስሜት ይጠነቀቅ ነበር። ነገር ግን ፈሪሳውያን ብዙ ሰዎችን ወደ ኃጢአትና የሐሰት ሃይማኖት እየመሩ በመሆናቸው፥ ክርስቶስ በግልጽ ለመናገር ፈለገ። ደቀ መዛሙርቱ ፈሪሳውያን በቃሉ እንደ ተቀየሙ ሲነግሩት፥ ሰዎች ሰምተው ይማሩ ዘንድ አንዳንድ ጊዜ በግልጽ መናገሩ አስፈላጊ እንደሆነ ገለፁላቸዋል። ፈሪሳውያን እግዚኣብሔር ፈጥኖ ሊነቅላቸው የሚገባ አረሞች ነበሩ። የደኅንነትን መንገድ የሚያውቁ ቢመስሉም፥ ለራሳቸው ዕውሮች ሆነው ሳለ፥ ሌሎች መንፈሳዊ ዕውራንን ለመምራት ይፈልጉ ነበር። ውጤቱ ግን እነርሱም ሆኑ የሚመሯቸው ሰዎች ወደ ሐሰት ትምህርትና የእግዚአብሔር ፍርድ ጉድጓድ መውደቃቸው ነበር።

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

Leave a Reply

%d bloggers like this: